ፈጣሪንም ሰውንም የማተፈሪ ወያኔ እፈሪ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ፈጣሪንም ሰውንም የማተፈሪ ወያኔ እፈሪ

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Jan 12, 2018 6:59 pm

አንቺው ነሽ
በህገመንግስትሽ… ያልተከለከለ፤
መደገፍ መቃወም መብቴ ሆኖ ሳለ።
በማላውቀው ነገር አስረሽ የገረፍሽኝ፤
በጊዜ ቀጠሮ ስቃይ ያስፈረምሽኝ።
ከሳሽ ምስክሩ…ዳኛውም አንቺ ነሽ፤
ይግባኝ አልጠይቅም ፍረጂ እደፈለግሽ።
ተሟጋች ጠበቃ ማስረጃ ነስተሽኝ፤
መከራከር ሳልችል ተከላከል አለሽኝ።
ምን እደበደልኩሽ ወንጀሌን ሳላውቀው፤
ያ ጊዜ ቀጠሮሽ ሚስጥረሽን ደበቀው።
በማላውቀው ነገር አጉል ተጠርጥሬ፤
አለአግባብ ተይዤ ቆጨኝ መታሰሬ።
ወድሀለሁ ስትይ ካንጀትሽ መስሎኝ፤
ልብ እጄን ሰጠሁሽ ወረት አታሎኝ።
እኔን ጊዜ ጥሎ አንቺን ሲአነሳሽ፤
አጋድመሽ ገረፍሽኝ ሆኜ ተከሳሽ።
ደካማውን ብርቱ፤ ብርቱውን ደካማ፤
አድርጎ የጣለኝ አምላክ አንቺን ሰማ??
ደግሞም የኔ ተራ በደረሰ ጊዜ፤
አዙሮ ይጥልሻል በያዘሽ አባዜ።
የፈዸምሽብኝ ግፍ ብድር ደርሶሽ ሲገኝ፤
አከፋፈሉ ላይ ያኔ አንቺን አያረገኝ።
እኔ በአከበርኩሽ በወደድኩሽ መጠን፤
ጠልተሽ ያዋረድሽኝ ውጤቱ ሀዘን ይሁን።
ቤተሰብ ዘመድሽን ስንከባከብ ኖሬ፤
መልሰሽ ወጋሽኝ እንደ አባያ በሬ።
በግፍ ግፍ ስትገዢኝ ይህን ዓመት ሙሉ፤
ብሶቱ አንገፍግፎኝ ጠፍቶብኛል ውሉ።
በራሴ ሀብት ንብረት ከቤቴ ስገፋ፤
መብቴን ተገፍፌ ኑሮዬ ሲከፋ፤
በዘረኞች በትር ስጠቃ በይፋ፤
ምነው ሀይ የሚለኝ የሚረዳኝ ጠፋ።
እኔን የወደድሽኝ የአዘንሽልኝ መስለሽ፤
በመቃብሬ ላይ ቆመሽ ታለቅሻለሽ:፡
በቁም የገደልሽኝ የቀበርሽኝ አንሶ፤
በደለኝ ትያለሽ ጭራሽ ባንቺ ብሶ።
ሰው የዘራውን ነው አጭዶ እሚከምረው፤
መከሩን እንጠብቅ ይደረሳል አዝመራው።
አክብሬ ደግፌ ካሾምኩሽ በሁዋላ፤
ባለሥልጣን ሆነሽ ከዳሽ ሳንጣላ።
ለፍቼ ደክሜ በአቋቋምኩት ቤቴ፤
ገብተሽ አዘዝሽበት ተራምደሽ በመብቴ።
መናኝ ባህታዊ የእግዚአብሔር ሰው መስለሽ፤
ከጫካ ስትወጪ ያየሽን አታለልሽ።
በጎጥ የተለከፍሽ መሆንሽን ሳላውቀው፤
ያልሽኝ ማመኔ ጉድሽን ደበቀው።
ከአጋም የተጠጋ እርጥብ ቁልቋል ሆኜ፤
በወጋሽኝ ቁጥር…አለቅሳለሁ ሞኜ።
ተው ትቅርብህ…ብለው ወዳጆች ሲመክሩኝ፤
እኔ አልሰማም ብዬ… ሆኖአል የነገሩኝ።
ከእህት ወንድሞቼ እርስ በእርስ አባልተሽ፤
ደም ልታቃቢኝ ነው በክልል አጋጭተሽ።
በአባቴ ኦሮሞ …በእናቴ አማራ፤
ኢትዬጵያዊ ዜጋ ተብዬ የምጠራ።
አኩሪ ታሪክና ስርወ ግንድ ያለን፤
እንደ ዘረኞች ሟርት እሳት ጭድ የማንሆን፤
የአንድ እናት ልጆች እማንለያይ ነን፤
ችክ ድርቅ ብለሽ ያለ ውሃ አትስዋኚን።
ከሳሽ ምስክሩ ዳኛውም አንቺ ነሽ፤
ይግባኝ አልጠይቅም በይ ቅጪኝ እንዳሻሽ።
ሰውን እግዚአብሔርም ስለማትፈሪ፤
ሁሉን ትዋጊአለሽ ይፍረደን ፈጣሪ።

ከሽመልስ ተሊላ።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1504
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests