በወያኔ ብልቱ የተኮላሸ ታሳሪ ለፍርድ ቤት አሳየ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በወያኔ ብልቱ የተኮላሸ ታሳሪ ለፍርድ ቤት አሳየ

Postby እሰፋ ማሩ » Sat Nov 25, 2017 4:54 am

ዶቼቬሌ የጀርመን ራዲዮ ኖቬምበር 24/2017
ወያኔ በኢትዮጲያ የሰው መብት ክፉኛ በመጣስ ላይ ሲሆን ይህን የሚቃወሙ እጅግ አረመኔያዊ ግርፋትና ግድያ እየደረሰባቸው ይገኛል፡፡
በእስር ቤት እንግልትና ሰቆቃ የደረሰባቸው እስረኞች በፍርድ ቤት ስለሚገጥማቸው በደል የሚያወሱ ጽሑፎች በማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ተነበዋል። ከጽሑፎቹ መካከል አንድ ታሳሪ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ሲማጸኑ ከዳኞች ፈቃድ ባለማግኘታቸው «ህዝብ ይፍረደኝ» ብለው በሰቆቃ የተኮላሸ ሐፍረታቸውን በፍርድ ቤት ውስጥ አሳዩ፤ «ያለቀሱም ነበሩ» የሚለውን ጽሑፍ ብዙዎች በትዊተር እና በፌስቡክ ተቀባብለውታል።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1526
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: በወያኔ ብልቱ የተኮላሸ ታሳሪ ለፍርድ ቤት አሳየ

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Dec 07, 2017 5:33 pm

ጨካኙ ወያኔ የሰላማዊ ዜጎችን ብልት መቀጥቀጥ ማኮላሸት ቀጥሏል፡፡
ዳንሻ ወስደው ደብድበውኛል፣ ከዛ ወደ ትግራይ ወሰዱኝ…(ጌታቸው ሽፈራው)
ሳተናው
December 5, 2017
“ህዳር 9/2009 ዓም ከእርሻ ስመለስ ነው የያዙኝ። ዳንሻ ወስደው ደብድበውኛል። ከዛ ወደ ትግራይ ወሰዱኝ። ወደ ትግራይ መሆኑን ከመገመት ውጭ ልዩ ቦታውን አላውቀውም። ትልቅ ጉድጓድ ውስጥ አስገቡኝና ግንዱ ላይ በተጠለፈ ገመድ አስረው ጉድጓዱ ውስጥ አስቀመጡኝ። የታሰርኩት ያለ ምግብና ያለ ውሃ ነው።

ከዛም ወደ ሁመራ መለሱኝ። ለረዥም ሰዓት እጆቼን ወደኋላ አስረው ፀሀይ ላይ አስጥተውኝ ዋሉ። ሁመራ ካለው የወታደራዊ ካምፕ ነው። በዱላ ክፉኛ ደብድበውኛል። በዛን ወቅት ነው ብልቴን የመቱኝ። አሞኝ ስለነበር ማዕከላዊ አላስገቡኝም። ያቆዩኝ ባህርዳር ነው። ብልቴን ስለመቱኝ ለረዥም ጊዜ ተሰቃይቻለሁ።

ቂሊንጦ ከመጣሁ በሁዋላ እንኳ ለሶስት ወራት ያህል ህክምና ማግኘት አልቻልኩም ነበር። ቃሊቲ ጤና ጣቢያ ከ5 ጊዜ በላይ ተመላልሻለሁ። ፖሊስ ሆስፒታል ለሶስተኛ ጊዜ ተመላልሻለሁ። ከዛ በኋላ ነው ጥቁር አንበሳ እየታከምኩ ያለሁት። በድብደባው ምክንያት ከብልቴ በተጨማሪ ሆዴ ላይ ጉዳት ደርሶብኝ ነበር። በቀዶ ጥገና ተደርጎልኛል።”

በእነ ሚፍታህ ሸህ ሱሩር 74ኛ ተከሳሽ ፈረደ ክንድሻቶ ይርጋ ከተናገረው የተወሰደ ነው። ፈረደ በደረሰበት ጉዳት ሱሪ መልበስ አይችልም። በጉዳቱ ምክንያትም ያነክሳል።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1526
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: በወያኔ ብልቱ የተኮላሸ ታሳሪ ለፍርድ ቤት አሳየ

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Dec 28, 2017 4:51 am

እስረኞችን የማስታወስ ዘመቻ
ታህሳስ 28, 2017
ጽዮን ግርማ
እስረኞቹ በምርመራ ወቅት አሰቃቂ ተግባር እንደተፈፀመባቸና ይህንንም ችሎት በሚቀርቡበት ወቅት እንደሚናገሩ አንዳንዶቹም ልብሳቸውን ገልጠው የተጎዳውን የሰውነታቸውን ክፍል ለችሎት እንደሚያሳዩ ጠበቀቻቸው ተናግረዋል።
ዋሽንግተን ዲሲ —
በአስተሳሰብና በአመለካከት ልዩነታቸው ብቻ በአሸባሪነት ተፈርጀው በእስር ላይ የሚገኙ እስረኞችን ለማሰብ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የአንድ ቀን ዘመቻ ማድረጋቸውን አስተባባሪዎቹ ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
የእስረኖቹ ቁጥር ለጊዜው እንደማይታወቅ የገለጹት አስተባባሪዎቹ በኦሮሚያና በአማራ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ተሳትፋችኋል በሚል በሽብር የተከሰሱት ሰዎችች ቁጥር ከ1,500 እንደሚበልጥ ይናገራሉ።በአሁኑ ሰዓት 900 ለሚደርሱ እስረኞች ጥብቅና ከሚቆሙ ጠበቆች መካከል የተወሰኑት ፤ ለአሜሪካ ድምጽ ሲናገሩ “እስረኞቹ ፍርድ ቤት በሚቀርቡበት ጊዜ ብልታቸው ላይ የውኃ ላስቲክ እየተንጠለጠለ እንደሚሰቃዩ ከመግለፅ ጀምሮ አሰቃቂ ድብደባ እንደሚፈፀመባቸው ለፍርድ ቤት ያስረዳሉ” ብለዋል።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1526
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests