ወያኔ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ይቅርታ ጠይቀው ከእስር ቤት እንዲወጡ ሽማግሌዎችን ላከ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያኔ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ይቅርታ ጠይቀው ከእስር ቤት እንዲወጡ ሽማግሌዎችን ላከ

Postby ኳስሜዳ » Tue Oct 10, 2017 5:48 pm

በከፍተኛ ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ መንግስት ካለአግባብ በግፍ ጠርጥሮ ያሰራቸውን ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናን እንዲፈታ በተለይ ከአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ግፊት እየተደረገበት ባለበትና ሃገር ቤት ያለውም ሕዝባዊ አመጽ እየተቀጣጠለ መንግስትን ወደ መጣል እየደረሰበት ባለበት በዚህ ወቅት መንግስት መረራ ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡ ሽማግሌዎችን መላኩን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::
Image
እንደምንጮቻችን ገለጻ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ያለው ሕወሓት መራሹ መንግስት ባለፈው ሳምንት አራት ሽማግሌዎችን ፕሮፌሰሩ ወደታሰሩበት እስር ቤት የላከ ሲሆን ሽማግሌዎቹም መራራ ይቅርታ ጠይቀው እንዲወጡና ይቅርታ የመፈረሚያ ወረቀት አቅርበውላቸዋል:: ፕሮፌስር “መረራ ይቅርታ አልጠይቅም የታገልኩለት ሕዝብ ሕዝብ ያስፈታኛል” በማለት ሽማግሌዎቹን እንደመለሷቸውም የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዘግበዋል::

ፕርፌሰር መረራ ይቅርታ አልጠይቅም ካሉ በኋላ ሽማግሌዎቹ ለማግባባት ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም ሳያሳካላቸው ተመልሰዋል::

በአሁኑ ወቅት በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየተደረጉ ባሉ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ሕዝቡ ከሚያነሳቸው አንደኛው ጥያቄ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እና ጋዜጠኞች እንዲፈቱ ሲሆን ስር ዓቱ በቀጥታ ለሕዝቡ ምላሽ መስጠት ሲገባው ታሳሪዎችን ይቅርታ ጠይቃችሁ ውጡ ወደሚል የተለመደ ተልካሻ ሴራው እየገባ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይናገራሉ::
http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81397
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Majestic-12 [Bot] and 6 guests