የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ታመው ሆስፒታል ዋሉ * የምግብ መመረዝ ነው

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ለማ መገርሳ ታመው ሆስፒታል ዋሉ * የምግብ መመረዝ ነው

Postby ኳስሜዳ » Mon Oct 16, 2017 10:39 pm

(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ኦቦ ለማ መገርሳ ታመው ሆስፒታል መዋላቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ:: የዘ-ሐበሻ ምንጮች እንዳስታወቁት አቶ ለማ ህመማቸው የምግብ መመረዝ ሳይሆን እንደማይቀር እየተነገረ ነው::

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ በምግብ መመረዝ ሕይወታቸው ማለፉ አይዘነጋም::

ባለፈው ሳምንት በሁለት የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ ከሕወሓት ደህንነቶች የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸው እንደነበር በተለያዩ ሚዲያዎች መዘገቡ አይዘነጋም:::

አቶ ለማ መገርሳ በህመም ላይ ያሉ ሲሆን ምናልባትም ሕወሓት የሚቆጣጠራቸው ሚድያዎች የርሳቸውን የቆዩ ቭዲዮች በማሳየት የተለያዩ ልማታዊ ዜናዎችን እንደሚሰሩና ደህና መሆናቸውን ለማሳየት እንደሚሞክሩ ሲሉ እነዚሁ ምንጮች አስታውቀውናል::

የአቶ ለማ መገርሳን ጤንነት ምንጮቻችን ተከታትለው ያለውን ነገር እንደሚያሳውቁን ቃል ገብተውልናል – እንደደረሰን እናቀርበዋለን::

ብዙዎች በአድናቆት ያዩትና የሕወሃት ሰዎችን ያስቆጣው የለማ መገርሳ የሰሞኑ ንግግር እዚህ ይገኛል – ይጫኑት::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦህዴድ “ተወዳጁ እና እጅግ የተከበሩት የኦሮሚያ ብዬራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሣ የት ጠፉ?”በሚል ር ዕስ በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን አስነብቧል::

” ተወዳጁ እና እጅግ የተከበሩት የኦሮሚያ ብዬራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ለማ መገርሣ የት ጠፉ?
እያላችሁ ከልብ በመነጨ የመሳሳት ስሜት ስትጠይቁን ለነበራችሁ ወዳጆቻችን ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድ የኦህደድ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ሃላፊ ክቡር ፕሬዝዳንታችን ለስራ ጉዳይ ወደ ውጭ እንደሄዱና ምንም ችግር እንዳልገጠማቸው የተናገሩትን ወደናንተ ማድረሣችን ይታወሳል።

ዛሬ ደግሞ ተወዳጁ መሪ የሄዱበትን ስራ አጠናቀው ፊንፊኔ ገብተዋል።
የኦሮሚያ ተሃድሶ መሪ እና የጀመርነው ሁሉን አቀፍ ለውጥ መሀንዲስ ክቡር አቶ ለማ እንኳን ደህና መጡ ። እንኳንም ደስ አለን!።”

ይህ ባልተለመደ መልኩ የወጣው የኦህዴድ ጽሁፍ አነጋጋሪ ሆኗል:: ከበስተጀርባው ከባድ ነገር እንዳለ የሚያሳይ ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች በርክተዋል:::

http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81632
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 4 guests