የህወሓት አባላት የትግራይ ተወላጆች የነበሩበትን ቦታ ለቀው እየወጡ ነው ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የህወሓት አባላት የትግራይ ተወላጆች የነበሩበትን ቦታ ለቀው እየወጡ ነው ፡፡

Postby ኳስሜዳ » Mon Nov 20, 2017 9:06 pm

ህዳር 9 ቀን 2010 ዓ/ም ከሰዓት በኃላ በመከላከያ ታጅበው እቃቸውን በመጫን በሰሜን ጎንደር ዞን በጎንደር ከተማ ይኖሩ የነበሩ የህወሓት አባላት በመውጣት ላይ ናቸው በተለይም በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 እና በአራዳ ቀበሌ 07 የሚኖሩ የህወሓት አባላት በመከላከያ እየታጀቡ በመውጣት ላይ ሲሆኑ የአካባቢው ህብረተሰብም በመውጣታቸው ደስታውን ይገልፅ ነበር ፣

"እናንተ ባዶጃቹሁን መጥታቹሁ ከእኛ አገር ሀብታም ሁናቹህ በዚህ ማመስገን ሲገባቹህ እኛን ታስገድላላቹህ ፡ ታሳስራላቹህ ፡ መሬታችን ትወስዳላቹህ ፡ አሁን ደግሞ እርቅ እያላቹህ ታፊዙብን አላቹህ " ወዘተ የሚል ወቀሳ የቀረበባቸው ሲሆን እነሱም ኤርትራዊያንን ሲባረሩ በእንባ ሸኝተው እኛን በስድብ የሚያባሩን ህዝቡ ለጭካኔ እና ለርምጃ መዘጋጀቱን ያሳያል " ብለዋል አንዳንዶቹ ባለፈው ወደ ትግራይ ከሄድ በኃላ ሁኔታው ተረጋግታል ብለው በራሳቸው እና በካድሬዎች ግፊት የተመለሱ ነበሩ ፡

አሁን "ለቀን ለመሄድ ያነሳሳን መንግስት የነበረውን ችግር ዘላቂ መፍተሄ መስጠት ሲገባው ነገሮችን አለባብሶ በተለይም የወልቃይትና የጠገዴን ጥያቂ አለመፍታቱ እየቀረበ ያለውን የመልካም አስተዳደር ጥያቂ አለመመለሱን እንዴሁም አንዳንድ የብአዴን ሰዎች እኛን በጠላትነት እያዩን ነው በዚህ ሁለት ቀን ቦንቦች ተወርውረውብናል የጥይት ተተኩስ ማታ ማታ እየተለመደ መጥታል በአሁኑ ጊዜ አይደለም ለሊቱ ቀንም አስፈሪ ሁኖብናል ፡ በተለይም እርቅ በማለት ጎንደር ላይ የተደረገው ስብሰባ ለነገሮች መፍትሔ ሳይሆን የሰጠው ነገሮችን እጅግ ነው ያባባሳቸው ፡ በቅርብም ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ እርምጃ እንደሚወስድ ፍንጮች ታይተዋል ፡ በመሆኑም ለአንዳንድ የህወሓት አመራሮች ችግሮቻችንን ብንነግራቸውም ፡ ችግሩ በቅርብ ቀን ይወገዳል ማለት እንደማይችሉ ነገር ግን ብአዴን ራሱን አደሚፈትሽና በትምክህት የተወጠሩ አመራሮች እስከ ሚተነፍሱ ጊዜ ይወስዳል የሚል ምላሽ ስለሰጡን እኛም ተስፋ ቆርጠን እየወጣን ነው " ብለዋል ፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ባለፈው ሳምንት በደቡብ ወሎ ደሴ ከተማ ያሉ የህወሓት አባላት እወጡ እንደሆነ መግለፃችን ይታወቃል ፡፡ በመሆኑም ህወሓት እየተከተለው ያለው የዘረኛነት አገዛዝ በመጨረሻው ጊዜ የኢትዮጰያ ህዝብ በመንቃቱ ራሱን ዘረኛውን ህወሓትን ዋጋ እያስከፈለው ይገኛል ፡፡
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2155
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 8 guests