አላሙዲ መሬቱን ሊያጣ ይችላል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አላሙዲ መሬቱን ሊያጣ ይችላል

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Feb 18, 2018 10:22 pm

ሼኽ ሙሐመድ አላሙዲ የኢትዮዽያን መሬት ከተቀራመቱት ስግብግብ ባለሃብቶች አንዱ መሆኑን የማንገነዘብ ብንኖር ምናልባት ለአንዳንዶች(በተለይ አርቲስቶችና ስፖርተኞች) ሲያደርግ በነበረው በጎአድራጎት አእምሮአችን የታወረ መሆን አለበት::ላለፋት 25 ዓመታት አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ እንኳ ተጫርቶ በግሉና ሚ ድሮክ በተባለው ድርጅቱ አማካኝነት የተቆጣጠራቸው ቦታዎች ምን ያህል እንደሆኑ እሱና ህወሓት ብቻ ናቸው የሚያውቁት።የግለሰቡን ሥም ለማንሳት የገፋፋኝ የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል እንዲሉ ህወሓት በሼኹ ላይ ፊቱን ያዞረበት ስለመሠለኝ ነው::ለዚህም ያነሳሳኝ በሼኹ ላይ ሊወሰድ የታሰበው እርምጃ ነው::ምናልባት ምን ያህሎቻችን እንደምናውቅ እርግጠኛ ባልሆንም ግለሰቡ ህንፃ ከሠራባቸው ቦታዎች በተጨማሪ በርካታ ቦታዎችን ከአስርና ሃያ ዓመታት በላይ አጥሮ አስቀምጧል::በተለይ ድሮ የእግር ኳስ ሜዳ የነበረውና ከማዘጋጃ ቤት ትይዩ የሚገኘው መሬት የከተማዋ ነዋሪዎችን ሲያነጋግር የኖረ ነው::ድርጅቱ የየያዘው መሬት ከሃምሳ ሄክታር (1ሄክታር 10000 ካሬሜትር ነው) በላይ እንደሆነ ይገመታል፡፡
ታዲያ አሁን ሚድሮክ ኩባንያ በተደጋጋሚ አጥሮ በያዛቸው ቦታዎች ላይ ሥራ እንዲሠራባቸው ማስጠንቀቂያ ቢሰጠውም የገባውን ቃል ተግባራዊ ባለማድረጉ የሚመለከተው ክፍል(የአዲስ አበባ አስተዳደር የመሬት ልማትናእስተዳደር) የመሬቶቹ ካርታዎች እንዲመክኑ ወስኗል::ውሳኔው ግን ለከተማው አስተዳደርና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ቀርቦ መጽደቅ አለበት።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1018
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot], Majestic-12 [Bot] and 9 guests