እሸቱን ያየህ ተቀጣ- የደርግ አባል እድሜ ልክ ተፈረደበት

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

እሸቱን ያየህ ተቀጣ- የደርግ አባል እድሜ ልክ ተፈረደበት

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Dec 15, 2017 10:19 pm

በኢትዮጲያ ከመንግስቱ ሃ/ማሪያም ጋር ሞት የተፈረደበት እሸቱ አለሙ እድሜ ልክ ፍርድ በኔዘርላንድ አገኘ፡፡በ15 አመቱ በደርግ የታሰረ ንጉሱ ገበየሁ ፍትህ መገኘቱን በዚያ ተገኝቶ መሰከረ፡፡የደርግ ግፈኞች ፍርድ እንዳገኙ ህዝቡን የጨፈጨፉ ወያኔዎችም ፍርድ ይቀበላሉ፡፡

ዘሄግ (14 dec. 17) ዛሬ ዲሴምበር 15 ቀን 2017 ከቀትር በኋላ በሆላንድ ዘሄግ ከተማ የዋለው ችሎት በመቶ አለቃ በእሸቱ አለሙ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው የጦር ወንጀል ክስ እድሜልክ እስራት በይኖባቸዋል። በተጠቀሳባቸው ክስ በሙሉ ጥፋተኛ ተብለዋል። ከሁለተኛው አለም ጦርነት በህዋላ እንዲህ አይነት ፍርድ በሆላንድ ሃገር ሲሰጥ የመጀመርያው መሆኑን አቃቤ ህግ ተናግረዋል። በሃገሪቱ ህግ የእድሜ ልክ እስራት አመክሮ የለውም።
አቶ እሸቱ አለሙ በውሳኔው ሰዓት ችሎቱ ላይ መገኘት አልፈለጉም።በአራት ዳኞች በተሰየመው በዚህ International Crime Chamber የተሰኘ ችሎት የመሃል ዳኛዋ ማርየት ሬከንስ የፍርድ ውሳኔውን ባሰሙበት ወቅት አቃቢያን ህጎቹ እና የተበዳይ ጠበቆች በውሳኔው የደስታ ስሜት ታይቶባቸዋል። ከ29 ኦክቶበር 2017 ጀምሮ ሲታይ የነበረው ይህ የፍርድ ሂደት የከሳሽ አቃቤ ህግንና የተከሳሽ ጠበቆችን ክርክክር ለወር ያህል ሲያዳምጥ ቆይቶ ፣ ውሳኔ ለመስጠት ከ3 ሳምንት በኋላ ቀጠሮ ይዞ እንደነበር የሚታወስ ነው።ከሁለት አመት በላይ የፈጀው ይህ በአይነቱ ለየት የሚለው፣ የአቶ እሸቱ አለሙ የምርመራ እና የክስ ሂደት አለም አቀፍ ትኩረትን ስቦ ነበር። ፍርዱ በተሰጠበት በዛሬው እለትም በርካታ የሃገር ውስጥ እና የውጭ ሃገራት ጋዜጠኞች ወደ ችሎቱ ታድመዋል።የ63 ዓመቱ እሸቱ አለሙ ከ 120 የደርግ አባላት አንዱ ሲሆኑ፣ በ1970ዎቹ ቀይ ሽብር ዘመን ደርግን ወክለው የጎጃም ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ እንደነበሩ በችሎቱ ፊት ቢመሰክሩም የተመሰረተባቸውን የጦር ወንጀል ክስ ግን ሲቃወሙ ነበር። አስራ ሁለት ዓመት ፈጅቶ የነበረው የኢትዮጵያው የቀይ ሽብር ወንጀል ችሎት እ.ኤ.አ 2006 አቶ እሸቱ አለሙ ላይ በሌሉበት የሞት ፍርድ መወሰኑ አይዘነጋም።በ1991 ኢህአዴግ ሃገሪቱን ሲቆጣጠር አቶ እሸቱ አለሙ ከነበሩበት ከቡልጋርያ ወደ ሆላንድ በመምጣት የፖለቲካ ጥገኝነት በመጠየቅ በ1992 የሆላንድ መኖርያ ወረቀት ያገኙ ሲሆን ከ5 አመት በኋላም የሃገሪቱ ዜጋ ሆነዋል። ግለሰቡ በ 2015 ክመኖርያ ቤታቸውባላሰቡበት መንገድ ተይዘው ታሰሩ። ኦክቶበር 29, 2017 – በታሰሩ ከ 2 ዓመት በኋላ – ጉዳዩ በሄግ ችሎት መታየት ጀመረ።በሆላንድ አቃቤ ህግ የቀረበባቸው ክስ በነሃሴ ወር 1978 ፣ በ75 ወጣቶች ግድያ (በቅዱስ ሚካኤል ቤተ–ክርስትያን ውስጥ ተገድለው በጅምላ የተቀበሩ) በዘጠኝ ዜጎች ላይ የተደረገ ድብደባ እና የማሰቃየት ወንጀል እና በ 321 ሰዎች ላይ በደረሰ ህገ–ወጥ እስራትየሚል ነው።
ለክሶቹ ክ3000 ገጽ ያላነሰ የጽሁፍ ማስረጃዎች ፣ ፎቶ እና ተንቀሳቃሽ ምስልሎች፣ ከኢትዮጵያ፣ ከአሜሪካ፣ ከካናዳ እና ከእንግሊዝ የተገኙ ከ30 በላይ የአይን ምስክሮች ( ከነዚህ ውስት ስምንቱ ምስክሮች ከካናዳ እና ከአሜሪካ ተጉዘው በሄግ ችሎት በመገኘት ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን፣ በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ሶስት ባለሙያዎች (ፕ/ር ጃን አቢንክ ፣ ዶ/ር ካሳ እና ክፉሉ ታደሰ) በማስረጃነት ቀርበዋል።የሆላንድ ፍትህ ሚንስትር በአቶ እሸቱ ላይ ክሱን ለመመስረት መነሻ የሆነው፤ እ.ኤ.አ. በ1998 ‘ፍራይ ኔደርላንድ‘ (ነጻ ኔዜርላንድ) በሚል መጽሄት ስለ ተከሳሹ የወጣ ወንጀል ነክ ጽሁፍ ነው። የሆላንድ አለም ዓቀፍ የወንጀል ምርመራ ቡድን ይህንን ጽሁፍ እንደተመለከተ ከ2009 ጀምሮ የአቶ እሸቱን ስልክ በመጥለፍ መከታተል እንደጀመረ አቃቤ ህግዋ ሚስ ኒኮል ፎገለንዛግ ተናግረዋል።

ይህ ቡድን በ2012 ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ የኢዮጵያን መንግስት መረጃ ቢጠይቅም ከመንግስት በኩል ትብብር እንደተነፈገውም አቃቤ ህግዋ ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ አልተባበርም ለማለቱ የሰጠው ምክንያት ጉዳዩ በሃገር ውስጥ በቀይ ሽብርየወንጀል ችሎት ስላለቀ መቶ አለቃ እሸቱን አሳልፋችሁ ስጡን በሚል ሰበብ ነው። በሆላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የወንጀለኛ ልውውጥ ስምምነት ባለመኖሩ እና በኢትዮጵያ የሞት ፍርድ መሰጠቱ ተጠርጣሪውን የማስረከቡ ጥያቄ ውድቅ ሊሆን ችሏል። አቶ እሸቱ አለሙ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሱ በተደመጠበት ወቅት “የተሳሳተ ሰው ነው የያዛችሁት” ብለው ነበር። ማስረጃዎች ሲቀርቡና የምስክሮች ቃል መሰማት ሲጀምር በወቅቱ አስከፊ ነገር እንደተፈጸመ ተናግረው ፣ ለተፈጠረው ነገር ሁሉ ይቅርታ ጠይቀዋል።ይሁን እንጂ እሳቸው በወቅቱ በፕሮፓጋንዳ ስራ እንደተሰማሩና አንድም ሰው እንዳልገደሉ፣ ሰው እንዲገደልም ሆነ እንዲታሰር ትዕዛዝ እንዳልሰጡም ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።“ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ የኢትዮጵያን ሕዝብ ይቅርታ እንዳደርግ ፍርድ ቤቱ እድል ስለሰጠኝ አመሰግናለሁ። 120 የደርግ አባላት ውስጥ አንዱ ሆኜ ስለተሰራው ወንጀል አዝናለሁ። ግን የቀረቡብኝ ክሶች በሙሉ አልቀበልም።” ብለዋል።የ4 ሺህ አመት ታሪክ ያላት ሃገራችን እንዳትፈራርስ አሜሪካንን እርዳታ ብንጠይቅ እንቢ ስላሉን ነው ወደ ሶቭየት ለመሄድ የተገደድነው። በወቅቱ የተደራጀው ሃይል ደርግ ብቻ ነው። ኢህአፓ ሃገሪቱን ሊያፈርስ በእብደት የተነሳ ሃይል ነበር። አቶ ክፍሉ ታደሰየኢህአፓ አመራር የነበሩ በመሆናቸው ሃሳባቸው ነጻና ገለልተኛ ሊሆን አይችልም።” ሲሉም ኢህአፓን በፍርድ ቤት ውሎ ኮንነዋል።ሚ/ር ሳንደር አርት፤ የአቶ እሸቱ ጠበቃ የስም መደባለቅን እንደ ለመከራከርያ አቅርበው ነበር። ወንጀሉን የፈጸሙት ተከሳሹ እሸቱ አለሙ ሳይሆኑ ሌላ እሸቱ ናቸው ሲሉ ተከራክረዋል።

“የግድያውን ትዕዛዝ የያዙ ፊርማዎች የሱ ሳይሆኑ የሌላ እሸቱ ናቸው። ምስክሮቹም የተናገሩት የሚያሳምን አይደለም። የፍርዱ ሂደት ፍትሃዊ አይደለም። አቶ እሸቱ አለሙ በ2015 ከቤታቸው ተወስደው ሲታሰሩ ወንጀለኝነታቸው አስቀድሞ እንደተረጋገጠይተቁማል።” የሚል ነበር የመከራከርያቸው ጭብጥ።ሌላው የጠበውቃው መከራከርያ ነጥብ ደግሞ “በ1978 ጎጃም ውስጥ የርስበርስ ውግያ ባለመካሄዱ ጉዳዩ የጦር ወንጀል ሊሆን አይችልም። ተራ ወንጀል ደግሞ በዚህ ችሎት መታየት አይችልም።” የሚል ሲሆን፣ ቀደም ሲል አቶ እሸቱ አለሙ በጎጃም ኢህአፓበተደራጀ መልክ ጦርነት ከፍቶ እንደነበር ለፍርድ ቤቱ የተናገሩት ቃል ይህንን መከራከርያ ነጥብ አፍርሶታል።
የተበዳዮች ጠበቃ የሆኑት ሚስ ባርባራ ፋን ስትራተን – ለእያንዳንዱ ተበዳይ 200 ካሳ ኤሮ እንዲከፈል ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል። ይህ ካሳ ምንም እንኳን መጠኑ ዝቅተኛ ቢሆንም ጥፋቱን ለማስረገጥ የተደረግ ተምሳሌታዊ (ሲምቦሊክ) ነው ብለዋል።ከዚህ ቀደም ሁለት የሩዋንዳ እና አንድ የኢራቅ ተወላጆች ላይ ተመሳሳይ ክስ ተመስርቶ እንዳንዳቸው በ 16 17 አመት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል። በሆላንድ የእድሜ ልክ እስራት የሚበየነው እጅግ አስከፊ ለሆነ ወንጀል ስለሆነ የተመክሮ መብትም የለውም። በሃገሪቱ እድሜልክ የተፈረደባቸው ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።አቶ እሸቱ አለሙ ባለትዳር እና የሁለት ልጆች የነበሩ ሲሆን ባለቤታቸው እና ልጆቻቸው በውል በማይታወቅ ምክንያት ከአመታት በፊት ጥለዋቸው ወደ አሜሪካ በመሄድ ኑሯቸውን እዚያ አድርገዋል። በ2015 ከመታሰራቸው በፊት ሆላንዳዊት የትዳር ጓደኛቸው ጋር ይኖሩ ነበር።የአቶ እሸቱ መያዝ እና መታሰር የዚህን ትውልድ ትኩረት ባይስብም አሁን በሃገሪቱ እየተፈጸመ ላለው ተመሳሳይ ወንጀል አይን ከፋች ነው። በሰብአዊነት ላይ ወንጀል ሰርቶ ከሃገር መውጣት እና መደበቅ እንደማይቻል ትምህርት ይሆናል። የሆላንድ ፍትህ ሚኒስቴርያሉትም ይህንኑ ነው። “ሃገራችን ዜጋቸውን ጨፍጭፈው ለሚመጡ ወንጀለኞች የመደበቅያ ገነት መሆን የለባትም!”

“እሸቱን ያየህ ተቀጣ!”
News ዲሰምበር 15/2017 አማርኛ BBC
የቀይ ሽብር ተከሳሹ በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነበት።
በኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው እሸቱ ዓለሙ 75 ሰዎችን በመግደል በጦር ወንጀለኝነት በቀረበበት ክስ ጥፋተኛ ተብሏል።
የቀድሞው ኮሚኒስት መሪ መንግሥቱ ኃይለማሪያም ረዳት ነበር የተባለው ይህ ግለሰብ በሰዎች ላይ ሰቆቃን በመፈፀምና በከፋ አያያዝ ውስጥ እንዲቆዩ በማድረግ ጭምር ተከሶ ነበር።
ኢትዮጵያ ውስጥም በሌለበት በቀረበበት ክስ ሞት ተፈርዶበታል።አቃቤ ሕግ ባቀረበው ክስ ''በአንድ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ 75 የሚሆኑ እስረኞች እንዲገደሉ ትዕዛዝ ሰጥቷል'' ብሏል።
የሟቾቹም አስከሬን በአንድ የጅምላ መቃብር ውስጥ እንዲቀበር ማድረጉንም አትቶ ነበር።
እስረኞች እጅና እግራቸው ታስሮ እንዲንጠለጠሉ በማድረግ የውስጥ እግራቸው በዱላ እንዲገረፉ አድረጓልም ተብሏል።
እርሱ ግን ችሎት ሲቀርብ "ወንጀለኛ አይደለሁም፤ ከዚህ በኋላ መኖርም አልፈለግም" ሲልም ተናግሮ ነበር፡፡
Ethiopia ‘Red Terror’ aide Alemu jailed for war crimes
December 15, 2017 | Filed under: News,News Feature | Posted by: zehabesha
(BBC) A Dutch court has sentenced an aide to Ethiopia’s former communist ruler to life imprisonment for war crimes.
Eshetu Alemu, 63, was found guilty of crimes including execution of 75 people in Ethiopia’s purges in the late 1970s.
Eshetu Alemu is accused of ordering the execution of 75 people during Ethiopia’s “Red Terror”
The dual Ethiopian-Dutch national and former aide to then-ruler Mengistu Haile Mariam denied all the charges against him.
More than 300 victims were named in four war crimes charges.
Ethiopia has already sentenced him to death in absentia.Prosecutors said that Alemu was a henchman for Mengistu in the north-west Gojjam province.
The case was tried under Dutch universal jurisdiction laws at the district court in The Hague.
Presiding judge Mariette Renckens told the court that Alemu was “guilty of war crimes and treated his fellow citizens in a cold and calculating manner… including robbing them of their right to life”.Families of victims applauded the sentence, but neither Alemu nor his lawyers were present in court.
The Mengistu regime and the Red TerrorMarxist strongman Mengistu Haile Mariam ruled Ethiopia between 1977 and 1991 following the overthrow of Emperor Haile Selassie in 1974.Mengistu Haile Mariam governed Ethiopia between 1977 and 1991There was significant repression under his communist regime. This became known as the “Red Terror”.
Mengistu was ousted in 1991 after a series of revolts by insurgent groups. He then fled to Zimbabwe, where he still resides.
In 2007, Mengistu was found guilty in absentia at an Ethiopian court of genocide.
--------------------------------==============================--------------
Dutch court convicts 63-year-old of war crimes in Ethiopia
(AP) — THE HAGUE, Netherlands — A court in the Netherlands convicted a 63-year-old man Friday of committing war crimes under a brutal Marxist regime in Ethiopia in the 1970s and sentenced him to life imprisonment, a ruling that one victim hailed as delivering justice to survivors.
Eshetu Alemu was not present in The Hague District Court as he was convicted of ordering the murder of 75 political opponents and the arbitrary detention in cruel and degrading conditions of more than 300. He was also found guilty of failing to prevent the torture of six people.

Some experts say 150,000 university students, intellectuals and politicians were killed in a nationwide purge by the Dergue regime of former dictator Mengistu Haile Mariam, though no one knows for sure how many suspected opponents were killed. Human Rights Watch has described the 1977-78 Red Terror campaign as “one of the most systematic uses of mass murder by a state ever witnessed in Africa.”The court ruled that Alemu was the highest representative of the Dergue regime in Gojam province and, as such, was responsible for eliminating opposition.“It was in this context that he had a large group of mainly teenagers arrested, tortured and killed on the pretext of their affiliation with the EPRP, the main opposition movement in Gojam at the time,” a court statement said.In an emotional speech during his trial, Alemu accepted blame for crimes by the Dergue but told judges he did not personally commit them.But the court ruled that he was responsible and said the crimes were “so serious that only a life sentence” is the fitting punishment.
Negus Gebeyehu, who said he was imprisoned as a 15-year-old, told the court on Friday: “Justice has been done for Ethiopia.”Alemu was tried in a Dutch court because he moved to the Netherlands in the early 1990s and was granted Dutch citizenship in 1998.Mengistu now lives in exile in Zimbabwe. He was convicted in absentia by an Ethiopian court in 2006 of genocide and later sentenced to death.
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: እሸቱን ያየህ ተቀጣ- የደርግ አባል እድሜ ልክ ተፈረደበት

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Dec 25, 2017 5:07 am

የአለም የሰው መብት አስጠባቂ ድርጅት ተጠሪ የደርጉ እሸቱ ፍርድ ለግፈኛው ወያኔም እንደማይቀር መሰከሩ፡፡
Felix Horne
Senior Researcher, Horn of Africa
Felix Horne – Senior Researcher, Horn of Africa, December 21, 2017 —The many victims of the brutal communist military dictatorship that ruled Ethiopia from 1974 to 1991, known as the Derg, had a rare victory this week. On December 15, former Ethiopian government official Eshetu Alemu was convicted of war crimes and sentenced to life in prison by a Dutch court for his role in ordering the executions of 75 people, including children under 18, in the 1970s.

Over 150,000 students, academics, and political opponents were killed during the Derg’s “Red Terror” campaign. Countless others were disappeared, arrested, or tortured. Senior Derg officials, including Chairman Mengistu Haile Mariam, were convicted of genocide in absentia in 2006 after a 12-year trial in Ethiopia’s courts. They were sentenced to life in prison. Eshetu, the Derg’s senior representative in Gojam province at the time of his crimes, had been sentenced to death in absentia by an earlier Ethiopian court. In 1991 when the Tigrayan Peoples’ Liberation Front (TPLF) overthrew the dictatorship, Mengistu fled to Zimbabwe where he was afforded protection by then-president Robert Mugabe. Eshetu fled to the Netherlands.Eshetu’s conviction should send a powerful message that officials can and will be held to account for atrocities, and that the passage of time is no guarantee of impunity. This message is especially important in Ethiopia, where the TPLF, who has been in power since the Derg’s overthrow, has also committed serious abuses with impunity. These include its military’s murder, rape, and torture of Anuak civilians in Gambella in 2003 and 2004, and war crimes and crimes against humanity in the Somali Region in 2007. Additionally, a brutal crackdown by government security forces against protesters beginning in 2015 left over a thousand dead. The government has not permitted independent investigations into any of these events and Ethiopia has strongly resisted calls for an international investigation. Justice and accountability for Ethiopia’s many victims in the last 50 years, has been all too rare.For families of Ethiopia’s many victims of torture, killings, and other serious abuses, Eshetu’s conviction should give them hope that those responsible will one day be held to account.
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1529
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 10 guests