"መሬቱን እንጅ እኛን አይፈልጉንም" የወልቃይት እናት

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

"መሬቱን እንጅ እኛን አይፈልጉንም" የወልቃይት እናት

Postby ኳስሜዳ » Sat Dec 16, 2017 9:15 pm

ሲሳይ ዳኛው መምህር ይባላል። የ"ሽብር" ክስ ቀርቦበት ቂሊንጦ ይገኛል። አባቱ ከሞቱ ቆይተዋል። በእርሻ ስራ ተሰማርቶ ቤተሰቡን ያስተዳድር የነበረው እሱ ነው። ሁለት ታናናሽ ወንድሞቹ ትምህርት አቋርጠዋል። እናቱ በልጇ እስርና ችግር የአልጋ ቁራኛ ሆናለች። ቤተሰቡ ፈርሷል።

ሲሳይን ትግራይ ወስደው አሳሩን አሳይተውታል። ጉድጓድ ውስጥ አስረውታል፣ ደብድበውታል። ይህ ሁሉ በግድ "ትግሬ ነኝ በል" ነው ይላል። ሲሳይ ጋር ታስሮ የነበረው በስቃይ ብዛት፣ በዱላ ብዛት " እሽ ትግሬ ነኝ" ብሎ ከክስ ተረፈ። ሲሳይ ማንነቴን አልቀይርም ብዬ እዚህ ደርሻለሁ ብሎኛል።


ከሳምንት በፊት አንዲት የወልቃይት እናት አግኝቼ ነበር። ተከሳሹን ሊጠይቁ መጥተው ነው። ወልቃይት ላይ የሚፈፀመውን በደል የእናቶችን ያህል የሚገልፀው የለም። ልጆቻቸውን፣ ባሎቻቸውን፣ ቤተሰባቸውን የሚያጡት እነሱ ናቸውና። ይች እናት ብዙ አውርተውኛል። የወልቃይት እናቶች ፖለቲከኛ ሆነዋል። እንዲህ አሉኝ:_

"እኛ ትግሬ ሆነን አናውቅም። ለእኛ ቅርብም አይደለም። ከትግራይ ይልቅ ኤርትራ ሄደን ነበር የምንገበያየው፣ ከትግራይ ከተማ ይልቅ የኤርትራ ኦምናጅር ይቀርበናል። በግድ ነው ትግሬ ሁኑ የሚሉን። እውነቱን ልንገርህ፣ መሬቱ ለም ነው። መሬቱን እንጅ እኛን አይፈልጉንም። እኛን ቢፈልጉማ ህዝቡን ባላሰቃዩት ነበር።"

በእርግጥ ህዝቡን ቢፈልጉት የሲሳይ ቤተሰብ ባልተፈታ፣ እውነት ህዝቡን ቢፈልጉት ኖሮ ፈረደን ባላኮላሹት፣ እውነት ህዝቡን ቢፈልጉ መብራቱን፣ ነጋን፣… … እጅግ በርካቶችን ሽብር በሚሉት የሌለ ክስ ባላጎሩ!

እውነትም መሬቱንና መሬቱን ብቻ ነው የሚፈልጉት! ለህዝቡማ ወልቃይት ሲኦል ሆናለች! ሲኦል!
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Bing [Bot], Google [Bot] and 2 guests