የታሳሪ ጥፍር ነቃይና ብልት ቀጥቃጭ ወያኔ ይጠፋል

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የታሳሪ ጥፍር ነቃይና ብልት ቀጥቃጭ ወያኔ ይጠፋል

Postby እሰፋ ማሩ » Fri Mar 23, 2018 9:28 pm

አበበ ካሴ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመበት ነው
መጋቢት 14/2010)በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተከሶ በቃሊቲ እስር ቤት የሚገኘው አበበ ካሴ ከፍተኛ ስቃይ እየተፈጸመበት መሆኑን ገለጸ።
ከ2006 ጀምሮ 7 አመት ተፈርዶበት በእስር ላይ የሚገኘው አበበ ካሴ በተፈጸመበት ኢሰብአዊ ድርጊት ሽንቱን መቆጣጠር እንደማይችል ገልጿል።

ከወልቃይት ማንነት ጋር በተያያዘ በእስር ቤቱ ሃላፊዎች አሁንም ድብደባ እየደረሰበት ነውም ተብሏል።

አበበ ካሴ በአርበኞች ግንቦት ሰባት ስም ከተወነጀለበት ክስ ሌላ በአማራ ክልል ፍርድቤትም ሌላ የቅጣት ውሳኔ እንደመጣበት ይናገራል።

በግንቦት ሰባት ስም በቀረበበት ክስ 7 አመት ሲፈረድበት በወልቃይት ማንነት ሰበብ በተወነጀለበት ጉዳይ ደግሞ 20 አመት እንደተፈረደበትም ነው የተነገረው።

አበበ ካሴ በማዕከላዊ እስር ቤት በነበረበት ወቅት በደረሰበት ድብደባም 20 የእግሩና የእጁ ጥፍሮች ሙሉ በሙሉ ተነቅለዋል።

ይህ ብቻ አይደለም በኤሌክትሪክ ንዝርት በተፈጸመበት ጉዳትም የዘር ፍሬው መምከኑን ገልጿል።

በግብረሰዶም ወንጀል ከተፈረደባቸውና ከአእምሮ ህሙማን ጋር ከአንድ አመት በላይ አንድ ላይ እንድታሰር ተደርጌያለሁ ማለቱም ታውቋል።

አበበ ካሴ በጓደኛው ዳንኤል ተስፋዬ በኩል እንደተገለጸው በደረሰበት ኢሰብአዊ ድርጊት ኩላሊቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶብታል።

በዚህም ሳቢያ ሽንቱን መቆጣጠር እንደማይችልና ሕክምናም እንዳላገኘም ተገልጿል።
እሰፋ ማሩ
ዋና ውሃ አጠጪ
ዋና ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1550
Joined: Mon Sep 12, 2016 8:47 pm

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google [Bot] and 6 guests