ወያኔ የፈረንሳዩን እውቅ ዘጋቢ አባረረ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያኔ የፈረንሳዩን እውቅ ዘጋቢ አባረረ

Postby እሰፋ ማሩ » Wed Nov 22, 2017 4:39 pm

የሰው ልጆችን መብት በማፈን በአፍሪካ ቀዳሚ የሆነ ወያኔ የፈረንሳይ ዜና ዘጋቢን አባረረ፡፡የፈረንሳዩ ምሁርና ዘጋቢ የተባረሩት የወያኔን ግፍ እንደተለመደው እንዳያጋልጡበት ነው፡፡
November 22, 2017 – ቆንጅት ስጦታው
ፈረንሳዊው ምሁር ሬኔ ለፎ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ህዳር 5 ቀን 2010 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ አምርተው ነበር፡፡ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንደደረሱ ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው በቀጥታ ወደ ፓሪስ መመለሳቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ ሀገራት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በሚያቀርቧቸው ትንታኔያቸው ስማቸው ጎልቶ ይጠራል፡፡ ፈረንሳዊው ጸሀፊ ሬኔ ለፎ፡፡ ለረጅም ዓመታት በጋዜጠኝነት በፈረንሳይ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ አሁን ደግሞ በጥናት እና ምርምር ጽሁፎችን በማቅረብ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሬኔ ለፎ ለበርካታ ጊዜያት ወደ ኢትዮጵያ ሲመላለሱ ቆይተዋል፡፡ ፓሪስ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የጠየቁትን የስራ ቪዛ ካገኙ በኋላ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ወደ አዲስ አበባ ያመሩት ለፎ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ ያልጠበቁት ነበር ያጋጠማቸው፡፡ በአየር ማረፊያ ከሚገኙ የኤምግሬሽን ኃላፊዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንደማይችሉ ተነግሯቸው በቀጥታ ወደ ፓሪስ እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 2 guests