በጎሬ ከተማ ዉስጥ ታላቅ ተቃዉሞ ተደረገ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በጎሬ ከተማ ዉስጥ ታላቅ ተቃዉሞ ተደረገ!

Postby ኳስሜዳ » Tue Oct 17, 2017 3:23 pm

Image

ቢቢኤን ) በዛሬው እለት በጎሬ ከተማ ዉስጥ ታላቅ ተቃዉሞ መደረጉ ታወቀ።ቁጥራቸው እስከ አስር ሺ የሚደርሱ የጎሬና የአካባቢው ነዋሪዎች የተሳተፉበት ይኸው ሰልፍ በህወሃት የሚመራዉን መንግስት በመቃወም የተደረገ ሲሆን የተለያዩ መፈክሮችም ተደርገውበታል።

ቢቢኤን ከደረሰው የድምጽና የፎቶ ግራፍ መረጃዎች ለማወቅ እንደቻለው ህዝቡ «ወያኔ የመሬት ሌባ፣ወያኔ የዘይት ሌባ፣ወያኔ የስኳር ሌባ፣ወያኔ ገዳይ፣ወያኔ አያስተዳድረንም» በማለት በጎሬ ዉስጥ በመንቀሳቀስ ድምጹን አሰምቷል።ከገጠር ድረስ ተሳትፊዎች መጥተው የተገኙበት ይኸው ተቃዉሞ የሁለተኛ ደረጃ ትመርት ቤት ተማሪዎች ትምርታቸዉን አቋርጠው ተቀላቅለዉበታል።

ተቃዉሞው በዜማ፣በእንጉርጉሮና በሽለላ ጭምር የተከናወነ ሲሆን በህወሃት የሚመራዉ መንግስት የኦሮምያ መሬትን መስረቁን አንቀበልም፣የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅደመ ሁናቴ ባስቸኳይ እንዲፈቱ የሚል ጥያቄ የቀረበበት እንደነበር ታዉቋል።

የህዝቡን ብሶት ለማዳመጥና ሰልፉን ስርዓት ለማስያዝ የአካባቢዉ አስተዳደር ከሙስሊምና ከክርስቲያን የሆኑ የሐይማኖት አባቶችን፣ አባ ገዳን እና የአገር ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ አነጋግሯል ሲሉ የጎሬ የቢቢኤን ምንጮች አሳዉቀዋል።
የከተማዉ አስተዳደር ለሐይማኖትና ለማህብበረሰብ መሪዎች የህዝባችንን ብሶት አናፍንም፣ህዝባችን ተቃዉሞ ማድረግ መብቱ ነው ማለቱ ታዉቋል። ተቃዉሞ ስርዓት እንዲኖረው፣ በሰዉ ህይወትና በንብረት ላይ አደጋ እንዳይደርስ እንደሀይማኖትና የማህበረሰብ መሪነታቹ የበኩላቹን አስተዋጽ ኦ አድርጉ በማለት ተማጽንኦ ማቅረቡን ቢቢኤን ያነጋገራቸው በስፍራዉ የነበሩ እማኞች አሳውቀዋል።

http://www.zehabesha.com/amharic/?p=81699
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests