Updated: አስራ ሁለቱ የአባይ ጸሃዬ ልጆች ወደ ውጭ ሃገር እንዲወጡ ተደረገ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Updated: አስራ ሁለቱ የአባይ ጸሃዬ ልጆች ወደ ውጭ ሃገር እንዲወጡ ተደረገ

Postby ኳስሜዳ » Thu Sep 07, 2017 3:51 pm

በሙስና ወንጀል ውስጥ እጃቸው አለበት የሚነገረው አቶ አባይ ጸሃዬ ልጆቹን በሙሉ ወደ ውጭ እንዲሸሹ ማድረጉን ከታማኝ ምንጮች የተገኘ መረጃ ለማረጋገጥ ችለናል።
Image
የውጩን ንግድ በሞኖፖል ይዘውት የነበሩት የአባይ ልጆች በአሁን ሰዓት በአሜሪካን ሃገር ውስጥ ናቸው።

የአስራ ሁለት ልጆች አባት የሆነው አቶ አባይ ጸሃዬ ከኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን 77 ቢሊየን ብር በማባከን የሚጠቀስ ሙሰኛ ቢሆንም እስካሁን ተይዞ ሊጠየቅ ግን አልቻለም። አቶ አባይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በፌደራል ጉዳዮች እና በስኳር ኮርፖሬሽን ውስጥ በሃላፊነት ሲሰራ የዘረፈውን ገንዘብ በልጆቹ ስም ንግድ ላይ ማዋሉንም የደረሰን መረጃ ይጠቁማል።

ከአባይ ጸሃዬ ልጆች ውስጥ ቤቢ የተባለችው ልጁ በአዲስ አበባ ብቻ 7 ሕንጻዎች ያላት ሲሆን፤ በዱባይ እና በአሜሪካም ትላልቅ ህንጻዎች እና የንግድ ተቋማት እንዳላት ምንጮቹ ገልጸዋል። ጤፍ፣ በርበሬ፤ እንጀራ ወደ አውሮፓ እና ሰሜን አመሪካ የሚላኩ የእርሻ እና የባልትና ውጤቶች በሙሉ የተያዙት በአባይ ጸሃይ ልጆች መሆኑንም ካገኘነው መረጃ ለመረዳት ችለናል።
Image
በፎቶው ላይ የምትታየው ሳባ የአባይ ጸሐዬ የእንጀራ ልጅ ናት:: በቀደመው መረጃ ላይ የአባይ ጸሐዬ ልጅ ተብሎ ተዘግቦ ነበር:: :: ከአባይ ጸሐዬ ከሚወልዳት ቤቢ አባይ ጸሐዬ ጋር በ እናት ይገናኛሉ:: ስለ ሳባ ተጨማሪ መረጃዎችን ከመቀሌ እስከ ቻይና ያሉትን እንቀርባለን::)

ምንም እንኳ እንደ ሪፖርተር ያሉ የ ሥር ዓቱ ሚዲያዎች ሆን ብለው ባለቤታቸው አይደለችም እያሉ ለማስወራትና መረጃውን ለማደናገር ቢሞክሩም ሳሌም ከበደ ከወር በፊት በሙስና ተጠርጥራ መታሰርዋ የሚታወስ ሲሆን በእስር ላይ የሚገኙ ባለሀብቶችም ከአባይ ጸሃዬ ጋር ስላላችሁ የዝርፍያ ግንኙነት እየተናገሩ ይገኛሉ።

የኦሮሞ ሕዝብ ላይ ሲዝቱ የነበሩት እኚህ ሰው ባለበታቸው በታሰሩ ግዜ የተለያዩ ጀኔራሎች ዘንድ በመደወል “አድኑኝ” እያሉ ሲማጸኑ እንደነበር ውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል።

በአሁን ሰዓት በህወሃት አመራር መካከል በተፈጠረው የከረረ ክፍፍል እና ያለመግባባት ሳብያ ስጋት ውስጥ የገቡት አቶ አባይ ጸሃዬ የተዘረፈውን የሃገርን ሃብት እና ልጆቻቸውን በሙሉ ከሃገር አሽሽተዋል።

ከአቶ አባይ ጸሃዬ ውጪ ጄነራል ሳሞራ የኑስ፣ ስብሃት ነጋ፣ አርከበ እቁባይ፣ ደብረጽዮን ገብረ ሚካአኤል፣ … በቢሊዮን የሚቆጠር የሕዝብ ገንዘብ እና ዘመድ አዝማዳቸውን በማሸሽ ላይ እንደሚገኙም የተጠቆመ ሲሆን አቶ ብርሃኔ ገብረ ክርስቶስ ወርደው የቻይና አምባሳደር እንዲሆኑ የተደረገው ለባለስልጣናቱ የመጨረሻ የማምለጫ አማራጭ ለማበጀት ነው ተብሏል።

በትግራይ ህዝብ ስም እየነገዱ ያሉት እነዚህ ጥቂት ሰዎች፣ ሃገሪቱን ለማስተዳደር ያልቻሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ አለም አቀፍ ሜዲያም እየተናገሩ ነው። የህወሃት ሰዎች በሁለት ጎራ ተከፍለው አሁን የማይወጡበት ችግር ውስጥ ስለገቡ ያላቸው አማራጭ ሃብት እና ዘመዶቻቸውን ማሸሽ በመሆኑ ይህንን ተያይዘውታል። በስሙ ሲነግዱበት የነበረውን የትግራይ ሕዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር ሆድና ጀርባ ሆኖ እንዲጫረስ አድርገው እነሱ እግሬ አውጭኝ ማለታቸውን የትግራይ ሕዝብ ከወዲሁ ሊያወግዘው ይገባል።
http://www.zehabesha.com/amharic/?p=80256
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests