ሕወሃት እንኳን ተለውጦ ሞቶም ከራሱ የበላይነት ሌላ ለውጥ አያመጣም!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሕወሃት እንኳን ተለውጦ ሞቶም ከራሱ የበላይነት ሌላ ለውጥ አያመጣም!

Postby ኳስሜዳ » Mon Nov 27, 2017 10:13 pm

ሕወሃት አባይ ወልዱን ከሊቀመንበርነት አወረደ-አላወረደ፣ አዜብ መስፍንን ከድርጅቱ አገደ-አላገደ፣ አርከበ ዕቁባይ ወጣ፣ ዶ/ር ደብረፂዮን መጣ፣ … የአቦይ ስብሃት ቤተሰብ ሰባ፣ አባይ ፀሐዬ ገባ፣ … ወዘተ፣ ማንም ወጣ፥ ማንም መጣ፣ "የሕወሃት_የበላይነት_ይብቃ!" ሊል አይችልም፡፡ በሕወሃት አመራሮች መካከል የተፈጠረው ልዩነት፣ ዛሬ ደርሶ "እከሌ ተቀጣ፣ እከሌ ደግሞ ተቀጣ!" የሚሉት ከትጥቅ ትግል ጀምሮ የተለመደ፣ የማይቀየር የሕወሃት ድርጅታዊ ባህል (Organizational Culture) ነው፡፡ ይህ ድርጅት በውጫዊ ሃይል አስገዳጅነት ካልሆነ በስተቀር በራሱ ተነሳሽነት ለውጥና መሻሻል አምጥቶ አያውቅም፡፡ የተለወጠ መስሎ ቢቀርብ እንኳን የቀድሞውን ዓላማና ግብ ለማሳካት እንጂ አዲስ ራዕይና ተልዕኮ ሰንቆ እንቆ አይደለም፡፡ ልብ አድርጉ…ሕወሃት ከዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው #በኦሮማራ ጫናና ግፊት ነው፡፡ አባይ እና አዜብ የተመቱት ትምክህተኛና ጠባብ ሃይሎችን ለመምታት በሚደረገው ጥረት አጋዥ ሆነው ባለመገኘታቸው እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ አስሬ ቢቀየር፣ ቢቀያየር "#የሕወሃት_የበላይነት_ይብቃ!" የሚል አመራር ሊኖረው አይችልም፡፡ ምክንያቱም ድርጅቱ የተፈጠረው የኦሮሞና አማራ ህዝብን በመለያየትና በማጋጨት የራሱን የበላይነትን ለማስቀጠል ነው፡፡ ስለዚህ ሕወሃት አይደለም በአመራርና በአሰራር ለውጥ፣ #ሞቶ_ቢነሳ እንኳን ለኦሮሞና አማራ ህዝብ አንድነትና ተጠቃሚነት ማሠብና መስራት ሆነ ማሠራት አይችልም፡፡ አንዳንዶች ሕወሃት ውስጥ የሚስተዋለው "ለውጥና ሽግሽግ የፖለቲካ ለውጥ ያመጣል" የሚል ተስፋ አላቸው፡፡ ነገር ግን፣ ሕወሃት በህይወት እያለ ቀርቶ ሞቶና ተቀብሮ እንኳን የራሱን የበላይነት ከማስቀጠል ሌላ አያስብም፣ አይሰራም፣ አያሰራም!!
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot] and 3 guests