የህወሃት ቁልፍ የመረጃ ሰራተኞች ወታደራዊ ጥቃቶች!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የህወሃት ቁልፍ የመረጃ ሰራተኞች ወታደራዊ ጥቃቶች!

Postby ኳስሜዳ » Mon Nov 20, 2017 1:53 pm

የህወሃት ቁልፍ የመረጃ ሰራተኞች ወታደራዊ ጥቃቶችን በተመለከተ ተደጋጋሚ መልእክቶችን ወደ ወታደራዊ ደህንነቱ እያስተላለፉ ነዉ እነሆ የጥይት ድምጾች የባሩድ ጠረኖች በህወሃት የመከላከያ መንደር ከአርበኞቹ ዘንድ መንፏለል ከጀመረ ቀናቶች ተቆጠሩ በህወሃት የመከላከያ ሐይል ላይ አንድ ግራ የሆነ ነገር ተከስቷል… አርበኞቹ የት መቼ እንደሚመጡ ያዉቃሉ የህወሃት መከላከያ ወይም ወታደራዊ ደህንነቱ ደግሞ አያዉቅም።

ወታደራዊ ደህንነቱ አለኝ በሚለዉ የስለላ ስልት መሰረት ከወራቶች በፊት የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት የተጠናከረ ሐይል እርሱም ” በቂ ገንዘብ ጥቂት ሰርጎ ገቦች በቂ ትጥቅ ጥቂት ግለሰቦች ” አሰግስጎ አስገብቷል…. የሚል ሲሆን ይህንን ለማረጋገጥና ለማጣራት ከተሄደበት ስልት በቀደመ ሁኔታ ሰርጎ ገቦቹ ከዉስጥ ሐይሎች ጋር በመናበብና በመቀናጀት ጥቃት መፈጸማቸዉን አረጋጧል።

የደህንነቱ ክንፍ ጥቃት ከተፈጸመ በሗላ ሁል ግዜም እንደሚያደርገዉ ከአርበኞቹ ጋር ግንኑነት ይኖራቸዋል ተብሎ የሚገመታቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባላት በመላምት ማሳደዱን ቀጥሎበታል።

በሰራዊቱ ዉስጥ እየኖሩ መመሪያ የሚሰጡ እና ጥበቃ የሚደረግላቸዉ የመከላከያ መኮንኖች ላይ የተደረጉ ጥቃቶችን ግምት ዉስጥ ባስገባ መልኩ በራሱ በሰራዊቱ ዉስጥ መሰረታዊ አለመተማመንን እየተፈጠረ እንደሚገኝ ያመለከተዉ ምንጫችን.. አያይዞ የአርበኞች ግንቦት 7 የተጠና የጥቃት ስልት የ24ተኛ ክፍለ ጦርንና የ41ኛ ክፍለ ጦርን እየገዘገዘዉ እንደሚገኝ አመላክቷል።
ልዑል አለሜ
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2162
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests