2017 የፈረንጆቹ አመት ለኢትዮጵያና ሕዝቧ እጅግ አስከፊ አመት ነበር።

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

2017 የፈረንጆቹ አመት ለኢትዮጵያና ሕዝቧ እጅግ አስከፊ አመት ነበር።

Postby ኳስሜዳ » Sat Dec 30, 2017 3:07 pm

2017 የፈረንጆቹ አመት ለኢትዮጵያና ሕዝቧ እጅግ አስከፊ አመት ነበር። የመንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለውል። ይህም አልበቃ ያለው አገዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት እንዳይነሳ አድርጎ ደቁሶታል፤ ይህ ኢሰብዓዊ የሆነ ድርጊት በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወግዟል። ሚሊዮኖች ታስረዋል። ተሰደዋል። ቤተሰባቸውን በትነዋል። የሚራሩና ያዘኑ ልቦች በመታጠፋቸው የበርካቶች ቅስም ተሰብሯል።

ከዚህም በተጨማሪ ዜጎች በገዛ ሃገራቸው እመራቹሃለሁ በሚል አገዛዝ ሲፈናቀሉ በዓለም የመጀመሪያ አገር ኢትዮጵያ ሆናለች። ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የኦሮሞ ተወላጆች በገዛ አገራቸው ተዘዋውሮ የመስራት (ሕገመንግስታዊ) መብታቸው ተገፎ በባዶ እጃቸው ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉበት የፖለቲካ ቁማር የአገዛዙ ሌላኛው በሕዝብ ላይ የጣለው ከባድ አደጋ ነበር።

ይህ ብቻ አይደለም በዐማራ ክልል ዜጎች የመኖር ይሁን በኢኮኖሚ የማደግ መብታቸውን ተነጥቀዋል። የአገዛዙ የጎሳ ፖለቲካ ግንባር ቀደም በግድያና እስር ተጎጂ ሆነዋል። መንግስታዊ ሽብሩ በዚህ አላበቃም። በአፋር ፣ በጋምቤላ ፣ በደቡብ ሕዝቦች ከፍተኛ የሆነ ወንጀሎችን ከመስራቱም በላይ የብሔር ግጭቶችን በመቀስቀስ በርካቶችን ለሞትና ለእስር ዳርጓል ፤ ገላጋይ መስሎ ገብቶ የበርካቶችን ሕይወት በሞት አጨልሟል። ኢሕ አዴግ ምን ያህል ለሕዝቦች ጥላቻ እንዳለውና በሕዝብ ስም እንደሚነግድ በይፋ ያሳየበት አመት ነው። ራሱ ገድሎ ራሱ ለቅሶ የተቀመጠበት አመት ነው። ይህ ስርዓት መወገድ አለበት። እያንዳንዱ ዜጋ በገሃድም ይሁን በተዘዋዋሪ ተጎጂ መሆኑን አውቆ ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ ለማምጣት ሊታገል ይገባል።
ምንጭ፡ ሚኒሊክ ሳልሳዊ
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2140
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests