የኢትዮጵያ ብር ከነገ ጀምሮ 15% ዋጋ ያጣል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የኢትዮጵያ ብር ከነገ ጀምሮ 15% ዋጋ ያጣል

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Oct 10, 2017 7:45 pm

የአንድ አገር መገበያያ ገንዘብ የመግዛት ዋጋ በተለያዩ ምክንያቶች እንደሚቀንስና እንደሚጨምር ሁላችንም ብናውቅም ብዙዎቻችን የማይገቡን ዝርዝር ነገሮች እንዳሉ ግልጽ ነው::ከነዚህ ምክንያቶች መካከል የነገው የብሄራዊ ባንክ ውሳኔ አልገባኝም::ባንኩ እንደሚለው ከሆነ የአገሪቱን የውጭ ንግድ ኢኮኖሚ ለማሳደግ መገበያያውን ብር ዋጋ ማሳጣት አስፈላጊ ነው::ስለሆነም ዛሬ 1የአሜሪካ ዶላር 23ብር ቢመነዘርም ከነገ ጀምሮ ግን ወደ 26 ብር አካባቢ ያሻቅባል::የኢትዮጵያ ብር ከ7 ዓመት በፊትም በአንድ ጊዜ 17% ዋጋ ማጣቱም ተዘግቧል::አንድ የአሜሪካ ዶላር በ2ብር ከ 7 ሳንቲም ሲመነዘር የምናስታውስ ሰዎች ኢኮኖሚው በ11 % አደገ ሲሉን እንዴት ይግባን?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1089
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests