ትዝብት [፪] - አቻምየለህ ታምሩ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ትዝብት [፪] - አቻምየለህ ታምሩ

Postby ዘረ ያቆብ » Fri Oct 27, 2017 10:04 pm

Image

ትዝብት [፪]

ኢትዮጵያን እያጋጠማት ያለውን ችግር በተንሸዋረረ አይን እያየንና በግማሽ አእምሮ እያሰላን ብቻ ስላስተጋባናው ሊቃለል አይችልም። እንደ አንድ አገር ሰዎች አንድ ልብ መሆንና አንድ ግንባር መፍጠር ያቃጠን ችግራችንን እዚህም እዚያም በሚፈጠሩ ወቅታዊ ሞቅታዎች በመሸፈን እያቃለልንና የትናንትናውን ሙሉ በሙሉ በመርሳታችን ይመስለኛል።

ላንዳንዶቻችን እውነታው መራርም ቢሆን ከችግራችን ጋር ኮስተር ብለን እንድንታገል የተጋረጠብንን ችግር ከምንጩ ማወቅ ያስፈልጋል። ራሳችንን በራሳችን መደለል ካልፈለግን በስተቀር ኦሮሞንና አማራን ለማለያየት የቀሰቀሰውና የሚቀሰቅሰው ወያኔ ብቻ አይደለም። በርግጥ ወያኔ ስልጣን ላይ እንዳለ ነውረኛ ቡድን የሚፈልገውን ለማሳካት ኦሮሞንና አማራን ለማለያየት የተዘራውን የጥላቻ ዘር ፍሬ ተጠቅሞበታል።

እውነቱን እንነጋገር። ወያኔ አማራና ትግሬን በማለያየትና ትግሬ በአማራ ላይ እንዲነሳ በመቀስቀስ ፖለቲካውን እንደጀመረ ሁሉ ኦሮሞና አማራ እንዲለያዩ በመቀስቀስ ከምስረታው ጀምሮ የአማራን ጥላቻ የትግሉ ሞተር ያደረገው ኦነግ ነው። ወያኔ ዛሬ ያደረገው ነገር ቢኖር ኦነግ አማራና ኦሮሞን ለማለያየት የቀመመውን የጥላቻ መርዝ ከብልቂያጡ በማውጣት የግፍ ዘመኑን ለማራዘም መጠቀሙ ብቻ እንጂ ጥላቻውን የዘራው ኦነግ ነው።

በኢትዮጵያ ውስጥ እንደ አማራና ኦሮሞ የተዋሃደና የተዋለደ ኢትዮጵያዊ የለም። አማራ በተደራቢነት የራሱ ያደረገው የኦሮሞ ወግና ባህል ተቆጥሮ አያልቅም። ኦሮሞም በተደራቢነት የራሱ ያደረገው የአማራ ወግና ባህል የትየለሌ ነው። አማራና ኦሮሞ ለዘመናት የተገመዱበትንና በመካከላቸው እንደ ድልድይ ሆነው ለዘመናት ያገለግሉ የነበሩ ማናቸውንም ነገር ሁሉ በመበጣጠስ ረገድ የኦነግን ያልህ በደልና ጥፋት የፈጸመ የለም። ዛሬም ድረስ «አማራ አታግቡ!» እያሉ የሚቀሰቅሱ እዚህ ማህበራዊ መድረኮች ሲሳተፉ የምናውቃቸውን ኦነጋውያን በስም መጥቀስ እንችላለን።

ኦነግ የዘራው የመከፋፈል ፍሬ ሙሉ በሙሉም ባይሆን በከፊል ፍሬ አፍርቷል። አንዱና ትልቁ ፍሬ የወያኔ የ26 ዓመታት የግፍ ዘመን ነው። ዛሬ ወያኔ ስልጣን ላይ ያለው ኦነግ የዘራውን የጥላቻ ፖለቲካ ተጠቅሞ ኦሮሞና አማራን በማለያየት የኢትዮጵያን ጉልበት አዳክሞ የራሱን ጡንቻ በማፈርጠሙ ነው። ትናንት ብቻ ሳይሆን ኦነጋውያን ዛሬም የሚሰሩት ወያኔ በግፍ ዙፋኑ ላይ የበለጠ እንዲደላደል ነው። ይህ እንዴት እንደሆነ ላስረዳ።

ኦነጋውያን ለኦሮሞ ወጣቶች ሲያስተምሩ አማራ የድሮ ስርዓት ናፋቂ እንደሆነና አማራ ወያኔን የሚታገለውም ያ ትውልድ ያሰየጠነውንና «የድሮ ስርዓት» የሚሉትን ለመመለስ እንደሆነ አድርገው ነው። በሌላ በኩል ዛሬ ወያኔ እየመተረን ያለበትን የጭካኔ አገዛዝ ደግሞ የነሱም የትግል ፍሬ ውጤት እንደሆነ አድርገው ይደሰኩሩላቸዋል። በዚህ የተነሳ የስብከታቸው ሰለባ የሆነው የኦሮሞ ወጣት ከወንድሙ ከአማራ ወጣት ጋር ተባብሮ ወያኔን ለመጣል መታገልን ሲያስብ ከፊቱ ድቅን የሚለው ኦነጋውያን ያስተማሩት ኦነጋውያን ያሰየጠኑትን «የድሮ ስርዓትን» መመለስ የሚለው ስብከት ነው።

በዚህ የተነሳ ወያኔን አንቅሮ የተፋው የኦሮሞ ወጣት ከአማራ ጋር አብሮ መታገልን ሲያስብ የድሮ ስርዓትን ከመመለስ ወያኔ ይሻላል የሚለውን የኦነግ ስብከት አሰሮ ይይዘዋል። ባጭሩ የኦሮሞ ወጣት ከአማራ ወጣት ጋር ተባብሮ ትግል በማድረግ ወያኔን አስወግዶ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንዳይገነባ አማራ የሚታገለው የድሮ ስርዓትን ለመመለስ ነው የሚለው የኦነግ ፖለቲካ ሳንካ ሆኖበታል።

ኦነጋውያን ዛሬም ቢሆን አይናቸው እያየ ወያኔ ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ኦሮሞ በአገሩ ውስጥ ስደተኛ እንዲሆን ሲያደርግ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሞ እንቦቀቅላዎች በትግራይ ወታደሮች ጥይት ሲረግፉ እየተመለከቱ፤ ከጸረ ወያኔ ተጋድሎ ይልቅ ጸረ ምኒልክና ጸረ ኢትዮጵያ ዘመቻ ካላደረጉ የአለም መጨረሻ መስሎ ይታያቸዋል። ይህ ፖለቲካቸው ለወያኔ ጉልበት ሆኗል፤ ከወያኔ ፕሮግራም ባልተናነሰ ኢትዮጵያውያንን አለያይቷል። ለዚህም ነው ኦነግና ስብከቱ የጋራ ትግል እንዳናከሂድ በማድረግ ወያኔን በግፍ ዙፋኑ ላይ የበለጠ እንዲደላደል እያደረገው ይገኛል ያልሁት።

ባጭሩ ከወያኔ ባልተናነሰ የኦነግ ፖለቲካ ኦሮሞ ከአማራ ጋር ሆኖ በወያኔ ላይ በተባበረ ክንድ እንዳይዘምት አድርጎታል ባይ ነኝ። ኦሮሞ ከአማራ ጋር የሚጋራውን ታሪክ፣ ደም፣ ባህል፣ ቋንቋ፣ እምነት፣ ወዘተ ያህል ከማናቸውን የኢትዮጵያ ነገድ ጋር አይጋራም። ኦነጋውያን ግን ኦሮሞን ከአማራ ጋር ከማሰብ ኦሮሞ ከአማራ ያነሰ ትስስር ካለው ጋር የሌለ ትርክት ሁሉ እየፈጠሩ አንድ እንደሆነ ለማሳየት ሲኳትኑ ትውላሉ።

ስለዚህ ጭንቅላታችንን አሸዋ ውስጥ ቀብረን፤ አንጎላችንን መርገን፤ ማሰቢያችንን ደፍነን ካልሆነ በስተቀር ኦሮሞና አማራን የማጋጨቱን ተልዕኮ ለወያኔ ብቻ መስጠታችን ችግራችንን አያቃልለውም። የዛሬ ወጣቶች ያለፈው ትውልድ የስልጣን ጥሙን ለማስታገስ የፈጠራቸውን የጥላቻ ትርክቶችና የፈጠራ ታሪኮች በመመርመር የተዋሸነውን በትንቃቄ ማጤንና በሙሉ አዕምሮ፣ በሁለት አይናችን በመመልከት በሀቀኛ ጎዳና ወደፊት መራመድ ካልቻልን ካጋጠመውን ችግር ልንወጣና በጠላቶቻችን ላይ አስተማማጭ ድል ልናገኝ አንችልም።

አቻምየለህ ታምሩ
ዘረ ያቆብ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 123
Joined: Fri Aug 22, 2003 1:10 am

Re: ትዝብት [፪] - አቻምየለህ ታምሩ

Postby ደጉ » Sat Oct 28, 2017 1:19 pm

በጣም ጥሩ ትዝብት ነው ...ነገሮችን በተለያየ መልኩ ማየት እንዳለብን ያሳያል .... ብዙ ነገሮች በ ኦነግ እንደሚፈርሱ ያለፍንበት ታሪክ ያስያል ለህዝቡ ችግር መባባስ የነሱ የጥላቻ ፖለቲካ መሆኑ መቼ እንደሚገባችው አላቅም...አንዳዶቹ ግን ትንሽ ትንሽ እየገባቸው ይመስላል .. :-)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4416
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests