ሊበረታታ የሚገባው የነለማ አቅጣጫና ግራ የገባው ወያኔ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሊበረታታ የሚገባው የነለማ አቅጣጫና ግራ የገባው ወያኔ

Postby እሰፋ ማሩ » Mon Dec 18, 2017 12:52 am

ግራ የገባውና ጊዜ ያለፈበት የህወሀት ጉዞና ሊበረታታ የሚገባው የነለማ መገርሳ አበረታች አቅጣጫ
ሳተናው
ዲሰምበር 16፣ 2017
ባተሮ በለተ
ህወሀትና አጋሮቹ ኦህዴድ ፣ ብአዴንና የደቡቡ በሀገሪቱ ዋና ዋና ጉዩዳዮች ላይ ያላቸው አመለካከትና የመፍትሄ ሀሳቦቻቸውም መሰረታዊ ልዩነትን እያንጸባረቁ ይገኛሉ።
ህወሀት በደረቅ የፖለቲካ ርእዮተአለምና የህብረተሰብ ትንተና አሁንም የዛሬ 42 አመት የጀመረውን ያጥፊና ጠፊ ፖለቲካ ርእዮት እያርገበገበ ጭቃ ውስጥ መንቦራጨቁን መርጣል።
“የኛ አመለካከት ሳይንሳዊ በመሆኑ ትክክል ነው ” የሚል እጅግ ሓላቀር አመለካከት በመከተላቸው እንደ ድርጅት የገቡበትን ማጥ እንደሀገርም ኢትዮጵያን ያደረሱባትን አደጋ ዘንግተው እነሆ በዚያው የጥፋት ጉዞ ለመጓዝ ወስነዋል።
አሁንም የሚነግሩን “ህገ መንግስታችን እንከን የሌለው ነው” “የብሄር ብሄረሰብ ወዘተ የሚለው አመለካከታችን ላኢትዮጵያ ችግሮች ሁሉ የተፈተነ መፍትሄ ነው” ፣ “ትግራችን ሁሉ ያፈጻጸም እንጂ መሰረታዊ የይዘት ችግር የለበትም” የሚል ራስን የማታለል ተረት ነው። ይህ ደግሞ ከሓላ ቀር ፖለቲካ አመለካከት የሚመነጭ “ማርክሲዝም ሌኒኒዝም ሳይንሳዊ አርእዩተ አለም ነው” ከሚለውና እያንዳንዷ የማርክሲዝም አስተምህሮትን እንዳለ እንደወረደ ትክክል አድርጎ ከመቀበል ጋር የሚያያዝ አባዜ አንዱ ገጽታ ነው።ይህ ሁሉ የሆነው ደግሞ ህወሀት “የቀደሙ ታጋዮች” የሚባሉት ሁላችንም አቋማቸውን ጠንቅቀን የምናውቃቸው ግለሰቦች በሌላቸው ስልጣን ድንገት በመቀሌው የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ ጉባኤ ተሳታፊ ተደርገው የስብሰባውን አካሄድና ውሳኔ እንደፈለጉ እንዲያሽከረክሩ ከተፈቀደላቸው በሓላ ነው።
ሽማግሌወቹም (“የቀደሙ ታጋዮች” ) የሚያወውቁት ያንኑ ቅድመ ሶቪየት መፈራረስ “ታላቅ” ተብሎ የተገመተ ርእዮት ስለሆነ አሁንም መልሰው ያንኑ ድሪቶ ነው ጎትተው የመጡት። ይህ ደግሞ ህወሀትን ራሱን ቀይሮ የሀገሪቱ የለውጥ አካል ከመሆን ይልቅ ከሌሎች ጋር የበለጠ ግብግብ ውስጥ እንዲገባ ያደርገዋል፣ ከሌሎች ይለየዋል።የኢትዮጵያ ህዝብም ሆነ ኢህአዴግ ው ስጥ የሚገኙት ድርጅቶች የሚሹት መሰረታዊ ለውጥ ነው ። ህወሀት የመረጠው ግን ወደ 1983 /84 ወደቀድሞ ጉድጓዱ መመለስን ነው። ሌሎች የፈለጉት ሰፊ መብትን ነው ህወሀት የመረጠው ደግሞ የህወሀትን ተጽእኖና የበላይነት ማጠናከር ነው፤ ሌሎች የፈለጉት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በደል ፣ የታሪክ ጠባሳ ቅሬታ ወዘተ እንዳላቸው ተገንዝቦ በሰፊው የሚያመሳስሉንን እሴቶቻችንን በማጠናከር ታላቅ ሀገርን ፣ ታላቅ የህዝብ አብሮነትን መመስረት ነው። ህወሀት ግን “ጨቋኝና ጭቁን አጥፊና ጠፊ ናቸው ፣ የማይታረቅ ጥቅም ነው ያላቸው “ በሚል ሽውራራ ፖለቲካ ልዩነትን፣ መከፋፈልን ወደውስጥ መመልከትን ማጠናከር ነው ።ይህ በመሆኑም ሀገሪቱ በተለያየ አቅጣጫ ወደ ተረጋጋ ሁኔታ ከመምጣቷ በፊት ትልቅ ምስቅልቅል ውስጥ እንድትገባ ህወሀት ያሰገድዳታል። ከመጥራቱ በፊት ሁኔታው ሁሉ እጅግ እንዲደፈርስ ህወሀት ያሰገድዳል።ይህ በ እንዲህ እንዳለ በ ኦፒዲኦወቹ በነለማ መገርሳና ዶክተር አቢይ በኩል የህዝቡን የልብ ትርታ ተረድተው፣ ከርእዩተ አለም ቀኖናና እስረኛነት ይልቅ ሀገራዊ አንድነትም ሆነ የህዝብን መብት በመጠበቅ አንጻር መሰረታዊ ለውጥን ለማምጣት እንደሚፈልጉ በተደጋጋሚ በተግባር እያሰመሰከሩ ነው። ይህ አበረታች ተግባራቸው አይዞህ የሚባል ብቻ ሳይሆን የሚደገፍም ነው።

ዛሬ እነ ለማ በሚያሰተዳድሩት ኦሮምያ ብቻ ሳይሆን በመላው ሀገሪቱ ፣ በራሳቸው ድርጅት አባላት ብቻ ሳይሆን በተተቃዋሚውም ጎራ ቀልብ እየሳቡ ነው። የሚመርቃቸውና አይዟችሁ የሚላቸው እንጂ የሚያወግዛቸው ቁጥሩ እየቀነሰ ነው።

ለ26 አመታት የተዘራውን የከፋፍለህ ግዛ አካሄድ አንዱን ማህበረሰብ ከሌላው ጋር ማጋጨቱን በንባጮ ነቀላ ታሪካዊ ጉዞና በመሳሰሉት ማከም መቻለቸው ትልቅ ተስፋን አጭሯል።

ሰላማዊ ስልፈኞች ላይ ጥይት ያርከፈከፈውን ያአግአዚ ሰራዊት ማውገዝ ባቻ ሳይሆን ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡም እናደርጋለን ማለታቸው ደግሞ አካሄዳቸው አዲስ ጅምርን ለማምጣት እንደሆነ ሌላ ተጨማሪ አበረታች ማስረጃ ነው፡ከዚህ ጎን የህዝብ ትኩረትን እየሳበ የሚገኘው ደግሞ ባአዴን ነው። ባአዴን ከህወሀት እስር ተላቆ የሌላውን ኢትዮጵያዊ ራእይ ማደራመዱን ቢገፋበት ትልቅ የማደግና ባጭር ጊዜ የመጠናከር ተስፋ አለው። በሚያሰተዳድረውም ህዝብ በኩል ትልቅ የለውጥ ፍላጎት እንዳለ ግልጥ ነው። በአዴን ይህን እድል በትክክል ሊጠቀምነትና በለውጥ ሀይልነት ሊሰለፍ ሁኔታው ግድ ይላል።ባዴኖች ከሚያሰተዳደሩት ህዝብ ፍላጎት በተጻራሪ መጓዝም ሆነ የህዝብን ፍላጎት አለማንጸባረቅ የሚያሰከፍለው ዋጋ ከባድ እንደሆነ የሚገነዘቡት ጉዳይ ነው፡:ባጠቃላይ ህወሀት ግራ በተጋባው ጉዞው ያለፈውን የ26 አመት የጭቆና ስርአት ለማስቀጠል እንደወሰነ ይታያል። በኦፒዲኦና በብአዴን (በተለይም ደግሞ ኦፒዲኦ) በኩል ደግሞ የተለየ ተስፋ ሰጭ አቅጣጫ እያመላከቱን ነው።በህወሀት ደጋፊወች የሚነገሩና የሚጻፉትን ስንመረምር ህወሀት በነ ለማ መገርሳ ያስተሳሰብ ለውጥ እና ህዝብን የማቀራረብ እርምጃ እየተርበተበተ ፣ እየተቃጠለም ነው:: ይህ አጅግ እጅግ ያሳዝናል ያሳፍራልም።አሁን የህወሀት ስራ አስፈጻሚ ሁኖ የተመረጠው እና የቀድሞው የፌደራሉ መንግስት የኮሚኒኬሽን ሚኒስቴር ጌታቸው ረዳ አማራና ኦሮሞ አንዱ አንዱን ፡ “የአማራ ደም የኔም ደም ነው የኦሮሞ ደም የኔም ደም ነው “ ሲሉ ሰምቶ የሁለቱን መቀራርብ “የእሳትና ጭድ መቀራረብ” አስመስሎ መተረኩና “ይህ ማለት እኛ ስራችንን አለመስራታችንን ያሳያል” ማለቱ የህወሀትን ደካማ ብቻ ሳይሆን መጥፎና አጥፊ ስነልቦና በትክክል የሚያሳይ ነው።እዚህ ላይ የህወሀትን እንጂ የትግራይን ህዝብ አልወቀስኩም ። የትግራይ ህዝብ ሁሉንም ኢትዮጵአዊ የሚወዱ እነ አረጋዊ በርሄን የመሳሰሉ የቀድሞ ታጋዮች፣ እነ አብርሀ ደስታን የመሳሰሉ ወጣት ኢትዮጵያውያን እንዳፈራች አውቃለሁ። በብዙ ሽወች የሚቆጠሩ አረጋዊወች፣ አብርሀም ድስታወች ከሁሉም ኢትዮጵያያዊያን ጋር እጅ ኢጅ ተያይዘው ሀገራችን ኢትዮጵያን እንደሚታደጉ ምንም ጥርጥር የለኝም::
ሳተናው
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests