በሶማሊያ በደረሰዉ የቦንብ ፍንዳታ የሕወሓት እጅ አለበት!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በሶማሊያ በደረሰዉ የቦንብ ፍንዳታ የሕወሓት እጅ አለበት!

Postby ኳስሜዳ » Sat Oct 21, 2017 10:56 am

በኦክቶምበር 14 በሶማሊያ ዋና ከተማ በሆነችዉ መቋዲሾ ከፍተኛ የሆነ የቦንብ ጥቃት መድረሱ የሚታወስ ሲሆን በዚሁ የቦንብ ጥቃት ከ300 ሰዉ በላይ ንጹሃን ዜጎችን ቀጥፎ ከ 400 በላይ የሆኑትን ለክፍተኛ አካል ጉዳት እንዳደረሳቸዉ መዘገባችን ይታወሳል።

በዚህ ፍንዳታ ምን አልባትም የአልሸባብ ቡድን እጁ አለበት ሲባል የቆየ ቢሆንም አልሸባብ ለጥቃቱ ሃላፊነቱን አለመዉሰዱና ፍንዳታዉ የሕዉሐት እጅ እንዳለበት የሚያሳዩ አንዳንድ መረጃዎች እየወጡ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ መንግስትን በበላይነት የሚቆጣጠረዉ የሕዉሐት ቡድን በአገር ዉስጥ በከፍተኛ ሕዝባዊ ሱናሚ እየተናወጠ በዉጭም በHR128/SR168 ከፍተኛ ቀዉስ የገጠመው በመሆኑ ከዚህ አጣብቂኝ በተለይ ዓለም ዓቀፉን እርዳታና ድጋፍ ለማግኘት የሔደበት ጉዞም ነዉ ሲሉ እነዚሁ የወጡት መረጃዎች ያሳያሉ። የሕዉሐት ቡድን በአለም አቀፉ የአሸባሪ መዝገብ ላይ ስሙ ሰፍሮ እንድሚገኝም ይታወቃል።

በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከሚደረገዉ የሕዝብ አመፅ በተጨማሪ የHR128 ረቂቅ አዋጅ የባለስልጣናቱን ቤተሰብን ጨምሮ ከፍተኛ ጭንቀት ዉስጥ እንደከተተ የሚታወቅ ሲሆን ሕዉሐት የዚህ ረቂቅ መጽደቅ የሕልውናቸው ማክተሚያ እድርገዉ እንደሚያዩትም የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

ከመቋዲሾ የቦንብ ፍንዳታ በኋላ የኢትዮጵያ መንግስት በአሜሪካ ተወካዮች ለአሜሪካ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ ሰራዊት ከሱማሊያ መዉጣት ለዚህ አይነት አደጋ ሱማሌን እንደጋበዛትና የነሱ ሱማሌ ዉስጥ መቆየት የተሻለ እንደሆነ ለማግባባት መሞከራቸዉን ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ አገዛዝ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በዓለም ዓቀፉ ማሕበረሰብም ጨምሮ ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ያመጣል የሚል እምነታቸዉ ከዜሮ በታች መሆኑ በሚገለጽበት በአሁኑ ሰዓት የመቀሌዉ የሕዉሐት ስብሰባም በተለይ በኤርትራ ጉዳይ ላይ የሕዉሐትን ጉባኤ 3 ቦታ መክፈሉና ስብሰባዉም ስምምነት ላይ ሳይደርስ ማለቁንም ለማወቅ ተችሏል::

http://amharic.abbaymedia.com/archives/37454
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2146
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Re: በሶማሊያ በደረሰዉ የቦንብ ፍንዳታ የሕወሓት እጅ አለበት!

Postby ደጉ » Sat Oct 21, 2017 7:42 pm

ኩዋስ ሜዳ ይመስለኛል አልሻባብንም ሆነ አይሲስን የምሰረቱት አሜሪካኖችም ሆኑ ምእራባውያኑ ስለ አልሻባብ በደንብ ያቃሉ ..የ ወያኔ መንግስትን እነ ኦባማ እንደ ኮንዶም ነው የተጠቀሙበት ...ዋናው ነገር የ አሜሪካን ወታደሮች አይሙቱ ...ወያኔም ቢሆን ስለ ሚያገኝው ገነዝብ እንጂ ለ ድሀው ወታደር ህይወት ቅንጣት እሚያስብ አይደለም
HR128/SR168 ወያኔ ዲሞክራሲያዊ ..ልማታዊ መንግስት ነኝ እያለ ለመን ይሄን እንደፈራው አልገባኝም ቅቅቅቅቅ ፈሩም ምንም ሆኑ እሚያመልጡ አይመስለኝም በመን አቅማቸው ስልጣን ላይ ያወጣቸው እያሩዋሩዋጠ ያወርዳቸዋል ቅቅቅቅ
ከዚህ ሁሉ ስልጣኑን አስረክበው ሲንከር ጫማ ገዝተው ሮጠው ቢወጡ ይሻላቸዋል ... ለመአት ሆነው አገር መዝረፍ እንጂ መምራት አልቻሉም፡፡ ይሄ ደግሞ ለ አመታት እያየነው ያለ ነው ፡-)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4413
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: በሶማሊያ በደረሰዉ የቦንብ ፍንዳታ የሕወሓት እጅ አለበት!

Postby ቢተወደድ1 » Wed Nov 01, 2017 11:16 am

በእንግሊዘኛ ሳኩብሽ
ቂቃቂቃቂቂቂቂ
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 210
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests