አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው ?

Postby ቆቁ » Sun Feb 10, 2019 6:20 pm

ምንድነው ጥቅማ ጥቅሙ ? እሴቱ ?
መሬት በሲግናል ?
ወይስ የስራ እድል በለገሐር ?
ወይስ ነዋሪው ሕዝብ ?

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun Feb 10, 2019 6:38 pm

London has a diverse range of people and cultures, and more than 300 languages are spoken in the region.[54] Its estimated mid-2016 municipal population (corresponding to Greater London) was 8,787,892,[4] the most populous of any city in the European Union[55] and accounting for 13.4% of the UK population.[56] London's urban area is the second most populous in the EU, after Paris, with 9,787,426 inhabitants at the 2011 census.[57] The population within the London commuter belt is the most populous in the EU with 14,040,163 inhabitants in 2016.[note 4][3][58] London was the world's most populous city from c. 1831 to 1925.[59]
300 ቁዋንቁዋ ?
ለየትኛው ቁዋንቁዋ ነው የለንደን እሴት ? ጥቅማ ጥቅሙ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Feb 10, 2019 7:01 pm

እንደ አመለካከትህ ነው፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Tue Feb 12, 2019 6:22 pm

አመለካከቴ እንደ ጣይቱ ብጡል ነው
የአንተስ አመለካከት እንዴት ነው ?

ያኔ አዲስ አበባ በፍልውሃ ( ፊንፊኔ) ፡ በአዋሬ፡ በየካ ፡ በጉለሌ ፡ በገፈረሳ ፡ ተከፋፍላ መንደራ መንደር በነበረችበት ዘመን ክረምት አልፎ የበጋው ወራት ሊመጣ ሲል ክእንጦጦ ተራራ ወደ ታች ለተመለከታት እጅግ ውበት ያላት በአደይ አበባ ያሸበረቀች የመንደሮች ጥርቅም ነበረች
ይህንን ተመልክታ ነው ጣይቱ ብጡል አደይ አባባ በማለት አዲስ አበባን የገለጸቻት

አዲስ አበባ ከአደይ አበባ የፈነደቀ ነው ፡፡
ፈላስፋው ቆቁ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች አንዱ
ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ፍቅርና ሰላም
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Tue Feb 12, 2019 8:21 pm

የእቴጌ ጣይቱን አዲስ አበባ አንተ አታውቃትም።የአሁኗን አዲስ አበባ እቴጌ ጣይቱ አያውቋትም።እንዴት ነው ተመሳሳይ አመለካከት የሚኖራችሁ?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Feb 14, 2019 6:05 pm

ከእንጦጦ ተራራ ሆነህ ወደ ታች ስትመለከት ልክ ጣይቱ ብጡል እንደተመለከተችው ነው አዲስ አበባን የምትመለከታት
ከምኒሊክ ቤተ መንግስት እናት ላይ ሆነህ ዙሪያውን ብትመለከት የእዲስ አበባን ራዲየስ በትክክል እንደ ጣይቱ ብጡል ልትመለከት ትችላለህ

ምናልባት ልዩነታችን
ዛሬ ህንጻ ፡ ያኔ አደይ አበባ
ያኔ ኢትዮጵያ ዛሬ ክልል
እኔም እንደ ጣይቱ ኢትዮጵያ ስል
እኔም እንደ ጣይቱ አዲስ አበባ ስል
አንተም እንደ ጣይቱ አዲስ አበባ ስትል
እንተም እንደ ጣይቱ ኢትዮጵያ ስትል
አመለካከታችን እንደ ጣይቱ ብጡል ይሆናል ማለት ነው
አይደለም ?
ጃዋርና በቀለ ገርባ ፊንፊኔ ሲሉስ ?

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sat Feb 16, 2019 6:08 pm

ያኔ ፡_ጥንት፡ አዲስ አባባ ፡ልዩ፡ መልክ፡ ነበራት ፡፡
እንደ፡ ዛሬው፡ ፈርሰው፡የማይታደሱ፡ ሕንጻዎች፡ ቢቆለሉባት፣ኢንቨስተር፡ የሚባሉ፡ ድንጋይ ፡ራሶች ፡ድንጋይ፡ በድንጋይ ፡ሳይክቡባት፤
መንደሮቹዋ ፡ሁላ፡ በእንጨት፡ ምሰሶና፡ በጭቃ ፡ተመርገው ፡የተሰሩ፡ ቢፈርሱም፡ ለመስራት፡ ቀናት፡ የማይፈጁ ፡ ክብ፡ ቤቶች ፤እርጭ እምጭ ያለች ፡አበባ ፡የሆነች፡ ከተማ ፡ነበረች፡፡
የገፈርሳ፡የቀበና፡ የቡልቡላ ፡ወንዞችና፡ ገባሪ፡ እና፡ ትናንሽ ፡ወንዞች ፡እዚህም ፡እዛም ፡ብቅ፡ ብቅ፡.የሚሉባት፡ ውብ፡. አዲስ ፣ውብ ፡አደይ፡ አበባ፡ ነበረች ፡፡
በአደይ፡ አዲስ አበባ ፡የሚኖሩት ፡ፍጡራን ፡እንደ ፡ዳርዊን፡ የጋላፓጎስ፡ ደሴት ፡ ፍጡራን፡ በብዛት፡ ተመሳሳይ ፡ናቸው ፡ብንል ፡ምንም፡ ስህተት ፡አይኖርም ፡፡
ያን፡ ጊዜ ፡አዲስ፡ አበባን፡ እንደ ፡ጋላፓጎስ ፡የሚያጠናት፡ የሚመራመርባት፡ ሐገራዊ፡ ፍጡር፡ ባለመኖሩ ፡ብዙም፡ ባንበሳጭም፤ ዛሬ ፡ግን ፡በመኪና፡ ለዛውም ፡በተሰባበረ ፡መኪና፡ ጭስና ፡ የሰይጣኖች፡ መዳቀሊያ ፡በሚመስሉ፡ የተዘጉ ፡ቪላ ፡ቤቶች ፡እና ፡እንደ፡ ባቢሎን ፡ግምብ ፡ከኪሎሜትር፡ በላይ፡ በሚርቁ ፡የሰይጣኖች፡ መደነሻ፡ በሚመስሉ፡ ፎቆች፡ መልኩዋ፡ እጅጉን፡ ተቀይሮ፡ እንመለከታለን ፡፡
ስልጣኔ ፡እንበለው ?
ስልጣኔን.፡ እኛ ፡ኢትዮጵያውያን ፡ከውጭ፡ እንማር ?
ምናለን ፡ደሳሳው፡ ክቡ ፡ጎጆእችን ፡ ?
ምናለን ፡ ብርጩማ ?
ምን ፡አለን፡ የመደብ ፡መቀመጫው?

ዛሬ ፡ከየት፡ ላግኘው፡ የሚያስብል፡ ባህላዊ ፡እቃችን፡ የቤት፡ አሰራር፡ ስልታችን፡ ሁላ ፡የትም፡ ተወርውሮ ፡ፎቅ፡ በፎቅ ፡እንደ ፡ኒዎርክ፡ ከተማ!
ዋ ፡አዲስ አበባ !!
ለዚህም፡ ነው ፡ጥቅሙ፡ ጥቅማ፡ ጥቅሙ ፡ እሴቱ ፡የሚባለው፡፡
ሕዝብን ፡የማይጠቅም፡ ነገር ፡ግን ፡ግለሰቦችን፡ በከንቱ፡ የሚያሳብጥ፡፡
ዋ፡ አዲስ አበባ !

የታሉ የአዲስ አበባ ሸረሪቶች?
የታሉ የአዲስ አበባ ጉንዳኖች?
የታሉ እነዛ ድንቅዬ የአዲስ አበባ ቢራቢሮውች ?
የታሉ እነዛ የአዲስ አበባ ብርቅዬ ወፎች ?
የታሉ እነዛ የአዲስ አበባ ርግቦች ፡ ያ ቃና ያለው ዜማቸው ?
የታሉ እነዛ የአዲስ አበባ ትክንትኮች?
እረ ስንቱ?
ከየት እናምጣቸው ከየት እንውለዳቸው ?
ዋ አዲስ አበባ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun Feb 17, 2019 3:51 pm

እስቲ እንጠያየቅ

የሎንዶን ከተማ እንዴት ተመሰረተች ? የፕራግ ከተማ እንዴት ተመሰረተች ? የሞስኮ ከተማ እንዴት ተመሰረተች?
ይህንን እንድጽፍ ያስገደደኝ የሆነ ግለሰብ በሆነ ካናል የልቡን ሲናገር ሰምቼው ነው፡፡
አሌክሳንዲርያ እንዴት ተመሰረተች?
እነዚህ ከላይ የጠቀስኩዋቸው ከተሞች እንደ አደይ አበባ እዛም እዚህም ብቅ ብቅ ያሉ ከተሞች አልነበሩም፡፡
ለነዚህ ከተሞች ከተማቸው እንዴትም ትመስረት ታሪካቸው ነው ቱሪስት መሳቢያም ነው፡፡
የኛዎች ግን የሚገርሙ ናቸው
አዲስ አበባ እሴቱዋም ጥቅሙዋም በመላው የኢትዮጵያ ልጆች ስራ የተከማቸው ነው ስለሆነም የምንመኘው እንደ ነገር ብቻ ይሆናል
መልካም አስተዳደር ፡፡
ምናልባት ለዚህ ግለሰብ ከልቡ እና በልጅነት ስሜት ሆኖ አዲስ አበባን ከመግለጽ የከተሞች አመሰራረት እንዴት እንደሆነ ቢያነብና ቢያጠና አዲስ አበባ እንዴት እንደተመሰረተች ሊገባው ይችላል ብዬ ስለማምን ነው፡፡
አዲስ አበባ በኢትዮጵያ ልጆች ነው የተመሰረተችው ፡፡ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተካፍለውባታል ፡፡
የአዲስ አበባ ምስረታ ከዓለም ታላላቅ ከተሞች የሚለያት በቅርብ ጊዜ መመስረቱዋ ሲሆን የሚያስደንቃት ደግሞ በዚህ በአጭር ዘመን ውስጥ ከለንደንና ከሞስኮ የምትወዳደር ከተማ መሆንዋ ነው ፡፡
አዲስ አበባ እንደዚህ እንድትሆን ያደረጉዋት የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው ፡፡ መፈናቀል መስፈር የመሳሰሉት ነገሮች ከከተማ ምስረታ ጋር የተያያዙ ለመሆናቸው ይህ ግለሰብ ሳይረዳው ቀርቶ አይደለም ፡፡
ገባርነት የሰለቸው የፊውዳል ኢትዮጵያ ገበሬ ወደ አዲስ አበባ መፍለሱ የሚያስደንቅ ነገር አልነበረም፡፡
ለመሆኑ ገባር ( ገባሮ) የሚለው ቃል ከየት መጣ?
ለመሆኑ ጅማ እንዴት ተመሰረተች ? ጎንደርስ፡ እክሱምስ ?
ጅማ በቅኝ አገዛዝ ነው የተመሰረተችው ?
ጎንደር በቅኝ አገዛዝ ነው የተመሰረተችው?
የጅማ አመሰራረትና የአዲስ አበባ አመሰራረት ልዩነቱ ምንድነው ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቢተወደድ1 » Mon Feb 18, 2019 1:44 pm

በስሜት የሚነዱና ጊዜ ስልጣን የሰጣቸው እንደፈለጉት ይለፈልፉብናል፡፡
የኢትዮጵያዊነት ስሜት እንጂ ሊመራን የሚገባው ያካባቢ ዘረኝነት መሆን አልነበረበትም፡፡
መቆየት ደጉ ብዙ ያሳየናል፡፡
እኛ እንኳን ስደት ላይ ሆነን በማናቀው አገር የሕዝባቸውን ጥቅም ከነሱ እኩል እየተካልፈልን፤
ወደ አገራችን ፖለጢቃ ስንመጣ ይሄን ዘር አስወጣው የሱ መሬት እይደለም ገለመሌ እንላለን
ዘር እኮ ለእህል እንጂ ለሰው ልጅ የተሰጠ መለያ አልነበረም፡፡
ከተማን ለመቆርቆርማ አስመራንም ራስ አሉላ አባ ነጋ ነበሩ የቆረቆሩዋት፤ እሁን እንዲህ ........
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 407
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Mon Feb 18, 2019 7:15 pm

የተማሩ ናቸው የምንላቸው፡ የተማንርን ነን የሚሉት ፡ግለሰቦች በዚህ በዓለማችን ከተሞች እንዴት እንደተመሰረቱ ሳይገባቸው ቀርቶ አይደለም፡፡
ነገሩን ያነሳሁት እንደው ለጨዋታ ያህል ነው ፡፡
ታሪክን መመራመር እና የሰው ዘር መጥላት የተለያዩ ነገሮች ናቸው
ሎንዶን ስትመሰረት ሺ አልቆ ሺ ተገፍቶ ነው ፡፡ሞስኮ ስትመሰረት ሺ አልቆ ሺ ተገፍቶ ነው
ጅማ አይናችን ላይ ያላቸው ከተማ ስትመሰረት ሺ አልቆ ሺ ተገፍቶ ነው
እነ ጃዋር ይህንን ሳያውቁ ነው ለማለት አያስደፍርም ነገር ግን የተጠናወታቸው የሰው ዘር ጥላቻ ነው ለማለት ግን ያስደፍራል፡፡

የቀጠለ ፡
የኦርቶዶክስ እምነት
መጀመሪያ የኦርቶዶክስ ክርስትና ከፕሮቴስታንት የሚለየው በአንድ ትልቅ ጉዳይ ነው፡፡
ፕሮቴስታንቲዝም በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ላይ የተመረኮዘ ስብከትና ጸሎት ሲያደርግ
ኦርቶዶክስና ካቶሊዝም ግን የራሳቸው የቤተ ክርስቲያን መገልገያ ቁዋንቁዋ አላቸው ፡ ግእዝና ላቲን ፡፡ በካቶሊዝም ላቲን እምብዛም እንደ ኢትዮጵያ ርቶዶክስ አይደለም ቢሆንም ቫቲካን ፓፓሱ ሲሰብኩ መስማች ይቻላል ፡፡
በተለይ የኦርቶዶክስ ክርስትና በኢትዮጵያ ፡ ከኢስተርን ኦርቶዶክስ ማለትም ከራሺያና ከሰርቢያ እንዲሁም ከግሪክ ኦርቶዶክስ ክርስትና በመለየት የራሱ የሆነ እና ራሱን የቻለ፡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሌላ በተጨማሪ ፈጣሪን ማገልገያ ቁዋንቁዋ አለው ይህም የግእዝ ቁዋንቁዋ ከዛም የቅዱስ ያሬድ መዝሙር ነው

ኩራ ኢትዮጵያዊ ሁላ፡ ኩራ ወገኔ ሁላ፡ ዛሬ በጎሳ እና በሰው ዘር ጥላቻ የሚነፋው አሉባልታን እዛ ወርውረህ ደረትህን ንፋ፡፡
እኔ ፈላስፋውበቅዱስ ያሬድ እኮራለሁ ይህንን ስል ግን ከወያኔ ጋር ምንም ጉዳይ የለኝም ከትግራይ ሕዝብ ጋር ግን የአንድ ሳንቲም ግልባጭ ነኝ፡፡ ፡፡
ምክንያቱም ያሬድ ከሞዛርት የማይተናነስ ኮምፖኒስት በመሆኑ ፡፡
አቦይ ስብሃት ነጋ ግን ኦርቶዶክስን ሰባበርነው ሲል ቅዱስ ያሬድን የት ረስቶት እንደሆነ ጊዜ ይጠይቀዋል ፡፡

እነ ጃዋር የኦርቶድክስን ክርስትና የመገልገያ ቁዋንቁዋ ለመተርጎም ብቃት ይኖራቸው ይሆን ?

ታዲያ ታሪክን ሳይመረምሩ እንደው ዘራፍ ማለቱ የሰው ዘር ጥላቻ !!
መጽሓፍ ቅዱስን ማርቲን ሉተር በጀርመን ፡ ከዛም ኦነሲሞስ ነሲብ በኢትዮጵያ ወደ ኦሮምኛ ለመተርጎም በቅተዋል
መጽሐፍ ቅዱስን በተፈለገው ቁዋንቁዋ መተርጎም ይቻላል ነገር ግን የያሬድን ፡የቅዱስ ያሬድን ዜማ እንዴት አድርጎ ወደ የትኛው ቁዋንቁዋ መተርጎም ይቻላል?
እነ ጃዋር .....ለዚህ መላ ምት ካላቸው ፡
ሕዝቡን ከእምነቱ በጦርና በእዳፍኔ ማላቀቅ ወይም
ታሪክን አጥንቶ የሚሆን መፍትሄ መፈለግ

ፈላስፋው ይህንን ሲል እነ ጃዋርና ... ይህንን ኢትዮጵያዊነት እንደ ኢትዮጵያዊነት ቆጥረውት ነው ወይስ እንደ ጥላቻ የሚለው ጥያቄ ስለመጣበት ነው
እነ ጃዋር ስለዚህ ጉዳይ ምን ማለት ይችሉ ይሆን ?
ጃዋር ለመሆኑ ስምህ ከየት ነው የመጣ ነው?
ዳውድ ከየት የመጣ ስም ነው?
ቁርዓን የሚቀራው በየትኛው ቁዋንቁዋ ነው ?

ይቀጥላል አዲስ አበቦች መጤ ናቸው የሚለው ቃል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Mon Feb 18, 2019 8:01 pm

ዘረኛ የሚለውን ቃል ብሄርተኛ በሚለው ብንቀይረው አይሻልም?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Feb 21, 2019 3:19 pm

ዘረኛ እና ብሄርኛ

የደንቃራ ዶሮ ወይም የጦስ ዶሮ የሚለው ለዚህ ጥሩ መልስ ይሆናል
ወሰራ ዶሮ ወይም ገብስማ ዶሮ ወይም ነጭ ዶሮ ወይም ጥቁር ዶሮ የሆነ ዶሮ መርጦ ለደንቃራ ማረድ የተለመደ ነው ባህሉም ልማዱም ኢትዮጵያ ተወልዶ ላደገ የተደበቀ ነገር አይደለም

ስለ ከተማ ምስረታ ለማውራት ስትፈልግ
ስለ ሐይማኖት ማውራት ስትፈልግ ወይም ስለ ኢትዮጵያ ምስረታ ለማውራት ስትፈልግ
አክስቲቪስቶች የሚባሉት የሆነ የደንቃራ ዶሮ ( scapegoat) የት እንዳለ መፈለግ ከሆነ ዓላማቸው ሰንብቶአል

በነገራችን ላይ ከራስ አሊ ጋርም ሆነ ከቴዎድሮስ ፡ከዮሃንስ ጋርም ሆነ ከምኒልክ ጋር የተሰለፈውና ኢትዮጵያን ለመገንባት የዘመተው ተመሳስሎ ተዋህዶ ይኖር የኢትዮጵያ ህዝብ ነው ፡፡

ራስ መኮንን ጉግሳ ፡ ረስ ጎበና ፡ የመሰሳሉ ራሶች የተፈጠሩት እንዲሁ ከሰማይ አልነበረም ፡፡

ለምን ይሆን እነ ጃዋር እና ጸጋዬ አራርሳ የመሳሰሉት እነዚህን ግለሰቦች መጥቀስ የማይፈልጉት፡ ከነዚህ የኦሮሞ ተወላጆች ጀኔራሎች ጋር ተሰልፎ የነበረው የኦሮሞ ሕዝብስ ለምን አይጠቀስም ?


ለምን ይሆን በነጃዋር እና በነ ጸጋዬ እራርሳ ታሪክ ውስጥ የራስ አሊ ታሪክ የማይነሳው ?

ለዚህም ነው ብሄረኝነት የሚለው ቃል ወደ ዘረኝነት፡ ጎጠኝነት፡ ጎሰኝነት ከዛም ትራይባሊዝም ወደ ሚለው ቃል የሚመራን
አያት፡ ቅድመ አያቶቻችን እንደ እሁን ዘመን ትውልድ፡ ትራይባሊስት አልነበሩም ለምሳሌ ከምኒሊክ በፊት ራስ አሊ ቢጠቀሱ የኢትዮጵያ አንድነት የሁላችንም የታሪክ መፍትሄ ለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡
ራስ አሊ የራስ ጉግሳ ልጅ ናቸው ራስ ጉግሳ በደብረ ታቦር ( ጎንደር) መናገሻቸውን ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ነበሩ

ለምን ስለ ራስ ጉግሳ፡ ለምን ስለ ራስ አሊ ማውራት አላስፈለገም ?
ለምን የኢትዮጵያ ታሪክ ሁልጊዜ ከምኒሊክ ይጀምራል?
እኩልነትና ነጻነት ሌላ ፡የደንቃራ ዶሮ ፍለጋ ሌላ ፡፡ የታሪክ አተላ መሆን ሌላ ?

በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥት ኢትዮጵያን ለመመስረት የተላለቀው በዛሬይቱዋ ኢትዮጵያ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ በሙሉ ነው ፡፡
ጅማ በለው አዲስ አበባ፡ ሐረር በለው ጎንደር ባድሜ በለው ለቀምት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነው የተካፈለበት
መሪው ማነው ?የሚለው ጥያቄ ሌላ ጥያቄ ነው ፡፡

ዛሬ ለሁሉችንም ነጻነትና እኩልነት የምንመኝባት ሐገር ለመመስረት ቅንብሩን የጀመርው መሪ ምኒሊክ ነው ፡፡
ለምን ምኒሊክ ሆነ ለምን ተፈሪ ሆነ የሚለው ጥያቄ ሌላ ጥያቄ ነው፡፡

ለምን ናፖሊየን ሆነ ፡ ወይም ለምን ጆርጅ ዋሽንግተን ሆነ ዓይነት ጥያቄ የደንቃራ ዶሮ ፍለጋ አጭሩ ጎዳና ነው፡፡

ለምን ዘረኝነት ?

የደንቃራ ዶሮ ከመፈለግ ይልቅ ለመሆኑ የንጉስ አገዛዝ በዚች ምድር ላይ ምን ይመስል ነበር የሚለውን ጥያቄ እንዴት ይመልሱት ይሆን ?

በቀላሉ የአባ ጅፋር ታሪክ እንዴ ይመስል ነበር ?

የኢትዮጵያ ተማሪዎች ትግል ሲጀመር ፡ ሌላውን ነገር ሁላ ትተን ፡
ጭቆና በዛ ፡
ብዝበዛ በዛ በማለት ነበር የኢትዮጵያ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ተማሪዎች ጋር ሆኖ የተነሳው ፡
በአጭሩ ነጻነት እኩልነት ነበር ጥያቄው ፡፡ የማንነት ጥያቄ ወይም የብሄር ጥያቄ አለነበረም አውቶቡሱን ሁላ የሰባበረው፡፡
የሐይለስላሴ አገዛዝ ከወደቀ በሁዋላ በደርግ አገዛዝ የቀይ ሽብር ተፋላሚ የሆነው ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነበር
ገዳይ ኢትዮጵያዊ ሙዋች ኢትዮጵያዊ ፡
ገዳይ ኦሮሞ ሙዋች ኦሮሞ፡
ገዳይ አማራ ሙዋች አማራ ፡
ገዳይ ትግራይ ሙዋች ትግራይ ፡
ገዳይ ጉራጌ ሙዋች ጉራጌ እያለ ኢትዮጵያዊ ገዳይ ሙዋች ኢትዮጵያዊ የሆነበት ስርዓት ነበር ፡፡

ከዚህ ሞትና ልቅሶ በሁዋላ ነው በሶሺያሊዝም መመሪያ መሰረት የተጸነሰው የሐሳብ ልዩነት የነበረውን እንዳልነበረ ያደረገው
ተማሪዎች በትንንሽ ቃላት ሲነታረኩ፡ ልዩነት ሲመጣ መሸሸጊያው ብሄር ሆነ

በሓሳብ ሲለያዩ መሸሸጊያው ብሄር
ሲሰርቁ መሸሸጊያው ብሄር
ሲገሉ መሸሸጊያው ብሄር
ሲገርፉ መሸሸጊያው ብሄር
ይህ ነው ትራይባሊዝም የሚባለው ሌላም አገላለጽ አለው ይህንን እዚህ ለመጥቀስ ፈላስፋው አይፈልግም
ይህ ትራይባሊዝም ደግሞ በጥቂት ግለሰቦች ተነሳስቶ እንደ እሳት መቀጣጠሉ የትራይባሊስት ፖለቲካ ዋናው መለያ ምልክት ነው


ይነስም ይብዛም ራስ አሊ ኢትዮጵያን አልመሩም? ራስ ጉግሳ ደብረ ታቦር መናገሻ ከተማቸው አልነበረም?
ከራስ አሊ በፊት ሌላ ታሪክ ይኖረን ይሆን ?
ይህ እንግዲህ ከመሳፍንት አገዛዝ በሁዋላ ነበር፡፡
ራስ ጉግሳ ፡ ደጃት ቁቤ ፡ ደጃት ፋሪስ ፡ ደጃች መርሶ ፡ ደጃት ብሩ ጎሹ ፡ ራስ አሊ፡ ብሩ አሊጋዝ

እይገርሙም እነዚህ ስሞች ?
ልብ አድርጎ እነዚህ ስሞች ከቴዎድሮስ በፊት በራስ አሉላ ዘመን የነበሩ ናችው


የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ጆጆ » Thu Feb 21, 2019 4:20 pm

to me ADDIS remains as ADDIS before .no question about it but Addis in general its in side oromo zone .let it be .the capital city of Ethiopia can be the capital city of oromo .no problem .and there for what all benefits and happening in Addis to all of Ethiopians . in the first place all priority's must given to the residence of the city .the city has its quality ,ts development ,as international cities ,like London , Berlin ,or Paris as well new-york city .no question about it ADDIS IS an old city and well known all over the world . now if OROMO region seek Addis development concern me let them do batter ,but Addis is this days very expensive if they can afford it no one is against the idea .when we talk about new master plan is not very clear like now what is done in legatafo after 10 years sleeping for the so called illegal action .city developed with the interest of the people to the people by the people .other ways every seasonal moment each BoSS came say i demolished this area and i feel its anamorphoses and replace it in any form other then there is unclear strategy to bring people in battle which is BAD .ADDIS REMAINS AS ADDIS EVER last NO change is needed of its liability . this beloved city is good enough . for every and any body who can afforded to live in ..HaNDS UP:
ጆጆ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Oct 06, 2003 2:19 am

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri Feb 22, 2019 7:57 pm

ጆጆ ወንድሜ
አንደን ከተማ በአንድ ሐገር ለመመረት አንድን ቦታ ወይም አካባቢ ከጁፒተር ወይም ከጨረቃ ማምጣት አይቻልም ፡፡
ታሪክ ቢዞርበት ኖሮ ከተማችን አንኮበር ፡ ወይም ደብረ ብርሃን ወይም መናገሻ ወይም ጎንደር ወይም መቀሌ ነበር፡፡
ሁሉም ቦታ ተሞክሮእል ነገር ግን ጊዜና ሰአቱ ተገጣጥሞ አዲስ አበባ በዛሬዬዋ የኦሮሚያ ክልል ውስጥ ለመሆን በቅታለች፡፡

ታሪክን ወደ ሁዋላ መጎተት አይቻልም ይህንን አለመቻሉን የማያውቁ ምሁራን ነን የሚሉ ካሉ ወረቀታቸውን ለሽንት ቤት መጥረጊያ ቢጠቀሙበት መልካም ነው ፡ መማር ማለት ማበጣበጥ ማለት አይደለምና
ታሪክ ይመርመር ፡ የሚያሳፍረን ታሪክ የለም እኮ ፡ ያ ወረረ ፡ ያ ቤት አቃጠለ እያሉ የደንቃራ ዶሮ ከመፈለግ ወይም እሱ ነው እሱ ነው እሱ ነው ከማለት እኛም እንደዛው ነን ብሎ መተማመኑ ታሪካዊ ሂደት ነው ፡፡
አዲስ አበባ ላይ ለታጋዮች ሐውልት ይቁም ከተባለ ? ይቁም፡፡
ለራስ አሊም ፡ ለራስ አሊም ጦረኖችም ይቁም
ለሳህለስላሴ ፡ ለሳህለስላሴ ጦረኖችም ይቁም
ለምኒሊክ ጀኔራሎችም ይቁም ማንም የሚከለክል የለም

ለአንዱ ኢትዮጵያዊ ሐውልት ለሌላው ኢትዮጵያዊ አፈር ! ግላዊ የሳይኮሎጂካል ችግርን ማስተንፈሻ ይሆናል እንጂ ለሐገር ግንባታ የሚሆን አመለካከትም አስተያየትም አይሆንም ፡፡


እርስ በርስ የሚጣረሱ የትራይባሊስት ፖለቲካ እየረጩ አንዱ ሌላውን የደንቃራ ዶሮ የጦስ ዶሮ ለማድረግ የሚፈልግ ካለ ፖለቲካል ሳይሆን ችግሩ ሳይኮሎጂካል መሆን ይኖርበታል ፡፡
በመጀመሪያ የአዲስ አዲስ አበባ ታሪክ ከምኒሊክ በፊት የተጀመረ ታሪክ ነው ፡
በኢትዮጵያ ሁለት ነገስታት አንዱ በእንኮበር ሌላው በጎንደር ከዛም በየጁ በተመሳሳይ ወቅት ብቅ ያሉበት ዘመን እንደነበረ ታሪክ ይነግረናል ፡፡
በእንኮበርና በየጁ መካከል ያለውን ርቀት ለማጤን ሸዋንና ወሎን ማጤን ያስፈልጋል ፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ ምስረታ ሁልጊዜ የሚጠራው ምኒሊክ ነው ፡፡ ታሪኩ ግን ከበስተሁዋላው ሌላ መስመር የተከተለ ታሪክ ነው ፡፡
ከዛ በፊት ግን እስቲ አንድ ሁለት ጥያቄ ልጠይቅ ?
ሳህለስላሴ ንጉሰ ሸዋ እንኮበርን ከተማው አድርጎ ሲቀመጥ ለምን ወደ ሸገር ብቅ ብሎ በሸገር ሕዝቦች ላይ ችግር ፈጠረ ?
ከዛስ ለምን ወደ ከተማው ወደ አንኮበር ተመለሰ?
ሳህለ ስላሴ ንጉሰ ሸዋ ይከተሉት የነበሩት የጦር ተዋጊዎች እነማን ነበሩ ?
አንድ ከተማ ሲመሰረት ሺ አልቆ ሺ ተሰዶ ሸ ተማግዶ ነው እንጂ ከዩኒቨርስ ተወርውሮ ምድር ላይ የሚቆም የምድር አካል አልነበረም፡፡
የደብረሊባኖስ ገዳም ከአዲስ አበባ ምስረታ በፊት እዛ ምን ያደርግ ነበር ?
የራጉዔል ቤተ ክርስቲያን እንጦጦ ላይ ነበር ከምኒሊክ በፊት ምን ያደርግ ነበር?
የዋሻው ሚክኤል የካ ጋራ ላይ ከምኒሊክ በፊት ምን ይሰራ ነበር ?
አባ ባህሬ ባሌ ምን ሊሰሩ ወረዱ ?

እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ዋናው ነጥብ በረራ በለው ፡ ፊንፊኔ በለው ፡
ታሪካችን የጋራችን ነው፡ የተላለቁት ፡ እንንገስ ብለው ሲደባደቡ የነበሩት ፡ ከተማ የመሰረቱት ፡ በሶሺያል ፡ ፖለቲካ ፡ በንግዱ ተመሰጣጥረው ይኖሩ የነበሩት በዛሬዋ ኢትዮጵያ የምንኖረው የኢትዮጵያ ልጆች አባቶች፡ አያቶች፡ ቅድመ አያቶች ና የቅም ቅም አያቶች ነበሩ

አንድነታችንና ልዩነታችን አበጣብጦናል ፡ አጣልቶናል ከዚህ በመማር ፍቅርን በመመስረት በእኩልነት እንደወንድማማች ለመተያየት የማንችልበት መንገድ አይኖርም ሊኖርም አይችልም ፡፡ የምንገኘው 21ኛው ክፍለዘመን ላይ መስሎኝ ?
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Mon Feb 25, 2019 6:47 pm

መተማመን ያቅተናል አብሮ መኖራችን ያለም የነበረም አይመስለንም ፡፡
እንደው ተራርቀን እንደ ቻይና ግምብ በድምበር ተለያይተን የምንኖር ይመስለናል ምክንያትቱም በቁዋንቁዋ ስለምንለያይ ፡፡
ታሪክ እንደዛ አይደለም ፡፡ ቁዋንቁዋችን የተለያየ ቢሆንም ባህላችንና እምነታችን የተለያየ ቢሆንም ያስተሳሰረን ነገር እንዳለ ለማወቅ ግን አንድ ያልቻልንበት ነገር አለ፡፡
የማናውቀው ምስጢር አለ ፡፡
የተማረ ይግደለኝ እንደሚባለው የተማረው ወገናችን ነው እኛን በመግደል ላይ እና በማለያየት ላይ የሚገኘው
ኦሮሚያ ብሎ ሲገነጥለን አያት ቅድመ አያቶችናን ግን ተገንጥለው ለመኖር ፍላጎቱም ምኞቱም አልነበራቸውም ፡፡ ጊዜውም አይፈቅድላቸውም ነበር፡፡
ትግራይ ብሎ ሲገነጥለን ቅድመ አያቶቻችን ግን ራሳቸውን ገንጥለው ለመኖር ፍላጎቱም ምኞቱም አለነበራቸውም ጊዜውም አይፈቅድላቸውም ነበር፡፡
አማራ ብሎ ልግንጠል ሲል ቅድመ አያቶቻችን ግን ራሳቸውን ገንጠለው ለመኖር ፍላጎቱም ምኞቱም አልነበራቸውም ጊዜውም አይፈቅድላቸውም ነበር ፡፡
ሱማሌውም አፋሩም ሁሉም የኢትዮጵያ ሕብረተ ሰብ ተገንጥዬ ድምበር ከልዬ ልኖር የሚል ፍላጎቱም ምኞቱም ጊዜውም አልነበረውም ፡፡
ቅድመ አያቶቻችን ወዴትም በሚለው መመሪያ መሰረት ነበር ኑሮእቸውን ያቀኑ የነበረው ፡ ከዛ የሆነ ቦታ ላይ ሲገጣጠሙ ተፋልመው ወይም ተፋቅረው ነበር ሐገረ ኢትዮጵያን ያበቁን ፡ ወገን ለይተው ይፋለሙና ከዛ ደግሞ አንድ ሆነው ወዴትም በሚለው መመሪያ መሰረት አንድ ሆነው ይጉዋዙ ነበር

ለምን የተማረው የተማረረው ምሁር እንደዚህ ያለ ነገር እንደ ቅዠት ይታየዋል ? የሚለው ጉዳይ ነው ፈላስፋውን ፍልስፍና ውስጥ የከተተው ፡፡
1. የተማረው የተማረረው ምሁር የሚያነበው መጽሐፍ እንግሊዘኛ መጽሃፍ በመሆኑ ፡፡ ባህሉንና እምነቱን፡ የአያት ቅድመ አያት ታሪኩን ከማወቅ ይልቅ ፈረንጅ የጻፈውን ስለሚሸመድድ ፡ ፈረንጅ አምላኩ በመሆኑ ፡፡
በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ አዲስ አበባ ታሪክ ልመለስ
አብዛኞቹ መጽሐፎች በከተማችን ጉዳይ በእንግሊዘኛ ወይም ከራሺያኛ ወደ እንግሊዘኛ የተተረጎሙ መጽሐፎች በማንበብ የመነጩ ናቸው ፡፡
ማለትም ኢማም ( ግራኝ) መሐመድን የተከተለ የፈረንጅ ጸሐፊ ባይንኖርም ወይም ፖርቲጊሶች ከብዙ በአጭሩ ቢኖሩበትም የሳህለስላሴ ፡ የምኒሊክ እና የራስ አሊ የቴዎድሮስ እና የዮሐንስ ዘመነ መንግስቶች በእንግሊዝ ቆንስላዎች ተከታታይነት በጽሁፍ የቀረቡ ለመሆኑ ማስረጃዎች መጥቀስ ይቻላል፡፡
እዚህ ላይ ነው ፈላስፋው
ልዩነታችን እና አንድነታችን ለዘላለም ይኑር የሚለው
ከነዚህ ጸሐፊዎች ውጭ የተማረውና የተማረረው ልሂቁ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም ለማወቅም የሚችልበት አንድም መንገድ አይኖርም ምክንያቱም የማሰብ ችሎታው እንደ ሰይጣን ቤት የተዘጋ በመሆኑ
ለምሳሌ በግጦሽ ሳር ግጭት የተነሳ ምን ያህል የከፋ አምባ ጉዋሮ እንደሚነሳና ከዛም ሁለት መንደሮች ለጦርነት እንደሚዘጋጁ ለመግለጽ ፈረንጆች ምን ጽፈዋል ብሎ በየላይብራሪው መጽሐፍ ከመፈለግ በስተቀር አመዛዝኖ የራስን መላ ምት መሰንዘር ግን እንደ ሰማይ የራቃባቸው የሐገሬ ልሂቃን ብዛታቸው እኔን ፈላስፋውን ሳይከፋኝ ነገር ግን አክራሪ ትራይባሊስት መሆናቸው ነው የሚከረፋኝ ፡፡
በአንድ ግጦሽ መሬት ላይ ሁለት የተለያዩ ሰዎች ሊጣሉ ይችላሉ
1. የአንድ ሐገር ሰዎች የሆኑ ፡ለምሳሌ አማራና አማራ ፡ ኦሮሞና ኦሮሞ ፡ትግራይና ትግራይ ...
2. አማራና ኦሮሞ ፡ ትግራይና አማራ ፡ ጉራጌና ኦሮሞ ..... በሁለቱም ሁኔታዎች የሚጣሉት የሰው ልጆች ለመሆናቸው ምንም የሚካድ ነገር የለውም ነገር ግን የሁለተኛው ጠብ ስንመለከት ግን ሌላ መልክ ይዞ ረቀቅ ባለ መልኩ ሊጉዋዝ የሚችል የጠብ ዓይነት መሆኑን እንነረዳለን ፡፡
እዚህ ላይ ነው እንግዲህ የፈረንጅን መጽሐፍ ፍለጋ ለመሄድ የሚያዳግተው ፡፡
የትኛውንም የፈረንጅ ላይብራሪ ቢያገላብጡት ይህንን ጠብ አስመልክቶ የሚገኝ አንዳችም ነገር አይኖርም የለምም፡፡
ፍቅርንም አስመልክቶ የተጻፈ ነገር የትም አይገኝም፡፡
ይህንን ሰላምና ጦር አስመልከተን የሐገራችን ሕዝቦች ካልቸርና የጦር አደረጃጀት ብንመለከት እና ብንተነትን ልክ አያት ቅድመ አያቶቻችን እንደነገሩን ማለት ነው የዛሬይቱዋ ኢትዮጵያ እንዴት እንደተመሰረተች ለማወቅ አዳጋች አይሆንም፡፡
የዛሬይቱዋ ኢትዮጵያ የተመሰረተቸው፡ የዛሬይቱዋ አዲስ አበባ የተመሰረተቸው በሁለት ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ ድምበርተኞችና ወንድማማቾች ሕዝቦች መካከል በተደረገ ፍቅርና ፍልሚያ ምክንያት ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም ፡፡
ታሪኩ እንግዲህ እንደዚህ ነው
ሶሻሊዝም በነ ማኦ ትሴቱንግ እና በነ ማርክስ መጻህፍት
ትራይባሊዝም በኮሊኒያልዝም ዘመን ሚሊተሪ አታሼ ጸሐፊዎች


ለመሆኑ ከእንኮበር እስከ አዲስ አበባ ያለው ርቀት ምን ያህል ነው ?
ከጅማ እስከ አዲስ አበባ ያለውስ ርቀት ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 2 guests