ጎንደር ውጥረቱ አይሏል!! በርካታ ወጣቶች ከጎንደር በኮማንድ ፖስቱ እየታፈኑ እየተወሰዱ ነው!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ጎንደር ውጥረቱ አይሏል!! በርካታ ወጣቶች ከጎንደር በኮማንድ ፖስቱ እየታፈኑ እየተወሰዱ ነው!

Postby ኳስሜዳ » Tue Mar 13, 2018 1:29 pm

ጎንደር ውጥረቱ አይሏል!! በርካታ ወጣቶች ከጎንደር በኮማንድ ፖስቱ እየታፈኑ እየተወሰዱ ይገኛሉ። ከ30 በላይ ወጣቶች የት እንደደረሱ አልታወቀም። በ6ኛ እና 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከ10 በላይ ወጣቶች ታፍሰው መታሰራቸው ታውቋል።

መሳፍንት መዝገቡ ወይም በቅጽል ስሙ ዱቼ ተብሎ የሚታወቀው የጎንደር ወጣት ትናንት ጠዋት በኮማንድ ፖስቱ ወታደሮች ታፍኖ ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስዷል። ይህ ግለሰብ ባለፉት 6 ወራት በማይታወቅ ቦታ ታስሮ በቅርቡ የተፈታ እንደሆነ ይታወዋል። አሁን በድጋሚ አፍነው ሊወስዱት ችለዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኋላ ከጎንደር ከተማ ብቻ ከ30 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ታፍነው ወደ አልታወቀ ቦታ ተወስደዋል።

በተለይ ቀበሌ 18 ሁኔታው ጦዟል!! በየጎዳናው ፍተሻው ተጠናክሮ ቀጥሏል።በየአስፋልቱ የፌድራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት እየተርመሰመሰ ይገኛል!!

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ በቀበሌ 18 አዳራሽ ኮማንድ ፖስት የተባለው አፋኝ ቡድን ህዝቡን ሰብስቦ ስለ አስቸኳይጊዜ አዋጁ ሊሰጠው የነበረው ማብራሪያ በከፍተኛ ተቃውሞ እና ህዝቡ መድረኩን እየረገጠ በመውጣቱ ምክንያት ማብራሪያው መቋረጡን ታውቋል!! በዚህም ምክንያት የህወሃት ሎሌዎች ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ መዘፈቃቸውን ተሰምቷል።

ምንጭ፡ ምንሊክ ሳልሳዊ
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2162
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 2 guests