የፈራ ይመለስ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የፈራ ይመለስ!

Postby ኳስሜዳ » Thu Nov 23, 2017 1:45 pm

Image
የፈራ ይመለስ! አዎ የፈራ ይመለስ ። ትግሉ ቁርጠኝነትን ፤ ትግሉ ልበ ሙሉነትን ፣ ትግሉ ድፍረትን ፣ ትግሉ ጥንካሬን ፣ ትግሉ እውነተኛነትን ፣ ትግሉ ታማኝነትን ይፈልጋል። በተገኘ የወሬ ናዳ አሊያም በተሰማና በተነበበ የፈጠራ ዜና ለውጥ አይመጣም። መሬት ላይ በረገጠ እውነት ሕዝብ ነጻ ይወጣል። መሬት ላይ በረገጠ እውነት የሕዝብ መብት ይረጋገጣል። ወደ መሬት ወርዶ ለመታገል የፈራ ይመለስ። ብስለት ፣ ጥንቃቄ ፣ ጥንካሬ፣ ብልሃት ፣ ትብብር ፣ መቻቻል ፣ የአርበኝነት ወኔና ለምን እንደምንታገል ማወቅ ትልቁ የድል ስኬት ነው። አሉባልታ ፣ ፍረጃ ፣ ስም ማጥፋት፣ የወሬ ናዳ ፣ የፈጠራ ዜና፣ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ የፈሪ ስለሆነ የፈራ ይመለስ። የግፍ ፅዋ ሞልቶ ለኢትዮጵያውያን ጎርፍ ስለሆነ ወደ መሬት ወርዶ ሰፊ ስራ መስራት የሁሉም ለለውጥ እታገላለሁ የሚል ዜጋ ግዴታ ነው። የፈራ ይመለስ!
ምንሊክ ሳልሳዊ
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2162
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests