በ21ኛው ክፍለ ዘመን በስህተተኞች ስህተት የምትመራ ሀገር !

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

በ21ኛው ክፍለ ዘመን በስህተተኞች ስህተት የምትመራ ሀገር !

Postby ኳስሜዳ » Tue Mar 13, 2018 1:43 pm

Image
በስህተት ላይ ስህተት !!!!!
~ ከ400 በላይ የአኝዋክ ተወላጆች በስህተት ተገደሉ።
~ የምርጫ ኮረጆ ከድምፅ መስጫ ጣቢያዎች በስህተት ተሰረቀ ።
~ በአዲስ አበባ ኮንዶሚኒየም በስህተት ጠፋ ።
~በወልድያ ከተማ የጥምቀት በአል በማክበር ላይ የነበሩ ምእመን በስህተት ተገደሉ ።
~በባህር ዳር ከተማ 50 በላይ ወጣቶች በአንድ ቀን በስህተት ተገደሉ።
~ ብሔራዊ ባንክ ባሌስትራን ወርቅ ነው ብሎ በስህተት ተቀበለ።
~ ከ200 በላይ የአዲስ አበባ ወጣቶች ባንክ በሌለበት አካባቢ ባንክ ሊዘርፉ ነው በሚል በስህተት ተገደሉ።
~ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአንዋር፣ በኒንና አሰሳ መስጊዶች በፀሎት ላይ እንዳሉ በስህተት ተገደሉ ።
~ ባህታዌ ፈቃደ ሥላሴ በአዲስ አበባ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን በአቡነ ጳውሎስ ጠባቂዎች በስህተት ተገደሉ።
~ በቢሾፍቱ የኢሬቻ በአልን በማክበር ላይ የነበሩ ከ800 በላይ ሰላማዊ ዜጎች በስህተት ተገደሉ።
~በአዲስ አበባ አንድ አስፋልት መንገድ በስህተት ጠፋ።
~ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በስህተት ተሰረቀ
~ በኦሮሚያ ጨለንቆ በርካታ ዜጎች በስህተት ተገደሉ።
~ አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ የአስቸኳይ ጊዜ አወጁን የደገፉ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ቁጥርን በስህተት ጠቀሱ ይቅርታም ጠየቁ ።
~ ሜቴክ የተባለው የመከላከያ የበኩር ልጅ ለስኳር ፕሮጀክት የተመደበው በቢሊዮን የሚቆጠር ብር በስህተት ጠፋብኝ አለ……
~ ኮማንድ ፖስቱ በሞያሌ ነዋሪዎች ላይ በስህተት የሞትና የመቁሰል አደጋ አደረሰ ።
በስህተት.. እምየ ኢትዮጵያ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በስህተተኞች ስህተት የምትመራ ሀገር !
ምንጭ፡ ቆንጂት ስጦታው
ኳስሜዳ
አለቃ
አለቃ
 
Posts: 2162
Joined: Mon Dec 05, 2016 12:21 am

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 5 guests