የሕወሓት አጋዚ ሠራዊት በሐረር እስካሁን የተረጋገጠ 10 ሰዎችን በግፍ ገደለ!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የሕወሓት አጋዚ ሠራዊት በሐረር እስካሁን የተረጋገጠ 10 ሰዎችን በግፍ ገደለ!

Postby ኳስሜዳ » Sun Feb 11, 2018 7:45 pm

(ዘ-ሐበሻ) ከኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ሐረር ሃማሬሳ ካምፕ የሕወሓት አጋዚ ሠራዊት በፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት በዛሬው ዕለት እስካሁን የተረጋገጠ 10 ሰዎች መግደሉን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::

በሐማሬሳ ከተማ በተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ የሕወሓት አጋዚ ሰራዊት በቀጥታ ወደ ሕዝብ በመተኮስ የገደላቸው ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከ10 ሊበልጥ እንደሚችል የሚናገሩት ምንጮቻችን የቆሰሉት ወገኖች ቁጥር ከ30 እንደሚያልፍ ጠቁመዋል::

ከኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ተፈናቅለው በሃረር ሃመሬሳ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ዛሬ የተቃውሞ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ያሉት እነዚሁ ወገኖቻችን ከሕወሓት አጋዚ ሰራዊት የጠበቃቸው ምላሽ ጥይት ነው::

በአማሬሳ አካባቢ የትራንስፖርት አገልግሎት እንደተቋረጠ የሚገልጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ሕዝቡ በተቃውሞው ሰልፍ እየጠየቀ የነበረው የታሰሩ የሕሊና እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም ከሶማሊ ክልል የተፈናቀሉበት ለችግራቸው አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ነበር:: ሐማሬሳ ደም በደም ሆናለች::
Image
https://www.youtube.com/watch?time_cont ... SyM6CRpwBs
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2149
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 3 guests