ጋዜጠኛነት ወንጀል የሆነባት ኢትዮጲያ ግፉ ሲወሳ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ጋዜጠኛነት ወንጀል የሆነባት ኢትዮጲያ ግፉ ሲወሳ

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Dec 29, 2017 1:00 am

‹እጄን በካቴና አስረው ሲወስዱኝ የ4 ዓመት ልጄ ምርር ብላ አለቀሰች›› ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ
ሳተናው
December 27, 2017
ያን ቀፋፊ ዕለት አልረሳውም፤ መጋቢት 12/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ገደማ ሆኖ ነበር፡፡ ከቤቴ ወጥቼ ወደ ስራ እየሄድኩ ሳለ ትከሻየን ይከብደኝ ነበር፤ የሆነ ሰው እንደሚከተለኝ ይሰማኝ ነበር፡፡ ስራ ቦታየ ስደርስ በቀጥታ ወደ ቢሮ መግባት አልፈለግሁም፡፡ አካባቢውን ቃኘት ሳደርግ ደህንነቶችና ፌደራል ፖሊሶች በቅርብ እርቀት እየተከታተሉኝ እንደሆነ ገባኝ፡፡ ወዲያው ወደቢሮ መግባቱን ትቼ ቢሮ አካባቢ ካለች አንዲት ቤት ውስጥ ገብቼ ቡና አዘዝኩ፡፡
ቡናየን አዝዤ ስጠባበቅ ሁለት ሲቪል የለበሱ ወጣቶች መጥተው አጠገቤ ተቀመጡ፡፡

ደህንነቶች እንደሆኑ ስለገባኝ አጠገቤ ተቀምጦ የነበር አንድ ወጣትን ጠቀስ አድርጌ እንኔን የምታነሳ መስለህ ፎቶ አንሳቸው አልኩት፤ አነሳቸው፡፡ አሁንም ፎቷቸው አለ ብሎኛል፡፡ ወጣቶቹ ደህነንቶች አጠገቤ ተቀምጠው ቡናየን ጠጥቼ እስክወጣላቸው ይጠብቁኝ ጀመር፡፡ እኔ ግን ሁኔታው ስለገባኝ ባለሁበት ቁጭ እንዳልኩ ብዙ ጊዜ ወሰድኩ፡፡ እነሱም ተስፋ ቆረጡ መሰለኝ ከዚያች ቡና ቤት እንድወጣላቸው ስሜን ጠርተው ‹‹አንዴ ውጭ ፈልገንህ ነበር!›› አሉኝ በኃይለ ቃል፡፡ ሁለቱም ላይ ንዴት ይታይባቸው ነበር፡፡ እኔም ሰው ከምረብሽ ብየ ተነስቼ ወጣሁላቸው፡፡

ከቡና ቤቷ ወጣ እንዳልኩ ከደህንነቶቹ ራቅ ብለው የነበሩት ፌደራል ፖሊሶች ወደእኔ ፈጠን ብለው በመምጣት በግራ እና በቀኝ ጥብቅ አድርገው ይዘው መኪና ውስጥ አስገቡኝ፡፡ ለምን እንደሚፈልጉኝ እና እኔን ለመያዝ የሚያስችላቸው የፍርድ ቤት ወረቀት ካላቸው እንዲያሳዩኝ፣ ከሌላቸው ግን ህገ-ወጥ ስራ እየሰሩ እንደሆነ ነገርኳቸው፡፡ እነሱ ግን መልሳቸው ‹‹ዝም በል!›› የሚል ኃይለ ቃል ነበር፡፡ መኪና ውስጥ እንደገባሁ ቀጥታ ወደ ማዕከላዊ ነበር የወሰዱኝ፡፡
ማዕከላዊ እንደደረስኩ ከመኪና ሳልወርድ ለአንድ ሰዓት ያህል ግቢው ውስጥ አቆይተውኛል፡፡ ከዚያ የብርበራ ወረቀት ይዘው፣ የሰው ኃይልም ጨምረው ወደቤቴ ወሰዱኝ፡፡ ቤት ስደርስ ልጄ እና ባለቤቴ ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ ባለቤቴ በሁኔታው ብትደናገጥም እንዲህ አይነት ነገር ሊከሰት እንደሚችል ቀድሜ እነግራት ስለነበር ወዲያው ነው የተረጋጋችው፡፡ በዚያ ላይ ባልደረባዬ ጋዜጠኛ ካሊድ መሀመድ ቀደም ብሎ ታስሮ ስለነበር እኔንም ሊያስሩኝ እንደሚችሉ ግምቱ ነበረኝ፡፡ቤት ሲፈተሽ በጣም ረጂም ጊዜ ነበር የወሰደው፡፡ በጣም ብዙ ወረቀት ላይ እስኪደክመኝ አስፈርመውኛል፡፡ በጣም ደክሞኝ ስለነበር ውሃ ደጋግሜ እጠጣ ነበር፡፡ ቀና እያልኩ ልጄን ሳያት ፍርሃቷን አነብበው ነበር፡፡ ልጄ ሁኔታውን በፍርሃት ስትከታተልና እናቷ በተንቀሳቀሰችበት ቦታ ሁሉ አብራ እየተንቀሳቀሰች እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡ ፍተሻው አልቆ ከቤት ወጣን፡፡ ልጄን እና ባለቤቴን ዞሬ አየኋቸው፡፡ ወደመኪናው እንደተጠጋን እጄን በካቴና አስረው ሲወስዱኝ የ4 ዓመት ልጄ ምርር ብላ አለቀሰች፡፡ አንጄቴ ቢላወስም ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡
ማዕከላዊ እንደመለሱኝ ምዝገባ እንዳከናውን ከተደረግሁ በኋላ ሳይቤሪያ ወደሚባለው ቤት አስገቡኝ፡፡ እኔ ከገባሁበት ቤት ቀደም ብለው ገብተው የነበሩ እስረኞችም ከማጽናኛ ቃላት ጋር ተቀበሉኝ፡፡ ማዕከላዊ የልጄን ለቅሶ በአዕምሮዬ እያስታወስኩ ሌሊቱን እንቅልፍ እምቢ ብሎኝ አደረ፡፡
(ማስታወሻ፡- ጋዜጠኛ ዳርሰማ ሶሪ በእነ ከድር መሀመድ የክስ መዝገብ 13ኛ ተከሳሽ ሲሆን ዳርሰማ ሶሪ በጋዜጠኝነት ለ18 አመታት በተለያዩ ሚዲያዎች (ሪፖርተርን ጨምሮ) ሰርታል ፡፡፡ በተያዘበት ወቅት ደግሞ ለሬዲዮ ቢላል ይሰራ ነበር፡፡)
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests