“ከሳተላይት በሚታይ ምስል የመቀሌ ብርሃማነትና የጎንደር ጨለማነት አስገራሚ ነው” የአለም ባንክ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

“ከሳተላይት በሚታይ ምስል የመቀሌ ብርሃማነትና የጎንደር ጨለማነት አስገራሚ ነው” የአለም ባንክ

Postby ኳስሜዳ » Sat Sep 23, 2017 8:52 am

ትግራይ ክልልና አዲስ አበባ በመንገድ ልማት ቀዳሚዎች ሲሆን የአማራ ክልል ግን መጨረሻ እንደሆነ በቅርቡ የወጣው የአለም ባንክ ሪፓርት አስታወቀ።

በ10 ዓመታት ውስጥ (ከ2006-2016 እኤአ) ያለውን የመንገዶች ስርጭት ላይ በተደረገ ጥናት በትግራይ ክልልና በአዲስ አበባና በዙሪያዋ ባሉ የኦሮምያ ክልል ከተሞች የመንገድ ስርጭት ከፍተኛ ሲሆን፥ በአማራ ክልልና በገጠሪቱ የኢትዮጵያ ክፍል ደግሞ አነስተኛ የመንገድ ትስስርና ልማት መኖሩን የአለም ባንክ ጥናት ያመላክታል። ጥናቱ እንዳመለከተው የኢንቨስትመንትና ሌሎች መሰረተ-ልማቶች ስርጭትም እንደመንገዱ ሁሉ በአዲስ አበባና በትግራይ ቀዳሚ ሲሆን በአማራ ክልል ግን ኋላ ቀር ነው።

የአሜሪካ ብሄራዊ የውቂያኖስና የከበባቢ አየር አስተዳደር የሚታዩ ሞገዶችን በመጠቀም በሳተላይት ምልከታ ባደረገው ጥናት በጠቅላላውም ሆነ በጨለማ ግዜ አማካኝ የመቀሌ ከተማ ብርሃማነት ከፍተኛ ሲሆን (የመብራት ስርጭቷ ከፍተኛ እንደሆነ ይጠቁማል) ጎንደር ከተማ ግን በጠቅላላውም ሆነ በማታ ግዜ ባላት አማካኝ ብርሃናማነት መጨረሻ ናት።

በአለም ባንክ ስር ፕሪያንካ ካንትና በሚካኤል ጊገር ተሰርቶ መስከረም 11 ቀን 2010 ዓ\ም ይፋ የሆነው ይህ ሪፓርት እንደሚያሳየው ከመንገድ ልማት መስፋፋት ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ትኩረት በማዕከላዊ ኢትዮጵያና በሰሜን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ነው።

ከሳተላይት በሚታይ ምስል ሩቅና በኢኮኖሚ ኋላ ቀር የሆኑ ክልሎች እንዲሁም አማራ ክልል ጨለማማ ሲሆኑ፥ የመንገድ ስርጭት፥ የሌሎች መሰረተ ልማት ስርጭትም ሆነ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ኋላ ቀር ሲሆኑ በስርጭት ዘርፍም እኩልነትና ፍትሃዊነት እንዳልሰፈነነና እንደማይታይ ያመላክታል።

በአንዳንድ ክልሎች (አማራ ክልልንም ጨምሮ) በክልል ውስጥና ከክልል ውጭ ያለ የመንገዶች ትስስር በጣም ደካማ ሲሆን የሰው ሃይል ፍሰት፥ ሸቀጦችንና የግብርና ምርቶችን ማሰራጨት ላይ ተጽዕኖ እንዳለውና የገብያ ተደራሽነትን እንደሚገታ ጥናቱ ያመላክታል።

“በግብርናና አገልግሎት ዘርፉ ላይ በሚታዩ እድገቶች የተነሳ ሃገሪቱ የተወሰነ እድገት ማሳየት ብትችልም የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ የተጀመረው ሂደት የቅርብ ግዜ ስራ ሲሆን ከአዲስ አበባ ውጭ ባሉ ሁለተኛ ከተሞች ላይ በኢንዱስትሪ ዘርፍ ያን ያህል የጎላ ለውጥ የለም ይላል ጥናቱ። ወደ አዲስ አበባ ያለው ከፍተኛ የሆነ የሰው ሃይል ፍሰት እንደሚያሳየውም በሁለተኛ ከተሞች ህዝቦችን ተጠቃሚ ሊታደርግ የሚችል ለውጥ ያን ያህል እንዳልሆነ ነው” ይላል ሪፓርቱ።
Image
http://www.zehabesha.com/amharic/wp-con ... Gonder.jpg
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: “ከሳተላይት በሚታይ ምስል የመቀሌ ብርሃማነትና የጎንደር ጨለማነት አስገራሚ ነው” የአለም

Postby ቢተወደድ1 » Mon Sep 25, 2017 2:24 pm

በደማችን ያመጣነው እንጂ እንዳንተ ሳይበር ላይ ቁጭ ብለን ስንቀባጥር እንዳልሆነ ይታወቅልን፡፡
ጎንደርም እንዲ የሆነችው በራሷ ሕዝብ እንጂ አንተ እንደምታስበው አይደለም፡፡ የግምቦት 7 አለቅላቂ ከሆንክ፤ አእምሮ ይስጥህ፡፡
ጠብደል መሃይም፤ ፎቶሽ ደግሞ ከአይሮፕላን እንጂ ከሳተላይት የተነሳ አይመስልም፡፡ ሳተላይት የምታውቅም እትምውስልም!!!
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 214
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: “ከሳተላይት በሚታይ ምስል የመቀሌ ብርሃማነትና የጎንደር ጨለማነት አስገራሚ ነው” የአለም

Postby ዞብል2 » Tue Sep 26, 2017 12:48 am

ነፍሰ በላው!! ዕውነት ተናገርክ አልሰማ ብለን ነው፡ይህን ዘመን እላያችን ሆናችሁ፡የምትፈነጩብን፡፡ኢህአድግ ብላችሁ፡ከጀርባ የትግራይ ነፃአውጪ የሚል ስም ባንዲራና ጠመንጃ አንግባችሁ ዲሞክራሲያው ምርጫ እናድርግ ስትሉ ተንጋግተን ውሸትና መሳሪያ ካነገተ ነፍሰ በላ ጋር ለምርጫ እንቀርባለን፡፡

ነፍሰ በላው!! ዕውነቱን ልንገርህ ደምህን ያፈሰስከው ---- እያሉ በካልቾ ሲያላጉህ ለነበሩት ለናቅፋ ጌቶችህ ነው፡፡ የናፍቃ ጌቶችህ ውለታህን ረስተው በአይሮፕላን ሲያጋዩህ፡ያ ተራራ ያንቀጠቀጠው እንትናችሁ መሸታ ቤት ሲያንቀላፋ.....ቅቅቅቅቅ ቂም የማያውቁት የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው ከሻቢያ መንጋጋ ያዳኑህ፡፡

ነፍሰ ባላው!! አሁንም የኢትዮጵያን ልጆች ውለታ እረስታችሁ፡ በልማት፣በማንነት(ቅማንት አማራ ጠገዴ ፀገዴ)እርስ በርስ(ሶማሌና ኦሮሞ)ሰውን ለዘመናት ከኖረበት እያፈናቀላችሁ ታሰቃያላችሁ፡ይሄ ሁሉ የሚያሳየው፤ ከመጀመሪያውም ነፃ አውጪ ሳትሆኑ ዘራፊ ነፍሰ በላ ወንበዴዎች መሆናችሁን ነው!!!!
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2009
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm

Re: “ከሳተላይት በሚታይ ምስል የመቀሌ ብርሃማነትና የጎንደር ጨለማነት አስገራሚ ነው” የአለም

Postby ዞብል2 » Wed Sep 27, 2017 12:55 am

አይጫን ሆነ እንጂ ሃይቅ በመኪና
አይጫን ሆነ እንጂ ወንዝ በመኪና
ትግራይ ገብተው ነበር ዓባይና ጣና፡፡
ዞብል2
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2009
Joined: Fri Jan 30, 2004 11:23 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests

cron