ቻው ቻው ወያኔ!!!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ቻው ቻው ወያኔ!!!!

Postby ኳስሜዳ » Sat Oct 14, 2017 6:47 pm

በኦሮምያ እየተካሄደ ያለው ፀረ ወያኔ ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም መቀጠሉ ታወቀ ። በዛሬው እለት በኢሉባቡር መቱ ከተማ በተደረገው ህዝባዊ ተቃውሞ “ቻው ቻው ወያኔ” የሚሉ ድምፆች አስተጋብተዋል ።

በዛሬው እለት ረፋድ ከ3 ሰአት ጀምሮ በከተማዋ በተደረገው ፀረ ጭቆናና ፀረ ወያኔ ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ ዳውን ዳውን ወያኔ ፣ አባይ ፀሀይየ የስኳር ሌባ ፣ ገዳዬች ለፍርድ ይቅረቡ ፣ ቻው ቻው ወያኔ… የሚሉ ህዝባዊ ድምፆች የተሰሙ ሲሆን ተቃውሞውን መኪናዎችና ባጃጆች በክላክስ ሲያጅቡት እንደነበርም ምንጮቻችን አመላክተዋል።

የህወሃት ሰዎች አይናቸውን በጨው አጥበው በሬድዬ ፋናና በ EBC ላይ ህዝባዊ ተቃውሞ የለም አንዳንድ ፀረ ሰላም ሀይሎች ያደረጉት ሁከት ነው በሚል የገሀዱን እውነታ ለመካድና ለማለባበስ ቢሞክሩም ቄሮዎች ግን ዛሬም የጨቋኙን የህወሃት ስርአት ግብአተ መቃብር ሳንፈፅም የሚመልሰን አይኖርም በሚል ፅናት ህወሃትን ቻው ቻው ዳውን ዳውን በማለት ይብቃህ ብለውታል ።

የፀጥታ ሀይሉ ሳይቀር ከህዝብ ጋር እየቆመ በመምጣቱና ነገሮች እየባሰባቸው መምጣቱን የተረዳው ህወሃት ከፍተኛ መከፋፈልና መደናገጥ ፣ ግራ መግባት ውስጥም እንደገባ መረጃዎች በስፋት እየወጡም ይገኛሉ።

ቅዳሜ ጥቅምት 4/2010 ቢቢኤን ዜና –
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests