ወያኔ ኢህአዴግ ራሱን በራሱ እያጠፋ ነውን?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ወያኔ ኢህአዴግ ራሱን በራሱ እያጠፋ ነውን?

Postby ኳስሜዳ » Tue Nov 28, 2017 2:02 pm

ባለፉት ወራቶች ህውሓት ግምገማ ተቀምጦ አሸናፊው ቡድን ተሸናፊውን ቡዱን ለመጣል ብዙ ካንገራገረ ቦሃላ አሁን ይፋ በማድረግ የመለስን ቡድን ከጥቅም ውጭ አድርገዋል። አዜብ ስትፈራው የነበረውን የስብሃት ነጋ ዱላ ደረሰባት፣ አባይ ወልዱ የአዲስ አበባው ህውሓት ከትግራይ ህዝብ ለመነጠል ያደረገው ጥረት ሳይሳካለት ቀረ፣ የስብሓት ቡዱን የአባይ ወልዱን ሚስት ከትግራይ ራቅ ባለ ቦታ በአምባሳደርነት በአስትራልያ አስቀመጠ፣ አሁን ከመለስ ሞት ይልቅ የስብሓትን የስልጣን መጨበጥ ካንጀት ያስለቀሳት አዜብ ከህውሓት ተባረረች፣ አባይም ሳይወድ በግዱ የመለስን ራኢ ሳያሳካ ከስልጣኑ ወረደ።በነ አዜብ እና አባይ ስር ያሉት የትግራይ የዞን አመራሮች እጣ ፈንታም ገና ያላለቀ ድራማ ነው። የመለስ ቡድን ከትግራይ ከስር ተነቅሎ በስብሓት ቡዱን መተካቱ አይቀሬ ነው።

ስብሓት ስልጣን ወይሞት በማለት አሁንም ድረስ የህውሓትንም የፌደራል መንግስትንም ያሽከረክራል፣ ተረኛው ሳሞራስ፣ እጁን ይሰጣል ወይስ አገር እና ህዝብን ጨርሶ ራሱን ያጠፋል፣ የስብሃት ነጋ ቀጣዩ ትልቅ የቤት ስራ ሳሞራ ይሆናል፣ ከዛ በፊት በህውሓት ተጠፍጥፈው የተሰሩት የብአዴን እና የኦሆዴድ እጣም በስብሓት ነጋ ሳይሆን አይቀርም። የስብሓት ትልቁ ኢላማዎች አባዱላ ገዱ እና በረከት ሳይሆኑ አይቀሩም። ያኔ ስብሓት እንዳለው ኢህ አዴግ ራሱንበራሱን ያጠፋል ማለት ነው፡ በቀጣይ የሚታይ ይሆናል፡፡
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests