ምሕረት ወይስ ፍርሃት?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ምሕረት ወይስ ፍርሃት?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Feb 14, 2018 11:07 pm

በሕወሓት/ኢህአዲግ የሚመራው መንግሥት ሥልጣን ከተቆናጠጠበት ጊዜ ጀምሮ እንደ ሰሞኑን ለፖለቲካ እስረኞች ‘ምሕረት’ አድርጎ አያውቅም። ክስ ማቋረጥና ይቅርታ ማድረግ በሚል ሰበብ በሃይማኖት አክራሪነትና በአሸባሪነት ወንጅሏቸው የነበሩትን፦
1ኛ)ከአምስት አመት በፊት ተጀምሮ የነበረውን የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ተከትሎ 17 መፍትሔ አፈላላጊዎች ታስረው እንደነበር ይታወሳል።አስራ ሶስቱ በተለያየ ወቅት ተለቀው የነበረ ሲሆን(የመሪያቸውን አቡበከር መሐመድ መፈታት እርግጠኛ አይደለሁም።) ቀሪዎቹ አሕመዲን ጀበል፣ ካሊድ ኢብራሂም፣አሕመድ ሙስጠፋ ሙሐመድ አባተ በዛሬው ዕለት ተለቀዋል።
2ኛ)የአንድነት ፓርቲ ፖለቲከኛ የነበረው አንዱአለም አራጌ በዛሬው ዕለት ተለቋል (እስር ቤት ሆኖ ‘ያልተሄደበት መንገድና’ ‘የሀገር ፍቅር ዕዳ’ የሁለት መጽሐፍት አሳትሟል)
3ኛ)ከነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች አንዱ የነበረው እስክንድር ነጋም በዛሬው ዕለት ተለቋል ። [ከባለቤቱ ሠርክዓለም ፋሲል ጋር በመሆን ምኒልክ(መጽሔትና ጋዜጣ) አስኳል፣ዛሬነው፣ነፃነትና4ኛዋ(ጋዜጦች) ዘሃበሻ(በእንግሊዝኛ) የተባሉት የህትመት ውጤቶች ባለቤት ነበር።
4ኛ)በተለምዶ የዞን ዘጠኝ ጦማርያን በመባል ከሚታወቁት በማኅበራዊ ሚድያ ወቅታዊ የፖለቲካ ትንተና በማቅረብ በተለይ በወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ዝና ካተረፉት መካከል በፍቃዱ ኃይሉ፣ አጥናፋ ብርሃኔና ናትናኤል ፈለቀ መለቀቃቸውን ባላረጋግጥም በዛሬው ዕለት ክሳቸው ተቋርጧል
5ኛ) አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ሰባት የኦሮሞ መብት ታጋዮች በትላንትናው ዕለት ተፈተዋል
6ኛ)ከተቃዋሚው ጎራ ባይመደቡም የጋምቤላ ክል ልፕሬዚዳንት የነበሩት ኦኬሎ አኳይ በዛሬው ዕለት ተለቀዋል።
7ኛባለፉት ሁለት ዓመታት በኦሮሚያ፣በአማራና በደቡብ ክልሎች ከተነሱ ህዝባዊ አመጾችና ረብሻዎች ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ጀምሮ በመፈታት ላይ ያሉ በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1085
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ምሕረት ወይስ ፍርሃት?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Feb 20, 2018 12:27 am

8ኛ) ከጎንደር እስርቤትም በዛሬው ዕለት ኰሎኔል ደመቀና ሌሎች በርካታ እስረኞች ተለቀዋል::
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1085
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 7 guests