ሐረሪም የአመፁ ተቋዳሽ ሆነች።

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሐረሪም የአመፁ ተቋዳሽ ሆነች።

Postby ዘርዐይ ደረስ » Mon Feb 12, 2018 10:31 pm

እስካሁን ድረስ ከትግራይ ቀጥሎ ከበድ ያለ ረብሻም ሆነ ህዝባዊ አመፅ ያልጎበኛት ክልል በትላንትናው ዕለት መጠኑ በግልፅ ያልታወቀ ዕልቂት ደርሶባታል።በሐረሪ ክልል አማሬሳ በሚባለው አካባቢ በተነሳው ረብሻ የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 10የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል እንዲሁም ግምታቸው 150 ሚሊዮን ብር የሆኑ ማሽኖችና እህል የጫኑ 7 ከባድ የጭነት መኪናዎች ሙሉ በሙሉ ተቃጥለው ወድመዋል በማለት የህወሓት/ኢህአዲግ መንግሥት ሚዲያዎች ዘግበዋል።ዘጋቢዎቹ አመፁን ያነሳሱት ‘የተደራጁ ፀረ ሠላም ኃይሎች’ ናቸው ከማለት በቀር የረብሻው መነሻ ምን እንደሆነ አላወቅንም ብለዋል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሐረሪም የአመፁ ተቋዳሽ ሆነች።

Postby እሰፋ ማሩ » Tue Feb 13, 2018 1:09 pm

ዘርዐይ ደረስ
ይህ የወያኔ ደጋፊ የአናሳዎቹ ሃረሪዎች ትግል አይደለም፡፡በወያኔ ሴራ የተፈናቀሉ ኦሮሞዎች ከሃገር ወዳዶች የተላከ እርዳታና ኮንትሮባንድ እቃ በወያኔዎች ሲመዘበር ሲቃወሙ የተጨፈጨፉበት ነው፡፡ስፍራው ራሱ የአጼ ምኒሊክ ጦር ሃረማያን/አለማያን ሲወርር የተደበቁ ወታደሮች ኦሮሞዎቹ ' አማራ ኤሳ'በኦሮምኛ አማራ የት ነው? ብለው ሲጠይቁ ሰምተው የቦታውን መጠሪያ እንዳደረጉት ይታወቅ!
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ሐረሪም የአመፁ ተቋዳሽ ሆነች።

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Feb 28, 2018 10:09 pm

ግለሰቦችን በሥርዓቱ ውስጥ ባላቸው አስተዋፅዖና በሚሠሩት ጥፋት መወንጀል ይቻላል።አንድን ህዝብ ግን በጅምላ በንቀት አመለካከት በዚህ መልኩ ማቅረብ ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሐረሪም የአመፁ ተቋዳሽ ሆነች።

Postby እሰፋ ማሩ » Thu Mar 01, 2018 1:01 am

የት ነው ንቀት የዘገብኩት ? በጥቅሉ ሃረርም ታገለ ስትል በወቅቱ አጠራር ሃረሪ ክልል ነው የሚባለው የአደሬ ብሄረሰብ በቁጥር በጣም አናሳ ከወያኔ ጋር ያለመታገሉን መለስኩ፡፡ ኦሮሞውና አማራው ጉራጌው በልጦ እያለ ሃረር በሃረሪ ክልልነት ለአደሬዎች ሙሉ ስልጣን በወያኔ ተሰጠ፡፡ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ አንድም የሃረሪ ተወላጅ በወያኔ ላይ የተነሳ የለም፡፡ ለወያኔ በማደር ሌላውን አሳልፈው የሰጡ ግን እጥፍ ናቸው፡፡ አንተ የምታውቀው እንደከፈትከው አምድ ከሃረሪዎች/አደሬዎች የትግሉ ተሳታፊ ካለ አቅርብልን፡፡
ዘርዐይ ደረስ wrote:ግለሰቦችን በሥርዓቱ ውስጥ ባላቸው አስተዋፅዖና በሚሠሩት ጥፋት መወንጀል ይቻላል።አንድን ህዝብ ግን በጅምላ በንቀት አመለካከት በዚህ መልኩ ማቅረብ ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Re: ሐረሪም የአመፁ ተቋዳሽ ሆነች።

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Mar 02, 2018 10:15 pm

እሰፋ ማሩ

እስቲ ወደ ኋላ መለስ ብለን ህወሓት/ኢህአዴግ መላዋን ኢትዮጵያ ከተተቆጣጠረ በኋላ የነበረውን ሁኔታ እንመልከት።ከአማራው በስተቀር በብሄር ድርጅት ያልተወከለ አልነበረም።ኦነግ ለቆ እስኪወጣ ድረስ አብዛኛው ኦሮሞሥርዓቱን አይቃወምም ነ በር ።እንዲያውም ገና ከጅምሩ የሥርዓቱ ከፋፋይ አካሄድ አደገኛነትን በመገንዘብ ያስጠነቅቁ የነበሩ ሁሉ በኦሮሞ ኢሊቶች ብቻ ሳይሆን በበርካታ የኦሮሞ ተወላጆች በነፍጠኝነት ይፈረጁ እንደነበር የሚረሳ አይደለም።የሐረሪ ማኅበረሰብም መርጦ ሳይሆን እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሥርዓቱ የጫነበትን ክልልም ሆነ አስተዳደር ተቀብሎ መኖር ግዴታው ሆኗል።ከዚህ ማኀበረሰብ የወጣ ተቃዋሚ የለም ላልከው ደግሞ እንዳንተ እርግጠኛ ሆኜ መናገር ይከብደኛል።አንተ የምታውቀው ካለ ንገረኝ ላልከው ደግሞ፤እኔ በበኩሌ እንኳን በተቃዋሚ ደረጃ ቀርቶ ሐረሪ መሆናቸውን የማውቃቸው ግለሰቦች በጣም ጥቂቶች ናቸው።በሌላ በኩል ግን ሐረሪዎች ሙስሊም በመሆናቸው ከስድስት ዓመታት በፊት በተጀመረው የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ውስጥ ያሉበት ይመስለኛል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests