ዜና ከጎንደር! ህዝቡ እምብይ ብሏል! –

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ዜና ከጎንደር! ህዝቡ እምብይ ብሏል! –

Postby ኳስሜዳ » Mon Nov 20, 2017 11:48 pm

ሰበር ዜና ከጎንደር! ይሰራጭ!
♦ህዝቡ እምብይ ብሏል!
♦የህዝብ የሙያ ማህበራት አንሳተፍም አሉ!
♦ታዋቂ የሃገር ሽማግሌዎችም ጥሪውን አልተቀበሉም!
♦የጎንደር ህዝብ ተጠይፎናል፦ ጉባኤተኛ ትግሬወች!
ህዳር 9 2010
ጎንደር

ወያኔና ብአዴን ዛሬ በከፈቱት እናሞኛቹህ ድራማ ከመነሻው ጀምሮ የህዝብ ቁጣና ማግለል ገጥሞታል። ሲገቡ ተሸማቀው ከተማውን በወታደር አሳጥረው ነው። ዛሬ በክከፈተው የድራማ ጉባኤ ደግሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተለያዩ የጎንደር ህዝባዊ የሙያና ንግድ ማህበራት አባላት እርቁ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ትናንት ትዕዛዝ ቢሠጣቸውም አሳስተፍም ብውለ ወስነው ቀርተዋል። የህዝባቸውን እውነተኛ እልህና ቁጭት የተረዱት ማህበራት ከህዝብ ውጭ አንሆንም ብለዋል። ህዝቡን ባይሰሙ ሊደርስባቸው የሚችለውንም ከባድ እርምጃ ቀድሞ እንደተነግሯቸውና ይህን አክብረው ከድርጊቱ ራሳቸውን ማግለላቸው ታውቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለእርቁ የፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ተፅእኖ ፈጣሪ ሰወች በየግላውቸ ህዝቡ ማስጠንቀቂያወችን ስላደረሳቸው ፕሮግራሙ ላይ ሳይሳተፉ ቀርተዋል። ፕሮግራሙን ወያኔወች ብቻቸውን ከብአዴን ካድሬወች፣ ሊጠብቋቸው ከመጡ ወታደር መኮንኖች እና ብዛት ካላቸው ቄሶች ተቀምጠውበታል፡፡ ለእርቅ መጥተን ጎንደሮች ተጠየፉን ሲሉ አንድ ታዳሚ የትግራይ ቄስ በምሬት ተናግረዋል። የእቅድ መክሸፉ ያጋጠመው ወያኔ ከፍተኛ የሆነ ንዴትና ከባድ ጭንቅ ውስጥ ነው። ይህን ዜና ከምስሉ ጋር አስተያዩት።

የጎንደር ህዝብ ተቃውሞ በዚህ እንደማይቆም የደረሰን መረጃ አስጠንቅቋል::
አስናቀው አበበ
Image
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2155
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests