በኢሉባቦር የብሔር ጦርነት ተቀሰቀሰ በማለት ENN በሰበር ዜና ዘገበ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በኢሉባቦር የብሔር ጦርነት ተቀሰቀሰ በማለት ENN በሰበር ዜና ዘገበ!

Postby ኳስሜዳ » Sun Oct 22, 2017 7:51 pm

በኢሉባቦር ዞን በአማራና ኦሮሞ ብሔር መካከል የእርሰበርስ ጦርነት ተከፈተ በሚል ርእስ ንብረትነቱ የህወሃት የሆነው ENN ቴሌቪዢን ጣቢያ በሰበር ዜና አቀረበ።

የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት በኢሉባቦር ዞን በደጋና ጮራ ወረዳዎች ከጥቅምት አስር ጀምሮ እጅግ በርካታ ማንነታቸው ያልታወቀ ጸጉረ ልውጥ ሰዎች በአካባቢው በታዩ ማግስት የአማርኛን ቋንቋ ተናጋሪዎችን እየነጠለ
የተካሄደ ዘግናኝ ጥቃት/ጭፍጨፋ መካሄዱን ይናገራሉ።

ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ የአማራ ተወላጆች ላይ አሰቃቂ እርምጃ መፈጸሙን ለማወቅ የተቻለ ሲሆን ህይወታቸውን ለማዳን የተፈናቀሉትም በሺህ የሚቆጠሩ መሆናቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ንብረትነቱ የህወሃት የሆነው ENN ቴሌቪዢን ጣቢያ ዛሬ በሰበር ዜና እወጃው በዞኑ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ በኦሮሞ ተወላጆች እየተፈጸመ ያለ ጥቃት በሚል ሃላፊነት በጎደለውና የብሔርን ግጭት በሚያባብስና በሚያቀጣጥል መልኩ ሲዘግብ ተስተውላል።

በቅርቡ ጣናን ኬኛ በሚል መሪ መፈክር ከ200 በላይ የኦሮሞ ወጣቶች ጣናን ለመታደግ ወደ ባሕር ዳር በተጋዙበት ወቅት የህወሃት ድርጅት ደስተኛአለመሆን ብቻ ሳይሆን ፕሮግራሙንም ከእነ አካቴው ለማስቀረት ሞክሮ እንዳልተሳካለት ይታወቃል።

የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር መገናኛ ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ በኦህዴድ ወሳኝ የለውጥ እርምጃ ጥቅማቸው የተነካባቸው ሃይሎች በህዝባዊው ዓመጽ ውስጥ ተደብቀው የእርሰበርስ ብጥብጥና ሁከት የሚፈጥር እርምጃ እየወሰዱ ነው በማለት ለቪ.ኦ.ኤ የገለጹ ሲሆን በዚህ ተግባር የተያዙ ያላቸውንም ከመቶ በላይ ተጠርጣሪዎችን መያዛቸውን ገልጸው እንደነበር አይዘነጋም።

በተያያዘ ዜና በአምቦ ከተማ የኦሮሞ ቄሮ ተመስሎ ንብረትነቱ የአማራ ተወላጅ የሆነ ቤት ለማቃጠል የሞከረ የህወሃት ሰላይ በቄሮዎቹ ጥረት መያዙ የኦሮሚያ ፖሊስ አስታውቋል።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests