አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Wed Feb 27, 2019 10:32 pm

የተማረው የተማረረው ልሂቅ የፈረንጅ መጽሐፎቹን ከሸመደደ በሁዋላ እዋቂ የሆነ ስለሚመስለው እንካ ሰላምታውን በተማሪዎች የትግል ዘመን መጀመሩ ለሁሉም እውቅ ነው ፡፡
ወደ አማርኛው ጽሁፍ ስንመጣ ደግሞ ሌላው የባሰ ነገር መፈጠሩን ለመናገር ብዙ አያዳግትም
አለቃ ታየ የጻፉት አባ ባህሬይ የጻፉት እየተባለ በተማረው በተማረረው ሊሂቅ አካባቢ ሌላው እንካ ሰላምታ ተጡዋጡፎ የነጻ አውጭ ድርጅቶች እና በብሄር የተደራጁ ፓርቲዎች ማቆጥቆጥ ጀመሩ
ምሁር ይመራመራል እንጂ ይበጣበጣል እንዴ ? ይሄ ችግር ነው ጥራዝ ነጠቅ ልሂቃንን ለመፍጠር ያስቻለው ሁኔታ
ምሁር ለሰብአዊ መብት ይከራከራል እንጂ የሰዎችን መብት ረጋጭ ይሆናል ?
ምሁር ለዲሞክራሲ ይከራከራል እንጂ የዲሞክራሲን መብት አፋኝ ይሆናል ?
ለመሆኑ ሰብአዊ መብት ማለት ምን ማለት ነው የአንድ ብሄር መብት ማለት ይሆን ?
ዲሞክራሲ ማለት ሰብአዊ መብት ማለት ነው እና ይህም ዲሞክራሲ የሚባለው ነገር የአንድ ብሄር ሰብ መብት ማለት ይሆን ?
እንግዲህ የፈረንጁና የአማርኛው የታሪክ መጻህፍት ጥራዝ ነጠቅ የሆነውን ልሂቅ ለመፍጠር እንደቻሉ ለማስረዳት በጣም ቀላል ነው
ጥራዝ ነጠቁ ልሂቅ እንዴት ተፈጠረ ? የሚለው ጥያቄ ሳይኮሎጂካል በመሆኑ ፈላስፋው እዚህ ዓምድ ላይ ማንሳት አይፈልግም
ጥቅማ ጥቅሙ የሚለው ቃል ዲሞክራዊያዊ የሆነ እና ሰብአዊ መብትን ያልደፈረ እና ያልረገጠ እንዳይሆን እንዴት መደረግ ይኖርበታል ለሚለው መፍትሄ ምን ይሆን ?
ብዙ አስተያየቶች በዚህ ጉዳይ ተሰጥተዋል
ፈላስፋውን የማይጥመው አንድ ነገር አለ፡፡
እስከ ዛሬ አዲስ አበባ በማን ጉልበት በማን እውቀት እዚህ ያለችበት ደረጃ ደረሰች የሚለው ነው ፡፡
እኔ ፈላስፋው እስከ ዛሬ ድረስ መላው የኢትዮጵያ ልጆች ለዚህች ሐገር ጉልበታቸውን ደማቸውን እውቀታቸውን አፍሰዋል ፡፡
ከገፈርሳ የሚመጣውን የውሃ ቱቦ ለመዘርጋት ፡ መላው የኢትዮጵያ ልጆች ተረባርበዋል
የአዲስ አበባን መንገድ ለመስራት መላው የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉም ተረባርበዋል
የመብራት ምሰሶ ለማቆም ጉራጌው ፡ አማራው ትግራዩ ኦሮሞው ሁሉም ተረባርቦአል
ትምህርትቤቱን ለመስራት ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተረባርበዋል

ታዲያ ጥቅማ ጥቅሙ የሚለው ቃል እዚህ ምን አመጣው?
ሌላው ደግሞ ወደ አዲስ አበባ ከሁሉም አቅጣጫ የሚገባው የማገዶ ማለትም እንጨትና ቅጠል፡ የቤት መስሪያው ጭድና ሳሩ ሁላ ከየት ይሆን የሚመጣው ?
ቄጤማው አሪቲው በዓሉን የሚያደምቀው ሁላ ከየት ይሆን የሚመጣው
ወደ አዲስ አበባ ከሁሉም አቅጣጫ በየዓመት በዓሉ የሚገባው በሬ በግ ፍየል ዶሮ እንቁላል እረ ስንቱ ከየት ይሆን የሚመጣው ?
በየካ ገበያ ብቻ የበሬና የበግ ንግድ ከመላው ኢትዮጵያ ነው የሚመጣው ማለት ይቻላል ለዛውም ከ ከወሎ ሳይቀር ማለት ይቻላል
መርካቶን እዛው እናስቀምጠው
ለመሆኑ ደሴ ከአዲስ አበባ ስንት ኪሎ ሜትር ይርቃል ? በሬና በግ ይዞ ለመምጣት
ከደሴ እስከ አዲስ አበባ ስንት የተለያዩ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ይኖራሉ ይገኛል ?
ይህ ሁላ ሲሆን ፡፡ ይህንን ሁላ ድርጊት የአዲስ አበባ ሕዝብ ያለምንም ጥያቄ እምኖ ተቀብሎት ሲኖር ዛሬ እንዴት እንደዚህ ያለ ነገር ድንገት ብልጭ ሊል በቃ የሚለው ጥያቄ ፈላስፋውን ካፈላሰፉት ጉዳዮች ዋነኛው ነው ፡፡

ለመሆኑ የአዲስ አበባ የነዳጅ ጉልበት የሆነው የባህርዛፍ ከየት ነው የሚመጣው? የአዲስ አበባ ተራሮች በባህር ዛፍ ደን የተከለሉ መሆናችውን የማያውቅ ሰው ይኖር ይሆን ?
ለመሆኑ ባህር ዛፍ ከየት መጣ ?
እምዬ ምኒሊክ

አዲስ አበባ ከተቆረቆረች ጀምሮ ለመላው የኢትዮጵያ ልጆች የደም ስር ቢኖር አንድ ነገር ነው ባህርዛፍ ፡፡
1. ከማገዶነቱ አልፎ በመላው የአዲስ አበባ አካባቢ የሚገኙ ቤቶች የተሰሩት በባህርዛፍ ነው
2. ባህርዛፍ የሜንቶል ኮንቴንቱ ለሕክምና ፈረንጆች ሲጠቀሙበት፡ እኛም በወንዛችን በሐገራችን ባህር ዛፍን ቀቅለን እየታጠንን ኢንፍሉዌንዛና ኮመን ኮልድ የመሳሰሉ በሽታዎችን ለመከላከል እንጠቀምበታለን
3. ትክንትክና ጉንዳን ቤታችን ገብቶ ችግር እንዳይፈጥርብን ለመከላከል በባህርዛፍ ሽታ እናስወግደዋለን

ለመሆኑ ከአዲስ አበባ ( ከዛሬው የአድዋ ድልድይ ከጥንቱ የቀበና ድልድይ ጀምሮ ) እስከ አድዋ ድረስ ስንት ኪሎ ሜትር ይሆናል ?
ከአድዋ ድልድይ እስከ አድዋ ድረስ ስንት የተለያዩ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ይኖራሉ ?
አንድነታችንና ልዩነታችን ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ጆጆ » Thu Feb 28, 2019 5:44 pm

thank you felasfaw
now again we approach in the same level which is good .we talk about now Addis.the capital city of Ethiopia and beyond that Africa centre.this city was in the SHEWA kefele hager .shewa most residence ware mixed and still mixed most probably Amehara is more in number .when we drive in all direction most densely populated area belong to mixed people like Gurage ,welayta ,like kembata oromo and amhara .Shewa was this . now WEYANE he divided shewa in two three oromo amahra beher beherseboch .and center amhara behirdar oromo adama beherbehroch hawassa .and yet at the beginig addis remain as region (14 kilele )before and stay as capital city of Ethiopia . latter in 1997 ec under the state government inside oromo region and latter now before he left to mekele one year or two year ago Addis belong to direct under oromo region even as the capital city of them called as finfine .this very complicated disease system of MELESE ZENAWI .bring this consequence.shame on him this bustard boy (sorry to say it though insulting its not my ar) .he do it anxiolytic and purposelessly to give home work as such for our battle now ....the man is Dade .good to know ,.......what we must do now its so easy .we don't quarrel for interrogation. ADDIS BOYS we should unite and make organization it is important this days this organization is nothing but in order for presentation to protecting the city to remain as whole to belong of Ethiopians. as free of the any administration of regions. means Addis stand as example of city Berlin city Hamburg like city pairs like city New york even for that matter cap town .this means ADDIS back to the origin.and we all have peace .for development of Addis are concerned all region (kilel )if there is a good fortune to became from Addis all region can participate it . the city Mayer can be for that matter from any region who batter know Addis and of course with the election of the city duellers. i hope with break news we understand more now .take care .peace.
ጆጆ
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 152
Joined: Mon Oct 06, 2003 2:19 am

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri Mar 01, 2019 6:52 pm

መልካም ጆጆ

የማንነት ጥያቄ
ብዙ እያጨቃጨቀ የሚገኘው ይህ የማንነት ጥያቄ ነው ፡፡
ነገሩ እያጨቃጨቀ እያወዛገበ መሄዱን የሚያውቁት ጥራዝ ነጠቅ ምሁራን ለነገሩ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ በቴልቬዥን መስኮት ብቅ እያሉ ችግሩን እያቀጣጠሉት ይገኛሉ ፡፡
በዚህ በማንንት ጥያቄ ከአንዱ የቴለቪዥን መስኮት ወደ ሌላው የቴሎቪዥን መስኮት እየፈለሱ የፈለጉትን ይቀዳሉ ይዘባርቃሉ ፡፡ ወገናቸው
በፍልሰት ከቦታ ቦታ ፡ ከሐገሩ ፡ ከወንዙ ፡ ወዲያና ወዲህ ከነቤተ ሰቡ ከነሕጻናቱ ሲንከራተት እያዩ በቲቪ መስኮት የሚሰጡት አተካራ ትክክል ለመሆኑ ሊያሳምኑን ፡ እውቀታቸው ከዩኒቨርስ አልፎ ሌላኛው ዩኒቨርስ ላይ የደረሰ መሆኑን ሊያስረዱን ይሞክራሉ፡፡
ለመሆኑ ፍልሰተ ኢትዮጵያ እንዴት ተነሳ ?
ምንም አዲስ ምክንያት የለውም የጥራዝ ነጠቆች ልሂቃን ከታህታይ ምስቅልቅል ( ኢንፊሪየር ኮምፕሌክስ ) ለመነሳቱ በቂ ማስረጃዎች አሉ ፡፡
ከታህታይ ምስቅልቅል የተነሳ ፡ረኮግኔሽን ለማግኘት የሚደረገው የሳይኮሎጂካል ችግር ዋናው ምክንያት ለመሆኑ ብዙም መሄድ አያስፈልግም ፡፡

ቀላል ምሳሌ ለመጥቀስ የአዲስ አበባ ልጆች ቁዋንቁዋ ቀላል ምሳሌ ነው ፡፡
ለምሳሌ፡
እናትህን ል... ልህ ቢል አንድ የአዲስ አበባ ልጅ ዘር መርጦ ማንነትን መርጦ ሳይሆን ቁዋንቁዋው በመሆኑ ነው ፡፡
ይህንን እናትህን ል... ልህ የሚሉት ደግሞ ሁሉም የአዲስ አበባ ልጆች ናቸው ፡፡
እዚህ ላይ ነው ችግሩ በዚህ ስድብ የሚያለቅስ አለ በዚህ ስድብ ተናዶ ቦክስ የሚጨብጥ አለ ይህንን ስድብ ሲሰማ መልሶ የሚሳደብ አለ፡፡

ይሄ ችግር ፈላስፋው በቅርብ ጊዜ በተከታተለው የቲቪ የመስኮት ቀደዳ ( የጥራዝ ነጠቆች ልሂቃን ቀደዳ) የአዲስ አባን ልጆች ስድብ እና ድርጊት እንደ ዘረኝነት እንደ ጎጠኝነት ተጠቅሶ በእንድ ግለሰብ መነገሩ አሳዝኖት ነው ይህንን ዓምድ ለመጻፍ የተነሳሳው

አውሮፓውያንና አሜሪካኖች ስድተኖችን እንደት እንደሚከፋፈሉ በተቸገሩበት ወቅት ከዛም አልፎ በፖለቲካው መስክ አምባ ጉዋሮ በፈጠሩበት ወቅት በኢትዮጵያ እንደዚህ ያለ ነገር መነሳቱ ምን ይባላል ? አ
አውሮፓውያን ስደተኖችን ለመከፋፈል ስትራቴጂና ታክቲክ በማውጣት ችግሩን ለማቃለል ሲሞክሩ ጥራዝ ነጠቆች ልሂቃን በለቀቁት ስቱፒድ አስተሳሰብ የሚፈልሰው ኢትዮጵያዊ ከአንዱ የኢትዮጵያ ግዛት ወደ ሌላው የኢትዮጵያ ግዛት ፡ ለመንግስት ልመና በማቅረብ ፡ሐገሬ ኢትዮጵያ ወንዜ ኢትዮጵያ በማለት ነው ፡፡

በአውሮፓና በአሜሪካ የፈለሰው ስደተኛ የመኖሪያ ፈቃድ ከተሰጠው ሲፈልግ ሎንዶን ፡ ሳይፈልግ በርሊን ፡ ሳይፈልግ ባርሲሎና ፡ ሳይፈልግ ፓሪስ ሳይፈልግ ሊስቦን ሳይፈልግ አምስተርዳም ፡ የአሜሪካኑ ሲፈልግ መሪላንድ ሳይፈልግ ዲሲ ሳይፈልግ ሎስአንጀለስ ሳይፈልግ ካሊፎርኒያ ሳይፈልግ ሚኖሶታ ሳይፈልግ ጆርጂያ እያለ ሲኖር ፡ለዛውም በአሜሪካ የሚኖር ኢትዮጵያዊ እንደፈለገው ስራ ፍለጋ በየትኛውም የአሜሪካ ከተሞች ሲምነሸነሽ የአውሮፓው ስደተኛ በአውሮፓ ከተማ ሲምነሸነሽ ፡
አዲስ አበባ የኛ ነች ፡ ያ የኛ ነው ፡ ይሄ የኛ ነው በሚል በጥራዝ ነጠቅ ልሂቃን በተነሳው የሚዘበራረቅ እና እርስ በራሱ የሚቃረን ሐሳብ በዚህ በሰለጠነው ዘመናችን የሰው ልጅ በወንዙ ፡ በሐገሩ መኖሪያ አጥቶ ሲንከራተት መስማቱ እጅግ በጣም የሚያሳዝን ነው ፡፡
እኔ ፈላስፋው በማንነት ጥያቄ ሳይሆን በሰው ልጅነት ጥያቄ ፡ መቀሌ የሁሉም ናት ፡ ባህርዳር የሁሉም ናት ፡አዳማ የሁሉም ናት ፡ደሴ የሁሉም ናት ድሬደዋ የሁሉም ናት ፡የኢትዮጵያ ከተሞች የኢትዮጵያ ልጆች ከተሞች ናቸው ብዬ ነው የምደመድመው ፡፡
ለዚህ የፈላስፋው ድምደማ የዛም ፓርቲ መሪ ሁን የዛም ነጻ አውጭ ድርጅት ሊቀመንበር ሁን ሰባዊ ግዴታ አለብህ ፡፡
የማንነት ጥያቄ ፈላስፋው እንደተከታተለው የሰው ልጆችን መብት የጣሰ መጥፎ የሚባል የጥራዝ ነጠቆች ስቱፒድ አስተሳሰብ ነው
ስለሆነም የኢትዮጵያ ጥራዝ ነጠቅ ልሂቃን በሰብዓዊ መብት ረገጣ ለሕግ መቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
በማንነት ጥያቄ ድምበር ከተፈጠረ
በማንነት ጥያቄ ሕዝብ ከፈለሰ
በማንነት ጥያቄ ጥይት ከጮኸ
በማንነት ጥያቄ መፈላለጥ ከመጣ
በማንነት ጥያቄ አተካራና እንኪያ ሰላምታ መሰጣጠት ከተጀመረ


ከዚህ በላይ የሰው ልጅ መብት ረገጣ ምን አለ?

የኛ ጥራዝ ነጠቅ ልሂቃን የሰው ልጅ መብት ተረገጠ ሲባሉ ቃሉን በቃል ተርጉመው፡ አንድ ግለሰብ ሌላኛውን ግለሰብ መንገድ ላይ አጋድሞ በእግሩ ካረገጠ ሰብዓዊ መብት መርገጥ ማለት አይደለም ማለታቸው ይሆን ? ከማሳቅ አልፎ ባልማር ይሻለኛል የሚያስብል ነገር ነው ፡፡


ለአድዋ ዘመቻ ዝግጅት ምኒሊክ የኢትዮጵያን ሕዝብ" ወረኢሉ ጠብቀኝ" በማለት ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር
ወረኢሉ ወረ ኢሉ ማለት በምን ቁዋንቁዋ ነው ?
ወረ ኢሉ የሚኖሩትና በወረ ኢሉ አካባቢ የሚኖሩት ህዝቦች የትኞቹ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ናቸው ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun Mar 03, 2019 6:43 pm

ፌዴራሊዝም የጎሳ ፌዴራሊዝም[/u]
ለሐገራችን አይጠቅምም ፡፡ 27 ዓመታት ተመለከትነው አልጠቀመም ፡ አይጠቅምም፡፡
ይህንን መለወጥ መሳሳት አይደለም:: የሚያሳፍርም አይደለም ፡ መሸነፍም አይደለም::
ስለማይጠቅም አና በአንድ ብሄር ውስጥ የሚኖረውን የሌላውን ሕብረተሰብ መብት ረጋጭ ስለሆነ ብቻ ነው የሚለወጠው ፡፡
ይህ ፖለቲካ የጠቀመው ነገር ቢኖር ጽንፈኞችን ብቻ ነው ስለሆነም የማይፈለግ ፖለቲካ ነው በዚህ የፖለቲካ ፊልድ የተደነገገው ሕገ መንግስትም ትክክል ያልሆነ የዜጎችን መብት የሚጥስ ነው ፡፡
የዩቲዩብ ደፈጣ ተዋጊና ጥራዝ ነጠቁ ምሁር ይህንን ጸረ ሕዝብ የሆነ ስርዓትና ሕገ መንግስት በልዩ መልኩ በመጠቀም ሕዝብንና መሪዎችን ለማጣላት ወጥመድ አየሰራበት ይገኛል

የጎሳ ፌዴራሊዝም ያመጣው ነገር ቢኖር ጥርጣሬ ነው ፡ ፍልሰት ነው ፡ መፋጠጥን ነው ፡ በዚህ መሰረት ላይ የቆመው ሕገመንግስት ለሐገር ፡ ለወገን ፡ ለሕዝብ አለመጥቀሙን እያሳየ እያስመሰከረ ነው ፡፡ የሆነን የጎሳ ክፍል ላይ ስልጣን ላይ አቆይቶ ሕገ መንግስቱ ይሰራል ማለት ትክክል አይደለም ፡፡ ትክክለኛ ሕገ መንግስት ቢሆን ኖሮ አሁንም ለሕዝቦች ሰላምና መረጋጋትን በፈጠረ ነበር ፡፡ እዚህ ላይ እገሌ ነው እገሌ ነው ወይም ያ ብሄር ነው ያ ብሄር ነው የሚለው የቃላት ጨዋታ አይሰራም ሕዝቦች እየተበደሉ ነው የሚለው ነው ትልቁ ጨዋታ፡፡
ጣትን ግለሰቦች ላይ መቀሰር ለግል ጥቅም መሩዋሩዋጥ ነው እንጂ የፖለቲካ መስመር አይደለም
ለግል ጥቅም ሲባል የጎሳ ፌዴራሊዝም መደበቂያ ማድረግ ለሐገር አልጠቀመም አይጠቅምም
ለዚህም ምሳሌ
1. የቃላት ጨዋታ
ቃላት እየተሰነጣጠቁ መጣረቢያ ሆነዋል ፡ በኦሮምኛ የተነገረው ለትግርኛ ፡ በትግርኛ የተነገረው ለአማርኛ በእብድ ተርጉዋሚዎች ሆን ተብሎ ወይም በዩ ቲዩብ ደፈጣ ተዋጊዎች አተረጉዋጎሙ እንደ ውጫሌ ውል እየሆነ ሌላ ክስክስ ውስጥ እየከተተን ነው

2. የዩቲዩብ የደፈጣ ተዋጊዎች ስድቦች እና ጋጠ ወጥ አነጋገሮች ሌላው የጎሳን ፌዴራሊዝም ጥርጣሪ ውስጥ የሚከቱ ፡ በህዝቦች መካከል አለመጣጣምን የሚያስነሱ የደፈጣ ውጊያ ስልት ከሆኑ መሰንበታቸው ነው ፡፡ የሚገርመው የዩቲዩብ ቀባጣሪዎች ሳይሆኑ የሚያስገርመው እነሱን የሚመለከተው ተጠራጠሪ ወገን የቁጥሩ ብዛት አስጊና አደገኛ መሆኑ ነው ፡፡

3. የሐውልቶች በየቦታው መቆም ከአድዋ ድል በዓል በሁዋላ አዲስ የመጣው መላ ምት መሆኑ ፡፡ አንድ ሐውልት በየትኛውም ዓለም ሲቆም ሁለት ገጽታዎች ይዞ ነው. ጥሩና መጥፎ ፡በየትኛውም ሐገር የንጉስ ሐውልት ሲቆም ሁለት ጎኖቹን ይዞ ነው ፡፡ ነገር ግን የዚህ ንጉስ ታሪክ በትምህርት ሲሰጥ እነዚህን ሁለት ገጽታዎች ይዞ ካልሆነ የሐውልት መቆም ብቻ ትርጉም የለሽ ሆኖ ነው የሚቀረው ፡፡ ትምህርት ዋናው የሰው ልጅ መሰረቱ እና መግባቢያው ነው ፡፡
እውነተኛው የኢትዮጵያ ታሪክ በትምህርት ቤት መሰጠት ይገባዋል ፡፡ ያለፈ ነገር ያለፈ ነው ፡፡ ልክ ትናንት እንደተፈጸመ የሚያወሩ እና የሚቀባጥሩ ጥራዝ ነጠቅ ምሁራን ከዚህ ስራ ቢወገዱና ወደ ልማቱ ስራ ቢገቡ ይመረጣል ፡፡

አንስታይን ስለ ሶስተኛው ዓለም ጦርነት ሲጠየቅ የመለሰው መልስ የሚደነቅ ነው፡፡ ለኔ የሶስተኛው ዓለም ጦርነት ሳይሆን የአራተኛው ዓለም ጦርነት ነው ስጋቴ ያን ጊዜ ስዎች በድንጋይና በክትክታ ወይም በወይራ ዱላ መከታከት ይጀምራሉ ብሎአል፡ ( ተሻሽሎ የተተረጎመ ) ፡፡ ይህም ማለት
በጎሳ ፌዴራሊዝም ምክንያት የቆሙ ሐውልቶች መራመድ ጀምረው የሚከታከቱበት ዘመን እንዳይመጣ ነው ፈላስፋው ስጋቱ

አክቲቪስቶች ፡ የእክቲቪስቶች ስራ ሰላምን በህዝቦች መካከል መፍጠር እንጂ ሕዝቦችን ለማጋጨት ከሆነ የአክቲቪስት ስራ ሳይሆን የደፈጣ ውጊያ ስራ ነው ፡፡


በዋለልኝ መኮንን ዙሪያ ሲያቀነቅን የነበረ ተማሪ ዛሬ እንዴት ወደ ማንነት ጥያቄ ፊቱን አዞሮ ድምበር መካለል ጀመረ ?
ጭቆና በዛ መብቴ ተረገጠ ፡ እኩልነት ጠፋ ፡ ብሎ የተነሳ ተማሪ ዛሬ ከየት ተወለድኩ ፡ ከየት መጣሁ ወዴት ነው የምሄደው የሚለውን ጥያቄ ለማንሳት ተገደደ?

ዛሬም ምኒሊክ አለ እንዴ ያስብላል የአዲስ አበባ የትላንት ሁኔታ
የአድዋው አርበኛ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ከምኒሊክ ጋራ ገብቶ ሲቀድስ ፡
ምኒሊክ በመድፉ ጊዮርጊስ በፈረሱ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Wed Mar 13, 2019 5:43 pm

"የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነኝ "
ይህ አባባል ለፈለሳፋው የሚገባው ነገር ሆኖ አልተገኘም
"እኔ የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ ነኝ "፡፡ እየተደጋገመ የምሰማው ነገር በመሆኑ ነው ዛሬ ብቅ ያልኩት
ጠቅላይ ሚንስቴር ዓቢይ የሆነ ጥያቄ ቢጠየቅ " እኔ ዶክተር ነኝ "
ብርሃኑ ነጋ የሆነ ጥያቄ ቢጠየቅ " እኔ ፕሮፌሰር ነኝ "
መራራ ጉዲና የሆነ ጥያቄ ቢጠየቅ " እኔ ፕሮፌሰር ነኝ "
ደብረ ጽዮን የሆነ ጥያቄ ቢጠየቅ " እኔ የኤሌክትሪካል ዶክተር ነኝ " እንደማለት ይመስላል
ጃዋር በጤናው ነው " እኔ ምርጥ የሆንኩ የፖለቲካል ሳይንስ ምሩቅ ነኝ "" የሚለው ወይስ ትንሽ ችግር ቢጤ ይኖር ይሆን ?

ጃዋር ወንድሜ ፡
አያት ቅድመ አያቶችህ በማህበረ ገዳ ሲስተም ውስጥ እንዳንተ ተምረናል እያሉ በመቀበጣር አልነበረም ሕዝባቸውን ይመሩ የነበሩት
መማር አስፈላጊ እንዳልሆነ የምትገነዘበው አያት ቅድመ አያቶቻችን ሳይማሩ ሳይመራመሩ ደመ ነፍሳቸው በሚነግራቸውና በሚያስተምራቸው ብቻ ሕዝብን መምራት ሐገርን ማስተዳደር የቻሉ ፍጡራን ነበሩ፡፡
ለአንድ ሕዝብ ቀና ነገር ለመስራት የግድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሩቅ መሆን እኮ አያስፈልግም ፡፡
መልካም ነገር ለመስራት በቀላሉ ደመነፍስህ የሚልህን ብትከተል መልካም ይመስለኛል ይልሃል ፈላስፋው
በተረፈ ዛሬ እንደፈለገኝ እመራዋለሁ የምትለው ወጣት ( ቄሮ ) ነገ አንተን ራስህን እየጋለበ እንደሚነዳህ እኔ ፈላስፋው ምንም ጥርጥር የለኝም
በመጀመሪያ ወጣቶችን ለእንደዚህ ያለ ነገር ማሰለፍ ራሱ ሰብዓዊ መብትን መርገጥ ነው
እነ ዓቢይ እነ ለማ በመሆናቸው ወይም ፈላስፋው ሊጠቅሰው በማይፈልግ በሌላ ምክንያት እስከ አሁን በወጣቶቹ ላይ ምን ችግር አልተነሳም
ጃዋር በተረፈ አንተን እየጋለቡ እስከሚነዱህ ድረስ ትንሽ ወራት ልትቀጥል ትችል ይሆናል
ሌላው መንግስት በወጣቶቹ ላይ ለሚወሰድ እርምጃ ተጠያቂው ግን አንተው ራስህ መሆንህን አትዘንጋ
የወጣቶች በትምህርት መታነጽ
የወጣቶች በዲስፕሊን መታነጽ
የወጣቶች በእውቀት መበልጸግ ነበር ዋናው ቁም ነገር መሆን የሚገባው ፡፡
የአንተም " የፖለቲካል ሳይንስ" ምሩቅ የመሆን ድርሻው እንደዚህ ሆኖ ሳለ ወጣቶችን ለዓመጽ ነገ መጥራት እችላለሁ ብሎ መፎከር የትም እንደማያደርስ ቢገባህ መልካም ነው እልላለሁ
በተረፈ የአንተን የራስህን ልጆች እንደ ቄሮዎች አሰልፈህ ለዓመጽ እንደማታዘጋጅ ግልጽ ነው
የአንተን ልጆች በትምህርት ፡ በእውቀት ፡ በሌላውም እንዲያድጉ አድርገህ ሌላውን ወጣት ግን ለዓመጽ ስታዘጋጅ ትንሽ ስለ ፖለቲካል ሳይንስ ይገባህ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
በተረፈ ቀይ ሽብር የሚባል ነገር የለም እንጂ ልክ እንዳለፈው ትውልድ ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸም ላይ መሆንህን ስነግርህ ይገባህ ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
ለዲሞክራሲ ለመታገል ከፈለግህ ከወጣቱ ትውልድ ( ቄሮ ) ጋር ሳይሆን ከእኩዮችህ ጋር እንዳንተው ከተማሩት ጋር ቢሆን አይከፋም
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቢተወደድ1 » Fri Mar 15, 2019 3:03 pm

ይሄን ማን ይሆን ወስዶ ለቄሮዎቹ የሚያሳይልኝ? ከገባቸው፡፡

ቆቁ wrote:London has a diverse range of people and cultures, and more than 300 languages are spoken in the region.[54] Its estimated mid-2016 municipal population (corresponding to Greater London) was 8,787,892,[4] the most populous of any city in the European Union[55] and accounting for 13.4% of the UK population.[56] London's urban area is the second most populous in the EU, after Paris, with 9,787,426 inhabitants at the 2011 census.[57] The population within the London commuter belt is the most populous in the EU with 14,040,163 inhabitants in 2016.[note 4][3][58] London was the world's most populous city from c. 1831 to 1925.[59]
300 ቁዋንቁዋ ?
ለየትኛው ቁዋንቁዋ ነው የለንደን እሴት ? ጥቅማ ጥቅሙ
ፈላስፋው
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 407
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri Mar 15, 2019 9:28 pm

ቢትወደድ ይህ ብቻ መስሎህ ነው እንዴ ?
በለንደን የሚኖሩት መጤዎች ናቸው ቢሉህስ ?
እሺ ብለህ ደግሞ ለምሳሌ የተባበሩት መንግስታት የስራ ቁዋንቁዋ ምንድነው ብትል ደግሞ ምን ይሉ ይሆን?
እንግሊዘኛ በአፍሪካ
እንግሊዘኛ በእስያ
እንግሊዘኛ በአሜሪካ በመላው ዓለም ዋናው የመግባቢያ የዓለም ቁዋንቁዋ ነው
እንግሊዘኛን የኮሎኒያል ቁዋንቁዋ ነው አልናገርም የሚለው ማንም የዓለም ሕዝብ የለም
በየትምህርት ቤቱ ሁላ እንግሊዘኛ ዋናው የትምህርት መጀመሪያ እና መጨረሺያ ከሆነ ዘመናት አለፉ ፡፡

እዚህ ላይ ቁዋንቁዋ መግባቢያ ነው እንጂ የአንድን ብሄር መግለጫ አይደለም እኔ እንግሊዛዊ ከሆነ ሰው ጋር ስናገር ንግስት ኤልሳቤት የእንግሊዝ ንግስት ነች ብዬ በማሰብ ወይም በንግስት ቪክቶሪያ ዘመን እንግሊዞች ገብርዬንና ቴዎድሮስን ገደሉ ብዬ ወይም ሴባስቶፖል ተገነባ ብዬ ሳይሆን ከግለሰቡ ጋር በቀጥታ ለመግባባት ብዬ ብቻ ነው ፡፡

ምሳሌ የኦሮሞን የእማራን የሱማሌን ሕዝቦች አዲግራት ላይ ለገበያ ብታገናኛቸው እጃቸውን እና እግራቸውን በማወዛወዝ ጀምረው ከዓመት በሁዋላ በሆነ በአንድ ቁዋንቁዋ እንደሚገበያዩ ሙከራ ማድረግ አያስፈልግም ፡፡ በሆነ ቁውዋንቁዋ መግባባት ችለው በዚህ የንግድ ቦታ አንድን ቁዋንቁዋ የንግድ ቁዋንቁዋ አድርገው እንደሚፈጥሩ ያለምንም ጥርጥር ፈላስፋው ይናገራል፡

ምሳሌ 1. አዲግራት

በአዲግራት የሚዲካል ዶክትሬት ምረቃ በምረቃው ስርዓት ላይ ሲነገር የነበረው የአማርኛ ቁዋንቁዋ ነበር ፡ እና ምን ይጠበስ የሴም ቁውዋንቁዋ ነው ይሉ ይሆናል ፖለቲካል ሳይንቲስቶቹ ፡፡ ነገሩ ግን ሌላ ነው በአምቦ ወይም በሌሎች የኦሮሚያ ክልሎች ተመራቂዎች ቢኖሩ በበየትኛው ቁዋንቁዋ ምረቃው ሊነገር ነው ይሆናል ብለን ብንጠይቅስ ፡፡
ለዚህ መልሱ ቀላል ነው ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ኦሮምኛ ብቻ እንዲነገር የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በሙሉ የኦሮሚያ ተወላጆች መሆን ይኖርባቸዋል ማለት ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ቁዋንቁዋ መግባቢያ ሳይሆን ሌላ ጉዳይ ሆነ ማለት ይሆናል ፡ ይህንን ነው " ፖለቲካል ሳይንቲስቱ" ሊያስረዳን
የሚሞክረው
ፈላስፋው የማይዘነጋው ነገር አለ

ለመሆኑ ቁዋንቁዋችን ጠፋ ፡ ቁዋንቁዋችን ተበደለ ሲባል የነበረው ምኑ ላይ ይሆን ?
ጥንት ይነገሩ የነበሩት ቁዋንቁዎች ዛሬም በመላው ኢትዮጵያ ይነገራሉ እና የትኛው ቁዋንቁዋ ነው ዛሬ በኢትዮጵያ ቦታ የሌለው ?
ቢኖርስ በቅኝ ግዛት ምክንያት ወይስ በንግድ እና በማህበራዊ ግንኙተ ምክንያት ?
ቁዋንቁዋ ያድጋል ቁዋንቁዋ ይከስማል ሲባል የዲያሌክቲክስ ሕግ መሆኑን " የፖለቲካል ሳይንቲስቶቹ " አይዘነጉትም
ኦሮምኛ በመላው ኢትዮጵያ የመግባቢያ ቁዋንቁዋ እንዲሆን በጥቂቱ ለ50 ዓመታት ያህል በመላው ኢትዮጵያ ዋና ትምህርት ሆኖ መሰጠት ሊኖርበት ነው ፡፡ መልካም ነው ይላል ፈላስፋው


መጤ የሚለው ቃል
ለመሆኑ መጤ ያልሆነ ማነው ቢባል በዛው በቦታው የተወለደ እትብቱ የተቀበረ ብቻ ሊሆን ይችላል
ነገር ግን የፒያሳ ልጅ ለመርካቶ መጤ ነው የመርካቶው ለቄራው መጤ ነው እያልን ብናሰፋው የአድዋው ለእዲግራቱ መጤ ነው
የዳሞቱ ለማርቆስ መጤ ነው የወለጋው ለአርሲው መጤ ነው ፡፡ ታዲያ መጤ ማለት ምን ማለት ይሆን ? ይህንን ለማወቅ ደግሞ የግድ የምኒሊክ ታሪክ ላይ ሳይሆን ማተኮር የሚገባው ራሱ የገዳው ማህበራዊ ሲስተምን በጥሞና መመልከቱ ለፖለቲካል ሳይንቲስቶች ሳይጠቅም አይቀርም ብሎ ፈላስፋው ይገምታል

የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Wed Mar 20, 2019 10:12 pm

ተናግረናል ጣጥፈናል ከድጡ ወደማጡ እንዳይሆን ጮኸናል
1. የፖለቲካ ሂደት ፡ በፖለቲካ ሂደት ውስጥ የአስተስሰብ ልዩነት ሲፈጠር አንጀኛ መፈጠሩ አይቀሬ ነው ስለሆነም ቄሮዎች እንደዚህ ያለ አጣብቂኝ ውስጥ
ቢገቡ ተጠያቂው ማን ሊሆን ነው ?
2. ሕገ መንግስቱ ፡ ስለ ሕገ መንግስቱ ከማውራት በፊት በመጀመሪያ ኢትዮጵያዊነት መረጋገጥ አለበት ፡ ሕገ መንግስቱ መደበቂያ አይደለም፡
ሕገ መንግስቱ እንደ ሙሴ ሕግጋትም አይደለም፡፡ ሕገ መንግስቱ ይከበር፡ሕገ መንግስቱ ይከበር የሚለው በሙሉ የሚያመለክተው በሕገ መንግስቱ ውስጥ የተደበቀ ነገር እንዳለ ነው፡፡ ለምን ሕገ መንግስቱ ይሻሻል የሚልች ጩሀት እስከአሁን አይነሳም ?
3. የብሄር ፖለቲካ ፡ ሕገመንግስቱ በብሄር ላይ ያተኮረ በመሆኑ መለወጥ ይኖርበታል፡ ይህ የክልል ሕገ መንግስት እስከ አሁን ድረስ መፍትሄ በሐገርራችን ውስጥ አላመጣም፡፡ እስከ ዛሬ የታየው ጸጥታ ወይም ሰላም የሚመስል ነገር በጠመንጃ አፈ ሙዝ በመሆኑ እንደ መፍትሄ መቆጠር የሚገባው ነገር አይደለም
የሚታየው የሚሰማው ነገር
- በዬክልሉ የደምበሩ ሽኩቻ እና እልቂት ፤
- በየክልሉ ጥቅማ ጥቅም በሚባል ነገር መተላለቅ እና በመነታረክ ጊዜ ማውደም ፡
- የሰፈሩ ልጆች እንደ ፍለጠውና ቦምባርዲን በአጠናና በገጀራ መጠራረግ
- ሰው በግፍ መፈናቀል ፡ አናቱ ላይ ቤት ማፍረስ
- ሰው እንደ Migratory birds በደመ ነፍሱ መብረር
- ፍርሃት ፡ ድንጋጤ በምድረ ኢትዮጵያ
- ሽብር ቴረረሲም የጭፍን ማንን ከማን የማይነጥል ግድያ
የብሄር ፖለቲከኞች በተለይም አንዳንዶቹ ነጻ አውጭ የሚል የቅጥል ስም ያላቸው የሚያወሩት እና የሚያልሙት ሁላ ሕገ መንግስቱ ሕገመንግስቱ ሕገ መንግስቱ ብቻ ነው ሌላ ነገር የለም፡፡
ለምሳሌ
ትላንት ሰው በሽብርር ተገደለ ሕገ መንግስቱ መከበር አለበት
ትላንት ቤት በሰዎች ላይ ፈረሰ ሲባል ሕገ መንግስቱ ይከበር
ትላንት ክትክት በሆነ ድምበር ተፈጠረ ሲባል ሕገ መንግስቱ ይከበር
እንደዚህ ያለ ነገር ይቁም ይላል ፈላስፋ
የምን ሰውን ማጃጃል ነው
የምን ሰውን ማደነባበር ነው
ሕገ መንግስቱ አልሰራም አሁንም አይሰራም ወደፊትም አይሰራም
ትራይባሊዝም ማለት ኢትዮጵያዊነት አይደለም ፡ የክልል መንግስት የመጨረሻው ደረጃ መፋጀት ነው ከዛም ደግሞ በክልሉም ረግቶ የሚቆም አይደለም ፡፡ ይህንን ለማወቅ በ16ኛውን ክፍለ ዘመን ግራኝን መሐመድንን ተከትሎ የተፈጠረውን የኢትዮጵያ ታሪክ አጢኖ መመርመር ነው ፡፡
ያን ጊዜ መፍለስ ነበር ፡ ያን ጊዜ መለያየት ነበር

የኢትዮጵያ ታሪክ የዛም በለው የዚህም ወደ ሁዋላው የሚሽከረከር ጎማ አይደለም
ወደዛም ወደዚህም ተነከራተት ነገር ግን አንደ ነገር ግልጽ እንዲሆን ፈላስፋው አጥብቆ ይፈላሰፋል
ምኒሊክ ማረኝ የሚባልበት ዘመን ጊዜው ሩቅ አይደለም
አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነች
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነትት ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri Mar 22, 2019 5:14 pm

ኢትዮጵያ በምትባል ሐገር እያደር የማይሰማው ነገር የለም
ባለፈው "ፊንፊኔ" የሚባል ቃል አዲስ አበባን መተካት አለበት ተብሎ አንዴ በረራ ፡ ሌላ ጊዜ ሸገር ሌላ ጊዜ ደግሞ ሌላ......
ለመሆኑ ፊን አለ፡ ፊን ፊን አለ የሚለውን ቃል ብንወስድ በእርግጥ " ፊንፊኔ" አማርኛ ነው ወይስ ኦሮምኛ ? በማለት ፈላስፋው ጥያቄ ያስቀምጣል ፡፡

ይህንን ፈላስፋው ያነሳው ምክንያት ስለኖረው ነው ይላል ፈላስፋው
ሜቃ ብለህ ጠይቀው ካልመለሰ ነጋቲ ብለኸው ሂድ የሚል አለመግባቢያ አጠቃቀም ከበቀለ ገርባ ስለሰማሁ ነው
በእውነት ይህ ሰው ትክክል ነኝ ብሎ ያምን ይሆን ?

ስንት ነው ብሎ ሲጠይቅህ አማርኛ አልችልም በለው እንደማለት ሆኖብኝ እኔ ፈላስፋው የማልስቀው ስቅ ብዬ አለቀስኩ

ግለሰቡ ማለትም ልሂቅ የሚባለው ቁዋንቁዋ የሰው ልጆች መግባቢያ መሆኑን ረስቶ መጣረሻ ሲያድርገው በማየቴ ነው ያለቀስኩት
እስቲ ይህንን ምሳሌ ወስዳችሁ
በየትምርህት ቤቱ፡ በየዩኒቨርሲቲው ፡ በየስራው ቦታ እንዴት ነው ብላችሁ አስቡ
በነገራችን ግለሰቡ እንደዚህ አስቦ ይሆን ? በጣም ነው የሚያስለቅሰው ይላል ፈላስፋው
የሰው ልጅ እግርሩንና እጁን እያወናጨፈ፡ በጣቱ በዓይኑ እያጣቀሰ እንዳልተግባባና ከዛም ቁዋንቁዋን እንዳልፈጠረ ተዘንግቶ ዛሬ የሆነ ሰው ሲያነጋግርህ ቁዋንቁዋህን ካላወቀ ዘግተኽው ሂድ የሚል ዲስኩር የሚሰጥባት ሐገር ብትኖርር የኔዋ የፈላስፋው ሐገር ኢትዮጵያ መሆኑዋ ነው መሰለኝ ባልሳሳት ፡፡

አሺ አንድ የእንግሊዝ ቱሪስት ቢመጣ እንዴት ይሆን ሁኔታው ብሎ ፈላስፋው ይጠይቃል
Can you help me please ለሚለው ጥያቄ ነጋቲ ብለኸው ሂድ ማለቱ ይሆን ? ምክንያቱም ቁዋንቁዋህን ስላልተናገረ
ለምሳሌ በአይሮፕላን አደጋ ከደረሰባቸው ሰዎች መካከል ፈጣሪ ብሎ የሆኑ ሰዎች ተርፈው መንገድ አሳዩን፡ እርዳታ ስጡን ብለው በእንግሊዘኛ ወይም በአረብኛ ወይም በስዋሂልኛ በቻይንኛ ቢጠይቁ ነጋቲ ይሆን መልሱ ? ያሳዝናል ፡፡
ለአማርኛ ብቻ ይሆን ነጋቲ የሚለው መልሱ ለምን አኒ ኢምቤኩ አልሆነም ?
አዝናለሁ ለእንደዚህ ያሉ " ልሂቃን"
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Mar 23, 2019 6:37 pm

አማርኛ እንዴት ተስፋፋ?ኦሮምኛ በቀለ ገርባ በሚለው መንገድ ሊስፋፋ ይችላል?ቆቁ ኦሮምኛ ይችላል?ካልቻለስ ለመማር ተዘጋጅቷል?የአዲስ አበባ ህዝብ ኦሮምኛን ቢማር የኦሮሞ ኢሊቶችን ማስታገስ ይቻላል?የአዲስ አበባ ህዝብስ ኦሮምኛን መማር ይፈልጋል?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Mon Mar 25, 2019 6:46 pm

ዘርዓይ
ራሱ በአማርኛ እየቀደደ ሌላውን አማርኛ ወይም ሌላ ቁዋንቁዋ አትናገር በማለቱ ሰው ምን ይለኛል ብሎ አለማሰቡ ነው የሚገርመው ፡፡
ባለፈፈው ""ፊንፊኔን በተመለከተ "" በማለት ያነበበው መግለጫ በአማርኛ ነው፡፡
ለምን በአማርኛ ቀደደ ብለህ ብትጠይቅ ምን ይሆን መልሱ?
እንደ እስስት የሚለዋወጥ ባህርይ የጤነኛ ሰዎች ባህርይ እንዳልሆነ መቸም ይገባሃል ፡፡
ራሱ የፌዴራል መንግስቱ መመሪያዎችን የሚያወጣው በአማርኛ ነው ፡፡
ታዲያ የበቀለ ገርባ አባባል እኮ የሚሰጠውን መመሪያ ሁላ " ነጋቲ " ብላችሁ እለፉት እንደማለት እኮ ነው ፡፡
ስለሆነም መስማማት መግባባት የሚባል ነገር በኢትዮጵያ የለም አይኖርም ማለት ነው ፡፡

ከዚህ በፊት እንደጻፍኩት የሰው ልጅ እጁና እግሩን እያወናጨፈ መግባባት የቻለበት ዘመን ከዛም አልፎ ቁዋንቁዋ ፈጥሮ መግባባት የጀመረበት ታሪክ ነው ያለን በማለት ነበር ፡፡

ከዛም አልፎ አዲግራት ላይ የኦሮሞ ተናጋሪ፡ የአማርኛ ተናጋሪ ፡የትግሬኛ ተናጋሪ፡ የአፋርኛ ተናጋሪ፡... እንዲገበያዩ ብታደርግ ከዓመት በሁዋላ በሆነ ቁዋንቁዋ ተግባብተው ንግዱን ያጦፉት ነበር ነው የምልህ ፡፡
አዲስ ቁዋንቁዋ ፈጥረው ለመገበያየት ይበቁ ነበር ነው የምልህ

በነገራችን ላይ እንግሊዘኛ ተናገርን ብለን እንዘላብድም መግባባት ብቻ ነው የምንፈልገው ፡፡
ሕንድ ውስጥ እንግሊዘኛ ተነገረ ስለሆነም የኮሎኒያል ገለመሌ የሚል ሐሳብ የለም፡፡ መግባቢያ ነው፡፡ ቁዋንቁዋ መግባቢያ ብቻ ነው ሌላ ነገር አይደለም
ለምሳሌ የተባበሩት መንግስታት
በተባበሩት መንግስታት ውስጥ የሚገኙት መንግስታት የተለያየ ቁዋንቁዋ ነው የሚናገሩት በተባበሩት መንግስታት የሚነገሩት የስራ ቁዋንቁዋች በአስተርጉዋሚ ለሁሉም ሐገራት ሲተላለፉ እንመለከታለን ፡፡ የተባበሩት መንግስታትን አባላት ይህንን ቁዋንቁዋ በግድ ተማሩ በማለት ማንም አያስገድድም ብትማር ተማር ባትማር የራስህ ጉዳይ ነው ፡፡

በኢትዮጵያም ያለው ይህንኑ ይመስላል ባንልም ለገጠሩ ሕዝብ የሚነገረው ከሞላ ጎደል እንደ ተባበሩት መንግስታት ዓይነት ዘዴ ነው ፡፡
አንዱ የሰማውን ሌላው ማለት ነው ፡፡

ዘርዓይ
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሞላ ጎደል አንድም ቁዋንቁዋ የጠፋ እንደሌለ ማወቅ ይኖርብናል፡፡ የጠፋም ካለ ምክንያት ይኖረው ይሆናል፡፡
ወደ ሚቀጥለው ፍልስፍና ከመግባታችን በፊት
ኦሮምኛ አልጠፋም
ወደ ወሎ አካባቢ የተፈጠረው ሌላ ነገር ነው
የኦሮሞ ህዝብ እዛ ከሚኖረው ሕዝብ ጋር ተዋህዶ ስለኖረ ብቻ ነው
የቴዎድሮስ ጦር ለምሳሌ የራስ ዓሊ ጦር ነበር ከዛም በሙሉ የምኒሊክ ጦር ለመሆን በቃ ፡፡ እንደዛ እያለ ነው ታሪካችን ታሪክ የሆነው

ትላንት የሞት ታናሽ ወንድም ነው በማለት ፍልስፍናችንን እንቀጥል

1.እስከ አሁን ድረስ እንደሚታየው በአማርኛ የተነገረው ሁላ አብዛኛውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሞላ ጎደል እንደሚገባው ነው የሚታወቀው
ይህንን ማሻሻል ነው ለእድገታችን አፋጣኝ ምክንያት ወይስ ሌሎችን ቁዋንቁዎች እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲማር ማድረግ ?

2. ለምን ኦሮምኛ ብቻ ? ሱማሌኛ ፡ አፋርኛ ጉራጌኛ ፡ ትግሬኛ ...እያልን ብንቀጥልስ ?

3. ለምን ይሆን እነበቀለ ገርባ የኦሮምኛ ቁዋንቁዋ በሚመለከት እንደዚህ ያለ እሰጥ አገባ ውስጥ የሚገቡት ? ኦሮምኛ እሁንም በስፋት የሚነገረው የኢትዮጵያ ቁዋንቁዋ ነው ፡ አይደለም እንዴ ?

4. ቁዋንቁዋን መማር በዚህ በ21ኛ ክፍለ ዘመን እንዴት ? የሰው ልጅ ስንት ቁዋንቁዋ ሊማር ነው? ፡ በዚህስ ጊዜውን ማባከኑ ምን ይባላል ? እድለኛ የሆነ ፡ጎበዝ የሆነ አራት አምስት ቁዋንቁዋ መናገር ይችላል ለዛ ችግር የለም ፡፡

ይህ ፍልስፍና ነው
የሐገራችን ሁኔታ ወዴትና እንዴት እንደሚያመራ የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ወሳኙ
የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ምክክር » Tue Mar 26, 2019 4:28 am

ፈላሥፋው ሆይ
የአንድ አገር ቋንቋ እንደ አገሪቱ እድሜና ታሪክ ይገዝፋል ይበዛል፡፡
ኢትዮጵያ ታላቅና ታሪካዊ አገር ለመሆኗ አንዱ መገለጫው የቋንቋና ባህል
ምንጭ ለመሆኗ እንስማማለን፡፡ ብሔራዊ ቋንቋችን አማርኛ መባሉ ቀርቶ
ኢትዮጵያውኛ ቢባልስ? ከዚያ ሌሎች በሃገሪቱ በስፋት የሚነገሩትን ቋንቋዎች
ከብሄራዊ ው ቀጥሎ ማሰለፍ ነው ወይስ ምን ይሁን ነው ምትሉት፡፡
ችግር መዘብዘብ በዛ፡፡ መአት እንደ ነጋሪት መጎሰም.....፣ አንዱ የሌላዉን ማጥላላት
Be nice to yourself
ምክክር
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 402
Joined: Thu Jun 26, 2008 10:10 am
Location: Super Earth

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Wed Mar 27, 2019 10:05 pm

ምስክር ትክክል ነህ መግባቢያነቱ እንጂ መጠራጠሻነቱ አልገባኝም

1. ቁዋንቁዋ ባህርዛፍ አይደለም ፡ ሰው የሚያሳድገው ነገር አይደለም ፡ የሰው ልጅ ታሪኩ ወይም የታሪኩ ሂደት ነው ለቁዋንቁዋ እድገት ምክንያት የሚሆነው ፡ ፡
2. ለቁዋንቁዋና ለጥቅማ ጥቅም መጠራጠስ መነሻው ሕገመንግስቱ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦችን ችግር ውስጥ የዘፈቀው ይህ የትራይባል ፌዴራሊዝም ነው ፡፡ ሕገ መንግስቱ ለጠባቦች መቀባጠሪያ ሜዳ በመሆኑ ቁዋንቁዋና ጥቅማ ጥቅም የሚባሉት ነገሮች መጠራጠሻ ለመሆን በቅተዋል

3. ለምን ሕገመንግስቱ እንደማይሻሻል ነው ፈላስፋውን ግራ ያጋባው ፡ ስለ ዲሞክራሲ ከተወራ በመንግስት አውታሮች አካባቢና በአመራሮች ላይም ዲሞክራሲ የሚባለው ጉዳይ መታየት አለበት ፡፡ ሕገ መንግስትን ማሻሻል የዲሞክራቲክ መንገድ ነው ፡፡ለሐገራችንም መፍትሄው ይሄ ነው

4. ለምን ጠባቦች ስለ ሕገ መንግስቱ ብዙ ያወራሉ ፡ እዛ ረብሻ ሲነሳ ሕገ መንግስቱ ይከበር ፡ እዚህ ረብሻ ሲነሳ ሕገ መንግስቱ ይከበር የሚባለው ተራ አሉባልታ ፈላስፋውን አልገባውም ፡፡ ስለ ሕገመንግስቱ የሚያወሩ ጠባቦች ለምን ስለ መሻሻሉ በዲሞክራቲክ መንገድ ለመወያየት አይፈልጉም
ዲሞክራሲን የማያውቅ ዲሞክራሲን ማስተማር አይችልምና ይሆን ?
5. የሕገመንግስቱ በተጀቦኑ ቃላቶች የተወሳሰበ ነው ፡፡ ይህንንስ የፈጠረው ማንነው ፡ ለዚህ መጠራጠሻ የሆነውን ሕገመንግስት የፈጠሩ ግለሰቦች በዲሞክራቲክ መንገድ ለውይይት ቀርበው ማሻሻያ እንዲሰጡ ቢጠየቁስ ?

እነ ጀኔራል ተፈሪ ባንቲ እነ ደበላ ዲንሳ እነ አብዲሳ አጋ ፡ እነ ሜጀር ጀኔራል አበበ ገመዳን የምናውቃቸው በኢትዮጵያዊነታቸው ብቻ ነበር
ዛሬ የሆነ የኦሮሞ ተወላጅ ሲነሳ የኦሮሞ ድርጅት አባል ነው ፡
የሆነ የትግራይ ተወላጅ ሲም ሲነሳ የህወሃት አባል ነው ፡
የሆነ የአማራ ተወላጅ ስም ሲነሳ የአማራ ድርርጅት አባል ነው ....
ለጆሮ የሚቀፍ ለጭንቀት የሚዳርግ ሰውን በሰውነቱ ሳይሆን በብሄሩ እየፈረጁ መጠራጠስ
የሆነ ስራ ውስጥ የተቀጠረ ሰራተኛ ዘሩ እየተቆጠረ
የሆነ አመራር ውስጥ የተቀጠረ ሰራተኛ ዘሩ እየተቆጠረ
ዘር ቆጠራ በቤተ ክርስቲያን ፡
ዘር ቆጠራ በመስጊዱ
ዘር ቆጠራ እዛ ፡ ዘር ቆጠራ እዚህ
በየድርጅቱ ውስጥ ዘር ቆጠራ
ለምን ?
እንዴት እንደዚህ ያለ ያለ የዘር ለቀማ እና ቆጠራ ፖለቲካ ሊነሳ ቻለ ? የሚለው ጥያቄ ነው ፈላስፋውን ፍልስፍና ውስጥ የከተተው
ሁሉም አመራር ላይ የሚገኘ በሌላ አመራር ሊያላክክ ይሞክራል
በትግራይ መጠራጠስ
በአማራ መጠራጠስ
በኦሮሞ መጠራጠስ
እንዴት የመጠራጠስ ፖለቲካ ሊፈጠር ቻለ
የዘር ፖለቲካ ዲሞክራቲክ አይደለም ስለሆነም የዘር ፌዴራሊዝም ይወገድ ይላል ፈላስፋው ፡፡
እንደገና
የመልቲ ፓርቲ ሲስተም ብቻ ነው ለሐገራችን የሚጠቅማት
የምናየው የመጠራጠስ ፖለቲካ ትራይባሊዝም ስለሆነ ሊታሰብበት ይገባል
አያቶቻችን ይህንን ከኛ በአሁኑ ሰዓት ከምንገኘው ትውልድ በልጠው አስቀድመው ተገንዝበው አንድ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቅተዋል ይህን ሲያደርጉ ግን እርስ በራሳችን እንድንጠራጠስ ብለው አልነበረም፡፡

ሌላው ደግሞ ያለፍነው የቀይ ሽብርና የነጭ ሽብር በሌላ ሽብር እንዳይተካ ፈላስፋው ሊያሳስብ ይወዳል
አረንጉዋዴው ሽብር

የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Mar 28, 2019 9:08 pm

የአረንጉዋዴውን ሽብር ለጊዜው አቁሜ እስቲ ስለ አዲስ አበባ ልፈላሰፍ

1. ዓቢይም ስለ አዲስ አበባ እስክንድር ነጋም ስለ አዲስ አበባ ከዛም በሁለቱ መካከል በተነሳው ልዩነት የተነሱት ተንታኞች ምሁራን ጋዜጠኞች ፡ የሚዲያ ምላሰ ረዣዥሞች
2. እነ ጃዋር ፡ ጸጋዬ አራርሳ፡በቀለ ገርባ ፡ ዳውድ ኤቢሳ ስለ አዲስ አበባ ከዛም በአዲስ አበባ ነዋሪ ስለተነሳው ግራ መጋባት ፡ አለመረጋጋት ፡ አለመተማመን መፈጠር
3. የፌክ ቡክ እና የዩቲዩብ ምላሰ ረዛዥሞች ማሽቅበጥ ከዛም አልፎ ዘለፋና ስድብ
እነዚህን ሶስቱን ፈላስፋው በሶስት ዳርቻዎች ያስቀምጥና የሚቀጥለውን ይፈላሰፋል

የመልቲ ፓርቲ ሲይስተም ተጠናክሮ ሐገራችን ከጎሳ ፌዴራሊዝም እስክትላቀቅ ድረስ
አዲስ አበባ በፈረቃ ለምን ከንቲባ አይኖራትም?
1. አንድ ጊዜ ከኦሮሞ ፡ ሌላ ጊዜ ከአማራ ፡ ሌላ ጊዜ ከትግራይ ፡ ሌላ ጊዜ ከአፋር ፡ ሌላ ጊዜ ከደቡብ ፡ ሌላ ጊዜ ከሱማሌ እያለ እያለ ቢቀጥልስ ???
2. በችግር የሚፈናቀሉት ወገኖቻችን አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን ለምን ወደ ሌላ ከተሞች ለምሳሌ ባህርዳር ፡ መቀሌ ፡ ደብረ ብርሃን በመሄድ የመጠለያ ስፍራ የሚያገኙበት መንገድ አይከፈትም

አንድነታችን እና ልዩነታችን ለዘላለም ይኖራል
ፍቅር ያሸንፋል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sat Mar 30, 2019 8:57 pm

እኛ ጥሩ ብንሆን ኖሮ ሁሉም ነገር ጥሩ ነገር ይሆን ነበር

ችግር 1. ጋዜጠኞች የሚዲያ ሰዎች
ምን እንደሚፈልጉ ለማወቅ ያስቸግራል፡፡ በተለይ የውጭ የሚዲያ ሰዎች ለኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን መሪ ለመምረጥ እየተዘጋጁ ይመስላል ፡፡
ከደብረሊባኖስ ወይም ለ27 ዓመታት የቆረበ ወይም ከአንዋር መስጊድ የሚገኝ መሪ በመፈለግ ላይ የሚገኙ ይመስላል ፡፡
ግለሰብና መዋቅር ልዩነቱ የጠፋባቸው ይመስላል፡፡
ሌላው ደግሞ መሪ ለመሆን ብዙ ውጣ እና ውረድ መኖሩን መዘንጋት ደግሞ ሌላው የጋዜጠኝነት ችግር ነው
በሌላ በኩል ደግሞ የመንግስትን ጥንካሬ በቅጡ አለመገንዘብ ለብዙ መቀባጠር ሲዳርግ እየተሰማ ነው፡፡
የዘር ቆጠራው ደግሞ ሌላ ችግር ነው ፡፡


ችግር 2. አክቲቪስቶች
ማን ይህን ሹመት እንደሚሰጥ ፈላስፋው አይገባውም ፡ የመዘባረቅ መብት የአክቲቪስቶች መብት እንዴት ሊሆን ይችላል ? የመሳደብ መብት እንዴት የአክቲቪስቶች መብት ሊሆን ይችላል ? እክቲቪስትነንት በአፍጢሙ እየደፉ የሚገኙት የፌክ ኒውስ እና የዩቲብ ምላሰ ረዥሞች ናቸው
የመናገር የመሰብሰብ እና የመጻፍ መብት ግን አግባብ ነው፡፡ ምንድነው የሚነገረው ? ምንድነው የሚጻፈው?
ይህንን መብት አለማወቅ አዳማጩን ስሜታዊ በማድረጉ በሚላኩ መልክቶች ላይ ማንበብ ይቻላል ፡፡
ዘሎ ዘር ቆጠራ ከዛም ዘር ማጥላላት ብቻ ነው በየመልክቱ የሚነበበው
የዘር ጥላቻ በመልእክት ላይ ሲነሳ ወይም ሲገለጥ አክቲቪስቱ ይህንን እቁም በማለት ማገድ ሲገባው ሲንከተክት እና ሲስቅ ማየቱ በጣም የሚያሳዝን ነው ፡፡

ችግር 3. ጠባቦች
ጠባቦች ከአክቲቪስቶች ጋር ተደበላልቀዋል ፡ ጠባቦች ሲጠቡ ወገናችን ዘር ቆጠራ ውስጥ ነው ዘሎ የሚገባው ፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበባ ፡ "ፊንፊኔ" የሚለው ነገር ሕዝባችንን ግራ የሚያጋባ ነገር ነው እንደዚህ ያለ ነገር ሲሰማ አንባቢው ወይም ሰሚው ጆሮው ላይ የሚደውልበት ይኸው የዘር ጉዳይ ነው ፡፡ ይህም በመሆኑ ወገናችን ስሜታዊ እንዲሆን ተደርጎእል
መንግስት ጠባቦችን በቅጡ መለየት ይገባዋል ይህ ጠባብነት በቸልታ ከታለፈ ራሱ መንግስት ጠባብ ነው የሚል አመለካከት ስለሚኖር ጠባብነትን የመከላከሉ ጉዳይ በዝምታ መታየት አይንሮበትም ፡፡ በነገራችን ላይ " ፊንፊኔ" የሚለው ቃል ከየት እንደመጣ ታሪካዊ ትንተና ያፈልገዋል ፡ የፈጠራ ቃል ከሆነ በአስቸኩዋይ ከምድረ ኢትዮጵያ መወገድ ይኖርበታል ፡፡ ለመሆኑ ማን ነበር ሸገርን "ፊንፊኔ" ብሎ ይጠራት የነበረው ?

ችግር 4 የውጭ ዜግነት ያላቸው አክቲቪስቶችም ሆኑ የሚዲያ ሰዎች እዛው ውጭ ቢቀመጡ አይከፋም ፡ ምክንያቱም ሐገራችንን የሚመለከቱት ልክ እንደ ውጭው እንደ ሚኖሩባት ሐገር ነውና ፡ ለምሳሌ በአሜሪካ የሚኖሩ የሚዲያ ሰዎች የሐገራቸውን መሪ እንደ አሜሪካ መሪ ስለሆነ የሚመለከቱት እንጭጭና የዞረ ድምር የሚያሳዩ ትንታኔዎች እና መግለጫዎች ሲሰጡ ይታያሉ ፡፡
አሜሪካ ኮንስቲትውሽን በማይናወጥበት ማህበረ ስርዓት ላይ የምትገኝ ሐገር መሆኑዋን በመዘንጋት ኢትዮጵያ ሐገራችንን አሁን ባለችበት ሁኔታ ከአሜሪካ ጋር በማነጻጸር የሚደረገው ሙከራ ስህተት መሆኑ ማወቅ ይገባቸዋል

ከዛም
የትራይባል ፖለቲካ ከሐገራችን የሚወገድበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡
በተጨማሪም
የገዳ ማህበራዊ ሲስተም ከሌሎች ማህበራዊ ሲስተም ጋር ራሱን አደባልቆ የሚሰራበት መንገድ ቢጀመር አይከፋም
የትግራይ የአማራ የጉራጌ የኦሮሞ የመላው የኢትዮጵያ ብሄረ ሰብ ሽማግሌውች መልቲ የጋዳ ሲስተም ዓይነት እና የመልቲ ፓርቲ ሲስተም አደረጃጀት እንዲኖራቸው የሚያስፈልግበት ጊዜው አሁን ነው ፡፡
የጎሳ ፖለቲካ ለማንም አይጠቅምም የዞረ ድምር ነው ፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነትና አንድነት ለዘላለም ይኖራል
ፍቅር ያሸንፋል ( የሆነ የሚዲያ ሰው ፍቅር ያሸንፋል የሚባል ነገር አይሰራም ብሎ በመዘባረቅ የሰሚውን ቀልብ ሲስብ ፈላስፋው አዳምጦአል ) ፡፡ ጦርነት ያሸንፋል ብንል እና ስንከሳከስ ቢያይ ምን ይል ይሆን ብዬ ይህንን ሰው ማሰብ ጀመርኩ ፡፡ ምን ይሆን ይሆን ?

የጎሳ ፖለቲካ የለውጡ ዋና ችግር ነው
ይህንን የጎሳ ፖለቲካ ያመጡ ቡድኖች የፖለቲካ ፓርቲዎች ከራሳቸው ጋር ተነጋግረው የመልቲ ፓርቲ ሲስተም መመስረት ይገባቸዋል ይላል ፈላስፋው
ሐገራችን ብቻ የዚህ የጎሳ ፖለቲካ መሞከሪያ መሆን አይገባትም፡፡
ሕወሃት ከኦዴፓ ከአዴፓ ከሱማሌ ከአፋሩ ጋር ከሌላውም ጋር ተደበላልቆ መልቲ ኢትኒክ ፓርቲ መመስረት ይገባዋል ነው ፈላስፋው የሚለው
በጎሳ ፖለቲካ ደቂቃዎች ሰዓታቶች ወራቶች ዓመታቶች እየባከኑ ነውና ይታሰብበት
የነጻ አውጪ ድርጅቶች መፈራረስ ይኖርባቸዋል ምክንያቱም ከማን ነጻ ለመውጣት ነው ይህ ስም እንዲኖራቸው ያስፈለገው ?
በጎሳ የተደራጁ ፓርቲዎች ይህን ለውጥ ነውጥ እንዲሆን ያደረጉት እነሱ በመሆናቸው ሊያስቡበት ይገባል
ፈላስፋው በጎሳ ፖለቲካ የማያምነው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 5 guests

cron