ተላላኪው ብአዴን የእነ አርበኛ ጎቤን እርስት ለወያኔ ሲያስረክብ አባቶች በቁጭት እየታዘቡ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ተላላኪው ብአዴን የእነ አርበኛ ጎቤን እርስት ለወያኔ ሲያስረክብ አባቶች በቁጭት እየታዘቡ

Postby ኳስሜዳ » Sat Sep 09, 2017 5:27 pm

Image

እነዚህ ወገኖቼ ፊት ላይ የተፃፈውን ቁጭትና መጠቃት እንደ ትልቅ ጥራዝ እያነበብኩኝ ነው። አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚሰማ ህመም አለው። አሁንም አንዳንዶች ከታሪክ ለመማር አለመቻላቸው ያሳዝናል። እነዚህ ህዝቦች ይሄን መሬት ወስደው በሰላም እንኖራለን ብለው ካሰቡ የክፍለ ዘመኑ ሞኞች ናቸው ።

በ 20ኛው ምእተ አመት ጀርመን ውስጥ ብቅ ብሎ አለምን በአንድ እግሯ ያቆመው ሂትለር ዝም ብሎ እንደ ሙጃ የበቀለ አልነበረም ። ሂትለር የጀርመን ህዝብ የመገፋት ፣ የቁጭት ውጤት ነበር።

ጀርመን በአሻጥረኞች ከጀርባዋ ባትወጋ ኖሮ እንደ አዶልፍ ያለ መሪ ባልወለደች ነበር። ጀርመን ሉአላዊ ግዛቶቿን ” ቨርሳይሌ ውል ” ተነጠቀች ይሄን ያስፈፅም ዘንድ እንደ እኛው ብአዴን ያለ አሻንጉሊት የሆነ Weimar Republic የሚባል ተላላኪ ስልጣን ላይ ቁጭ አደረጉለት። ከቨርሳይሌ ውል በኋላ የጀርመን ህዝብ ቂም አረገዘ ። የእርግዝናው ወራት ሲጠናቀቅ ሂትለር የሚባል ልጅ ተወለደ። ከዛ በኋላ በአውሮፓ የሆነውን ስለምትውቁት እዚህ መፃፍ አያስፈልገኝም።

አሁን ብአዴን የትግሬ ተላላኪነት ኮንትራቱን እንደ ጀርመኑ Weimar አደገኛ ውል በመዋዋል የአማራን ህዝብ ከጀርባው እየወጋው ነው። ይሄ ግፍ ቁጭት፣ መጠቃትና ከጀርባ መወጋት አርግዞ ምን እንደሚወልድ መገመት አያስቸግርም። የፖለቲካ ሳይንቲስቶች “ማንም ሰላምን የሚፈልግ ለጦርነት ይዘጋጅ ።” የሚል ብሂል አላቸው። እኔ ጦርነት እያወጅኩኝ አይደለም። ነገር ግን አማራ ህዝብ ውስጥ ያረገዘ ነገር ይታየኛል። አማራ መሬቱን ተነጥቆ ዝም ይላል ማለት ዘበት ነው። አሁንም የከፋው ነገር ሳይመጣ በፊት ወልቃይት ፣ጠገዴና ጠለምትን መመለስ የፖለቲካ ብልህነት ነው። ያ ካልሆነ ግን በህዝብ መካከል ሊፈጠር የሚችለውን መፃኢ ሁኔታ ማሰብ አልፈልግም።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2143
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests