የስርዓቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቅጥፈቶች ኢትዮጵያን ከቀውስ ወደ ቀውስ እየወሰዷት ነው

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የስርዓቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቅጥፈቶች ኢትዮጵያን ከቀውስ ወደ ቀውስ እየወሰዷት ነው

Postby ኳስሜዳ » Fri Jan 12, 2018 10:12 pm

የስርዓቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ቅጥፈቶች ኢትዮጵያን ከቀውስ ወደ ቀውስ እየወሰዷት ነው የሚሉት ምእራባውያን ዲፕሎማቶች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጥረታቸውን ቀጥለዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ለውጦች እንዲኖሩ በኢሕአዴግ አገዛዝ ላይ ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ ። ይህ ካለማቋረጥ በተከታታይ አገዛዙ ላይ ጫና በማሳደር በቀጣይነት ሊኖር የሚችለውን አሁን ሃገሪቷ ካለችበት ቀውስ የምትወጣበትን ስራ እየሰሩ መሆኑን የዲፕሎማቲክ ምንጮች ይናገራሉ።
Image
ዓለም ባንክና የዓለም የገንዘብ ድርጅት የብር ዋጋ የመግዛት አቅሙ መሞቱን በመናገር ላይ ሲሆኑ አንድ ዶላር ከ40 - 45 ብር በላይ (IMF is insisting that Ethiopia should devalue Birr to $45) ሊሆን እንደሚችልና ይህም ችግሩ አገዛዙ የሚከተለው የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፖሊሲ ሕዝባዊ ተቃውሞ ተደምሮበት የፈጠረው መሆኑን ለስርዓቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የኢሕአዴግ ድርቅና ፖለቲካውን እንዳደነቆረውና ቀውሱን እንዳባባሰው የሚናገሩት ዲፕሎማቶቹ መጭው ጊዜ አገዛዙ ራሱ ከደነቀረው ከባድ ቀውስ ሃገሪቷን ለመታደግ ጥረት ላይ መሆናቸውን ይገልጻሉ ። በምስራቅ አፍሪካ ይከሰታል ብለው የሰጉት ቀውስ ብሔራዊ ጥቅማቸውን እንዳይጎዳባቸው የተለያየ የትብብርና የእርዳታ ቃል ኪዳኖችን በመግባት የኢሕአዴግ አገዛዝን ለማለሳለስ እየተጉ ይገኛሉ ሲሉ አውሮፓ ሕብረት ውስጥ የሚሰሩ ምንጮች ጠቁመዋል።
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2148
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 4 guests