በኦክቶምበር 14 በሶማሊያ ዋና ከተማ በሆነችዉ መቋዲሾ ከፍተኛ የሆነ የቦንብ ጥቃት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ የቦንብ ጥቃት ከ300 ሰዉ በላይ ንጹሃን ዜጎችን ቀጥፎ ከ 400 በላይ የሆኑትን ለክፍተኛ አካል ጉዳት እንዳደረሳቸዉ መዘገባችን ይታወሳል።
በዚህ ፍንዳታ ምን አልባትም የአልሸባብ ቡድን እጁ አለበት ሲባል የቆየ ቢሆንም አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን አለመዉሰዱና ፍንዳታዉ የሕዉሐት እጅ እንዳለበት የሚያሳዩ አንዳንድ መረጃዎች እየወጡ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
የኢትዮጵያ መንግስትን በበላይነት የሚቆጣጠረዉ የሕዉሐት ቡድን በአገር ዉስጥ በከፍተኛ ሕዝባዊ ሱናሚ እየተናወጠ በዉጭም በHR128/SR168 ከፍተኛ ቀዉስ የገጠመው በመሆኑ ከዚህ አጣብቂኝ በተለይ ዓለም ዓቀፉን እርዳታና ድጋፍ ለማግኘት የሔደበት ጉዞም ነዉ ሲሉ እነዚሁ የወጡት መረጃዎች ያሳያሉ። የሕዉሐት ቡድን በአለም አቀፉ የአሸባሪ መዝገብ ላይ ስሙ ሰፍሮ እንድሚገኝም ይታወቃል።
በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከሚደረገዉ የሕዝብ አመፅ በተጨማሪ የHR128 ረቂቅ አዋጅ የባለስልጣናቱን ቤተሰብን ጨምሮ ከፍተኛ ጭንቀት ዉስጥ እንደከተተ የሚታወቅ ሲሆን ሕዉሐት የዚህ ረቂቅ መጽደቅ የሕልውናቸው ማክተሚያ እድርገዉ እንደሚያዩትም የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
ከመቋዲሾ የቦንብ ፍንዳታ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካ ተወካዮች ለአሜሪካ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ሰራዊት ከሱማሊያ መዉጣት ለዚህ አይነት አደጋ ሱማሌን እንደጋበዛትና የነሱ ሱማሌ ዉስጥ መቆየት የተሻለ እንደሆነ ለማግባባት መሞከራቸዉን ለማወቅ ተችሏል።
የኢትዮጵያ አገዛዝ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዓቀፉ ማሕበረሰብም ጨምሮ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ያመጣል የሚል እምነታቸዉ ከዜሮ በታች መሆኑ በሚገለጽበት በአሁኑ ሰዓት የመቀሌዉ የሕዉሐት ስብሰባም በተለይ በኤርትራ ጉዳይ ላይ የሕዉሐትን ጉባኤ 3 ቦታ መክፈሉና ስብሰባዉም ስምምነት ላይ ሳይደርስ ማለቁንም ለማወቅ ተችሏል::
http://amharic.abbaymedia.com/archives/37454