መውደቅ በስልጣን እያሉም፤ እየሌሉም ነው!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

መውደቅ በስልጣን እያሉም፤ እየሌሉም ነው!!

Postby ኳስሜዳ » Mon Sep 18, 2017 8:52 am

ኢህአዴግ ሰዓት የሚቆመው መቼ ነው? የትኛውም የመንግስት ሰርዓት ይወድቃል ፤ ያልፋል።ይህ እውነታ በኢህአዴግ ላይ እውን የሚሆንበት ቀን አለው።ለእኔ ኢህአዴግ የወደቀ ስርዓት ነው።አሁን በሀገሩቱ የሚታዩት የብሄር ግጭት ፣የሀገር ፍቅር ስሜት መጥፋት ፣የሰበዓዊ መብት ጥሰት ፣ፀረ_ዲሞክራሲያዊነት ፣ኢ_ፍትሃዊነት ፣ የዜጎች እኩልነት ማጣት ፣የሀገር ጥላቻ ፣ ፓርቲው በአብዛኛው ህዝብ መጣላቱ ይህ ሰርዓት መውደቁን የሚያሳይ ነው።መውደቅ ከስልጣን መውረድ ብቻ ሳይሆን በስልጣን እያሉም ነው።ስለዚህም የኢህአዴግ ሰዓት ያበቃው የዘር ፌደራሊዝም እንደ ሰርዓት የተቀበለ ቀን ነው።የኢህአዴግ ሰርዓት የወደቀው ህዝብ የጠላው ሰዓት ነው።

ፓርቲው ዜጎች ፍትህ ሲያሳጣ ሰዓቱ ቆሞል፣ ፓርቲው አንባገነነ ሲሆን ሰዓቱ ቆሞል ፣ፓርቲው ነፃነት እና ሀገራዊ ጥላቻ የፈጠረ ቀን ነው ሰዓቱ የቆመው።መውደቅ በስልጣን እያሉም ፤ እየሌሉም ነው።ኢህአዴግ የወደቀው በስልጣን ላይ እያለ ነው።በውድቀት ውስጥ ያለ መንግስት ህዝቦቹን አያስደስትም፣ በህዝቦቹም ተቀባይነት የለውም ፣የራሱ አገልጋይ ቅጥረኞች የፖለቲካ ታማኝነት ይጎላቸዋል ፣ ወታደራዊ እርምጃዎችን ይወስዳል ፣ ተመሳሳይ ህዝባዊ ተቃውሞዎች በተደጋጋሚ ይበረታበታል ፣መጀመሪያ ቃል የገባውን ሁሉ በተቃራኒ ያውለዋል።በይህ ደሞ በኢህአዴግ ላይ ሆኖል።

ፓርቲው እርስ በራስ ባለመተማመን ወድቋል፣ ያለመተማመን ፌደራሊዝምና የጋራ ሀገራዊ አጀንዳው የተናደበት ቀን ወድቋል ፣ብሄራዊ መግባባት ላይ አለመደረሱ የፓርቲወን መውደቅ ብቻ ሳይሆን መበስበስም ያሳያል።በዘር መተማመን ለመፍጠር እየሞከረ ያለው ይህ ስርዓት ምሁራንና ባለሞያተኛን እያራቀ ተመሪ መሪ እንዲሆን አድርጎታል።በዚህ ሂደት ውስጥ ጠብመንጃ ስለያዘ ብቻ አንድ ሰርዓት አለ አይባልም።

በ1983 አዲስ የፖለቲካ ሰርዓት ሲመጣ ያልተወራ መዓት የለም።በኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ ተሰፋ ከተነገረበት አመተት መካከል አንዱ ነው።ሀገር በዲሞክራሲ ትደምቃለች ፣ በነፃነት ማሸብረቅ ፣ የፍትህ አሸናፊነት ፣ የህግ የበላይነት በሀገሪቱ በቀጣይ እንደሚሰፍን ተነገረን።

ኢህአዴግም ኢትዮጵያን ከመበታታን ማዳን እስከ የመጪው እድገት፣ ከነፃነት እስከ ነፃ ምርጫ ፣ ከነፃ ፕሬስ እስከ መደራጀት አመጣለው ብሎ ያሳወጀበት ነበር።ገና ከጅማሬ የብሄር ፖለቲካ ማቀንቀኑ በህዝቡ ዘንድ ተቃውሞና ስጋት የፈጠረ ቢሆንም በስልታው ማታለልና ተንኮል የሚፈልገው ነገር ፓርቲው መስራቱን ተያያዘው።
ከ1983 እስከ 1997 ኢህአዴግ በጣላትነት የፈረጃቸውን ብሄሮች ማዳከም፣ ተፅኖ ፈጣሪ ሰዎችን በማሰርና በማባረር ውስጥ ለውስጥ ሲሰራ ፤ ከላይ ከላይ ደሞ ለኢትዮጵያ ብሄሮች ትንሳኤ አመጣለው እያለ የብሄር እኩልነትና ተጠቃሚነትን በልዮነት ለስልት እያሰፋ መሰራቱን ተያያዘው።

ከፍተኛ የስልጣን ሹክቻ ፣የዘር ፖለቲካ ገና በልጅነቱ ያሰረው ኢህአዴግ አይወጡ ችግር ውስጥ እንደሚገባ ገና ከአጀማመሩ ያሰታውቅ ነበር።በተለይ በሀገሪቱ የዘረጋው የብሄር ፖለቲካ የኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን የቀጣይ የሀገሪቱ ፈታና እንደሚሆን ሁሉም ተረዳ።

ገና ከጅምሩ የሚሰሙት መጠነኛ የዘር ግጭት ፣ልዮነት ፣የጎሳ ፖለቲካ ፣ዘረኝነት እና ፀረ―ኢትዮጵያ እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጣ።ይህ ደሞ መንግስት በዘረጋው ፌደራሊዝም ይበልጥ ተግባራው ለማድረግ የቀለል ነበር።የእኛ የዘር ፌደራሊዝም አቅዶ ወይም ሳያቅድ ለሚነሳ የትኛውም ዘረኛ ቀላል መንገድ ሆነለት።ለዘረኞች የሚመቸው ይህ ፌደራሊዝም መንግስት ሆን ብሎ የዘረጋው ሰርዓት ነው።

ባለፍት 26 አመታት በኢህአዴግ ሰዓት የመጣው የትኛው ቁሳዊ ልማት እና ሁሉን አቀፍ ሀገራው ልማት የፈለገ ያክል ቢደርስ በሀገሪቱ ወሳኝ መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች አሉ።ሀገር ማለት መሬትና ህዝብ ከሆኑ ፤ የትኛውም መንግስት በመሬትም ፣በህዝብ ላይ መሰራት አለበት።የእኛ መንግስት ህዝብ ላይ የሰራው መከፋፈል ፣ዘረኝነትና ጎጠኝንት ሲሆን ይህ ደሞ ሀገሪቱ የትም ደረጃ ላይ ብትደርስ ነገ ወደ ታች የሚመልሳት ሰራ ነው።የነገ ትውልድ ላይ ያልተሰራ የትኛው ሰራ ዜሮ ነው።የነገው ትውልድ ዘረኛ አድርጎ የሀገር ፍቅር ሳይሆን ክስረትና ውድቀት ነው።በዘረኝነት የተሰራ ልማት በአንድ ቀን አፈር ይበላዋል።
ቶማስ ሰብስቤ
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2146
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests