መሬት ላራሹ ትላንትና ዛሬ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

መሬት ላራሹ ትላንትና ዛሬ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Oct 11, 2017 1:37 pm

የደርግ ሥርዐት ከሚመሰገንባቸው ውሳኔዎች(በጠላቶቹ ጭምር) መካከል የመሬት ላራሹ አዋጅ አንዱነበር::ከዛሬ 42 ዓመታት በፊት የወጣው ይህ አዋጅ ዛሬም ቢሆን ለሕዝብ ለሚያስብ ሰው ሁሉ ተቀባይነት ያለው ነው::በተከታዩ አንቀጽ የሚጀምረው ይህ አዋጅ በተለይ ለገጠሩ ማኅረሰብ ዘመን የማይሽረው ድል ያስገኘ ነበር::አሁን ያለውን ሁኔታ መቼም ሁላችንም ስለምናውቀው ለማወዳደር የዘርፉ ባለሙያ መሆን አያስፈልግም::
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ በእርሻ በሚተዳደሩ አገሮች አንድ ሰው በህብረተሰቡ ውስጥ ሊኖረው የሚችለው የኑሮ ደረጃ ፣መብት እንዲሁም ክብርና ማእረግ የሚወሰነው ከመሬት ጋር ባለው ግንኙነት በመሆኑ፣

ምዕራፍ 2
አንቀጽ 3 የገጠርን መሬት የሕዝብ ሀብት ስለማድረግ
ቁ 1 ይህ አዋጅ ከጸናበት ቀን ጀምሮ የገጠር መሬት በሙሉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብት ሆኗል:
ቁ 2 ማንኛውም ሰው ወይም የንግድ ማኅበር ወይም ሌላ ድርጅት የገጠር መሬትን በግል ባለሀብትነት ለመያዝ አይችልም::
አንቀጽ5 መሬት ማስተላለፍ ስለመከልከሉ

ማናቸውም ሰው በይዞታ ያገኘውን መሬት የመሸጥ ፣ የመለወጥ ፣ የማውረስ ፣ የማስያዝ፣በወለድ አግድ የመስጠት ወይም በሌላ መንገድ የማስተላለፍ መብት አይኖረውም::ሆኖም ባለይዞታው ሲሞት፣የሟች ሚስት ወይም ባል ወይም አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ ወይም እነዚህ ከሌሉ አካለ መጠን ያደረሰ ልጅ በይዞታው ተተክቶ የመጠቀም መብት ይኖረዋል::


''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1034
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 9 guests

cron