ሰላም ዋርካውያን

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ሰላም ዋርካውያን

Postby ኮኮቴ » Sun Feb 18, 2018 12:33 am

ዋርካውያን
አማን ነው አይደል?
እነ ክቡ ... ካርቦኔ ... ቀለማቸው አለቀ አይደል?
እስረኞችን እየፈቱ ... ወደ ፊት የሚገቡበት ቦታ እያዘጋጁ ይመስላል።
ሰላም ለሃገራችን ... ለህዝባችን!

ለገ-ኮኮቴ
o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o-o
".... Indeed, we Ethiopians are a beautiful multi-lingual and multi-cultural people who in a flower vase called Ethiopia decorate the great continent of Africa", Professor Ephraim Isaac
ኮኮቴ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1290
Joined: Wed Nov 04, 2009 2:07 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Sun Feb 18, 2018 2:24 pm

[url]

[/url]1
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያምን ማን ይተካቸው?
በሃገራችን የተከሰተውን ሁከትና ብጥብጥ ተከትሎ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በራሳቸው ፈቃድ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ ይህችን "ክፍት የስልጣን ቦታ" ለመያዝ ከየአቅጣጫው የሚሰማው ጩሆት በጣም የሚያስገርም ነው፡፡ የስልጣን ጥማት ለካ ከውሃ ጥማት የባሰ የሚያንገበግብ አምሮት ኖሯል! ኮሎኔል መንግስቱ ሀይለማርያም በአንድ ወቅት የተናገሩትን ቃል በቃል በትክክል ባላስታውሰውም "ይህችን ወንበር ለመያዝ ሁሉም ሰው ይመኛል፣ ወንበርዋ ግን አንድ ናት እስዋም እኔ ተቀምጨባታለሁ" ያሉት ለካ ወደው አልነበረም፡፡
ኢትዮጵያ የምትባል ኢምፓየር ፈርሳ ኦሮሚያ ነፃ መውጣት አለባት ሲለን የከረመው ጀዋር መሃመድና የኦነግ ደቀመዛሙርቱም ከጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ስልጣን መልቀቅ በኋላ የሃገሪቱ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒሰትር የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት የሆኑት ክቡር አቶ ለማ መገርሳ መሆን አለባቸው የሚል በግልፅ የታወጀ ዘመቻ ማካሄድ ጀምረዋል፡፡ "እኔ ባልቀምሰውም ኢትዮጵያዊነት ማለት ሓሺሽ ነው፣ ሱስ ነው፣ የግለሰብ ስልጣንና ክብር ከሃገርና ከህዝብ በላይ ስላልሆነ ገደል ይግባ... ወዘተ" በሚሉ መሳጭ የሚድያ ንግግሮቻቸው የታለሉ አንዳንድ የዋህ ኢትዮጵያውያንም ይህንን የጃዋርና ተከታዮቹን ሃሳብ ሲያስተጋቡ ይደመጣል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር የመሰለን ከባድ የመንግስትና የህዝብ ሃላፊነት ዝም ብሎ እንዲሁ የሚያዝ ስልጣን አይደለም፡፡ ለዚህ ከባድ የሃላፊነት ቦታ የሚመጥን የትምህርት ዝግጅት፣ ብቃትና ችሎታ እንዲሁም ልምድና ተሞክሮ በአጠቃላይ ፈረንጆች merit የሚሉት መመዘኛ ከሁሉም በላይ ደግሞ በሃገራችን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር፣ የብሔርና የሃይማኖት ብዝሃነታችንን የሚያስተናግድ፣ ዜጎችን በእኩል አይን የሚያይ ህዝባዊ አመለካከት መላበስን ይጠይቃል፡፡
ከዚህ አንፃር ክቡር አቶ ለማ መገርሳ እስከአሁን ድረስ በተግባር ባሳዩት እንቅስቃሴ ለዚህ ከባድ ሃላፊነት የሚያበቃ ችሎታ፣ የጠራና በተግባር የተፈተነ ህዝባዊ አመለካከት አላቸው ወይ ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው፡፡ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ከሁሉም በፊት ውስብስብ የሆነው ሃገራዊ፣ ከባቢያዊና አለምአቀፋዊ ሁኔታ በሚገባ በመተንተን አመራርና ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል የትምህርት ዝግጅት፣ ቢያንስ የተፈጥሮ ክህሎት ያላቸው መሪ አይመስሉኝም፡፡ የ12ኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተናን ብዙ ጊዜ ወስደው የረባ ውጤት ማግኘት ባለመቻላቸው ከመንግስት የድጋፍ ደብዳቤ ተፅፎላቸው ሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ ገብተው በመከራ ትምህርታቸውን ከጨረሱ በኋላ በኮሌጁ የሚሰጠውን ዲግሪ ይዘው በመውጣት እንደዘመኑ የሃገራችን ፖለቲከኞች ወደ ፖለቲካው አለም የተቀላቀሉ ሰው መሆናቸው ይነገራላቸዋል፡፡
2
በዚህ ሁኔታ ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ የሆነ የህዝብ ቁጥር እንዲሁም የተወሳሰበ የብሔረሰብና የሀይማኖት ስብጥር ያለበትና በሚሊዮኖች የሚገመቱ በአስከፊ ድህነትና ኋላቀርነት የሚኖሩ ዜጎች የሚኖሩባት፣ በተወሳሰበ ከባቢያዊ የፀጥታ ሁኔታና በፈረሱ መንግስታት የተከበበች ሃገር መምራት ቀላል አይመስለኝም፡፡ እንዲህ አይነት ከባድ የሃገርና የህዝብ ሃላፊነት መሸከምን ካላስፈራ ምን ሊያስፈራ እንደሚችል በፍፁም አይገባኝም፡፡ ነጋ ጠባ ጆሮአችንን ባደነቆረው ነገር ግን ምንም አይነት ህጋዊም ሆነ ዲሞክራሲያዊ መሰረት በሌለው የህዝብ ብዛት፣ የመሬት የቆዳ ስፋት...ወዘተ በሚለው መከራከሪያ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ሃገር የመምራቱን ሃላፊነት ተረከቡ እንኳን ቢባሉ "አይ እኔ አልችለውም፣ ይከብደኛል" የማለት ድፍረት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሃገር መምራት በቤተሙከራ የሚገኝ ልምድና ብቃት አይደለም፡፡
ሃገር ለመምራት የሚያስችል ብቃትና ችሎታ መኖርን ለጊዜው ወደ ጎን ትተን ክቡር አቶ ለማ መገርሳ ምን ስለሰሩ ነው ለዚህ ከፍተኛ ሃላፊነት የሚበቁት? ብሎ መጠየቁም ተገቢ ነው፡፡ ሁሉም እንደሚያውቀው እሳቸው ስልጣን ከተረከቡበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት ሶስት አመታት የኦሮሚያ ክልል በሁከትና በብጥብጥ በመታመስ ላይ የሚገኝ ክልል ነው፡፡ በብሔሩ ተወላጆችና ለትውልድ ከክልሉ ህዝብ ጋር ተጋብተውና ተዋልደው ሲኖሩ በነበሩ የሌሎች ብሔር ተወላጆች ህይወትና ንብረት ላይ ከዚህ በፊት በሃገራችን ታይቶም ሆነ ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በየቀኑ ዘግናኝ የሆነ እልቂት እየደረሰ ነው፡፡ እሳቸው በሚመሩት የኦሮሚያ ክልል ዜጎች ፈልገው ባልተላበሱት ማንነት እንደ አውሬ እየታደኑ በጭካኔ እየተገደሉና እየተጨፈጨፉ ነው፡፡ ክቡር አቶ ለማ መገርሳ በሚመሩት ክልል እንዲህ አይነቱን የጭካኔ ተግባር ለማስቆም ጥረት አላደረጉም ብቻ ሳይሆን ቢያንስ አደባባይ ወጥተው በማያሻማ ቋንቋ ድርጊቱን ሲያወግዙ አልሰማንም፡፡ የክልሉ ፕሬዚዳንት ስለኢትዮጵያውነት ለኛ ባማርኛ ቋንቋ የሚያስተላልፉት ሆድን የሚያባባ መልእክትና ለቄሮ ጀሌዎቻቸው በኦሮሚኛ ቋንቋ የሚሰጡት መመሪያ ለየቅል እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ እሳቸው በሚመሩት ክልል በመፈፀም ላይ ያለው ይህ ዘግናኝ ድርጊት በሃላፊነት የሚያስጠይቅ እንጂ ለበለጠ ሃላፊነትና ስልጣን የሚያበቃ ሊሆን አይችልም፡፡
ክቡር አቶ ለማ መገርሳና ጀሌዎቻቸው በክልላቸው ያቀጣጠሉት ዘርን ማእከል ያደረገ ሁከትና ብጥብጥ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ከተቆናጠጡ በኋላ ችግሩን ሃገራዊ መልክ በማስያዝ ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማ ያለው እና ከስድሳ አመታት በላይ የቆየው የነኦነግን የጥፋት አጀንዳ ለማስፈፀም የታቀደ እንዳይሆንም መጠርጠር ያስፈልጋል፡፡
3
ከዚህ በተጨማሪ ቄሮዎችን በማደራጀት ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ስልጣን ማግኘት የሚቻል ከሆነስ ሁሉም በየክልሉ የጎበዝ አለቃ እያደራጀ እድሉን ከመሞከር ወደኋላ የማይልበት ምን ማረጋገጫ አለን? ማቆሚያውስ የት ሊሆን ይችላል ብሎ መጠየቁም ተገቢ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያምን መተካት ያለበት ከኦሮሞ ብሔር ነው የሚባለው የክርክር መነሻም ግልፅ አይደለም፡፡ አመራር ብቃትና ህዝባዊ አመለካከት መላበስን ይጠይቃል ከተባለ በህገመንግስቱ መሰረት ብቃትና ህዝባዊ አመለካከት ያለው ከሌላ የሃገራችን ብሔር/ብሔረሰብ የተገኘ ጠቅላይ ሚነስትር መሆን የማይችለበት ምክንያት ምንድነው? ምን ይከለክለዋል?
ቀጣዩ የሃገራችን መሪ ከኦሮሞ ብሔር መሆን አለበት ከተባለስ ከ35 ሚሊዮን በላይ ከሆነው የኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ከክቡር አቶ ለማ መገርሳ የተሻለ ብቃትና በተግባር የተፈተነ ህዝባዊ አመለካከት ያለው ሌላ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ የለም ማለት ነው?
ህዝባዊ አመለከካከት ስለኢትዮጵያዊነት በሚድያ በመስበክ የሚገኝ ሳይሆን በተግባር ህዝባዊ ሆኖ መገኘትን እንዲሁም የራስን ጨምሮ በማንኛውም ሀዝብ ላይ የሚፈፀም ፀረህዝብ ተግባራት አምርሮ መታገልን፣ የሚጠይቅ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝን የሚተካ መሪ ኦሮሞን ጨምሮ ከየትም ብሔር ይሁን ከየት ቢያንስ ይህንን ስብእና የሚያሟላና ህዝባዊነቱን በተግባር ያረጋገጠ ሰው መሆን አለበት፡፡
አምላክ ሃገራችንን ሰላም ያድርግልን፡፡
አለባቸው ሁነኛው
የካቲት 10 ቀን 2010
ፍንፍኔ/ሸገር/አዲስ አበባ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Tue Feb 20, 2018 6:31 pm

“በአሁኑ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ሊተካ የሚችል ማን እንደሆነ ታውቋል!!”
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን መልቀቃቸውን በተመለከት ተኪ መሪ ማን ይሁን በማለት በዓይጋ ፎረምም ሆነ በፌስቡክ ክርክር እየተነሳ ነው። አንዳንድ ሰዎች ለማ መገርሳን ብቁ አይደሉም ይላሉ። አቶ ታምራት ሁንዴ ደግሞ እንደው እንደ አቶ ለማ መገርሳ ብቁ የለም ሲሉ ሃሳባቸው ያሳረፉበትን ፅሁፍ በማንበቤ እኔም እርምትና ያለኝ ሃሳብም በአጭሩ ለመጫር ወደድኩኝ።
በእርማቱ ልጀምርና አንዳንድ የኦሮሞ ወንድሞቻችን አቶ ታምራት ሁንዴም “የኦሮሞ ህዝብ ከጠቅላላው የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ቁጥር የያዘ” ህዝብ መሆኑን ፅፈዋል። ይህ አስተሳሰብ የኦሮሞ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ የአብዘሃ (majority) ቦታ እንዳለው በማስቀመጥ እንደአብዘሃነቱ ደግሞ የሱ ቋንቋ፣ አመለካከትና የኢትዮጵያን መፃኢ እድል የመወሰን ስልጣን ወይም ድምፅ እንዳለው አድርገው የሚያስቡና ያሰቡትንም የሚያጋሩ ቁጥር እየበዛ ነው። ኦህዴድም ይህ አስተሳሰብ እየተከተለ እንደሆነ አላውቅም ግን እንደ ድርጅት የኦሮሞ ቋንቋ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሆን ፍላጎት እንዳለው ገልፆልናል። ያውም ኢትዮጵያዊ ወይም አፍሪካዊ ያልሆነው የላቲን ፊደል ከኦሮሞ አልፎ የኢትዮጵያ እንዲሆን ማለት ነው። እዚሁ ላይ በማያሻማ መልኩ መቀመጥ ያለበት የኦሮሞ ህዝብ ከጠቅላላ የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ቁጥር የለውም የሚለው ነው:: በብሄር ደረጃ ከብሄሮች ሁሉ ከፍተኛ የህዝብ ቁጥር ግን አለው። ስለ ኦሮምኛ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋ መሆንና አለመሆን ሌላ ጊዜ ልመለስበት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያምን ማን ይተካ ለሚለው ግን በኔ እምነት የዲግሪ መኖር እና አለመኖር መመዘኛ ባይሆን እመርጣለሁኝ። ነገር ግን ከብሄር አስተሳሰብ የወጣና የኢትዮጵያ አንድነትን የሚያምንና የሚያስቀድም ለተግባራዊነቱም ኢህአዴግን ወደ አንድ ሃገራዊ ፓርቲ ለማምጣት የሚታገል፣ ብሄራዊና ክልላዊ አመለካከቶችን በጎጂነታቸው የተረዳና የጋራችን አጀንዳችን ኢትዮጵያዊነት መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ ዳግም የሚያበስር መሪ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁኝ። ይህም ማለት የክልሎችና የፌደራል ስልጣን በተመጣጠነ መልኩ ማለትም የፌደራል መንግስት በክልሎች መተግበር ያለባቸውን የዜጎች መብት የማስጠበቅ ስልጣን እንዳለው ማረጋገጥ የሚችል፣ ዜጎች በፈለጉትን የአገሪቱ ምድር የመኖር መብታቸው ክልሎች በግድ ማስከበር እንዳለባቸው መቆጣጠርና የዜጎች መብት በተጣሰ ቁጥርም የመብት ጥሰቱን የፈፀሙና ያስፈፀሙ የክልሉ ባለስልጣናትን በፌደራል ፍርድ ቤት ማስቀጣትና ተበዳዮችንም መካስ እንዲቻል ለዚሁ ሁሉ የግለሰቦች መብትና ጥቅም ጠበቃ የሚሆን መሆን አለበት እላለሁ። ለዚሁም ብቁ የአመራር ችሎታና ልምድም ያስፈልጋል። ማን ይሁን ለሚለው ግን ምርጫው የኔ ቢሆን ከብአዴን መሆን አለበት ባይ ነኝ። እንደውም “በጥልቅ ተሃድሶው” ካልተመቱ በቀር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን ቦታቸው ነው የሚል እምነት አለኝ።
ስለ አቶ ለማ ግን በዚሁና በሌላ መመዘኛም ህዝብን የማስተዳደር ብቃታቸው ገና ያልታወቀና ያልታየ ነው። በእውነቱ ከሆነ አሁን በግርግሩ ወቅት ለዘብ ያለ ሃሳብ እና ኢትዮጵያውያንን የማለሳለስ ስልት ከመጠቀም ውጭ ግን በኦሮሚያ ያለው አድማ፣ ንብረት የማውደምና ህይወት የማጥፋት ሂደትም ለማስቆም ያልቻሉና ምንም ዓይነት ለውጥ ማምጣት ያልቻሉ ሰው መሆናቸው በተግባር እያየን ነው። ስለዚህ አቶ ለማ ችሎታቸውና ብቃታቸው ገና ማሳየት ያለባቸው ሰው ናቸው።
ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!
ሙሉጌታ ታዘለ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Feb 20, 2018 11:10 pm

Article 73 Appointment of the Prime Minister 1. The Prime Minister shall be elected from among members of the House of Peoples’ Representatives. 2. Power of Government shall be assumed by the political party or a coalition of political parties that constitutes a majority in the House of Peoples’ Representatives.
በነገራችን ላይ የሕገመንግሥቱ አንቀፅ 73 እያለ አቶ ለማ መገርሳ እንዴት ነው ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1096
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Thu Feb 22, 2018 5:58 pm

1
ተንጋሎ ቢተፉ ተመልሶ ታፉ!
የህግ የበላይነት ይከበር!
ውድ የኢትዮ ጵያ ብሔሮች፣፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች!!
ውድ ህይወታቸውንንና የወጣትነነት ዘመናቸውንን ለአፍታም ቢሆንን ሳይሰስቱ የገበሩ መላ የአገራችንን ሕዝቦች፣፣
ብሄሮችና ብሄረ ሰቦች እንንዲሁም የተለያዩ የፖለቲካ አቋም የነነበራቸው ድርጅቶች የዛሬ 2277 ዓመት በፊት ጋህድ
የሆነነውንን ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንንባት፣፣ ህግና ህገ--መንንግስታዊ ስርዓት የሚከበርባት አገር እንንድትኖረ ንን
በማሰብ ነነበር። እንንደታሰበውም ህዝብና መንንግስት ባደረ ጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ከዘመነነ መሳፍንንት ጀምሮ
እስከ ደርግ ዘመነነ መንንግስት በነነበሩ የጨለማ ዓመታት ለማሰብ እንንኳንን የማይሞከሩ የነነበሩ የመቃወም፣፣ ሃሳብንን
በነነፃፃነነት የመግለፅ መብት፣፣ የመደራጀትና ሃብትንን የማፍራት መብቶች እና ሌሎች መሰረ ታዊ የሚባሉ ሰብአዊና
ዴሞክራሲያዊ መብቶች ከመረ ጋገጣቸውም ባለፈ የአገሪቱ ኢኮኖሚም ከቁልቁለት ጉዞ ((ከሚታወቅበት
የረ ሃብና ድርቁርና ታሪክ)) ተላ ቆ አዛኛዎቹ ዜ ጎቿ በቀንን 33 ጊዜ በልተው የሚኖሩባት አገር ፈጥረዋል።
ይሁንንና ኢህአዴግ የሚመራውንን መንንግስት ባለፉት 2277 ዓመታት መስራት ይገባው የነነበረ ፖለቲካዊ፣፣
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ስራዎች ባለመስራቱ የተነነሳ ሩብ ክ//ዘመንን የተለፋባቸው ትልልቅ አገራዊ ስራዎች
በቀናት ውስጥ ወደ አመድ ሲቀየሩ ማየት በዚህ 44 እና 55 ዓመታት ውስጥ የተለመደ ሆኗል። የሚገርመውም ለ
1177 ዓመታት ያህል በርካታ ፈታኝ ወቅቶች እየበገረ የመጣውንን ኢህአዴግ ከተማ ከገባ በኋላ የታገለበትንን አላማ
ረ ስቶ ህዝባዊ ወገንንተኝ ነነቱንን እየተሸረ ሸረ ፣፣ የሃሳብ ብዝሃነነትንን ማስተናገድ ተስኖት፣፣ በትግራይ በረ ሃዎች ከህዝብ
አብራክ እንንዳልተፈጠረ ህዝብንን የማዳመጥ ባህሉ ጠፍቶ፣፣ ““እኔኔ ልሙት እናንንተ ትግሉንን አስቀጥሉ”” እያሉ ፈንንጅ
በእግራቸው የጠረ ጉ ጓዶቻቸው አደራ ረ ስቶ በአሁኑ ወቅት ““አንንተ ሙት እኔኔ ልኑር”” ወደሚለው የስስት ጫፍ
እያመራ፣፣ ብሄራዊ ድርጅቶቹም ባዕድ እስኪመስሉ አንንዱ ሌላውንን በጠላ ትነነት ዓይንን እያየ ጥሎ ለማለፍ
የሚፎካከሩ እንንዲሁም ““እኔኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል”” እንንዳለችው አህያ አይነነት አስተሳሰብ በእጅጉ ቦታ
እየያዘ መጥቷል። ውጤቱም በግልፅ መታየት ጀምሯል ብቻም ሳይሆንን አገር ለማፍረ ስም እየተንንደረ ደረ ነነው።
ጉዳዩ አገር የማዳንን ጉዳይ ስለሆነነ ኢህአዴግ ጥልቅ ተሃድሶ እያለ በያዝ ለቀቅ የሚያጠፋውንን ጊዜ ብዙ
ሊያሰራው እንንደሚችል ተረ ድቶና እርስ በርስ በጎሪጥ ከመተያየት ወጥቶ ምንንም እንንኳንን የራስህንን እጅ በራስ
መቁረጥ ድፍረ ትና ጥንንካሬ የሚጠይቅ ቢሆንንም ህዝብንንና አገርንን የሚያስቀድም አመራር ይኼንን ከማድረግ
ወደኋላ አይልም ብቻ ሳይሆንን ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ ስለሌለው የፖለቲካ አመራሩ በዚህ መንንገድ
ተበጥሮ ማለፍ ግድ ይለዋል። ከዚህ ባልተናነነሰ ግንን ህገ--መንንግስቱንንና ህገ--መንንግስታዊ ስርዓቱንን ለመጠበቅ
ተብለው የተቋቋሙ እንንደ የአገር መከላ ከያ ሰራዊት፣፣ የፌዴራልና የክልል ፖሊስ፣፣ ፍርድ ቤቶች፣፣ የፀጥታ አካላ ት
የመሳሰሉት ተቋማት ያለማወላወል የህግ የበላ ይነነትንን ማስከበር አለባቸው።
እዚህ ላ ይ ልብ ሊባል የሚገባው ትላ ንንትና ላ ይመለሱ የቀበርናቸው ዘውዳዊና አምባገነነንን ስርዓቶች ርዝራዦች
ማጣጣም የጀመርነነውንን ዴሞክራሲ ለማኮላ ሸትና የድሮ ስርዓት ዳግም ለመመለስ የሚታትሩ ሃይሎች ባጠፉት
ልክ መቀጣት ሲገባቸው በአጉል ጫጫታና ህዝበኝ ነነት//ጭራነነት ((Pooppuulliissm)) ባላ ቸው የፖለቲካ ተሳትፎ
ምክንንያት የተያዙ ((የፖለቲካ እስረ ኞች)) ሳይኖሩንን ““የዴሞክራሲ ምህዳሩንን ለማስፋትና ብሔራዊ መግባባትንን
ለመፍጠር”” በሚል አጉል ፈሊጥ ይህንን ያህል የፖለቲካ እስረ ኞች ፈትተናል መባሉ በአንንድ በኩል ህዝቡ
የታገለለትንን አላማ መፃፃረ ር ሲሆንን በሌላ በኩል ደግሞ የህግ የበላ ይነነትንን እንንዲያስከብሩ ተብለው የተቋቋሙ
ተቋማት ሃላ ፊነነትና ስልጣንን መጋፋት ይሆናል። በዚህ ከቀጠለም ““ሴት አስገድዶ በመድፈር”” ወንንጀል
የተከሰሰንን ግለሰብ ሳይቀር በጫጫታ መፈታቱ አይቀርም። ምክንንያቱም ዴሞክራሲያዊ ምህዳሩ ማስፋት እና
ብሔራዊ መግባባት መፍጠር የሚቻለው ኢህአዴግ ““እመራበታለሁኝ ”” የሚለውንን ልማታዊ ዴሚክራሲያዊ
((አብዮ ታዊ)) መስመር ልዕልና እንንዲያገኝ የሚሰሩ እንንደ ት//ቤቶች፣፣ የፍትህ ተቋማት፣፣ ሚዲያዎች፣፣ ነነፃፃ የሲቪክ
ማህበራትና አደረ ጃጀቶች፣፣ የፖለቲካ ድርጅቶች… ወዘተ ያላ ቸውንን የአሰራር ክፍተት//አቅም በማስተካከል እና
ቀጣይነነት ያላ ቸው የግንንባታ ስራዎች በመስራት እንንጂ ህገ--መንንግስታዊ ስርዓቱንን ለማፍረ ስ ሲንንቀሳቀሱ የተገኙ
2
ወንንጀለኞችንን በመልቀቅ አይደለም። ይህ በየትኛውም አገርና መንንግስት ተደርጎ አይተንንም ሰምተንንም
አናውቅም። በቂ መረ ጃና ማስረ ጃ ሳይኖራቸው የታዙ ሰዎች ከነነበሩም ከመጀመሪያውኑ ትክክል አልነነበረም፣፣
አለበለዚያ ግንን ማንንም ከህግ በላ ይ ስላ ልሆነነ የፍርድ ቤት ውሳኔኔ ተግባራዊ መደረግ አለበት።
ከወንንጀል ህግ አላማዎች ውስጥ ““አጥፊዎችንን ማስተማር”” አንንዱ ሲሆንን መንንግስት እየሄደበት ያለው
እስረ ኞችንን በጅምላ የመፍታት ሂደት ““ተንንጋሎ ቢተፉ ተመልሶ ታፉ”” እንንዲሉ በሌላው የማህበረ ሰብ ክፍል
““ህግ የለም”” እንንዲል፣፣ አጥፊው ““ከመጀመሪያውም ሳናጠፋ ነነው የተያዝነነው”” እንንዲልና ሌላውም ህግንን
እንንፈራና እንንዲያከብር ሳይሆንን ““እኔኔም ወንንጀል ብሰራ ነነገ እለቀቃለሁኝ ”” የሚል የተሳሳተ አረ ዳድ በመያዝ
ተመልሶ ፈተና የሚሆንንበት ዕድል ከመስጠት አልፎ ሌት ተቀንን ህግንን በማስከበር ስራ ላ ይ የተሰማሩ
አካላ ት//ሰዎች ልፋታቸውንን ገደል ከቶ ተሰፋ የሚያስቆርጥ ተግባር ነነው። በመሆኑም የአገራችንን የፀጥታ
ሃይሎችና ህግ አስከባሪ ተቋማት ህገ--መንንግስቱ የሰጣቸው ስልጣንን ሳይሸራርፉና ለህዝብ ወግነነው በአገር
ውስጥም ሆነነ ውጭ ሆነነው ስልጣንን በአቋራጭ ለማግኘት እየተንንቀሳቀሱ ያሉ እንንዲሁም በኢህአዴግ ውስጥ
((Doouubbllee Sttaannddaarrdd)) እና ከኢህአዴግ ውጭ ያሉ ህዝቡንን እርስ በርሱ እያናቆሩ የሚገኙ የኪራይ ሰብሳቢ
ፖለቲካል ኢኮኖሚ ሃይሎች አገራችንን ሊያፈርሷት ስለማይገባ ከየትኛውም ጊዜ በላ ይ ተከታትለው አገር
የማዳንን ሃላ ፊነነታቸው መወጣት አለባቸው። በነነገራችንን ላ ይ የአንንድ አገር ጥንንካሬ ወይም ኃያልነነት የሚለካው
በዜ ጎች የማምረ ት አቅም ((Mooddeess ooff Prroodduuccttiioonn)) ከሚፈጠረው ኢኮኖሚ በተጨማሪ ዜ ጎች በነነፃፃነነት
የሚንንቀሳቀሱባት፣፣ ሰርተው የሚኖሩባት እና የአገሪቱንን ሰላምና መረ ጋጋት ሊያረ ጋግጡ የሚችሉ የፍትህ
ተቋማት ((Puubblliicc IInnssttiittuuttiioonnss)) ሲኖሩ፣፣ ከውስጥና ከውጭ የሚቃጡ ጥቃቶችንን መመከት የሚችል ግዙፍ
የመከላ ከያ ኃይል እንንዲሁም ከውስጥም ሆነነ ከውጭ የሚሰነነዘሩ የኢኮኖሚና የፖለቲካ አሻጥሮችንን ማክሸፍ
የሚችል ለህዝብና ለህገ--መንንግስቱ ውግንንና ያለው ጠንንካራ የፀጥታ መዋቅር ካላ ት ነነው። የቱርክና የግብፅ
የፀጥታ ሃይሎች በተለያዩ አጋጣሚዎች በየአገራቸው ተፈጥረው የነነበሩ ቀውሶች የፈቱበትንን መንንገድ ለእኛ
((ለአገራችንን)) ከበቂ በላ ይ ማሳያ ናቸውና ልንንማርባቸው ይገባል።
ኩራባቸው ታዬ
አዲስ አበባ
1144//0066//22001100 ዓ..ም
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ደጉ » Fri Feb 23, 2018 3:03 pm

ኮኮቴ wrote:ዋርካውያን
አማን ነው አይደል?
እነ ክቡ ... ካርቦኔ ... ቀለማቸው አለቀ አይደል?
እስረኞችን እየፈቱ ... ወደ ፊት የሚገቡበት ቦታ እያዘጋጁ ይመስላል።
ሰላም ለሃገራችን ... ለህዝባችን!

ለገ-ኮኮቴ

...ምን የነን ቀለም ብቻ የ ሳይበር ኢትዮጵያንም ቀለም ጨርሰውት ነበር ... :-) አዎ እስረኞች ካልተፈቱ በቂ ቦታ ለነሱ ስለማይኖር ብዙ እስረኞችን መልቀቅ ግድ ነው ... ይመስለኛል በቅርብ ቀን እነ ክብራንና መስሎቹን ሙዚየም በሚሆነው ማእከላ ውስጥ እንደ ዱር እንስሳ እናያቸዋለን.... :-)
እንባቸውን እና ንፍጣቸውን እያዝረከረኩ ሲያለቅሱ የነበሩት ሁሉ የት ገቡ ግን..??? ቅቅቅቅ
"STUPID IS AS STUPID DOES " :D
ደጉ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4421
Joined: Mon Dec 15, 2003 10:39 am
Location: afghanistan

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Sat Feb 24, 2018 1:34 pm

ድድንንቄቄምም ተተሃሃድድሶሶ!!!!
የየስስልልጣጣንን አአተተያያያያችችንን ተተበበላላሽሽቷቷልል ብብሎሎ የየጀጀመመረረውው የየኢኢህህአአዴዴግግ ተተሃሃድድሶሶ ከከጠጠቅቅላላይይ ሚሚኒኒስስትትርር ሀሀይይለለማማርርያያምም የየሰሰልልጣጣንን መመልልቀቀቂቂያያ ደደብብዳዳቤቤ በበኋኋላላ መመታታደደሱሱንን ሳሳይይሆሆንን በበሽሽታታውው ኩኩፉፉኛኛ እእንንዳዳገገረረሸሸበበትት የየሚሚያያሳሳዩዩ ምምልልክክቶቶችች በበግግልልፅፅ እእየየታታዩዩ ነነውው፡፡፡፡
ጠጠቅቅላላይይ ሚሚኒኒስስትትርር ሀሀይይለለማማርርያያምም ስስልልጣጣንን በበቃቃኝኝ ብብለለውው ድድንንገገተተኝኝነነትት ያያለለውው በበሚሚመመስስልል መመልልኩኩ ለለድድርርጅጅታታቸቸውው በበኋኋላላምም በበቴቴቭቭዥዥንን መመስስኮኮትት ለለመመላላውው አአለለምም ከከገገለለፁፁ በበኋኋላላ በበግግልልፅፅ እእየየታታዩዩ ያያሉሉ ምምልልክክቶቶችች የየድድሮሮ ኢኢህህአአዴዴግግ ይይቅቅርርናና በበድድንንገገትት ካካረረፉፉትት ከከቀቀድድሞሞውው ጠጠቅቅላላይይ ሚሚኒኒሰሰትትርር መመለለስስ በበኋኋላላ ከከነነበበረረውው ከከቅቅርርብብ ጊጊዜዜውው ኢኢህህአአዴዴግግ ጋጋርር ፈፈፅፅሞሞ ለለማማነነፃፃፀፀርር የየሚሚቻቻልል አአይይመመስስልልምም፡፡፡፡ በበሌሌሎሎችች የየኢኢህህአአዴዴግግ አአባባልል ድድርርጅጅቶቶችች ውውስስጥጥ ምምንን ሁሁኔኔታታ እእንንዳዳለለ ባባላላውውቅቅምም በበኦኦሮሮሚሚያያ ያያለለውው ኦኦህህዴዴድድ ግግንን መመጀጀመመሪሪያያ የየአአቶቶ ለለማማ መመገገርርሳሳናና የየዶዶ//ርር አአብብይይ አአህህመመድድ ፎፎቶቶግግራራፍፍ በበተተሽሽከከርርካካሪሪዎዎችች መመስስተተዋዋትት ላላይይ ለለጥጥፎፎ የየምምረረጡጡኝኝ አአይይነነትት የየሚሚመመሰሰልል ቅቅስስቀቀሳሳ ወወይይምም እእኛኛ ካካልልተተመመረረጥጥንን የየሚሚልል ማማስስጠጠንንቀቀቂቂያያ አአዘዘልል መመልልእእክክትት ሲሲተተላላለለፍፍ ከከረረመመ፡፡፡፡
ከከዚዚያያምም በበመመቀቀጠጠልል በበየየድድረረገገፁፁ አአሁሁንን በበተተፈፈጠጠረረውው እእድድልል የየሃሃገገሪሪቱቱ ጠጠቅቅላላይይ ሚሚኒኒስስትትርር ኦኦሮሮሞሞ ካካልልሆሆነነ አአመመፅፅ ይይቀቀጣጣጠጠላላልል የየሚሚልል እእንንቅቅስስቃቃሴሴ መመታታየየትት ጀጀመመረረ፡፡፡፡ አአረረ በበአአንንዳዳንንድድ አአከከባባቢቢዎዎችች''ማማ የየኦኦህህዴዴድድ ከከፍፍተተኛኛ አአመመራራሮሮችች ሳሳይይቀቀሩሩ ህህዝዝቡቡንን ሰሰብብስስበበውው የየማማረረጋጋጋጋትት ስስራራ እእየየሰሰራራንን ነነውው ባባሉሉበበትት መመድድረረክክ ሁሁሉሉ ""ዘዘንንድድሮሮ የየኛኛ ነነውው፣፣ የየኛኛ ካካልልሆሆነነ የየምምናናደደርርገገውውንን እእናናውውቃቃለለንን"" የየሚሚልል ዛዛቻቻ በበአአደደባባባባይይ ሲሲያያስስተተጋጋቡቡ ተተደደምምጠጠዋዋልል፡፡፡፡
በበዚዚህህ ራራስስንን በበራራስስ የየመመሾሾምም ውውሳሳኔኔ መመሰሰረረትትምም እእንንትትናና የየሃሃገገራራችችንን ጠጠቅቅላላይይ ሚሚኒኒስስትትርር ይይሆሆናናልል!! አአይይ እእንንትትናና ነነውው ሊሊሆሆንን የየሚሚችችለለውው ብብሎሎ ማማወወዳዳደደርር ብብቻቻምም ሳሳይይሆሆንን አአይይ እእንንትትናና''ማማ እእንንዲዲህህ ነነውው እእንንዲዲህህ አአይይነነትት ጥጥፋፋትት ፈፈፅፅሟሟልል፣፣ እእንንዲዲህህ አአላላደደረረገገምም፣፣ እእንንትትናና ግግንን እእንንዲዲህህ ነነውው የየሚሚሉሉ ዘዘመመቻቻዎዎችችንን በበማማጧጧጧጧፍፍ አአንንዱዱንን ከከፍፍ ሌሌላላውውንን ደደግግሞሞ ዝዝቅቅ ማማድድረረግግ ብብቻቻምም ሳሳይይሆሆንን በበግግላላጭጭ የየስስምም ማማጥጥፋፋትት ዘዘመመቻቻውውንን ተተያያያያዙዙትት፡፡፡፡ ዘዘንንድድሮሮ የየኦኦሮሮሞሞ ተተራራ ወወይይምም እእድድልል ነነውው ካካሉሉ በበኋኋላላ አአንንዱዱንን ኦኦሮሮሞሞ ከከሌሌላላኛኛውው ኦኦሮሮሞሞ ጋጋርር ብብቃቃትትንን መመሰሰረረትት ባባደደረረገገ መመስስፈፈርርትት ብብቻቻ ማማወወዳዳደደርር እእየየተተቻቻለለ የየስስምም ማማጥጥፋፋትት ዘዘመመቻቻውው ምምንን እእንንዳዳመመጣጣውው በበቅቅጡጡ ለለመመረረዳዳትት አአስስቸቸግግሮሮ ሰሰነነበበተተ፡፡፡፡
የየአአንንድድንን ሃሃገገርር መመሪሪ የየሚሚመመረረጠጠውው በበምምርርጫጫ ወወይይስስ እእንንደደ እእቁቁብብ በበተተራራ ነነውው የየሚሚለለውውንን ስስናናስስብብ ደደግግሞሞ አአሁሁንን በበኦኦህህዴዴድድ እእየየተተካካሄሄደደ ያያለለውው ሁሁለለትት አአቅቅጣጣጫጫ ያያለለውው እእኔኔ ብብቻቻ ያያልልኩኩትት መመሆሆንን አአለለበበትት የየሚሚልል እእስስትትራራተተጂጂ መመሆሆኑኑ ግግልልፅፅ ሆሆኗኗልል፡፡፡፡ የየመመጀጀመመሪሪያያውው እእስስትትራራተተጂጂ ዘዘንንድድሮሮ የየአአቶቶ ሀሀይይለለማማርርያያምም ምምትትክክ ሆሆኖኖ ""መመመመረረጥጥ"" ያያለለበበትት የየግግድድ ኦኦሮሮሞሞ መመሆሆንን ያያለለበበትት ይይሉሉናና፣፣ ሁሁለለተተኛኛውው አአስስትትራራተተጂጂ ደደግግሞሞ ለለፎፎርርማማሊሊቲቲ ሁሁሉሉምም የየኢኢህህአአዴዴግግ አአባባልል ድድርርጅጅትት የየየየራራሱሱ ሰሰውው ያያቅቅርርብብናና ከከዛዛ በበኋኋላላ ምምርርጫጫውው ይይካካሄሄዳዳልል፡፡፡፡ በበዚዚህህ ምምርርጫጫ ""ባባለለተተራራውው ኦኦሮሮሞሞ ካካልልተተመመረረጠጠ"" ግግንን በበሃሃገገራራችችንን ስስላላምም አአይይኖኖርርምም ይይላላሉሉ፡፡፡፡
ግግንን ይይህህ ሁሁሉሉ የየኦኦሮሮሞሞ ወወጣጣትት የየሞሞተተውው፣፣ የየቆቆሰሰለለውው፣፣ የየህህዝዝብብ ሃሃብብትትናና ንንብብረረትት የየጋጋየየውውናና የየወወደደመመውው ለለዚዚህህ ነነበበርር ማማለለትት ነነውው?? አአቶቶ ሀሀይይለለማማርርያያምም ማማንን ወወራራሽሽ የየመመሰሰየየምም መመብብትትናና ስስልልጣጣንን እእንንደደሰሰጣጣቸቸውው ባባይይታታወወቅቅምም እእኔኔንን የየሚሚተተካካኝኝ ከከኦኦሮሮሞሞ ነነውው ብብለለዋዋልል እእየየተተባባለለምም በበኦኦህህዴዴድድ ሰሰፈፈርር በበስስፋፋትት እእየየተተወወራራ ነነውው፡፡፡፡ በበዚዚያያውውምም ""እእኔኔንን ነነውው፣፣ የየለለምም እእኔኔንን ነነውው"" ይይተተካካኛኛልል ያያሉሉትት እእየየተተባባባባሉሉ እእርርስስ በበርርስስ መመነነታታረረክክምም ተተጀጀምምሯሯልል አአሉሉ፡፡፡፡ ከከዚዚህህ
አልፎ ጠቅላይ ሚኒሰትሩ በእርስ በርስ ንትርክ ውስጥ የተጠመዱት እነዚህን ሰዎች በተናጠል እያገኙ
ቀጣዩ እኔን የሚተካ ጠቅላይ ሚኒስትር አንተ ብትሆን ትመቸኛለህ እያሉ በመሃከላቸው የተፈጠረውን
የውስጥ ንትርክ ቤንዚን በማርከፍከፍ እያጋጋሉት ነው ይባላል፡፡፡፡
የኢህአዴግ ውስጠ ዴሞክራሲ፣ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ......ወዘተ የሚባሉት መለያ ባህርያቶቹ በቅፅበት
በየትኛው በር በኩል በነው እንደጠፉ ለማወቅ ይቸግራል፡፡፡፡ ወይስ ሲተኩስ በማንኪያ........ እንደሚባለው
ሳይመች ሲቀር ምርጫ አያስፈልግም ምንም አይደለም ዝም ብላችሁ ተቀበሉ እየተባለ ይሆን?
የአለማችን አለቆችም ከበስተጀርባ ሆነው ግፋ በለው እያሉ እንደሆነ ይሰማል፡፡፡፡ አሮሞ ወደ ጎን ተገፍትሮ
((margiinalliized ሆኖ)) የቆየ ህዝብ በመሆኑ አሁን ወደዳችሁም ጠላችሁም ቀጣዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ
ሚኒሰትር መሆን ያለበት ከኦሮሞ ነው ብለው ወስነዋል እየተባለ በዚያው በኦህዴድ ጓዳ በስፋት እየተወራ
ነው፡፡፡፡ እንደዛ ከሆነ ታዲያ በሰመ ተሃድሶና ግምገማ ይህ ሁሉ ጭቅጭቅ ለምን አስፈለገ? የኢህአዴግ
ምክር ቤት ተሰብስቦ ለምን ምርጫ ያካሄዳል? የሃገሪቱ ፓርላማስ ተሰብስቦ ቀጣዩን ጠቅላይ ሚኒስትር
መምረጥ ለምን አስፈለገው? እንዲሁ በጨበጣ እንትናን ሹመናል ብለው ለምን አያሳውቁንም ወይም
አያውጁልንም? በማከታተልም ለምን ያች ድሮ ስንሰማት ያደግነው የፍየል ወጠጤ ...... አያሰዘፍኑልንም?
ይህንን አጭር መጣጥፍ እያዘጋጁሁ በነበረበት ቅፅበት አንድ ውስጡ ውስጡን ሲወራ የሰነበተ ሰበር ዜና
በሚል በሚድያ ሲያስተጋባ ብዕሬን በጣቶቼ መሃል እንደቀረቀኩኝ ቀና አልኩኝ፡፡፡፡ ዜና ሰባሪው ጋዜጠኛ
የኦህዴድ ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ ከሊቀመንበርነታቸው አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው፣ በሶሰተኛ ቦታ
በድርጅት ፀሃፊነት የነበሩት ዶ//ር አብይ አህመድ ደግሞ በብርሃን ፍጥነት ሁለት ደረጃ ወደላይ
ተስፈንጥረው የድርጅቱ ሊቀመንበር ሆነው እንደተሰየሙ ሲያበስር በድንጋጤ ክው አልኩኝ፡፡፡፡ ብዕሬን
ከጠረጴዛው ላይ አስቀምጨ በጣም ስቅስቅ ብዬ ሳቅሁኝ ይሻላል አለቀስኩኝ፡፡፡፡ ብቻ ግራ የሚያጋባ ስሜት
መላው ሰውነቴን ሲወረኝ ተሰማኝ፡፡፡፡ ብቻዬን ታጥቦ ጭቃ!! አልኩኝ፡፡፡፡ ነገሩ ሁሉ የልጆች እቃ እቃ ጨወታ
መስሎ ተሰማኝ፡፡፡፡ የስልጣን አተያያችንን ለማስተካከል ተብሎ የተጀመረው ተሃድሶ መጨረሻው ይኸው
ሆነና አረፈው አልኩኝ፡፡፡፡ በልቤ፡፡፡፡
መስከረም 2 ቀን 11967 ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ከስልጣናቸው እንደተነሱ የሆነው ሁሉ ትዝ ብሎኝ አርባ
አራት አመት ወደኋላ ነጎድኩኝ፡፡፡፡ በተፈጠረው ግርግር በትረ ስልጣኑ ከህዝቡ የነጠቀው ወታደራዊው
ደርግ መጀመሪያ የሾማቸውን ጄኔራል አማን አንዶምን ከገደለ በኋላ ጄኔራል ተፈሪ በንቲን ሊቀመንበር፣
ኮ//ል አጥናፉ አባተን ምክትል ሊቀመንበር ሻለቃ ((በኋላ ኮ//ል)) መንግስቱ ሀይለማርያምን ፀሃፊ አድርጎ
እንደሾመ ሲያበስረን ታወሰኝ፡፡፡፡ ብዙም ሳይቆይ ዋነኛው ሰውዬ ግን እኮ ከበስተኋላ ያለው ነው እየተባለ
መወራት ጀመረ........፣ ከዚያ በኋላ የሆነው ሁሉ ሆነ፡፡፡፡ አሁንስ? ከዚህ በኋላስ ባልቀጥል ይሻላል፡፡፡፡ ለጊዜው
እዚሁ ባበቃ የሚሻል መሰለኝ!! ቀይ ሽብር እንዳይፋፋምብኝ ፈራሁ፡፡፡፡ ዘንድሮ ምኑ ይታወቃል!!!!
መምህር መራራ ታዘበ
ከፍንፍኔ
የካቲት 115 ቀን 20110
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Sun Feb 25, 2018 5:40 pm

1
ኦህዴድና
የአስቸ የአስቸኳይ ኳይ ጊዜ አዋጁ
የኦህዴድ
ማዕከላዊ ኮሚቴ በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ ብዙም የመገናኛ ብዙኋን ብዙኋንን ትኩረት ያልሳበ ነገር ግን ለስብሰባ
በተጠሩት የድርጅቱ የማዕከላዊ ከሚቴ አባላት አማካይነት የሃገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ አንድ ትልቅ ጉዳይ ተነስቶ
ነበር፡፡
የአመራር
ሽግሽግ ማካሄድ በሚል አጀንዳ ላይ ለመነጋገር ለስብሰባ የተጠሩት እነዚ እነዚሁ የድርጅቱ የማዕከላዊ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት
ስብሰባውን የጠራው የድርጅቱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በእለቱ ወደተያዘው ዋና የመነጋገሪያ አጀንዳ ከመግባቱ በፊት አንድ
አንገብጋቢ ወቅታዊ ጉዳይ በማንሳት ስራ አስፈፃሚው ምላሽ እንዲሰጥበት ጠይቀው ነበር ነበር፡፡ ፡፡ ይኸውም "የኦህዴድ ስራ
አስፈፃሚ ከሚቴ በቅርቡ በሃገራችን ላይ የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቃውሞታል በሚል በስፋት እየተወራ ስለሆነ
ማብራሪያ እንድትሰጡን እንፈልጋለን እንፈልጋለን" የሚል ነበር፡፡
በወቅቱ
የድርጅ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ለማ መገርሳም "እንደ እውነቱ ከሆነ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲታወጅ
በው በውስጣችን ጣችን አልፈለግነውም ነበር፣ ነገር ግን መሬት ላይ ያለው ተጨባጭ የፀጥታ ችግር የዚህ አዋጅ መውጣት የሚያስገድድ
ስለሆነ የግድ መቀበል ነበረብን ነበረብን" የሚል ምላሽ ከሰጡበት በኋላ የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ወደ ዋና ዋናው የመወያያ
አጀንዳቸው እንደገቡ ለማወቅ ተችሏል ተችሏል፡፡ ፡፡
አቶ
ለማ መገርሳ የሰጡት ማብራሪያ ትክክል ነበር፡፡ የትም ቢሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሃገር መምራትና ህዝብን
ማስተዳደር የሚፈልግ መንግስት የለም፡፡ አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረበት በቀር ማንኛውም መንግስት ሃገሩንና ህዝቡን
በመደበኛ የህግ ማስከበር ስርዓት ማስተዳደርና መምራት ቀዳሚ ምርጫው እንደሆነ የታወቀ ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት መንግስትም
ቢሆን እንደተባለው መሬት ላይ በሚታየው ተጨባጭ የፀጥታ ችግር ተገዶ ካልሆነ በቀር ሃገራችንን በአስቸኳ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ለማስተዳደር ምንም አይነት ፍላጎት ሊኖረው ይችላል ተብሎ አይገመትም አይገመትም፡፡ ፡፡ ቀደም ሲል ታውጆ ለአስር ወራት ያህል የቆየው
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አዋጅም ሰላማችን በአስተማማኝ ሁኔታ ሳይረጋገጥ እንዲነሳ የተወሰነው ተወሰነው ሃገራችንን በመደበኛ የህግ ማስከበር
ስርዓት ለማስተዳደር መንግስት ከነበረው ከፍተኛ ፍላጎት ፍላጎትና ጉጉት የመነጨ መነጨ እንደነበር መካድ የሚቻል አይደለም አይደለም፡፡ ፡፡
በአሁኑ
ጊዜ ከአዲስ አበባ ወደ አራቱም የሃገራችን ሃገራችን አቅጣጫዎች የሚወስዱ አውራ መንገዶች ተዘግተው ዜጎች ከቦታ ወደ
ቦታ መንቀሳቀስ የማይችሉበት አስቸጋሪ የፀጥታ ሁኔታ በተፈጠረበትና በዚህ ሁከትና ብጥብጥ ከሁሉም የሃገራችን ህዝቦች
በከፋ መልኩ የኦሮሞ ህዝብ ተጎጂ በሆነበት ተጨባጭ ሁኔታ ከማንም ድርጅት በፊት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መቀበል
ብቻ ብቻም ሳይሆን እንዲወጣም ግፊት ማድረግም የነበረበት ኦህዴድ ነው፡፡ ምክንያቱም አዋጁ ከማንም በላይ የሚጠቅመ የሚጠቅመው
በዚህ ሁከትና ብጥብጥ ሰላሙ የታወከው እና ልማቱ የተስተጎጓጎለው የኦሮሞ ህዝብና የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር
በመሆናቸው ነው፡፡
የሚያሳዝነው
ትንሽ ኮሽ ባለ ቁጥር ለዜጎቹ የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፍ መደበኛ ስራው የሆነው የአሜሪካ መንግስት
የኢትዮጵያ መንግስት የደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቃወም ጠንካራ መግለጫ ማውጣቱ ነው፡፡ ሃገራችንና ህዝባችን
በሰላም እጦት እየታመሱ እየታመሱ፣ በየቀኑ የሰው ህይወትና ንብረት እንደዘበት እየወደመ፣ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ከአዲስ
አበባ ወደየትም አቅጣጫ መንቀሳቀስ የማይቻልበት ሁኔታ እየተፈጠረ በመሄዱ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኦሮሚያ ብቻ ሳይሆን
የፀጥታ ችግር ያልታየበት ወደ አማራ ክልል ጭምር እንዳይንቀሳቀሱ ከጥቂት ቀናት በፊት የጉዞ ማስጠንቀቂያ ማስተላለፉ
እየታወቀ የአሜሪካ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ዴሞክራሲያዊ ምህዳሩን ያጠባል፣ የሰብአዊ መብት መብትን ይጥሳል በሚል
ሽፋን በጥብቅ መቃወሙ በሌላው አለም እንደምናየው ሰላማችን ታውኮ ሃገራችን ብትንትንዋ ብትወጣ ደንታ
እንደማይሰጠው የሚያረጋግጥ ነው፡፡
ለነገሩ
ከሃገራችንና ህዝባችን ሰላምና ደህንነት በላይ ፈረንጆችን ለማስደሰት የሚወጣም ሆነ እነሱን ላለማስቀየም የሚቀር ህግ
ባለመኖሩ መንግስት በሃገራችን የተፈጠረውን የፀጥታ ችግር መልክ በማስያዝ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የመጠበቅና
የማረጋገጥ ባለበ ባለበት ህገመንግስታዊ ሃላፊነት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲወጣ መወሰኑ የሚያስመሰግነው እርምጃ ነው፡፡ አዋጁ
ዘግይቷል ከሚል በቀር ሰላሙ የታወከው ህዝባችን በአዋጁ መውጣት ደስተኛ ነው፡፡ እንዴት ቢባል አዋጁ በወጣ በአጭር
ጊዜ ውስጥ በተለያዩ የሃገራችን አከባቢዎች ተፈጥሮ የነበረው ሁከት ሁከትና ብጥብጥ ቆሞ ከሞላ ጎደል ሰላም ሲሰፍን በአይኑ
እየተመለከተ ነውና፡፡
2
በአስቸኳይ
ጊዜ አዋጁ ሰላማችን እንደሚረጋገጥ እና ያሰቡት የሁከትና የብጥብጥ አጀንዳ እንደማይሳካ አስቀድመው
የተረዱት የቀለም አብዮተኞች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዳይወጣ በብርቱ መቃወማቸው መቃወማቸውም የሚጠበቅ ነበር ነበር፡፡ ፡፡ ምክንያቱም
የእነሱ ዋናው አላማ በዚህ ሁከት ተጠቅመው መንግስት በማንበርከክ ማንበርከክ በአቋራጭ ስልጣን መያዝ ካልሆነም ስርዓቱን
(በዚያውም ሃገሪቱ ቢሆን ቢሆን) ማፍረስ መሆኑ ይታወቃል፡፡
አሁንም
ቢሆን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለመፈታተን ለመፈታተንና ተግባራዊ እንዳይሆ እንዳይሆን ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
በመንግስት የወጣው ይህ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፓርላማ እንዳይፀድቅ እንዳይፀድቅም በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች አማካይነት ከፍተኛ
የሆነ ቅስቀሳ እያካሄዱ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የሆነ የህዝብና የሃገር ሃላፊነት የተሸከመው የተወካዮች ምክር ቤት
ለህዝባችን ሰላምና ለሃገራችን ደህንነት ሲባል በመንግስት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተቀብሎ በማፅደቅ ነውጠኖቹን
በማሳፈር ታሪክ እንደሚሰራ ምንም ጥርጥር የለውም የለውም፡፡ ፡፡
ታደሰ
አለማዮህ
ከአዳማ
የካቲት
18 ቀን 2010
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Mon Feb 26, 2018 6:32 pm

1
ሌ/ጄኔራል ፃድቃንን ታዘብኳቸው!
(ክፍል አንድ)
ድረስ ማርዬ 02-26-18
ይህን ፅሑፍ እንዳሰናዳ ምክንያት የሆነኝ ሪፖርተር ጋዜጣ በቅርቡ በ‘ቆይታ’ አምዱ ላይ “አንድነታችን ሊጠናከር የሚችለው ስልጣን የሚያዝበት ስርዓት በህዝብ የሚታመን ሲሆን ነው” በሚል ርዕስ የቀረበ ቃለ ምልልስ ነው። የሪፖርተሩ ቋሚ አምደኛ ዮሐንስ አንበርብር ቃለ ምልልሱን ያደረገው፤ ከደርግ ውድቀት መባቻ ጀምሮ ለሰባት ዓመታት ያህል የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊትን በጠቅላይ ኤታማዦር ሹምነት ያገለገሉትንና ኋላ ላይም ከህወሓት/ኢህአዴግ ለሁለት መሰንጠቅ ጋር ተያይዞ፤ እንደ አንድ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አመራር (ለዚያውም እንደ የሰራዊት መሪ) ህገ መንግስቱ በአንቀፅ 87 (5) ላይ “መከላከያ ሰራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነፃ በሆነ አኳኋን ያከናውናል” የሚለውን ድንጋጌ በመተላለፍ የፖለቲካ ወገንተኝነት ታይቶባቸዋል በሚል “በአንጀኝነት” ተፈርጀው ከሰራዊቱ በጡረታ እንዲሰናበቱ የተደረጉት ሌተና ጄኔራል ፃድቃን ገ/ተንሳይ ናቸው።
የዚህ ፅሑፍ አቅራቢ እንደ ማንኛውም ዜጋ ጡረተኛው ጄኔራል መኮንን በተለያዩ ወቅቶች በህትመት ሚዲያዎች የሚያቀርቧችውን ትንታኔዎች እከታተላለሁ። አንዳንዶቹን ሃሳቦች ገንቢ በመሆናቸው አከብራቸዋለሁ፤ እጋራቸዋለሁም። ሆኖም አብዛኛዎቹ ሃሳቦቻቸውን ግን ለመቀበል ይከብደኛል። እንዲያውም እነዚህን ሃሳቦች በአርምሞ ስመለከታቸው፤ ትናንት ወጣትነታቸውን ሰውተው፣ ሞትን ከመጤፍ ካለመቁጠር ‘ዱር ቤቴ’ ብለው ለህዝቦች ሰላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ጥያቄዎች መስዋዕት ለመሆን ቆርጠው በመሰለፍ ደርግን ከተፋለሙ ታጋይና ኋላ ላይም የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ከነበሩ ግለሰብ የሚሰነዘሩ መስለው አይታዩኝም። እንደ እውነቱ ከሆነ ምንም ነገር ባለበት ቦታ አይቀጥልም—የሃሳቦች መለዋወጥ መኖሩ ነባራዊ ነው። በዚህ ረገድ ማንም ሰው ጥያቄ ያነሳል ብዬ አልገምትም። አንድ ሰው ትናንት የሰማውን ዛሬ በማይደግምበት ፈጣን ዓለም ውስጥ እየኖረ፤ እንቅስቃሴ እንደሌለው ኩሬ (Stagnant) ሆኖ ሊቆም አይችልም። ዳሩ ግን እንቅስቃሴው መሰረታዊ እምነትን የሚሸረሽሩ ሃሳቦች ሲቀርቡበት፣ ግላዊነትን ማዕከል ሲያደርግና አንዳንዴም ሃሳቦች የተምታቱና አንባቢን ለማደናገር ተብለው ሲቀርቡ፤ “ለምን?፣ እንዴት?፣ ወዴት?...ወዘተ.” ብሎ መጠየቅ ይገባል፤ ያስፈልጋልም።
ርግጥ የፃድቃን ገ/ተንሳይ (ሌ/ጄኔራል) በተለይ ትንታኔ ነክ ሃሳቦች ገሚሶቹ በግል ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ፣ አንዳንዶቹ እርስ በርሳቸው የሚቃረኑና መፍትሔ ያልሆኑ መፍትሔዎች የታጨቁባቸው ሲሆኑ፣ ሌሎቹ ደግሞ ምናልባትም የሃሳቦቹ ባለቤቶች እርሳቸው ሳይሆኑ “ሌሎች” ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ እንዳስብ የሚያደርጉኝ ናቸው። ይህን የምለው እርሳቸው በህትመት ሚዲያና በአንዳንድ ድረ ገፆች አማካኝነት የሚለቋቸውን ትንታኔዎችና ቃለ ምልልስ ዙሪያ በግሌ የተሰማኝን ጥቅል እይታ ለመግለፅ ያህል እንጂ፤ የፅሑፌ ዋነኛ ማጠንጠኛ በሰሞነኛ ቃለ ምልልሳቸው መሆኑን ውድ አንባቢያን እንዲገነዘቡልኝ እሻለሁ።
እንዳልኩት በዚህኛውም ቃለ ምልልሳቸው ላይም በንድፈ-ሃሳብ (theory) እና በትግበራ ደረጃ የምስማማባቸው ሃሳቦች ይኖራሉ። በተለይም ማናቸውንም ጉዳዩች በህገ መንግስቱ መሰረት መከናወን እንዳለባቸው፣ አንድን ብሔር በመለየት የሚከናወኑ የጥቃት ተግባሮች ፈፅሞ መቆም እንደሚኖርባቸውና የፀጥታ ሃይሎች ይህን ችግር ማስቆም እንደሚገባቸው እንዲሁም አንድነታችንን ማጠናከር እንደሚገባን ያነሷቸው ነጥቦች ለክፉ የሚሰጡ ሆነው
2
አላገኘኋቸውም። በአንፃሩ ደግሞ፤ የሀገራችንን ወቅታዊ ችግር ለመፍታት ተብለው ከህገ መንግስቱ ውጭ በሞራል
ግዴታና ኃላፊነት እንዲከናወን የተጠየቁና ህገ መንግስቱን የሚቃረኑ ብሎም የሚጥሱ፣ ይተግበሩ ቢባል እንኳን
ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ አኳያ መያዣና መጨበጫ የሌላቸው ጉዳዩች እንዲሁም ከሚዛናዊ ዕይታ በመነሳት የተሰጡ
ድምዳሜዎች አይደሉም ብዬ የማምንባቸውን ጉዳዩች መኖራቸውን ታዝቤያለሁ። እርሳቸውም በቃለ ምልልሱ ላይ
“የምሰጠው አስተያየት ጉድለት የለውም ብዬ አላምንም” ብለው ባቀረቧቸው ሃሳቦች ላይ እምነት እንደሌላቸው
እንደነገሩን ሁሉ፤ ይህ በዚህ ፅሑፍ በማልስማማባቸው ትላልቅ ጉድለቶች ዙሪያ ትዝብቴን አስቃኛለሁ።
እውነትም ጡረተኛውን ጄኔራል መኮንን የተነሳሁበትን ነጥብ ያስረዱልኛል ባልኳቸውና በውስጣቸው በርካታ ጉዳዩች
በታጨቁባቸው ሁለት አንኳር ጉዳዩች ታዝቤያቸዋለሁ። አንደኛው፤ አሁን ያለውን የሀገራችንን ተጨባጭ ችግር
ለመፍታት በፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ስር መቋቋም ይኖርበታል ያሉትን “ገለልተኛ ኮሚሽን”ን የሚመለከተው አስገራሚ
ሃሳብ ነው። ሁለተኛው ደግሞ፤ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 71 (6) መሰረት፤ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ለ61
የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛና ጄኔራል መኮንኖች ከብርጋዲየር ጄኔራልነት እስከ ሙሉ ጄኔራልነት ድረስ
በሰጡት ወታደራዊ የማዕረግ ዕድገት ያቀረቧቸው ትክክለኛ ያልሆኑና በቀናነት ያልቀረቡ እሳቤዎችን የሚዳስስ ነው።
ጡረተኛው ሌ/ጄኔራል ፃድቃን ከቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶክተር ነጋሶ ወዲህ እንደተዳከመ በነገሩን የፕሬዚደንቱ ፅህፈት
ቤት አማካኝነት “ገለልተኛ ኮሚሽን” በማቋቋም በሀገራችን ውስጥ የተፈጠረውን የፖለቲካ ቀውስ ልናስተነፍሰው
እንችላለን ብለው ያምናሉ። ይህ “ኮሚሽን” በፓርላማው የሚቋቋም ሆኖ፤ እስከ ምርጫ 2012 ድረስ የሚቆይ
ነው። ህዝቡም ቀልቡን በዚህ ኮሚሽን ላይ ያደርጋል ሲሉም ነግረውናል። ኮሚሽኑ ነፃ ሆኖ የሚሰራ፣ ዋና ዓላማውም
ከሁለት ዓመት በኋላ የሚደረገው ምርጫ ነፃና ዴሞክራሲያዊና ተዓማኒነት ያለው እንዲሆን የማስተካከል ያከናውናል
ብለው ያምናሉ። ታዲያ ይህን የ“ገለልተኛ ኮሚሽን” ሃሳብ ሲያቀርቡ አንዳንድ የኢህአዴግ ባለስልጣናት “የሽግግር
መንግስት ይመስረት እያልክ ነው” በማለት ሃሳቡን አጣመው እንደሚመለከቱባቸው አልሸሸጉም። “እኔ ግን እንደዛ
አላልኩም፤…ሆኖም (የሽግግር መንግስት ጉዳይ) ህገ መንግስታዊ መሰረት የሌለው ሃሳብ ነው” በማለት የኮሚሽኑ
ተግባር ግን ህገ መንግስታዊ እንደሆነ አስመስለው በገደምዳሜው ሊነግሩን ሞክረዋል። በጄ! ማለፊያ ነው።
ሆኖም ጡረተኛው ሌ/ጄኔራል ያነሱት “ገለልተኛ ኮሚሽን” ለማንም የሚገባ ጉዳይ አይደለም። ርግጥ በሪፐብሊኩ
ፕሬዚዳንቱ ስር የፕሬዚዳንት ፅሀፈት መኖሩ ግልፅ ነው። በእኔ እምነት ይህ ፅህፈት ቤት የሚያከናውነውና ከህገ
መንግስቱ ምስረታ ማግስት ጀምሮ እየፈፀማቸው የመጣቸው በህገ መንግስቱ ከአንቀፅ 69 ጀምሮ እስከ አንቀፅ 71
ድረስ የተዘረዘሩትንና ለሪፐብሊኩ ፕሬዚዳንት (ርዕሰ ብሔር) ተለይተው የተሰጡ ስልጣንና ተግባሮችን ነው። አንድ
ፅህፈት ቤት የሚወክለው የተሰጠን ተግባርና ሃላፊነት ብቻ ስለሆነ። እናም ህገ መንግስቱ ላይ ያሉት የፕሬዚዳንቱ
ስልጣንና ሃላፊነት የስልጣኑ ሉዓላዊ ባለቤት በሆኑት የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እስካልተሻሩ ወይም
እስካልተቀየሩ ድረስ፤ በዶክተር ነጋሶ ይሁን በቀድሞው ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደጊዩርጊስ አሊያም በአሁኑ ርዕሰ
ብሔር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የስልጣን ጊዜያት እንዴት ሊዳከሙ እንደሚችሉ ግልፅ አይደለም።
በህገ መንግስቱ አንቀፅ 71 የተዘረዘሩት የፕሬዚዳንቱ ስልጣንና ተግባር የሚገልፁት፤ የህዝብ ተወካዩችና የፌዴሬሽን
ምክር ቤቶችን ዓመታዊ የጋራ ስብሰባ ስለ መክፈት፣ በህገ መንግሰቱ መሰረት የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት
ያፀደቃቸውን ህጎችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በነጋሪት ጋዜጣ ስለ ማወጅ፣ ሀገሪቷን በውጭ ሀገራት የሚወክሉትን
አምባሳደሮችና ሌሎች መልዕክተኞችን በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት ስለ መሾም፣ የውጭ ሀገር አምባሳደሮችንና
የልዩ መልዕክተኞችን የሹመት ደብዳቤ ስለ መቀበል፣ በህግ መሰረት ኒሻኖችንና ሽልማቶችን እንዲሁም በጠቅላይ
ሚኒስትሩ አቅራቢነት በህግ በተወሰነው መሰረት ከፍተኛ የውትድርና ማዕረጎችን ስለ መስጠት እና በህግ መሰረት
3
ይቅርታ ማድረግ ናቸው። ታዲያ ከእነዚህ ስልጣንና ተግባሮች ውስጥ የትኞቹ ናቸው የተዳከሙትና ሳይተገበሩ
የቀሩት?፣ ከተዳከሙስ መቼና እንዴት ነው ሊዳከሙ የቻሉት?... ጡረተኛው ሌ/ጄኔራል በዚህ ረገድ ያሉት ነገር
ስለሌለ እኔም “ለማለት ብቻ የተባለ” ብዬ ላልፈው አልችልም። በእኔ እምነት የፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት በተሰጠው
ህገ መንግስታዊ ስልጣንና ተግባርና መሰረት የተጠናከሩ ስራዎችን እያከናወነ እንጂ እየተዳከመ የመጣ አይደለም።
ሌሎቹን ተግባሮች ትቼ በቅርቡ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታራሚዎች በህጉ መሰረት በይቅርታና በምህረት
እንዲለቀቁ መደረጉን ባነሳ እንኳን፤ ፅህፈት ቤቱ ምን ያህል ስራውን ሀገራዊ መግባባትን በሚያጠናክር መልኩ
እየፈፀመ ስለመሆኑ አንድ ማሳያ ማቅረብ እችላለሁ። ታዲያ ጡረተኛው ጄኔራል መኮንን ከቶ ምን እያሉን
ይሆን?...ርግጥ በዚህ ድፍን ያለና ሆን ተብሎ አንባቢን ለማምታታት በተነገረው የእርሳቸው አባባል መታዘብ
ያንሰኝ ያንሰኛል ብዬ አላምንም።
እንደ እውነቱ ከሆነ፤ የፕሬዚዳንቱ ፅህፈት ቤት ሀገር ፖለቲካዊ ቀውስ ሲያጋጥማት ኮሚሽን አቋቁሞ “ማስተንፈሻ
ገለልተኛ ኮሚሽን ያቋቁማል” የሚል ነገር በህገ መንግስቱ ላይ ተፈልጎ አይገኝም። የለምና። ሌ/ጄኔራል ፃድቃን ግን
ፅህፈት ቤቱ ሞራላዊ ኃላፊነት አለው ይሉናል። ግና ህገ መንግስትን እንደምን በሞራላዊ ሃላፊነት ተክቶ መቀየር
እንደሚቻል ለእርሳቸውም ግልፅ የሚሆን አይመስለኝም። በአንድ በኩል፤ በቃለ ምልልሳቸው ላይ ህገ መንግስቱን ብቻ
ተከትለን መሄድ ይገባል የሚሉን ሰው፤ አሁን ደግሞ ህገ መንግሰቱን በሞራላዊ እሳቤ መተካት አለብን እያሉን ነው—
ሁለት እርስ በርሳቸው የሚጣረሱ ሃሳቦች። ህገ መንግስቱ ተሸርሽሮ የህዝብ ሉዓላዊ ስልጣን ባለቤትነት ሲነጠቅ
ሊመጣ የሚችለውን ቀውስ እንዲሁም የህግና ስርዓት መፋለስ ችግሮችን ብሎም ሌሎች ሀገራዊ ኪሳራዎችን፤ ለእኚህ
ከዚህ ቀደም ታጋይ ለነበሩ፣ ህገ መንግስቱ ሲፀድቅ የእርሳቸው ድርሻ ይኖራል ብዬ ለምገምታቸው፣ የደቡብ ሱዳን
ሰራዊት “አማካሪ” ለነበሩት እና ከሁለትና ከሶስት ዓመታት ወዲህ ደግሞ “በአንጃነት” ከተፈረጁት አንዳንድ
ግለሰቦች ጋር በመሆን ‘የሁከት ጊዜ ተንታኝ’ ሆነው ብቅ ላሉት ግለሰብ ለመንገር ትንሽ የሚከብደኝ ይመስለኛል።
እኔ እርሳቸውን እንደታዘብኳቸው ሁሉ ውድ አንባቢዎቼ ደግሞ እኔንም ሊታዘቡኝ ይችላሉና።
ጡረተኛው ጄኔራል መኮንን “ገልልተኛ ኮሚሽኑን” አስመልክተው “አንዳንድ የኢህአዴግ ባለስልጣናት የሽግግር
መንግስት ይመስረት እያልክ ነው ይሉኛል። እኔ ግን እንደዚያ አላልኩም። (የሽግግር መንግስት ምስረታ ጉዳይ) ህገ
መንግስታዊ አይደለም” ቢሉም ቅሉ፤ በእኔ እምነት ግን የኢህአዴግ ባለስልጣናቱ ያሉት ትክከል ይመስለኛል—እርሳቸው
እንዲመሰረት በሚፈልጉት “ገለልተኛ ኮሚሽን” እና የሽግግር መንግስት መካከል የስም እንጂ የግብር ልዩነት የለምና።
ነገርዬው የሀገራችን አርሶ አደር “ስልቻም ቀልቀሎ፣ ቀልቀሎም ስልቻ” እንደሚለው ዓይነት ነው። የእርሳቸው ሃሳብ-
ወለድ “ኮሚሽን” አሁን ያለውንና በሀገሪቱ የምርጫ ህግ መሰረት ተወዳድሮ አሸንፎ ሀገሪቱን በመምራት ላይ
የሚገኘውን ገዥ ፓርቲና ስራ አስፈፃሚውን አካል (መንግስትን) ተክቶ ለሁለት ዓመት ማናቸውንም ተግባራት
እንዲያከናውን ይሻሉ። ፓርላማውም የነበረውን ስራ አስፈፃሚ ሽሮ የሌ/ጄኔራል ፃድቃንን “ኮሚሽን” አፈፃፀም
ይቆጣጠራል ማለት ነው። ይህ በእውነቱ ለእኔ ሽግግር መንግስት ብቻ አይደለም— የህዝብን ድምፅ በድምፅ አልባ
መፈንቅለ መንግስት ለመቀማት ማሰብ ጭምርም እንጂ።…ኧረ ለመሆኑ የሽግግር መንግስት ከዚህ የተለየ ምን ተግባር
ያከናውናል? የሽግግር መንግስት ግብሩ ቋሚ መንግስት እስኪመሰረት ድረስ መንግስታዊ ስራዎችን መፈፀም
አይደለምን?...እናስ ‘ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የሚደፈጥጠው የእርሳቸው “ገለልተኛ ኮሚሽን”
እንደምን ህገ መንግስታዊ ሊሆን ይችላል?’ ብለን ብንጠይቃቸው፤ እውነት…እውነት እላችኋለሁ ምላሹ የሚያጥራቸው
ይመስለኛል። ምክንያቱም እርሳቸው የሚያልሙት “ኮሚሽን” ህገ መንግስቱ ፈፅሞ የማያውቀው ስለሆነ ነው። ኢ-ህገ
መንግስታዊ ስለሆነ ነው። ያም ሆነ ይህ ግን፤ እርሳቸው እያሰቡት ያሉት ነገር በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት
4
የሚያውቁትን የድሮውን የሽግግር መንግስት በስም ቀይረው እውን ማድረግ ከሆነ፤ ያ ወቅት ፋይሉ ተዘግቶ የኢፌዴሪ
መንግስት ከተመሰረተ 23 ዓመታት ማለፋቸውን ከትዝብት ጋር ላስታውሳቸው የሚገባኝ ይመስለኛል።
እንደ ፃድቃን ገ/ተንሳይ (ሌ/ጄኔራል) ዓይነት “ተመራማሪና ለሀገር አሳቢ” ግለሰብ፤ ለማቋቋም የሚፈልገው
“ኮሚሽን” የችግር ማስተንፈሻ እንዲሆን የሚሻ አይመስለኝም ነበር። ግና ተሳስቻለሁ። ርግጥ እርሳቸውም በቃለ
ምልልሳቸው ‘የለም ተሳስተሃል’ ያሉኝ ይመስለኛል—‘ኮሚሽኔ እንደ ህመም ማስታገሻ (Pain killer)
ያገለግላል’ ብለውናልና። ሆኖም የህመም ማስታገሻ በቋሚው ህመም ምክንያት የተፈጠሩ ሌሎች ተቀፅላ ምልክቶችን
ከማጥፋት በስተቀር በሽታውን ዘላቂነት ባለው ሁኔታ እንደማይፈውስ የተገነዘቡት አልመሰለኝም። አሊያም ሊገነዘቡት
አልፈለጉም። ርግጥ ዋናውን በሽታ ለመፈወስ የህመሙን ትክክለኛ መድሃኒት እንጂ፣ በበሽታው ምክንያት ለተፈጠሩ
የራስ ምታት ዓይነት በሽታዎች ማስታገሻን ማዘዝ ማለት፤ ዝንቧን ከሚስቱ ግንባር ላይ አባርራለሁ ብሎ ባለቤቱን
በያዘው መዶሻ ግንባሯ ላይ መትቶ እንደ ገደላት አባወራ ዓይነት ጅልኛ እሳቤ ይመስለኛል።
ይህን የጡረተኛው ጄኔራል መኮንንን “የህመም ማስታገሻ” (Pain killer) ሳስበው ልጅ እያለሁ የሰፈራችንን
የመንደር መርፌ ወጊን ተግባር እንዳስታውስ ያደርገኛል—“ከበደ ሀኪሙ” እያልን የምንጠራቸውን ግለሰብ። “ከበደ
ሀኪሙ” የባህል አዋቂም ዘመናዊ ሃኪምም አይደሉም። ትልቅ ቦርሳ፣ ግን በውስጡ አንድ ሲሪንጋና ጥቂት
መርፌዎች እንዲሁም የተወሰኑ ብልቃጦችን ቤታቸው አስቀምጠው የሚያክሙ የመንደር መርፌ ወጊ ናቸው።
የመንደራችን ሰው ከእርሳቸው ምን እንዳየ ባላውቅም—ራሱን ሲያመው፣ ሆዱን ሲቆርጠውም ይሁን ውጋት ቀስፎ
ሲይዘው ወደ “ከበደ ሀኪሙ” ጋ መሮጥ ይወዳል። ከቤም የዋዛ ሰው አልነበሩም—ለሁሉም የበሽታ ዓይነቶች ሶስት
ብር እየተቀበሉ፤ ሆዱን ለቆረጠውም፣ ብርድ ብርብ ላለውም፣ ቁርጠት ላሰቃየውም ይሁን ውጋት ቀስፎ ለያዘው
ያንኑ መድሃኒት በአንድ መርፌ እየመላለሱ ይወጋሉ። አንዳንዴም ዳጎስ ያለ መቀመጫ ያላቸው የመንደራችን
ባልቴቶች ታመው ወደዚያው ሲያመሩ መርፌውን ሰክተው በዚያው በሃሳብ ጭልጥ ብለው ይጠፋሉ እየተባሉ
በራሳቸው ታካሚዎች የሚታሙት ጋሼ ከቤ፤ በአንድ መርፌና በአንድ ዓይነት መድሃኒት ስንቱን የመንደራችንን ሰው
ህመሙን እንዳስታገሱለት ወይም እንዳባባሱበት ቤቱ ይቁጠረው።…
በእኔ እምነት፤ የጡረተኛው ጄኔራል ሃሳብም በሽታውን ሳይገነዘቡ በማስታገሻነት “ገለልተኛ ኮሚሽን” እናቋቁም
ማለታቸው፤ እንደ መንደራችን መርፌ ወጊ “ከበደ ሀኪሙ” ዓይነት አሰራርን ከመፈለግ የመነጨ ይመስለኛል—ልክ
ጋሽ ከቤ የህክምናን ሙያ እንደደፈጠጡት ሁሉ፤ እርሳቸውም ህገ መንግስቱንንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን
በመደፍጠጥ ህመም አስታጋሽ “ኮሚሽናቸው”ን እያለሙ ነውና። ታዲያ እንዲህ ያለውን “የከበደ ሀኪሙን” አሰራር
የትኛውም የሀገራችን ብሔር፣ ብሔረሰብም ይሁን ህዝብ ፈፅሞ ሊቀበለው የሚችል አይመስለኝም—የተነጣጠረው
በሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነቱ ላይ ስለሆነ።
ያም ሆነ ይህ፤ በአንድ ሀገር ውስጥ የህዝብን ጥያቄ ተከትሎ የሚደረግ የሪፎርም ሂደት ጥገናዊና ለማስተንፈሻ ብቻ
የሚደረግ ለውጥን የሚያመጣ መሆን የለበትም—ዘላቂና ስር ነቀል (Radical) ለውጥን እንጂ። ከዚህ አኳያ፤
ገዥው ፓርቲና መንግስት በሀገራችን ህዝብ የተጠየቁትን ትክክለኛ ጥያቄዎች ለመመለስ ለህዝቡ ቃል ገብተው እየሰሩ
ነው። እንደ ጡረተኛው ጄኔራል መኮንን “ጊዜያዊ ማስተንፈሻ” ሳይሆን ዘላቂና የህዝቡን ችግር ስር ነቀል በሆነ
መንገድ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በጥናት ላይ የተመሰረተ ፍኖተ ካርታ (road map) ያለው ሪፎርም
አዘጋጅተው ወደ ተግባር ገብተዋል። በሪፎርሙ መሰረት ችግሩን ሊፈታ የሚችል እንደ ፓርቲዎች ጥልቅ ግምገማና
ሹም ሽር፣ በመንግስት ስራ ውስጥም ትክክለኛውን መንገድ የተከተለ የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ ለመፍጠር
እየተደረገ ያለው ጥረት የስር ነቀል መፍትሔ ሰራዎች አካል ይመሰሉኛል። እንዲሁም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር
5
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅርቡ በሀገራችን ላይ ያንዣበበውን አደጋ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቀልበስ በሪፎርሙ
መሰረት የመፍትሔው አካል በመሆን ስልጣናቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸው የዚሁ ተግባር ማሳያ ነው። ይህን ፅሑፍ
እስካሰናዳሁበት ድረስ ለፓርላማ ያልቀረበውና ሰሞኑን በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ሌላኛው ትክክለኛ የችግሩ መፍትሔ አካል ነው ብዬም አምናለሁ። ይህ ደግሞ በህገ መንግስቱ አንቀፅ 93 ላይ
በግልፅ የተቀመጠ ህገ መንግስታዊ አሰራር መሆኑን ጡረተኛው ጄኔራል መኮንን ይስቱታል ብዬ አልገምትም።
ፃድቃን ገ/ተንሳይ (ሌ/ጄኔራል) በሚያልሙት “ኮሚሽን” አማካኝነት በውጭ ያሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች በነፃነት
እንዲሳተፉ ድርድር ተደርጎ ጥሪ ሊደረግላቸው ይገባል ብለውናል። በእኔ እምነት ይህና ቀደም ሲል የጠቀስኳቸውና
“በኮሚሽኑ” ላይ ያነሷቸው ነጥቦች ኢ-ህገ መንግስታዊ ናቸው። ምክንያቴን እንደሚከተለው አስረዳለሁ። እርሳቸው
‘በውጭ ያሉ ተቃዋሚዎች’ የሚሏቸው እንደ አርበኞች ግንቦት ሰባት፣ ኦነግና ኦብነግ የመሳሰሉት በሀገራችን ጠላቶች
ሳንባ የሚተነፍሱ ተቃዋሚዎች ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የጠብ-መንጃ አፈሙዝን ጨምሮ
በማናቸውም መንገድ ለመጣል እንደሚሰሩ በይፋ ያወጁ ናቸው። የሀገራችን ህዝቦች እንደ ራሴዎችን ባቀፈው
ፓርላማም በአሸባሪነት የተሰየሙ ናቸው። ጥቂቶቹ ደግሞ “ሸንጎ…ምንትስ ነን” እየተባባሉ በሚያስቅ ሁኔታ አሜሪካና
አውሮፓ ካፌዎች ውስጥ ቁጭ ብለው ‘የሽግግር መንግስት መስርተናል’ የሚሉ ጉደኞች ናቸው—መጥተው ስልጣን
የሚይዙት በቦሌ ይሁን በባሌ ባይታወቅም።
ለእኔ እነዚህን ተቃዋሚዎች መጋበዝ ማለት ከማያውቁት አውድ (context) ጋር በግድ ለመደባለቅ መሞከር
ነው። በሌላ ቋንቋ፤ አንድን ትልቅ ብሎን በትንሽ አቃፊው ውስጥ በሃይል ቀጥቅጦ ለማስገባት የመሞከር ያህል
ይመስለኛል። ሰላማዊነትን የሚያቀነቅነው የሀገራችን ተጨባጭ ምህዳር ለእነዚህ ሃይሎች ይመቻቸዋል ብዬ አላስብም።
እነዚህን ሃይሎች በሀገራችን እየተካሄደ ያለው ሰላማዊና ህጋዊ የፖለቲካ ማህበረሰብ (political society)
አካል አይደሉም። ኢ- ህገ መንግስታዊ ናቸው። ርግጥ አሸባሪዎቹም ይሁኑ “የሽግግር መንግስት መስርተናል” ባይ
ኮሜዲያኖቹ ጥፋታቸውን አምነውና ተፀፀተው ህዝቡን ይቅርታ በመጠየቅ ሀገር ቤት መጥተን በሰላማዊ መንገድ
እንታገላለን ብለው ከወሰኑ፤ በህጉ መሰረት እንደ ማንኛውም ሀገር በቀል ፓርቲ በህገ መንግስቱ ጥላ ስር ሆነው
ተወዳድረው የህዝቡን ይሁንታ ካገኙ የመንግስት ስልጣን ሊይዙ የማይችሉበት ምክንያት የሚኖር አይመስለኝም። እኔ
እስከሚገባኝ ድረስ ግን፤ እነዚህ ሃይሎች የራሳቸው አጀንዳ የሌላቸውና ለባዕዳን ሃይሎች በተላላኪነት የሚንቀሳቀሱ
እንዲሁም ፖለቲካን ለህዝብ ካለው ጠቀሜታ አኳያ ሳይሆን፤ በገንዘብ አስገኚነቱ የሚመዝኑና ስራውንም የዕለት
እንጀራቸው አድርገው የያዙ የሌላ ዓለም ሰዎች ናቸው። ለእነርሱ ተቃዋሚነት እንደ ማንኛውም ሸቀጥ ንግድና ንግድ
ብቻ ነው።
በመሆኑም የጡረተኛው ጄኔራል መኮንን ምናባዊ “ኮሚሽን” በመጀመሪያ እነርሱን ለመጥራት ህገ መንግስቱን ሊጥስ
የግድ ይለዋል፣ ሲቀጥል ደግሞ እነርሱን በአሸባሪነት የፈረጃቸው ፓርላማ መፍረስ ይኖርበታል አሊያም አሸባሪነታቸውን
ማንሳት አለበት ማለት ነው። ይህ ደግሞ በተለያዩ ፖለቲካዊና ህጋዊ ጉዳዩች ሳቢያ የሚሆን አይመስለኝም። በአጭሩ
የሌ/ጄኔራል ፃድቃን ኢ-ህገ መንግስታዊ ሃሳብ-ወለድ “ኮሚሽን” ጥሪውን ሊያደርግ የሚችለው፤ ህገ መንግስቱን
ደፍጥጦና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ተቃርኖ ነው። ይህ ደግሞ፤ የጄኔራል መኮንኑ “ገለልተኛ ኮሚሽን” የማስተንፈሻነት
ምክረ-ሃሳብ (Proposal) ችግር ፈቺ ሳይሆን ችግር ፈጣሪ፣ ምናልባትም ‘እኔም የመፍትሔው አካል ነኝ’
በማለት በግል ዕይታ ስልጣንን አጮልቆ የመመልከት ፍላጎትን የያዘና የአንዳንድ ኒዮ ሊበራል ሃይሎች ቀጥተኛና
ተዘዋዋሪ አስተሳሰብ ትክክለኛ ግልባጭ (carbon copy) ሆኖ የተነገረ ሳይሆን የሚቀር አይመስለኝም።
6
ለነገሩ ይህ ህገ መንግስቱን ያለማከበር ጉዳይ እርሳቸው የዛሬ 16 ዓመታት ገደማ ሲፈፅሙት የነበረ ነው። ዛሬ
የተፈጠረ አዲስ ክስተት አይመስለኝም። ዳሩ ግን እርሳቸው ለመፍጠር እየሞከሩ ያሉት አዲሱ ጉዳይ በህገ መንግስቱ
እየማሉ ከላይ በጠቀስኳቸው ኢ-ህገ መንግስታዊ ኩነቶችን ገቢራዊ እናድርግ በማለት መልሶ ህገ መንግስቱን
ከጀርባው በጦር የመውጋት ጨዋታ ይመስለኛል። ይህ ኢ-ህገ መንግስታዊ ጨዋታም በእኔ በትንሿ አቅም እርሳቸውን
በትልቁ እንድታዘባቸው አድርጎኛል። ያም ሆኖ ሌ/ጄኔራል ፃድቃን መንግስት ለኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛና
ጄኔራል መኮንኖች የሰጠውን የማዕረግ ዕድገት አስመልክተው ባነሷቸው ሃሳቦች ይህን ትዝብቴን እንድቀይር ያደርጉኝ
ይሆን?...እስቲ ጉዳዩን በክፍል ሁለት ፅሑፌ ላይ አብረን ለመመልከት ወደዚያው እንዝለቅ።…
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Tue Feb 27, 2018 4:40 pm

ዶ/ር አቢይ አህመድን ጥላሸት የሚቀባው
የበረከት ስምኦን ደብዳቤ
ኢንሳን የመሰረተ አብይ አይደለም የተቋሙ ዳይሬክተርም ሆኖ አያውቅም፣ የትምህርት ማስረጃውም ፌክ
ነው፣ ብአዴን ሃገሪቱን ካልመራ እንጫረሳለን እያለን ነው ራሱን የአማራ እንደራሴ አድርጎ የሾመው
ትግሬው በረከት ስመኦን። አንብቡት
--------------
ሰላም የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች።
ልባዊ ሰላምታዬን ባላችሁበት አቀርባለሁ።
የውስጥ ድክመቶቻችን ያስከተሉት የህዝብ ቅሬታና ክፍተት እንዲሁም አጋጣሚውን የተጠቀሙበት ሀይሎች
አፍራሽ ሚና ተዳምሮ አሳሳቢ ሁኔታዎችን በመፍጠሩ ድርጅታችን ጥልቅ ተከታታይና ዙሪያ መለስ
የተሀድሶ ስራዎችን እያካሄደ እንደሆነ ይታወቃል። የዚህ አካል የሆነው የብአዴን ጥልቅ ግምገማ
መጠናቀቁንና የአቋም መግለጫውን ከሚዲያ ሰምታችኋል።
የተሀድሶ ሂደታችንን በሰፊው ህዝብ ዘንድ ለማስረጽ በተለይም ለስልጣን ያለ የተዛባ አተያይን እና
የህዝበኝነት ዝንባሌዎችን የሚተነትኑ ጽሑፎች በአዲስ ራዕይ መጽሔት በኩል በማውጣት ህዝቡ
እንዲወያይበት አድርገናል።
በነዚህ ሁለት ቁልፍ ችግሮች ዙሪያ በቀጣይም በሚመለከታቸው የኢህአዴግ መዋቅሮች አማካኝነት ሰፋፊና
ጥልቅ ውይይቶችን የሚደረጉ ይሆናል።
ይሁን እንጂ የድርጅታችን ሊቀመንበር የስራ መልቀቂያ ማስገባት እና የአመራሮች በተለያዩ ስራዎች
መጠመድን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለስልጣን ባለ የተዛባ አተያይ የተመሰረተ አደገኛና ትርምስ
የሚጋብዝ ህዝበኛ አካሄድ እየታየ በመሆኑ የተወሰኑ ነጥቦችን ግልጽ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ታይቶኛል።
በድርጅታችን ባህል ስልጣን ህዝብን ማገልገያ እና የማህበረሰብ ለውጥ ማምጫ የልማት መሳሪያ እንጂ
የግለሰብ ዝና (personality cult የሚባለው) የሚገነባበት አይደለም። ከሊቀመንበር ጀምሮ በየትኛውም ቦታ
ላይ የሚደረግ ምደባ የግለሰቡን ጽናት ልምድ የግምገማ ውጤት የመሳሰሉትን ነገሮች መሰረት ያደረገ
ብቻና ብቻ ነው። እነዚህን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሟላው እጩ ም/ጠቅላይ ሚኒስትር ጓድ ደመቀ መኮንን
ቢሆንም ሌሎች የተሻሉ ካሉ በአመራር ስብሰባ ላይ ቀርቦ የምንነጋገርበት እንጂ እንደኒዎ ሊበራል
ድርጅቶች በየሶሻል ሚዲያው ቅስቀሳ የሚደረግበት አሰራር የለም።
በክልል ቴሌቪዥን የአንድን እህት ድርጅት የአመራር አባል ማስታወቂያ የሚሰራበት እና ህዝቡ የተሳሳተ
ግንዛቤ እንዲይዝ የሚደረግበት አካሄድም ከድርጅታችን ባህል ያፈነገጠ ነው። በተለይ ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ
አንዱ ምክንያት የሆነው ዛሬ በኦሮሚያ ቴሌቪዥን በአማርኛ የቀረበው ዶኩመንታሪ ከአብዮታዊ ባህል
ያፈነገጠ የድርጅትን ስልጣን በህዝበኝነት ለመቆጣጠር የተደረገ እና ህዝቡን ለተሳሳተ ግንዛቤ ብሎም
ግርግር ሊሚመራ የሚችል ነው።
ዶኩመንታሪውን አስደንጋጭ የሚያደርገው ከድርጅታችን ባህል ማፈንገጡ ብቻ ሳይሆን ከእውነት የራቁ
መረጃዎችን የያዘ መሆኑን ነው።
የደርግ ስርአትን በሚገረሰስበት ወቅት በየቦታው የኦህዴድን መዋቅር ስናደራጅ ጓድ አብይ አህመድ
ድርጅቱን እንዲቀላቀል እንዳደረግን እና በክፍለ ህዝብ ክንፍ ተመድቦ የሰላምና መረጋጋት እንዲሁም
የቅስቀሳና ማደራጀት ስራዎችን እንዲያግዝ ማድረጋችን ትዝ ይለኛል። በ1987 የኢፌዴሪ ህገ መንግስት
ጸድቆ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲደራጅ የሰራዊቱን ተዋጽኦ ለማመጣጠን ወደ ሰራዊቱ እንዲገቡ ከተደረጉ
የድርጅት አባላት አንዱ ነበር። ሻዕቢያ በወረረን ወቅት በሀምሳ አለቃ ማዕረግ በራዲዮ ኦፕሬተርነት ይሰራ
እንደነበር የሰራዊቱን ዝግጅት ለመጎብኘት በሄድኩበት ወቅት ተረድቻለሁ።
በ1997ቱ ምርጫ ማግስት ከሰራዊቱ ጋር በነበሩ ስራዎች አጋጣሚ አግኝቸው መቶ አለቃ ደርሶ እንደነበር
አስታውሳለሁ። ከዛ በኋላ ሰራዊቱ ውስጥ በቆየባቸው ጥቂት አመታት ከመቶ አለቃ ወደ ሌተናል ኮሎኔል
ማዕረግ መድረሱ ያጠራጥረኛል። የሌተናል ኮሎኔል ማእረግ ከተሰጠውም ሊሆን የሚችለው የብሄር ተዋጽኦ
ማመጣጠን በሚባለው አካሄድ ነው። የብሄር ተዋጽኦ የማመጣጠን አሰራራችን ህገመንግስታዊና ትክክለኛ
ቢሆንም በዚህ አካሄድ ፈጣን እድገት ያገኙ አባላት አላማውን በመገንዘብ ሰራዊቱ ውስጥ እስካሉ ድረስ
ይገለገሉበታል እንጂ ከሰራዊቱ ከወጡ በኋላ ለማስታወቂያ ፍጆታ አያውሉትም።
ለስልጣን ያለንን የተዛባ አተያይ የሚያመለክቱ በርካታ ግነቶች በዶክመንታሪው ላይ መታየታቸው
የድርጅታችንን ጤንነት ቆም ብለን መመርመር ማየት እንዳለብን የሚጠቁም ነው። የኢንሳ መስራች ነው
ተብሎ የቀረበው ግራ የሚያጋባ ነው። ይህን ዘመናዊ ሀሳብ ያፈለቀው ጓድ መለስ ዜናዊ ነው። ሲከተል
ደግሞ ኢንሳ መስራች አለው ከተባለ መስራቹ መንግስት ነው። በመሰረቱ ኢንሳ ቀድሞ ሲግናል ሬጅመንት
ሲባል ከነበረው አሀድ ያደገ ተቋም ነው። እዚያ የነበሩ ዋነኛ ሞተሮች ደግሞ የብአዴን ፍሬዎች የሆኑት እነ
አህመድ ሀምዛ እነ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው። ለጓድ አብይ የኢንሳ ዳይሬክተር ሆኖ የተሾመበት አጋጣሚ
የነበረ አይመስለኝም። የመስሪያ ቤቱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደመሆኑ ጓድ መለስ የዳይሬክተር
ለውጥ ሹመት ሰጥተው ቢሆን ያሳውቁን ነበር።
ከግል ህይወት ታሪክ ወይም ሲቪ ጋር በተያያዘ ጓድ ሃይለማሪያም በሰጡት መመሪያ መሰረት
የአመራሮችን የትምህርት ማስረጃዎች ማሰባሰብና ማደራጀት ሲካሄድ ጓድ አብይ በውጭ ሀገር የማስተር
ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን አግኝቻለሁ በሚለው መረጃው ምክንያት ከጓድ ሙክታር ጋር ውዝግብ ውስጥ
ገብተው እንደነበር አስታውሳለሁ። የሰነድ አደራጅ ኮሚቴ የተጠቀሰውን ዩኒቨርሲቲ ሆነ የትምህርት ማስረጃ
ማረጋገጥ አለመቻሉን ለማዕከል ሪፖርት ሲያደርግ ጓድ ሙክታር ስልጣኑን ተጠቅሞ ባለማስቆሙ ከጓድ
አብይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደቀረበ ይታወሳል። ይህም ለስልጣን ያለ የተዛባ አተያይን የሚያመለክት መሆኑ
ተግልጾለት ሂሱን የዋጠ ሲሆን አጠቃላይ ጉዳዩ በእናት ድርጅት ተገምግሞ እንዲቀርብ አቅጣጫ ተሰጥቶ
ነበር። ዛሬ ዶኩመንታሪው ላይ ተደግሞ ሳየው የስንት አመታት ግምገማና ውይይት ምን ወንዝ ወሰደው
የሚያስብል ነበር።
የግለሰቦች ጉዳይ በተገቢው የድርጅት መድረክ ይታያል። እነዚህን መረጃዎች እዚህ ለማቅረብ ያስገደደው
ምክንያት ህዝብ የተሳሳተ ግንዛቤ ተፈጥሮበት ወደውዥንብርና ግርግር እንዳይገባ ከወዲሁ እርማት መስጠት
ግዜ የማይሰጥ ድርጅትንና ሀገርን የማዳን ተግባር በመሆኑ ነው። አመራሮች በተለያዩ ስራዎች በመያዛቸው
የተለመደውን መዋቅር ሳልጠብቅ የድርጅታችንን አባላትና ደጋፊዎች በቀጥታ እና በፍጥነት ማስገንዘብ
አስፈላጊ በመሆኑ ነው።
መላው የድርጅታችን አባላትና ደጋፊዎች በየአቅጣጫው በሚታዩ ነገሮች ሳይደናገሩ የኢህአዴግና የብአዴን
አመራሮች ስልጣንን የለውጥ መሳሪያ እንጂ የግል ጥቅም ማራመጃ አድርገው እንደማያዩት እምነት
ሊያሳድሩ ይገባል። አንዳንድ በየቦታው የሚታዩ ጤናማ ያልሆኑ ዝንባሌዎችም በዙሪያ መለስ ግምገማ
የሚስተካከሉ ናቸው። በአመራር ረገድ የሚፈጠር ክፍተት አይኖርም። ጓድ ኃይለማርያም በስራ ላይ
ናቸው። እሳቸው ፈጥነው መልቀቅ ቢያስፈልጋቸው እንኳን የኢህአዴግ ምክር ቤት ምርጫ እስከሚያደርግ
ድረስ በህገ-መንግስቱ መሰረት ምክትላቸው ስራውን እየሸፈኑ ይቆያሉ።
ከህዝባችን ጋር ሆነን የማንፈታው ችግር የለም!
የህዳሴ ጉዟችን ይሳካል!"
በረከት ስምኦን
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
February 27, 2018
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Wed Feb 28, 2018 1:22 pm

በውቮዴና በዒጭበዛበዛ ኶ቇዛ ኶ዴዏዙዔ
ሻዔበኴ ቬጦዲው (ጡዖዯኛ)
ኟቂዱዴ 21/2010
በቅዛቡ ኟክቡዛ ኟኢ.ዡ.ዲ.ዘ ጠ/ዑኒቬዳዛ ኶ድ ሃይኯዒዘኢዔ ደቪኯኝ ሿሃኲዟነዲዶው በዢቃዳዶው ኟዏኴቀቅኢ ዒቅዖብ ዯሿዴኵ ሁኰዔ በኟዟናው ግዒቯ ቩጠነቁኴና ቩኢቬጠነቁኴ ቇዑቨ ደግዕ እንደዯኯዏደው ብሄዙዊ ዒንነዴ ቂባ ኯብቭ ዯዖኛ እኛ ነን በዑኴ እቪቤ ኶ንዳንዱ ደግዕ በኢህ኶ዲግ ኶ባኴ ድዛጅድች ቂኰዴ ኶ዏዙዜች እኢበኲኯጠ ኶ቬዯኢኟደ በዏቬጠዴ ኲይ ይቇኛኴ፡፡ ኶ብኪኛው ግን ኟዏቧኯውን ሿዏናቇዛ ባኯዝ ይህ ነው ኟዑባኴ ኟኢህ኶ዲግ ኢኯዝ ባህዘውና እቫደ እንዲሁዔ ኶ቇዘደ ጏደዟዴ ኯዒቬቀጠኴ ኟዑችኴ ዏዏኧኛና ዔክንኢዴ ቩኢቬቀዔጥ ኶ኲቬዯዋኴቀዔ፡፡ ይባቬ ብኵ ኟግዔባ዗ ዏዘሆች ኴዔዶች ሿዏፃዖ዗ ባሻቇዛ ኟ኶ቇዘደ ዏፃኢ እድኴ ኟዑኢበኲሽ ኟጠባብና ኟዴዔክህዯኞች ኶ኯዢ ቩኴዔ ኟ኶ቇዙችን ኴዒዴና ቧኲዔ ኯዑኢቬጠኲዶው ኟውጭ ሃይኵች ኶ቪኴዣ ኟዑቧጥ ኶ቂሄድ ዯቬዯውኯዋኴ፡፡ ይህ ደግዕ በ኶ንዳንድ ኟኢህ኶ዴግ ኶ባኴ ድዛጅድዔ ጭዔዛ እኟቧ዗በዴ ዏሆኑ ኟሿዠ ኢደዛቇዋኴ፡፡
እኔ ኶ሁን ኯዏፃዢ ኢነቪቪኝ ቧኯሁኰዔ በኟዑድኢው ኟዑባኰ ነቇዜች ቪይሆን በዯጏቧኑ ቈዳዮች ኲይ ሃቪቤን ኯዏቬጠዴ ነው፡፡ ሿኲይ ኯዏጥቀቬ እንደዕሿዛቀዴ ሿቅዛብ ቉ካ ጏዲህ ኟጠቅኲይ ዑኒቬዳዛ ቦዲ ዒን ቢሆን ይሻኲኴ ኟዑኴ እኟዯንቮዙቮዖ ኢኯው ሃቪብ ኟዑጠኲና ክዠዴ ኢኯው ኶ይደኯዔ ቧዎች በኳኲዶው ነቇዛ በዏዷንዷን ጏደዟዴ ዒዔጣዴ ግን ኟጏንዷኴ ጏንዷኴ ነው፡፡ በኩህ ቈዳይ ኲይ ቬኯ ኟኢህዴድ ኶ዲቨ ኱ቀዏንበዛ ዶ/ዛ ኶ብይ በኦዜዑኢ ዳኳቪዥን ቪይቀዛ ዶቁዓንዲዘ ኟዯኲኯዝ እንዲሁዔ በዘፖዛዯዛ ቊካጣ ዯፃዝ ዯብኵ በ Ethiopiafirst ድዖ-ቇፅ ኟዯፃዞዴና ኟዯባኯው ቧውኟው ኢኴሆነውና ኟኳኯው ዒንነዴ እኟዯኧቇበ በዏሆኑ ይህ ደግዕ ነቇ ኟ኶ቇዘደ ዏዘ ሆኖ ቩዏጣ ኟዑኢቪድዖው ዯፅእኖ ጏኲዝኑ በእኢንዳንዳችን ኟዑኢዛዢ በዏሆኑ እንደድዜው በኬዔዲ ዏዲኯዢ ኟኳኯበዴ ቈዳይ በዏሆኑ በዏሿኲሿኢ ኶ብዖን በነበዖንበዴ ጏቅዴ ኟነበዖውን ዒንነዴ ኟዒውቀው በዏናቇዛ ኟካግነዴ ግዴዲኟን ዏጏጣዴ ቬኲኯብኝ ነው፡፡
እኔ ይህን ቬፅዢ በዶ/ዛ ኶ብይ ቊዛ ኶ብዖን ኶ኴቧዙንዔ ኟኢንቪዔ ኶ባኴ ኶ኴነበዛቀኝዔ ይሁን እንጂ እኔ ኟዔቧዙበዴ ኟነበዖው በ኶ሿባቢው ቬኯሆነ ኟዒውቀውና ዔናኴባዴዔ ቬህዯዴ እንዳይሆን ሿኦዜዑኢ ዱቪ ኟዯኲኯዝው ዶክዓንዲዘ ኶ይቼ እቬሿ኶ሁን በክዢኰ በቬዙ ኲይ ኢኰዴ ክዢኰ ቩዏቧዖዴዔ ቂኰዴ ጓዶኞቼ ኶ዖቊግጫኯሁ፡፡
በኩህ ኲይ ቬኯ ዶ/ዛ ኶ብይ ሿዏናቇዚ በዟዴ ግን ቬኯኢንቪ ኶ዏቧዙዖዴ ዴንሽ ኴበኴ ኶ሁን ኢንቪ በዏባኴ እኟዯጠዙ ኢኯው ዏቬዘኢ ቤዴ ዏዷዏዘኢ ኢዏደዒ (ኢንዣዛዓሽን ዏዖብ ደህንነዴ ዒዕሿኴ) ዯብኵ በ1987 ዓ.ዔ ኶ሿባቢ
ኟዯጏቧኑ በህጏሓዴ ኟጠኯዠ ቬዙ ቩቧ዗ በነበ዗ ጥቂዴ ዐኢዯኞች በዏሿኲሿኢ ቬዛ ሆነው ነው ኟዏዷዏ዗ዴ፡፡ በጏቅደ
ቬዙው ኶ዲቬ ቬኯነበዛ ኶ሁን ኟኢንቪ ዋና ዳይዚክዯዛ ሆነው በዏቬዙዴ ኲይ ኢኰዴ ዓ/ጄ ዯክኯብዛሃን ኟዑቇኘባዶው
኶ዔቬዴ ኟዑሆኑ ዲቊዮች እንግ኱ኬ ኶ቇዛ በዏሄድ ቬኴጠና እንዲጏቬዱ በዒድዖግ ነው ኟዯዷዏዖው፡፡ቀጥኵ
በሻዕቢኢ ጏዖዙ ጏቅዴ ቬዙው እንዲጠናሿዛ በዒቧብ ሿኟዏቬዘኢቤደ ኟዯጏቧኑ ዐኢዯኞች (በዯኯይ ኟGIS ዐኢ
ኢኲዶው) በዒዔጣዴ ቬኴጠና እንዲቧጡና እንዲኢግከ ኟዯጏቧኑዴ ደግዕ ውጪ ኶ቇዛ በዏኲክ ኟዖዥዔና ኶ጫጭዛ
ቬኴጠናዎች እንዲኢቇኘ ኟዯደዖቇበዴ ሁኔዲዔ በኟ቉ካው ኟቀጠኯ ዯግባዛ ነው:: እኩህ ዶክዯዛ ኶ብኡ ሿዯቀኲቀኰ
በኋኲዔ በ1997ዓ/ዔ ኶ሿባቢ ዏ/኶ኯቃ ኶ብኡን ጧዔዜ ኶ዔቬዴ ዐኢዯኞች ደቡብ ኶ዢዘቂ በዏኲክ ኟቭቬዴ ጏዛ
ቬኴጠና ጏቬደዋኴ::
ሿ1997ዓ/ዔ በኋኲዔ ቢዜው ኢዏድኤ (ኢንቪ) ዯብኵ ዙቨን ችኵ ሿዏሿኲሿኢ በዏውጣዴ በጠቅኲይ ዑኒቬዴዛ
ፅ/ቤዴ እንዲዏዙ ዯደዖቇ:: በኩህ ቉ካ ኟነበ዗ዴ ጏዲደዛ ኶ባኲዴ በቩቭኴ እንዲቀጥኰ ዯደዖቇ::ሿዯጏቧነ ኶ዏዴ ጏይ
ሁኯዴ ኶ዏዴ በኋኲ ግን ኶ባኲደ ጏደ ውዴድዛናው እንዲዏኯቨ ዯደዖቇ ይህ ቩሆን ግን በ኶ባኲደ ዢኲጎዴ ዯደዖጎ
በቩቭኴ ዏቀጠኴ ኟዑዝኴግ በቩቭኴ እንዲቀጥኴ ዯዝቅዶኯዴ ኟዯጏቧኑ በቩቭኴ ቀጥኯዋኴ ሿነኩህ ውቬጥ ዶክዯዛ
኶ብይ ኶ንዱ ነው::
ቬኯሆነዔ ኢንቪ ቩዏቧዖዴ ዶክዯዛ ኶ብይ ኶ኴነበዖዔ ዏቬዙችዔ ኶ይደኯዔ:: እኩህ ኲይ ኟዑነቪው ቈዳይ ዶ/ዛ
኶ብይ ዏቼና እንዴዴ ዯቀኲቀኯ ኟዑኯው ነው:: ዶ/ዛ በኢኔው ዏ/኶ኯቃ ኶ብይ በሻዕቢኢ ጦዛነዴ ጏቅዴ ኟኢኔው
ዓ/ዷነዙኴና ኟዔድዛ ሃይኴ ኶ኪዥ ኟ኶ሁኑ ኟኢዡድዘ ዯጏቂዮች ዔክዛቤዴ ኶ዝቈባኤ ኟሆኑዴ ኟዯሿበ዗ ኶ድ ኶ባዱኲ
ቇዏዳ ኦፕዚዯዛ ነበዖ (እኔዔ በዔድዛ ሃይኴ ኵጂቬዱክቬ ዏዔዘኢ ኶ባኴ ነበዛቀኝ):: ሿሻእቢኢ ጦዛነዴ በኋኲ ግን
ኢንቪን ዒጠናሿዛ በዒቬዝኯቈ በዯኯኢኟ ቦዲ በኦፕዚዯዛነዴና በIT ዐኢ ቩቧ዗ ኟነበ዗ ኶ባኲዴ እንዲዏኯዏኰ
ቬኯዯደዖቇ በኪን ቉ካ ዶ/ዛ ኶ብይ ኢንቪን ኯዏቀኲቀኴ እድኴ ኶ቇኗ በቃ ይሄ ነው ዘፖዛዯዛ ቊካጣና ኟኦዜዑኢ
ዯኳቪዥን ዏቬዙች ኟዑኯው ውቮዴ ሿኟዴ እንዳዏጡዴ ዙቪዶው ይዏኴቨዴ ይህ ውቮዴ ኶ንድ እንበኯው::
ሿኩህ ቀጥኵ ኟዑዏጣው ኟዘፖዛዯዛ ቊካጣና ኟኦዜዑኢ ዯኳቪዥን ሁኯዯኛ ውቮዴ ደግዕ ኟኢንቪ ዋና ዳይዘክዯዛ
ነበ዗ ኟዑኯው ነው:: እኔ እቬሿዒውቀውና ጠይቄዔ እንዳዖቊቇጥቀዴ ኢንቪ ኟዑባኯው ዯቋዔ ሿዯዏቧዖዯ ዷዔዜ
ሿዓ/ዷነዙኴ ዯክኯብዛሃን ውጪ ኳኲ ዋና ዳይዘክዯዛ እንዳኴዯቮዏ ነው:: ዶ/ዛ ኶ብይ በዋናነዴ ሿኢንቪ ኟዯኯኢአ
ዳይዚክዯዜች (ቅዛንጫዣች) ውቬጥኟ኶ንዱ ዳይዚክዯዛ እንደነበ዗ በ኶ንድ ጏቅዴ ግን ዓ/ዷ ዯሿዯኯብዛሃን
ኯዴዔህዛዴ ውጪ በሄዱበዴ ቉ካ ኯዯጏቧነ ቉ካ ዯጏቂይ ሆነው እንደቧ዗ና በኪች ኶ጭዛ ግካዔ ኶ሁንዔ ድዖቬ
ኟዯጠናጏዲዶው ኟዴግዚ ጥኲቻ ዯነቪቬዯው ዓ/ዷ ዯክኯብዛሃንን ሿ኶ባኲደ ኯዏነጠኴና ኯዒጥኲኲዴ ኟዯኯኢኟ ዯግባዙዴ
እንደዝፀዐ ሿዝፀዐዋዶው ዯግባዙዴ ኶ንዱና ጏንዷኴ ኟዑሆነውዔ ሁኰዔ ኶ባኴ ኟሿዯዒ ቦዲ ዒግኗዴ ቩችኴ
ዯክኯብዛሃን ቬኲኴዝኯቇ ነው ኢኲቇኛችሁዴ ኶ሁን እኔ ኶ቧጣችኋኯሁኝ በዒኯዴ በ኶ዲቬ ኶በባ ከዘኢ ባኰዯ ኟኦዜዑኢ
ኴአ ክኖች ቂኰዴ ሃኲዟዎች ቊዛ በዏነቊቇዛ ዏዚዴ ኯዒቧጠዴ ኟዯቻኲዶውን ጥዖዴ ኢደዛቈና ኯዯጏቧኑዔ ዒቧጠዴ
ኟቻኰበዴና በክዢኰ ኟዯጏቧነ ጫጫዲ ዯዝጥዜ እንደነበዖ ዏጧዖሻው እዛግጠኛ ባኴሆንዔ ህቇጏጥ ኟዏዚዴ ጏዖዙ
ዯብኵ እንደዯቋዖጠና ኟዯቧጣዶውዔ እንደዯነጠቁ ይጏዙኴ:: ቬኯሆነዔ ኟኢንቪ ዋና ዳይዘክዯዛ ኶ኴነበ዗ዔ ኟኦዜዑኢ
ዯኳቪዥንና ዘፖዛዯዛ ቊካጣ ነበ዗ ኟዑኰን ሿሆነ ደግዕ በኢዡድዘ ዏንግቬዴ ዋና ዳይዘክዯዛ በጠቅኲይ ዑኒቬዴ዗
በደብዳቤ ኟዑሾዔ ቬኯሆነ ኟቯዏዴ ደብዳቤ኶ዶው ቢኢቀዛብ:: ይህዔ በ኶ድ በዖሿዴ ቬዏኦን ዯፃዝ ዯብኵ በዡቬቡክ
ኟዯኯቀቀው እንደዯቇኯፀው ኟዴዔህዛዴ ዒቬዖጃ ዒቅዖብ እንዳኴቻኰና ሿቀድዕው ኟኦህዴድ ኱ቀዏንበዛ ሿነበ዗ዴ
኶ድ ዐክዲዛ ቊዛዔ በኩህዔ ዔክንኢዴ እንደዯጣኰ ዯዏቪቪይ ኱ሆን ነው ዒኯዴ ነው:: ቬኯሆነዔ ይህዔ ውቮዴ
ሁኯዴ ይባኲኴ::
ኳኲው ኱ነቪ ኟዑችኴ ጥኢቄ ኟዒእዛቊዶው ቈዳይ ነው እኔ እዒውቀው ዏ/኶ኯቃነዲዶው ነው ሿኪ በኋኲ ሻዔበኴ
ዏሆናዶውና ሻኯቃ ዏሆናዶው ቪኴቧዒ ነው ኳ/ኮኵኔኴ ነበ዗ ኟቧዒሁዴ ይህ ቈዳይ ብከዔ ጥኢቄ ውቬጥ
኶ኲቬቇባሁዴዔ እውነዴዔ ኱ሆን ይችኲኴ ዔክንኢደዔ ኶ንደኛ ነቇዛ ዯዋፅኦው ኯዒዏጣጠን ቩባኴ በዋናነዴ ዴግዘኛ
ዯናቊዘ ነው በ኶ንድ ዒእዛግ ዖዥዔ ቉ካ ኟዑቆኟው ቢኢንቬ ዏቆኢ ቉ካ ዏቮዝን ኢኯበዴ ቬኯሆነዔ በ኶ዠጣኝ
ዯቧጥድዴ ኱ሆን ይችኲኴ ሁኯዯኛ ሿኮ/ኴ በዲች ኢኯው ኟዒእዛግ ኶ቧጣጥ ቬኯዒይዲጏጅ ኢኯቧዒሁዔ ኱ሆን ይችኲኴ
ኟዑኴ ግዔዴ ብከዔ ኶ኴቇዖዏኝዔ ቢሆንዔ ግን በሁኯዴ ጏይዔ በቭቬዴ ኶ዏዴ እንዴዴ ሿዏ/኶ኯቃ ሻዔበኴና
ሻኯቃ ዯሻግዜ ኳ/ኮኵኔኴ እንደደዖቧ ግን ኟዒውቀው ነቇዛ ኟኯዔ::
ዲድኢ እንዲህ ሿሆነ ዶ/ዛ እንዴዴ ሿኢንቪ ኯቆ በክኴኴና በዡደዙኴ ቬኴጣን ኶ቇኗ ኟዑኯው ነቇዛ ኱ነቪ ይችኲኴ::
ነቇ዗ እንዲህ ነው ዶ/ዛ ኶ብይ በጣዔ ብኴጥ ነው ሿብኴጦችዔ ብኴጥ ኢንቪ ኶ሿባቢ ኢቺው ኟቬኴጣን ዏቆናጠጫ
ጏይዔ ኬግ ናዴ ቂኴሆነዔ በጣዔ ዴኧቇኢኯች በኧቇኟ ቁጥዛ ደግዕ ብኴጦች እንደዒይቪቂኯዶው በዑቇባ ኢጏቃኴ
(ኟ኶ሁኑ ጥድዟኢ ኴብ ይኯዋኴ) እናዔ ቀደዔ ብኟ እንደጠቀቬቀዴ ኶ብኪኛው ኟኢንቪ ኶ባኲዴ ጏደ ውዴድዛናው
ቩዏኯቨ እኔ በቩቭኴ ሁኜ (ኟ኶ሁን ኶ኢድዛቇውና ኟኦህዴድ ቬዙ ኶ቬዝፃዑና ኟፅ/ቤዴ ሃኲዟ እቬቁሆን ድዖቬ ኟእነ
኶ባዱኲዔ ሿዢዯኛ ድቊዢ ነበዖው) ኦህዴድን ዒጠናሿዛ እዝኴቊኯሁ በዒኯደ በኪው ቀዖ እንዳቧበውዔ ዯቪቂኯዴ
ባኯቤደዔ ጏዲደዛ ነበዖች እንድዴጏጣ ኶ደዖቇ እንደዯዏኗውዔ ኟኢዡድዘ ጠቅኲይ ዑኒቬዳዛ ኯዏሆን ኢኯ ኟኳኯ
኶ቅዐን ውቮዴዔ ቢሆን እኟዯጠቀዏ ይቇኛኴ::
በ኶ጠቃኲይ ግን ዶ/ዛ ኶ብይ ኢኯው ዢጥነዴ ክዢዯድች ኟዏጠቀዔ ችኵዲውና ቩቬዯዐ ኶ደንቅኯዲኯሁኝ:: ኯኩህዔ
ጏደ ኦህዴድ ኱ቀዏንበዛነዴ ኟደዖቧበዴ ዢጥነዴና ብኴሃዴ ኶ቬቇዙዑ ነው:: በ2009ዓ/ዔ ግንቦዴ ጏይዔ ቧኔ ጏዛ
኶ሿባቢ ኟኦህዴድ ኶ዏዙዜች ዏዝንቅኯ ቬኴጣን በዑዏቬኴ ኶ቂሄድ ኶ድ ኯዒን ኱ቀዏንበዛ ዶ/ዛ ጏዛቅነህ
ዔክዴኲዶው በዏሾዔ ኶ብይ ኟኦህዴድ ፅ/ቤዴ ሃኲዟ ሆኑ ሿቬድቬዴ ጏዛ በኋኲዔ ዶ/ዛ ጏዛቅነህ እና ኶ድ ኯዒ እጣ
ደዖቪዶውና ሃኲዟነዲዶው ኯዶ/ዛ ኶ብይ ኯዏሾዔ ዯቮቊቮቈ ዯባኰ ይህ ኶ቂሄድ ኶ንድ ፀሃዟ እንዳኯው ሿ40 ኶ዏዴ
በዟዴ ኳ/ኮኵኔኴ ዏንግቬደ ሃይኯዒዛኢዔ ጏደ ቬኴጣን ኟዏጣበዴ ዏንቇድ በጣዔ ይዏቪቧኲኴ::
኶ሁን ደግዕ በኟዡቬቡቀ ኶ንዱ ጠንቋይ ኶ኯች ኳኲ ግካ ኶ድ ኯዒ ኶ኰ እኟዯባኯ ሿኢህ኶ደግ እቫዴና ኶ቂሄድ በእጅቈ
ኟዙቀ እንደ ዔክዛ ቤዴ ኶ባኴ በህኬብ ድዔፅ ኟዑዏዖጥ ይዏቬኴ ሆን ዯብኵ ዯፅእኖ ኯዏዢጠዛ ዲቬቦበዴ ኟዯደዖቇ
ኟዔዖጡኝ ቅቬቀቪ እኟዯደዖቇ ይቇኛኴ::
ኯዏሆኑ ጠቅኲይ ዑኒቬዳዛ ኟዑዏዖጠው በብሄዙዊ ዯዋፅኦ ጏይዔ በዯዙ ነው ጏይቬ በብቃዴ ነው? ይህን ጥኢቄ
ዔኲቯ ኯኢህ኶ዴግ ኴዯጏው:: በኔ እዔነዴና በኢህ኶ዴግ ኟዒውቀው እቫዴና ኴዔድ ግን በብቃዴ ቂኰዴ ዯጏዳድዜ
ዏሆኑ ግኴፅ ነው:: ዶ/ዛ ኶ብይ ብቃዴና ኴዔድ ኟኯውዔ እንጂ ቢኖዖውና ሿቨ ኟዯቮኯ ሿኳኯ ግን ቢዏዖጥ ችግዛ
ኟኯኝዔ:: ዔክንኢደ እንደኩህ ኶ይነዴ ቬዙ ኴዔድ ኟኯውዔ ብቻ ቪይሆን ኶ሁን በክኴኰ ኢኯውና ኶ቇዘደ በቬድቬዴ
ጏዛ ኴአነዴ ኯሁኯዯኛ ቉ካ ጏደ ኶ቮዶኳይ ቉ካ ኶ዋጅ ኢቬቇባው ችግዛ ኶ቅዔና ዢኲጎዴ ቢኖዖው በዯዝዲ ነበዛ::
በነቇዙችን ኲይ ሿ኶ድ ኯዒ በዔን ቢበኴጥ ነው ኟዏጣው ኶ድ ኯዒ በዡደዙኴ ጏንበዛ ቬኯኳኲዶው ኟዑኯው ኶ባባኴ
ዴክክኴ ኶ይደኯዔ ቮዢጥ ነው ዔክንኢደዔ በዟዲችን ግንቦዴ ጏዛ በዑቂሄደው ኟዔክዛ ቤዴ ኟሟሟኢ ዔዛጫ ኱ቇቡ
ይችኲኰና ይህቺ ቈዳይ ኯ኶ድ ኯዒዔ ኟዯዋጠችኲዶው ኶ይዏቬኯኝ ዔክንኢደዔ ዔክዴኴ ኱ቀዏንበዛ ሿሆኑ በኋኲ
ሿዟዲዶው ኟዑነበበውና ኟዑናቇ዗ዴ ኟግብዛ ይውጣ ኶ይነዴ ነው:: ኯዒኛውዔ ኢህ኶ደግ ይህችን ዴኴቅ ኶ቇዛ
ኯዏዔዙዴ ኟዯቧጠህን ኟ኶ዔቬዴ ኶ዏዴ ኮንዴዙዴ በዑቇባና እንደጏዴዜው በበቧሿነና በበቧኯ ዏንቇድ
እንድዴጠቀዔበዴ እኢቪቧብቀኝ በቅዛቡ እንደዯኯዏደው በኟዡቬቡቀ እኟዯባኯ ኢኯው ዶ/ዛ ነቊቭ ኟኦህዴድ ኶ዒቂዘ
ሆነው ኱ሾዐ ነው ኟዑባኯው ጏዚዔ ኢህ኶ዴግ በዯኯይ ደግዕ ኦህዴድ ጏዴዴ እኟሄደ እንደሆነ ግዙ ኟዑኢቊባ ነው
እኲኯሁኝ::
ዶዛ ጏዚ ኢቧዒን ኶ዔኲክ ሿዡቬቡክ ኶ዛበኞች ኶ቇዙችን ይጠብቅ
ክብዛና ዕጎቬ ቈድዢ ኯዒይቇኝኲዶው ቧዒእዲዴ
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am

Re: ሰላም ዋርካውያን

Postby ለማ12 » Thu Mar 08, 2018 12:16 pm

በአሜሪካ የትግራይ ኮምዩኒቲዎች ፎረም
በአገራችን ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
እኛ በኣሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የምንገኝ የትግራይ ኮምዩኒቲ ማህበራት መሪዎች ባቋቋምነው የጋራ ፎረም አማካኝነት ዛሬ ማርች 4, 2018 ተሰባስበን ስለ ሃገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በጣም አሳስቦን፥ የተጀመረውን ፈጣን የኢኮኖሚ እድገትና ዳዴ በማለት ላይ ያለው የዲሞክራሲ ፋና ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ እንዲሁም ለዘመናት ተሳስቦና ተከባብሮ የኖረው ህዝባችን ኢትዮጵያዊ ጨዋነቱን ጠብቆ ለቀጣይ ትውልድ እንዲያስረክብ ባለን ጠንካራ ፍላጎትና ሃገራዊ ሃላፊነት ተነሳስተን በጥልቀት ከተወያየን በኋላ የሚቀጥለው ባለ 11 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል።
1. የሃገራችን ኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት መጪው ትውልድ ከድህነት ተላቆ የተሻለ ህይወት እንዲመራ ያስችለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ወጣቱ በአንዳንድ የሃገሪቱ ክልሎች የሚያወድማቸው መሰረተ-ልማቶች በወጣቱ የወደፊት እድል ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ስለሚኖራቸው በዚሁ ጉዳይ ላይ የነገው ሃገር ተረካቢ የሆነው ወጣቱን የሚጎዳ መሆኑን በቂ መረጃና ትምህርት እንዲሰጠውና ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንዲያስተጋባ እንዲደረግ እንጠይቃለን።
2. በትምህርት ጥራት ይሁን በስራ ፈጠራ መስክ መንግስት ያለበትን ሃላፊነት በመወጣት ወጣቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ እርምጃዎች በወቅቱ እንዲወሰድ እንጠይቃለን።
3. የሃገራችን የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት በማለት ኢህአዴግ የታሰሩትን የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዎችና አባላት በመፍታት ብሄራዊ መግባባት እንዲሰፍን ማሰቡ እንደግፋለን። ገዢው ፓርቲና ተቃዋሚ ሃይሎች ህዝብንና ሃገርን የመምራት ሃላፊነት ያለባቸው መሆኑን ተገንዝበው በሚያገናኙዋቸው አብረው የሚሰሩበት በማያገናኙዋቸው ደግሞ ህዝቡ ነፃና ፍትሃዊ በሆነ ምርጫ በካርዱ እንዲመርጣቸው የተመቻቸ ሁኔታ እንዲፈጥሩና ከጠላትነት አባዜ ወጥተው ተፎካካሪ ድርጅቶች ለመሆን እንዲበቁ አጥብቀን እናሳስባለን።
4. የሃገራችን ሰላም እየደፈረሰ፣ በሰው ህይወትና ንብረት አደጋ እየደረሰ ባለበት በአሁኑ ጊዜ መንግስት ያወጀው ያስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንደግፋለን። ይህ አዋጅ ስንደግፈው የሚያመጣውን ሰላም በመጠቀም መንግስትና የተቃዋሚ ሃይሎች ለተፈጠሩ ችግሮች ሰከን ብለው በማሰብ መፍትሄ ለማምጣት እንደሚጠቀሙበት በማመን ነው። ስለሆነም የሃገሪቱ መረጋጋት ሳይረጋገጥና አስፈላጊ መፍትሄዎች ሳይቀመጡ አዋጁ በችኮላ እንደበፊቱ እንዳይነሳና ሃገሪቱ እንደገና ወደ ህውከትና ብጥብጥ እንዳትመለስ አጥብቀን እናሳስባለን።
5. በጎንደር የተጀመረውና እስከ ወሎ ድረስ የዘለቀው የዘር ጥላቻ በትግራይ ተወላጆች ህይወትና ንብረት ላይ የተፈፀመው አረመኔዊና ከወገን የማይጠበቅ አፀያፊ ኋላቀር ድርጊት አጥብቀን እናወግዛለን።
በተመሳሳይም በኦሮሚያና በሶማሊያ ክልል አጎራባች መንደሮችና ከተሞች በተቀሰቀሱ ግጭቶች ምክንያት የደረሰው የህይወትና የንብረት ውድመት አጥብቀን እናወግዛለን። የመርማሪ ቡድን ባልተቋቋመባቸው አካባቢዎችም ባስቸኳይ ተቋቁሞ ድርጊቱን በሚገባ ተጣርቶ ወንጀሉን በፈፀሙ አካላት ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድና ለህዝቡም ይፋ እንዲሆን አጥብቀን እንጠይቃለን። መንግስትም ዜጎች ለህይወታቸው
ሳይፈሩ በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል የመኖር፣ የመስራትና ሃብት የማፍራት መብታቸውን የማስከበር ሃላፊነትና
ግዴታውን እንዲወጣ እንጠይቃለን። ለተፈፀሙ ወንጀሎችም ሃላፊነት በመውሰድ መንግስት ህይወታቸው ላጡና
በህይወት ላሉ ተጎጂዎች የገንዘብና የንብረት ካሳ እንዲያደርግላቸውና ወደነበሩበት ቦታ ተመልሰው ደህንነታቸው
ተጠብቆ በሰላም እንዲኖሩ ይደረግ ዘንድ እንጠይቃለን።
6. የተከሰተው የሃገሪቱ አለመረጋጋት፣ እጅግ አደገኛና አሳሳቢ ከመሆኑም በላይ እንዳይባባስ መንግስት፣ ተቃዋሚ
ሃይሉና ህዝብ ከሁሉም በፊት ያገሪቱን ህልውና ቅድሚያ እንዲሰጡ እንጠይቃለን።
7. ዜጎች የማንም ፖለቲካና ፓርቲ ደጋፊ በመሆናቸው ይሁን በብሄር ማንነታቸው እንደጠላት የሚፈርጁ፣ አደጋ
የሚያደርሱና ለማድረስ የሚሞክሩ ሰዎች የሚቀጡበት “የጥላቻ ወንጀል መቅጫ ህግ” ካለ ተግባራዊ እንዲሆን
ከሌለ ደግሞ እዲደነገግ ኣጥብቀን እናሳስባለን።
8. ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈፀመ ያለው መጠነ ሰፊና በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የስም ማጥፋትና የጥላቻ
ዘመቻ መሰረተ ቢስ ከመሆኑም በላይ በሃገራችን ላይ የሚኖረው አሉታዊ ተፅእኖ ቀላል ስለማይሆን ይህ ዘመቻ
በመንግስት፣ በሃይማኖት አባቶች፣ በታዋቂ ግለስቦችና ተቃዋሚ ሃይሎች በጥብቅ ተወግዞ ተከታታይ ትምህርትና
እርምት እንዲሰጠው አበክረን እንጠይቃለን።
9. በኢትዮጵያ ውስጥና ከኢትዮጵያ ውጪ የምንኖር የትግራይ ተወላጆች በዚሁ አሳሳቢና ፈታኝ ወቅት እንደ
ወትሮው ትእግስትን እንድንመርጥ እያሳሰብን በማንኛውም ጊዜ ከህዝባችን ጎን የምንሰለፍ መሆናችንን
እናረጋግጣለን።
10. በብዙ ሺህ የሚቆጠር ኢትዮጵያዊ የህይወት መስዋእትነት የከፈለባቸው መሰረታዊ የዲሞክራሲ መብቶች
ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ እንጠይቃለን። ፍትህና መልካም አስተዳደርን ያጎደሉ፣ የህዝብን ንብረትና ገንዘብ የዘረፉ፣
የመንግስትና የፓርቲ ባለስልጣናት በህግ ፊት ቀርበው እንዲቀጡ እንጠይቃለን።
11. የኢትዮጵያ ህልውናና የህዝቦቿን አንድነት የሚፈታተኑ በውስጥም ይሁን በውጭ ሃይሎች የሚዶለቱ ሴራዎችን
እናወግዛለን።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
ለማ12
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1108
Joined: Sat Jun 16, 2012 9:46 am


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Google Adsense [Bot] and 7 guests