ሃሮማያ ከተማ በተቃውሞ እየተናጠች ነው – ሕዝብ ሕወሓቶችን ሃገራችንን ለቃችሁ ውጡ አለ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሃሮማያ ከተማ በተቃውሞ እየተናጠች ነው – ሕዝብ ሕወሓቶችን ሃገራችንን ለቃችሁ ውጡ አለ

Postby ኳስሜዳ » Tue Oct 03, 2017 7:38 pm

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ ከ እለት ወደ እለት ወደ አስጊ ደረጃ እየደረሰ ይገኛል:: ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ግጭት በየቦታው እያስተናገደች ባለችው ኢትዮጵያ አለመረጋጋቱ አይሏል:: ዛሬ በሃሮማያ ከተማ ሕዝብ አደባባይ በመውጣት = የሕወሓት አስተዳደርን ሃገራችንን ለቃችሁ ውጡ በሚል ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሏል::

በሃሮማያ በተደረገውና በርካታ ወጣቶች በተሳተፉበት በዚህ ሰልፍ “ወያኔ ሌባ” ሲሉ የተቃወሙት ወገኖች የሃገሩ ባለቤት ኦሮሞ ነው ሃገሩን ለቃችሁ ውጡ ሲል ተቃውሞውን ከፍ ባለ ድምጽ አሰምቷል::

ገንፍሎ የወጣውን የሕዝብ ቁጣ ለመቆጣጠር የሕወሓት መራሹ መንግስት በአካባቢው ወታደሮችን እንዳሰማራም ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች ሲገልጹ እስካሁን በሰውና በንብረት ላይ ስለደረሰ ጉዳት የገለጹት ነገር የለም::

በሌላ በኩል የሕወሓት ልዩ ፖሊስ በም ዕራብ ሓረርጌ ዶባ ወረዳ 3 ወገኖችን መግደሉ ተሰማ:: እንደ አካባቢው ምንጮች ገለጻ ኢብራሂም አብዲ፣ ሮባ ዳዲ እና ለጊዜው ስሙ ያልተገለጸ አንድ ወገን ናቸው በሕወሓት ልዩ ፖሊስ የተገደሉት::

http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81151
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 8 guests