ሰበር ዜና!!አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰበር ዜና!!አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Feb 16, 2018 10:20 pm

ህወሓት/ኢህአዴግ ከዛሬ የካቲት 9 ቀን 2010 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁን ቢያስታውቅም አዋጁ እስከመቼ እንደሚቆይና ካለፈው የሚለይባቸውን ነጥቦች እስካሁን በዝርዝር አላሳወቀም።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1085
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰበር ዜና!!አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Mar 02, 2018 10:27 pm

ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው ይህ አዋጅ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተቃውሞ ገጥሞታል።በተለይም ከዓመት በፊት ከታወጀው ጋር ሲነፃፀር ለኮማንድ ፖስቱ የተሰጠው ሥልጣን ከተገቢው በላይ እንደሆነ ይነገራል።በተጨማሪም በርካታ የአዋጁ አንቀፆች ግልፅ አይደሉም።ከተቃዋሚዎች የተሰነዘሩት ትችቶች የሚጠበቅ ቢሆንም በሥርዓቱ ደጋፊዎችም ዘንድ መከፋፈል መፍጠሩ አስገርሟል።በተለይ በዛሬው ዕለት በምክር ቤቱ በተካሄደው የድምፅ አሰጣጥ ላይ ባልተለመደ መልኩ በርካታ አባላት አዋጁን መቃወማቸው ሥርዓቱ ውስጥ የተፈጠረውን አለመግባባት የሚያሳይ ይመስለኛል።እስካሁን ድረስ አብዛኛውን ጊዜ እንደታዘብነው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የወሰነውን የተወካዮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ ያፀድቀው ነበር።በዛሬው ድምፅ አሰጣጥ መሠረት ግን 395 አዋጁን ሲደግፋ 88 ተቃውመዋል 7 ደግሞ ድምፀ ተዓቅቦን መርጠዋል።57 ደግሞ በጭራሽ ድምፅ አሰጣጡ ላይ አልተገኙም።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1085
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰበር ዜና!!አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Jun 05, 2018 7:14 pm

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከየካቲት 9 ቀን 2010 ጀምሮ ተግባር ላይ ውሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት በአስፀደቀው ረቂቅ አዋጅ የተወሰነለት 6ወር ሳይደርስ እንዲነሳ አድርጓል።ስለዚህ ከነገ ጀምሮ ኮማንድ ፖስቱ ኃላፊነቱን ለሚመለከተው ክፍል ያስረክባል ማለት ነው።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1085
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests