ሰበር ዜና!! ሃይለማርያም እልቻልኩም ልቀቁኝ አለ!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰበር ዜና!! ሃይለማርያም እልቻልኩም ልቀቁኝ አለ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Feb 15, 2018 1:40 pm

ላለፉት 5 እመታት የ 'ጠቅላይ ሚኒስትርነት ' 'ሥልጣን' ላይ የነበረው ሃይለማርያም ደሣለኝ ከኢህ አዴግ ሊቀመንበርነቱና ከጠቅላይ ሚንስትርነቱ መልቀቁን እሳወቀ፡፡መልቀቂያው ተቀባይነት ካገኘ ምክትል ጠቅላይ ሚስትር ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ደመቀ መኮንን ሐሰን በቦታው አንደሚተካ ይገመታል፡፡በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ ታሪክ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሃገሪቱን ከፍተ ሥልጣን ያዘ ማለት ነው ፡፡ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ሌላ ሰው ከተሾመ (አንዳንዶች እርከበ ዕቁባይ ወይም ደብረፅዮን ገብረ ሚክኤል ሊሆን ይችላሉ ይላሉ) የተፈጠረው ችግር እንደሚባባስ ይገመታል፡.
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰበር ዜና!! ሃይለማርያም እልቻልኩም ልቀቁኝ አለ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Feb 23, 2018 10:17 pm

እስካሁን ድረስ ህወሓትኢህአዲግ የሚቀጥለው ጠቅላይ ሚኒስትር ማን ሊሆን እንደሚችልና ምርጫውስ መቼ እንደሚካሄድ ምንም ዓይነት ፍንጭ አልሰጠም።ይነስም ይብዛ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚከከታተል ሁሉ የራሱን ግምትና መላምት መስጠቱ አልቀረም።በየጊዜው ከሚነሱት ስሞች ውስጥ ማን ሊሆን ይችላል ከማለት ይልቅ ማን ሊሆን አይችልም የሚለውን ጥያቄ መመለስ የሚቀል ይመስለኛል።
1ኛ)ለማ መገርሳ ሕገመንግሥቱ ላይ እንደ ብቸኛ መመዘኛ የተቀመጠውን አያሟላም።ምክንያቱም የተወካዮች ምክር ቤት አባል አይደለም
2ኛ)ወርቅነህ ገበየሁ፦የኦህዴድ ከፍተኛ አመራር ባለመሆኑ እጩ የሚሆን አይመስልም።
3ኛ)በአምባሳደርነት ተሹመው የሄዱ ሁሉ አይመለከታቸውም
4ኛ)ከህወሓት ኦህዴድ ብአዴንና ደህዴን ውጭ ያሉት (በተለምዶ አጋር ድርጅቶች የሚባሉት) ለጥያቄ የሚቀርቡም አይመስሉም።በድጋሚ ከደህዴን የሚሆንምአይመስልም
5ኛ)ሴቶችን ለዚህ ቦታ ጨርሶ ያሰቧቸው አይመስልም
6ኛ)እንደ አባይ ፀሐይ ያሉ አንጋፋ አባላትም እንደእስካሁኑ ከኋላ ሆነው ተፅዕኖ ከመፍጠር ውጭ ወደፊት መጥተው መጋፈጥ የሚፈልጉ አይመስልም

ስለዚህ በእኔ ግምት ከወጪ ቀሪ ደመቀ መኮንን ወይም ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ይመስሉኛል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰበር ዜና!! ሃይለማርያም እልቻልኩም ልቀቁኝ አለ!!

Postby ደጉ » Sat Feb 24, 2018 8:25 am

ዘርዐይ ደረስ wrote:....
ስለዚህ በእኔ ግምት ከወጪ ቀሪ ደመቀ መኮንን ወይም ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ይመስሉኛል።

.... ከነዚህ ሰዎች አንዱ ወይም ሁለቱም 1 ላይ ጠ/ሚ ቢሆኑ ለ ህዝቡ እሚያመጡት ለውጥ አለ..??? ከዛ ይልቅ ተቃዋሚዎቹንም አሳትፈው ኢሀዴግም እንደ አንድ ፓርቲ ቢወዳደር ነው እሚበጀው ...ይሄ ደግሞ እማይሆንበት የራሱ ምክንያት አለ ..ድርጅቱ በሌብነት እን ዝርፊያ ላይ የተምሰረተ መሆኑም አንድ ችግር ነው :-)
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4420
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ሰበር ዜና!! ሃይለማርያም እልቻልኩም ልቀቁኝ አለ!!

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Feb 28, 2018 12:02 am

በእርግጥ ከዚህ ሥርዓት ሥር-ነቀል ለውጥ መጠበየቅ የዋህነት መሆኑን አምናለሁ።ታሪክ እራሱን ይደግማል እንዲሉ ከእኛ በፊት የነበሩት ኢትዮጵያውያን የ66ቱን አብዮት ሲያካሂዱ እንዳሉት ዛሬም ቢሆን ‘ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም’፤የሚለው ተረት ዘመን የማይሽረው እውነታ ነው።ቢሆንም የአገራችን ፖለቲካ ያገባናል እስካልን ድረስ ህወሓት/ኢህአዲግ የሚያደርጋቸውን እንቅስቃሴዎች መከታተልና አቋም መያዝ ጠቃሚ ይመስለኛል።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests