አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Mar 30, 2019 10:30 pm

ቆቁ ፊንፊኔ የፈጠራ ሥም ከሆነ ከምድረ ገጽ መጥፋት አለበት ሲል ምን ማለቱ ነው ?ሥሞች ሁሉ ፈጠራ ናቸው እኮ!አዲስ አበባም ቢሆን የእቴጌ ጣይቱ ‘ፈጠራ’ነው።በነገራችን ላይ አብይም እኮ ፊንፊኔ ይላል!በተለይም ከድርጅቱ(ኦህዴድ) አባላት ጋር ሲነጋገር።ድሮ የኦሮሞ ጎሳዎች ፊንፊኔ የሚሉትን ቦታ እቴጌ ጣይቱ አዲስ አበባ አሉት።አዳማ ናዝሬት ቢሾፍቱ ደብረ ዘይት እንደተባለው ማለት ነው።
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1287
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri Apr 05, 2019 8:19 pm

ዘርዓይ ችግሩ ያለው ቃሉ ላይ እና በዶክተርር ነጋሶ ጊዳዳ የተሰጠው አስተያየት ላይ ነው፡፡

1. ፊን ፊን አለ የሚለው ቃል አማርኛ ይመስላል ( ስትጣላ ለምን ፊን ፊን ትላለህ ወይም የሆነ የውሃ ምንጭ ነገር ካየህ ፊን ፊን ይላል ትላለህ)

2. የዛሬይቱዋ አዲስ አበባን የሚያጠቃልለው የየካን የአቡዋሬን የኮልፌ የጉለሌ የገፈርሳ እያለ እየቀጠለ የሰፋ የበዛ የመንደሮች ጥርቅም ነው
"ፊንፊኔ" የሆነች ትንሽ መንደር ወይም ሰፈር ነች ማለት ይሆናል፡፡ ፊንፊኔ ያለቻት ራሱዋ ጣይቱ ብጡል ትሆን ?

3. ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፊንፊኔ የሚባል ነገር አለማወቃቸው ነው ፈላስፋውን ለፍልስፍና የዳረገው፡፡ ፊንፊኔን የሚያውቁ የተወሰኑ የያኔዋ የአዲስ አበባ ማለት የጉለሌ የየካ የእቡዋሬ ( አባ ዋሬ ) ፡ የቡልቡላ ... ነዋሪዎች ናቸው ፡፡ ከሌሎች ክፍሎች መጥተህ ይህንን ስም ለመጥራት የሚያስችል መንገድ ያኔ አልነበረም ፡፡ አዲስ አበባ ፊንፊኔ መሆንዋ እንዴት ታወቀ? ከአዲስ አበባ በፊት ፊንፊኔ የገበያ መናኸሪያ ነበረችወይ? ፊንፊኔ እሬቻ እንደነበረ ታሪክ ይነግረናል ወይ ? ለምን አዲስ አበባ የሚለው ስም በፊንፊኔ እንዲተካ አስፈለገ ? ፡፡ ጅማ ከተማ ነው አይደለም ? ሌሎች ከተሞች የሉም ነበር ወይ ? ከየት መጣ እንደዚህ ያለ ማእከላዊ ስም? የሚለው ጥያቄ ነው ፈላስፋውን ያፈላሰፈው ፡፡ ትክክል ከሆነ ፈላስፋው ለመቀበል ዝግጁ ነው፡፡

4. ፊንፊኔ የሚለው ቃል በቅርብ ጊዜ ነው የተሰማው፡፡ ከአያት እስከ ቅድመ አያታችን እንደሰማነው ከዛም ብዙነሽ በቀለ እንደዘፈነችው ሸገር የሚባለውን ስም ነበር የሚታወቀው
5. አዳማ የሚለው በናዝሬት ቢሾፍቱ የሚለው በደብረ ዘይት መቀየሩ ግልጽ ሆኖ ይሰማል፡ ቢሾፍቱንም እናውቃለን አያት ቅድመ አያቶቻችን ሲነግሩን ነበር ፡፡አዳማንም እናውቃለን አያት ቅድመ አያቶቻችን ሲነግሩን ነበር ፡፡ ፊንፊኔን ግን የጥያቄ ምልክት ላስቀምጥልህ ? ????

ለማንኛውም ፊንፊኔ በለው በረራ በለው የፈለገኽን በለው አንድ ሐገር እንዲኖረን ፡ አንድ ኢትዮጵያ እንዲኖረን የአንድ የከተማ ስም ቢኖረን አይከፋም
ከስሙ በስተጀርባ ሌላ ታሪክ ይዞ ለመለያየት መሞከር ጠባብነት ይሆናል
ታሪክ እስኪነግረን ታሪክ እስከሚያስተምረን ድረስ ወይም ተመራምረን እስከምናገኘው ድረስ ፊንፊኔ= ሸገር= በረራ እያለን አዲስ አበባን መዘከር የሚቻል ይመስለኛል ጊዜ ሲሰጠን የሚበልጥብን ስምን ይዘን ወደፊት መጉዋዝ ነው፡፡
ያም ሆነ ይህ አዲስ አበባን ወደ ፊንፊኔ ማዞር ወይም ፊንፊኔን ወደ አዲስ አበባ ማዞር በዚህ በዘመነ ስልጣኔ ጊዜ ከመፍጀት በስተቀር ሌላ ፋይዳ ፤ ትርጉም የሌለው ጭቅጭቅ ነው ፡፡ የዛሬው የአዲስ አበባ ትውልድ አዲስ አበባን እንጂ ፊንፊኔን አያውቅምና

ሌላው የዚህን ዓይነት ነውጥ በኢትዮጵያችን የሚያስነሳው የባንዲራ ጥያቄ ነው አንድ ባንዲራ ሐገራችን ቢኖራት አይከፋም ሌሎች ባንዲራዎች እንደ ቦሎ መኪና ላይ የሚለጠፉ ፤በስብሰባ ላይ በወረቀት ወይም እንደ መፈክር በትልቅ ካርቱን ላይ የሚለጠፉ ምልክቶች ቢሆኑ መልካም ይመስለኛል ወይም በኢትዮጵያ ባንዲራ ላይ መሐከሉ ላይ ያለውን ነገር አንስቶ የየክልሉ ቦሎ ቢለጠፍበት የተሻለ ይመስላል፡ አረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራው ኢትዮጵያዊነትን ለመያዙ የአድዋ ጦርነትና የማይጨው ጦርነት ምስክር ናችው፡፡
ተመልከት ዓላማህን ተከተል አለቃህን የተባለለት ይህ ባንዲራ ነው፡፡
ዛሬ እንዴ አደይ አበባ ፈክተው የምናያቸው ባንዲራዎች የርስ በርስ መጨቃጨቂያ ፡ መጠራጠሺያ ከመሆን በስተቀር ትርፍ የሌላቸው ፡ እድገትን የማያሳዩ ለብልጽግና የማይሆኑ ተራ ውዥንብር ፈጣሪ ነገሮች ናቸው ፡፡

በነገራችን ላይ የጎሳ ክልል ለሐገራችን ለኢትዮጵያ አያስፈልግም ፡፡ ትርፉ መጨቃጨቅ ይሆናል ፡፡
እንጨቃጨቅ ጠ/ሚ ዓቢይ እንዳለው ነገር ግን ጭቅጭቁ የሆነ መፍትሄ ካላመጣስ? ካላመጣ ጭቅጭቁ ጊዜውን ጠብቆ ይከስማል ማለት ይሆናል ፡፡

ሌላው በቀለ ገርባ የተናገርኩት በስህተት ተተርጉሞእል ነው ያለው ከሆነ እንግዲህ ሐገራችን ባቢሎን ሆነች ማለት ይሆናል
በፌክ ኒውስ የትርጉም ልዩነት ፡ ሁሉም አስደንጋጭ ወሬ ፡ ሁሉም ሰበር ዜና ፡ ምላስ ማርዘም ፡ ስለሆነ ጠንቀቅ ማለቱ አይከፋም


የጎሳ ፖለቲካ እና የጎሳ ክልል ለኢትዮጵያ አይጠቅምም
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Apr 05, 2019 10:25 pm

ነጋሶ እኮ የቱለማ ጎሳ አባል አይደሉም፡፡እሳቸውን ስለ ሌቃና በከሬ ጠይቃቸው፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1287
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Tue Apr 09, 2019 9:02 pm

እሺ ዘርዓይ
እሳቸውንስ እንደሱ አልካቸው እነ በቀለስ የት ናቸው እነ ጃዋርስ የት ናቸው ?
እስቲ ልጠይቅህ ምነው "ግንፍሌ" የሚባል ነገር የለም ግንፍሌ ገነፈለ ከሚለው ቃል የወጣ መሰለኝ
ቀበናስ ቡልቡላስ ለምን የሉም፡፡

በነገራችን ላይ እክቲቪስቶቹ ማለትም የዩቲዩብ እና የፌስ ቡክ እንዲሁም የሳይበር አክቲቭስቶች ማለቴ ነው ልብ አድርግ መስመር የሳቱ መሰለኝ
እየመረቀኑ ነው እንዴ የሚለቁት

ከሒስ በስተቀር ሌላ ነገር ከሌላቸው ለምን ለሳይበር የሚሆን ጠቅላይ ሚኒስቴር መርጠው ሙዚቃ ቢያዳምጡ ጥሩ ነው ይላል ፈላስፋው

ሌላው ደግሞ ድሮ የሰፈር ልጅ ሲደባደብ ፡ በግጦሽ መሬት ሲጠራጠስ እርቅና ሰላም አለ በማለት ተስፋ እናደርግ ነበር

ዛሬ የሆነ ግጭት ተነሳ ከተባለ ፈላስፋው ሰምቶት አይቶት በማያውቀው መሳሪያ ልጅ አዋቂ ነው የሚያልቀው ፡፡
እጅግ የሚያሳዝን ነው
ይህስ ጉዳይ ከስልጣኔ ወደ አረመኔነት እየተጉዋዘ ነው መሰለኝ
በጥይት ነጻነት ሳይሆን የሚገኘው የሰው ልጅ ሕይወት ነው የሚጠፋው

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri Apr 12, 2019 4:32 pm

አሻጥሩ በዛ
በየቦታው አሻጥር
በየጢሻው አሻጥር
በሳይበር አሻጥር
የዲጂታል አሻጥር
የዩቲዩብ አሻጥር
የፌስ ቡክ አሻጥር
የሳተላይት ቲቪና የሳተላይት ራዴዮ አሻጥር

ለሁሉም ነገር ተጠያቂ አንድና አንድ ግለሰብ
ሌሎች የእስተዳደር ሰዎች ኢትዮጵያዊ አይደሉም ይሆን ?
እነዚህ የአሰተዳደር ሰዎች ባለፉት ዓመታት ምን አስተስሰብ ነበራቸው ? እንዴት ነበር ኑሮእቸው? እንዴት ነበር አመለካከታቸው የሚለውስ ጥያቄ ምን ይሆን መልሱ ?
ምሳሌ
ይህ ሁላ ቢልዮን ብር ለግለሰቦች የኪስ ማዳበሪያ ሲሆን ለእሳት ማጥፊያ የሚሆን ሂሊኮፕተር ለምን አልተገዛም ?
ተጠያቂው ?
ክአስተዳደር ብልሹነት በለገጣፎ ና በሱሉልታ ቤት በሰው ላይ ፈረሰ
ተጠያቂው ?
ቃላት በመሰንጠቅ ( በአሉ አሉ ) እንኪያ ሰላምታ ውስጥ መግባት
ለቃላቶቹ ተጠያቂ ?
የጎሳ ፖለቲካ ለሐገራችን ጠንቅ ነው
ተጠያቂው ?
"ያኔ ሰላም ነበረ ዛሬ ግን ....."
ተጠያቂው ?

ያደረ የከረመ የቢሮክራቲክ ስራ ሐገር ማበላለሸቱ ያልገባቸው ጣታቸውን የሚቀስሩት ማን ላይ ?

ያደረ የፖለቲካ ስሌት፡ የጎሳ ፖለቲካ ሐገር ማበላለሸቱ ያልገባቸው ጣት የሚቀሰሩት ማን ላይ ?

የጎሳ ፖለቲካ ሐገር እያጠፋ እርስ በርስ እያፋጀ እያዩ የጎሳ ፖለቲካ ይለምልም ፡ ሕገ መንግስቱ ይከበር በማለት ጣታቸውን የሚቀስሩት ማን ላይ?

እዛም ስደት እዛም መፈናቀል

በእውነት አእምሮእችን ትክክል ነው ፤ ጭንቅላታችን ትክክል ነው ? በእውነት እንደ ሰው የምንራመድ ፡ የምናስብ ነን ብለን እስቲ ራሳችንን ብንጠይቅስ?

ጣታችን ሌላ ላይ ከመቀሰራችን በፊት፡ ምላሳችንን በሌላ ላይ ከመጎልጎላችን በፊት ፡ ራሳችንን በራሳችን ብንመለክትስ? ምላሳችንን በቅድሚያ ብናጸዳስ?
ከማሰባችን በፊት ስለምናስበው ነገር በቅድሚያ ብናስብስ ?
ከመናገራችን በፊት የራሳችንን ንግግር እኛው ራሳችን ለማዳመጥ ብንሞክርስ?

ፈላስፋው እንደሚያስቀምጠው
በዚህ አሻጥር ውስጥ መረዳዳት የማይፈልግ ፡ የማይችል ፡ በሙሉ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
ሁሉም ወቀሳ
ሁሉም ትረባ
በዚህ አሻጥር ውስጥ ሳያውቀው ገብቶ ምላሱን ለሚጎለጉል መልካሙን ሁላ ፈላስፋው ይመኛል
የዚህ አሻጥር አነሳሺና ፈጣሪ ስለራሱ ቢያስብ የተሻለ ይመስላል መጨረሻው ለልጅ ልጅ አያምርምና


ፈላስፋው የሚገርመው ፡ ለሐገር የሚጠቅም ሐሳብ ማቅረብን የቻለ የጎሳ ድርጅትም ሆነ የሳይበር ምላሳምን አለመስማቱ ነው ፈላስፋውን የገረመው

አሻጥር ከነአሻጥረኛው ይጥፋ
የኢትዮጵያ አንድነትና ማንነት ለዘላለም ይኑር
ከዛም በአለማየሁ እሸቴ ዘፈን
ማን ይሆን ትልቅ ሰው

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Apr 18, 2019 8:45 pm

አዲስ አበባ የኛ ነች ፡ የኛ የፈላስፋዎቹ ነች ፡፡
በረራ በላት፡ ሸገር በላት ፡ ግንፍሌ በላት ወይም ፍንፍኔ ወይም ቡልቡላ ወይም ቀበና
አዲስ አበባ የኛ የፈላስፋዎቹ ነች ፡ እኛ ፈላስፋዎች ደግሞ ኢትዮጵያውያን ነን ፡፡
በዛሬው እትማችን ዶክተር ላጲሶ ይሁኑ ወይም የኢትዮጵያ ታሪክ እንዳስቀመጠው ሽምብራ ኩሬ የሚባል ቦታ የሚገኘው በናዝሬትና በድኮም መካከል ነው ይለናል ፤ በግምት ቢሾፍቱ አካባቢ ማለት ይሆናል ፡፡
ይህ ቃል ሽምብራ ኩሬ የሚለው አማርኛ ነው ወይስ የምን ቃል ነው ?
በካርታ አገላለጽ በደቡብ ምስራቅ የዛሬይቱዋ አዲስ አበባ 130 ኪሜ አካባቢ የሚገኝ ቦታ ነው ይለናል፡፡
ለመሆኑ በሽምብራ ኩሬ ምን ታሪካዊ ድርጊት ተፈጽሞአል የሚለው ነው የፈላስፋው የዛሬ ጥያቄ
በሽምብራ ኩሬ ታሪክ ሲሰራ በረራ በላት ወይም ሽገር ወይም ፊንፊኔ ያን ጊዜ የት ነበረች ?
የት ነበረች በረራ ፡ የት ነበረች ሸገር፡ የት ነበረች ፊንፊኔ ?

በነገራችን ላይ " አብዮታዊ ዲሞክራሲ " የሚለው ቃል ካምብሪጅ ዲክሽነሪ ወይም ኦክስፎር ዲክሽነሪ ወይም ዌብስተር ዲክሽነሪ ላይ ቢፈለግ ከዛም የአማርኛም ሆነ የኦሮሞ ወይም የሱማሌ ወይም የአፋር መዝገበ ቃላት ላይ ቢፈለግ ከዛም ደግሞ በትግሬኛ መዝገበ ቃላት ላይ ከሀ እስከ ፐ ቢፈለግ ሊገኝ አልተቻለም፡፡
እንደውም የራሺያው መዝገበ ቃላት አያውቀውም ይህ ቃል እንደው ትርጉም አልባ የመናፍስት ቃል ይሆን ?

ሌላው ችግሩ አሻጥሩ ነው

በዛ በዚህ አሻጥሩ እየሰፋ በመሄድ ላይ ነው
በመፈናቀል ስናዝን በጥይት
በጥይት ስናዝን በባህር አለቅን

ፌዴራሊዝም ይሰረዝ ፡
የሱማሌው ምክትል ፕሬዘዳንት ሙስጠፋ ኡመር እንዳለው " በዝም " የሚያልቁ ቃላቶች ለሐገር አይበጁም አያስፈልጉም
ሶሻሊዝም ፡ ኮሙኒዝም ፡ ካፒታሊዝም ፡ ናዚዝም ፡ ፋሺዝም ከዛም ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ የሚበጅ ነገር አይደለም
የኢትዮጵያ ሕዝብ የላቦራቶሪ እቃ አይደለም፡፡

የጎሳ ፌዴራሊዝም ይብቃ ውጤቱ እልቂት ፡ መፈናቀል ፡ በባህር በመሬት ስደት ነውና ይላል ፈላስፋው ቆቁ
እኩልነት ነጻነት ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sat Apr 20, 2019 7:04 pm

ፈላስፋው እንዲህ ይላል
አርኪሎጂካል ምስክር ያስፈልጋል
ያለፈ ነገር የሞት ታናሽ ወንድም ነው እንደሚባለው ሁሉንም ትተን ሰላምና ፍቅር ለመፍጠር እንዳንችል በፈጠራ ታሪክ እንዳልነበርን ስንሆን ማየት ለኛ ለፈላስፋዎች በጣም ይከብዳል
የነጻ አውጭ ብለው ራሳቸውን የሚጠሩትን ድርጅቶች ከፖለቲካው መድረክ በጽንፈኝነት ሳይሆን በትክክለኛ በሰብአዊ መብታቸው ፖለቲከኛ እንዲሆኑ የግድ የአርክዮሎጂካል ማረጋገጫ ያስፈልጋል ለዚህም ፈላስፋው ሽምብራ ኩሬን ያነሳው ፡፡
ሽምብራ ኩሬ ታሪካዊ ቦታ ነው ይህ ቦታ በኢማም ግራኝ መሐመድና በልብነ ድንግል መካከል የተደረገ ወሳኝ ጦርነ ነው ፡፡ በዚህ ጦርነት ኢማም ግራኝ መሐመድ በአሸናፊነት ድል ያደረገበት ጦርነት ነበር ፡፡
ጥያቄው ኢማም ግራኝ መሐመድ ማሸነፉ ልብነ ድንግል መሸነፉ ሳይሆን
1. ሽምብራ ኩሬ በናዝሬትና በድኮም መካከል ከሆነ የት ነበር ይህ ቦታ
2. በዚህ ጦርነት ውስጥ የተካፈሉ ያልተካፈሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ይገኛሉ ባይ ነው ፈላስፋው ያልተካፈሉት እነማናቸው?
ይህ አርኪዮሎጂካል ፍለጋ ወሳኝና እና የማያሻማ የኢትዮጵያ ታሪክ በመሆኑ ፡ የዚህ ታሪካዊ ቦታ መገኘት ለኢትዮጵያ ታሪክ ወሳኝ ነው ይላል ፈላስፋ
ጠባቦችም ቢሆኑ በዚህ የእርኪዮጂካል ፍለጋ ብቻ ነው ከጠባብነታቸው የሚሰፉት

በሌላ አቅጣጫ
1. ለዩቱቦዎች ና ለፈስቡኮች
ራሳችሁ በግላችሁ ብትሰዳደቡ መልካም ነው ነገር ግን የሆነን ጎሳ መከታ አድርጎ ልቃቂት አፍን መክፈት ግን ነውረኝነት ነው፡፡
2. ሕገ መንግስቱ ይከበር
በኢትዮጵያ ውስጥ ሕገ መንግስቱን የጣሱ ሁለት ግለሰቦች በግልጽ ይታያሉ
አንደኛው ዋራንቲ ተቆርጦበት የት እንዳለ የማይታወቀው
ሁለተኛው በገዳ አባቶች እርቅ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲመጣ የተለመነው ግለሰብ

ሁለቱም ግለሰቦች የሚገኙት የነጻ አውጪ ድርጅት ነን ብለው ራሳቸውን ከሚጠሩ ድርጅቶች ነው
እነዚህ ነጻ አውጭ ድርጅቶች ደግሞ በተነሳው ጥቃቅንም ሆነ ትላልቅ ለውጠ ድንቅፋት ሕገ መንግስቱ ይከበር የሚሉት ናቸው

በፈጠራ ታሪክ የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት አይፈርስም
እኩልነትና ነጻነት ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Tue Apr 23, 2019 7:09 pm

ለፍንጭ ያህል የኢማም ግራኝ መሐመድን ታሪክ ከበተንኩ በሁዋላ ወደ ዋናው ነጥብ እመለሰላሁ

ለምን የኢማም ግራኝ መሐመድ ታሪክ አስፈለገ?
ማነው በዚህ ጦርነት ያልተካፈለ ኢትዮጵያዊ? የሚሉት ጥያቄዎች ፈላስፋው ያቀርባል ፡፡

ልብነ ድንግል በለው ግራኝ መሐመድ በለው ሁለቱም የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ ያካተተ ጦርነት በሽምብራ ኩሬና በመሳሰሉት በዛሬይቱዋ ኢትዮጵያ ካርታ ላይ በሚገኙት ቦታዎች የሚገኙትን የኢትዮጵያ ልጆች በሙሉ አሳትፈዋል ፡፡
ኢማምንም ሆነ ልብነ ድንግልን የተከተሉት አውቀውም ሆነ ባለማወቅ ለአንድ አሐዳዊ ኢትዮጵያዊ ስርዓት ነበር ፡፡


በሁለቱም ጎራ ለአንድ አሐዳዊ መንግስት ማለትም ለአንድ ኢትዮጵያ ሁሉም የድርሻውን ተወጥቶል
ኢማም ግራኝ መሐመድም በለው አጼ ልብነ ድንግል ሁለቱም ለአንድ ኢትዮጵያ አሐዳዊ መንግስት ነበር ትግላቸው

ይህንን ታሪካዊ ክስተት ማንም ሊክደው አይችልም ነገር ግን የተካደው መቸ ነው ? የሚለው ጥያቄ ነው ፈላስፋውን ፍልስፍና ውስጥ የዘፈቀው
በኢትዮጵያ ውስጥ ለአሐዳዊ ስርዓት የሚደረገው ፍልሚያ [u]ኮሎኒያልዝም በኢትዮጵያ
ተብሎ መተርጎሙ የፈረንጆች ኮሎኒያሊስቶችን በጣም ከሚያስቃቸው ጉዳይ አንዱ የኢትዮጵያ ምላሰ ረጃጅሞች ልሂቃን ባለማወቅ የፈጠሩት የፈጠራ ቃል ነው ፡፡
እንደው ከፈረንጅ ሁሉንም መኮረጅ የነዚህ ልሂቃን ትልቁ የተጠናወታቸው ጂኒ መሆኑን ነው ፈላስፋው የሚረዳው
በጣም የሚያስቅ በጣም የሚያስገርም አባባል ነው ፡፡


ለመሆኑ በኢትዮጵያ ከኢማም ግራኝ መሐመድ እስከ መንግስቱ ሐይለማርያም ድረስ የተደረገው ፍልሚያ የኮሎኒያሊዝም ባህርይ አለው ?
ማነው ኮሎኒያሊስቱ ? ማነውስ ባንዳው ?

ይህ የኢማም እና የልብነ ድንግል ሩጫ ከሌላው የእውሮፓ ሐገሮች ወይም ከፊውዳል ባላባቶች የሚለየው በምን ይሆን ?
የ አውሮፓ Medival time history ከኢትዮጵያ የፈረሰኞችና የጎራዴ ውጊያ ማለትም ከኢማም ግራኝ መሐመድና ከልብነ ድንግል የጎራዴ እና የጦር ውጊያ ፡ ከዛም በሁዋላ ለተከሰተው የጎራዴ በለው የጥይት ውጊያ የሚለየው በምን ይሆን ?

እዚህ ላይ ነው የኛ የኢትዮጵያ ሐገራችን ጨዋታ የሚጀምረው ለዛውም በተማሪው ንቅናቄ ዘመን ማለት ነው፡፡

ኮሎኒያል የሚለው ቃል ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለአሐዳዊ መንግስት የታገለውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማዋረድ ነው በማለት ፈላስፋው ፍልስፍናውን ይቀጥላል

በነገራችን ላይ የተወሰኑ የኢትዮጵያ ጀኔራሎች ወይም ራሶች ፊታውራሪዎች ሲጠሩ የማይጠሩ ራሶች እና ፊታውራሪዎችንም ፈላስፋው ታዝቦአል

ኢትዮጵያን አንድ የማድረጉ ሁኔታ በልብነ ድንግልም በለው በኢማም ግራኝ መሐመድ ከዛም እስከ ሐይለስላሴ ከዛም እስከ ደርግ ድረስ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች የተካፈሉበት ስርዓና ጦርነት ፡ ነው፡፡
ጭቆናው ግን የትም በለው የትም ስፍር ቁጥር የሌሌው ነበር፡፡
ነገስታቱ ከዛም ባለሙዋላቸው ተደላድለው ሲኖሩ ፡ ሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መከራውን ሲቆጥር ነው የኖረው ፡ ለምሳሌ የኢትዮጵያዊነታችን ምሳሌ የሆነው የወሎ ረሐብ የማይረሳው ታሪካችን፡ ነው ፤፤
ከዛም የቀዩ ሽብር ሌላው ተከታዩ የማይረሳው ታሪካችን ነው ከዛም እያለ የሚቀጥል ይሆናል ፡፡

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun Apr 28, 2019 3:42 pm

ይድረስ ለአዲሱ አረጋ

አንተ ብቻ አይደለህም እውነቱን የተናገርከው ሌሎችም አንተ የተናገርከውን እውነት ተናግረውታል ፡፡
አንተ ስትናገር ሰላማዊ ሰልፍ ሌላው ሲናገር በጥሞና ማዳመጥ !!
ጥላሁን ገሰሰ እንዳለው ለእውነት እሞታለሁ አልሳሳም ለነፍሴ ብቻ ነው ትክክለኛው መንገድ

ታሪክ ሰሪው ሕዝብ ነው ፡፡
በዚህ በኛ በምንኖርበት ምዓተ ዓመት የአንድ ሕዝብ ታሪክ በልብወለድ ታሪክ አይፈጠርም
አንድ የልብወለድ ታሪክ ግን ከአንድ የሕዝብ ታሪክ ይፈጠራል ፡፡
እንደዛም ነው እስከ ዘመናችን ዝነኛ ጸሐፊ እስከነ ዳን ብራውን ድረስ የተጻፉት ልብ ወለድ ታሪኮች ልብወለድ ታሪካቸውን የሚተርኩልን ፡፡
ይህንን ልብ ወለድ ታሪክ " የቡርቃ ዝምታ" የተገላቢጦሽ ታሪክ ማድረግ ሐላፊነት አለብህ
የአኖሌ ሐውልትም መፍረስ አይኖርበትም ይላል ፈላስፋው ፡፡
ነገር ግን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚማርበት ታሪክ መሆን ይገባዋል ፡፡

በሐገራችን የጭቆና እና ባህላዊ ታሪኮችም ቢኖሩን እንደዚህ ያለ " በቡርቃ ዝምታ" ላይ የተጻፈ ታሪክ እኛ ኢትዮጵያውን የለንም ፡፡

እነዚህን ባህላዊ ታሪኮች ባህላዊ ስለሆኑ ነበሩ ብለን እንዘላቸዋለን፡፡
ፍቅር እንዲያመጡ ካስፈለገ አርኪዮሎጂካል ጥናት ተደርጎባቸው በታሪክ ተመዝገበው በትምህርት ቤት መሰጠት ይኖርባቸዋል፡፡
ከዛ በሁዋላ ልብወለድ መጽሐፍ ቢጻፍባቸውም ይህን ያህል የሚደንቁ አይሆንም ፡፡

ሰነድ አለኝ መረጃ አለኝ ከተባለ በትክክል ለታሪክ በታሪክ መዛግብት ይቀመጣሉ እንጂ በአንድ ግለሰብ ቤት እንደ ግል እቃ ተቀምጠው እየተመዘዙ የሚወጡ ተራ የቤት እቃዎች አይደሉም፡፡

እነዚህ ሰነዶችና ታሪኮች በአንድ ግለሰብ ቤት ተቀምጠው ከሆነ ይፋ መውጣት ይኖርበታል፡፡ ከዛም እንዴት ተገኙ ከየት ተገኙ የሚለው ጥያቄን ተከትሎ ግለሰቡ መልስ መስጠት ይኖርበታል ማለት ይሆናል ፡፡


ጦርነቶች በየትኛውም የኢትዮጵያ ክፍሎች ተከስተዋል በወላይታ በከፋ በሐረር በጎጃም በሸዋ በጠቅላላው በመሳፍንት ዘመን ኢትዮጵያ የጦርነት አውድማ ነበረች፡፡

ነገርግን "ደራሲው የቡርቅ ዝምታ" እንዳለው የሴት ልጅን ጡት ቆረጣ ግን በማንኛውም የኢትዮጵያ የጥንቱዋ ግዛቶች እንዳልተካሄደ ግልጽ ነው፡፡
ይህ ሐውልት የማይፈርስበት ምክንያት ሶስት ነገሮች ናቸው ፡፡

1. ራሱ ይህንን ሐውልት እንዲሰራ ያደረገው ስርዓትና መንግስት ፡ በትክክል ለማስታወስና ታሪካዊ ምስሉን በትክል አስቀምጦ ለትውልድ ለማስተላለፍ

2. ይህ ሐውልት እንዲሰራ ምክንያት የሆነው ልብ ወለዱ መጽሐፍ በየትኛው ጊዜ እንደተጻፈ ፡ለምን እንደተጻፈ ፡ ማን እንደጻፈው በምን ምክንያት እንደተጻፈ የሚቀጥለውን ትውልድ ለማስተማር

3. ሐውልቱ የማይፈርስበት ሶስተኛው ምክንያት ደግሞ ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፡ ለሰላምና ለፍቅር አስባለሁ የሚል መንግስትና የመንግስት ቡድን እንደዚህ ያለ ጸረ ሰላም የሆነ የውሸት መጽሐፍ ታትሞ ሲሸጥ አብሮ መጽሐፉን ማባዛቱን ለሚቀጥለው ትውልድ ለማሳየት ፡፡

ለመሆኑ ይህ ምናባዊ ትረካ ስንት መስመሮችን ይዞአል እያለ ፈላስፋው ፍልስፍናውን ይቀጥላል


ነፍስ ይማር ለዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
እንኩዋን አደረሰን
የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኖራል ፡፡
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Tue Apr 30, 2019 4:49 pm

አንድን ልብወለድ ታሪክ ለመጻፍ በመጀመሪያ በትክክል በሪሰርች የተደገፈ ታሪክ ያስፈልጋል
ይህም ታሪካዊ ልብወለድ የሚባለው ነው፡፡
ሌላው ማህበራዊ የሚባለው የልብወለድ ትረካ ነው፡፡ ስለ ፍቅር ወይም ግጥም ...
ትውፊትና የመሳሰሉትን በብዙ ክፍሎች ለያይተንን መፈላሰፉ የሚጠቅም ይሆናል
ትውፊት ከየት ይነሳል ? ይመጣል ? ብለን ብንጠይቅስ ? መልሱን ለእንባቢ
ለፍንጭ ያህል አንድ አእምሮውን ከሳተ ግለሰብም ሊመነጭ ይችላል ብለን መጀመር እንችላለን
ነገር ግን የሆኑ ማህበርተኞች ተሰባስበው ትውፊት መፍጠር አይችሉም ብለን ደግሞ መቀጠል እንችላለን

እስቲ ስለዝነኛው ትውፊት አንድ ልበላችሁ
ቢሾፍቱ ሆራ ራሱ " የቡርቃ ዝምታ የጻፈው ግለሰብ የተወለደበት ቦታ " ልውሰዳችሁ
ምንነበር የሚነገረው ?
ቆሪጥ
ማን ነበር ቆሪጥ ? ምን ይሰራ ነበር ቆሪጥ ፡ለቆሪጥ የሚደረገው ግብር ምን ነበር ? ማን ነበር ለቆሪጥ ግብር ያደርግ የነበረው ?

" የቡርቃ ዝምታ ጸሐፊው" ይህንን ተረት ተረት በደርግ ዘመን ቢኖር ኖሮ እንዴት አድርጎ ነበር የሚያስቀምጠው ??
የሚሉት የምንፈላሰፍባቸው ይሆናሉ

ዛሬ የሰማሁት ደግሞ የእጅ ቆረጣ ነው ፡፡ በጦርነት ዘመን የማይደረግ ጭካኔ የለም ፡፡

ነገር ግን አንድ የተማረከ ወይም በጦርነት ላይ እጁ የተቆረጠ ግለሰብ እንዴት ነበር የሚታከመው ?
በተለይ አንድ የተማረከ ግለሰብ እጁ ተቆርጦ እንዴት ነበር ሊተርፍ የሚያስችለው ሁኔታ ?
ታሪክ ተመራማሪዎች ይህንን ሁኔታ ማስረዳት ይችሉ ይሆን ? ወይስ ፍለጠው ቁረጠው ብቻ ነው የሚተርኩልን ?

እጅ መቁረጥ ከዛም አንገትን መቁረጥ በአካባቢያችን ከሚገኙት የአረብ ሐገሮች ከጥንትም ጀምሮ የነበረ ነው አንገታቸው በሐራም የተቆረጠ መመለሻ የላቸውም እጃቸው የተቆረጠ ግን በሕክምና ቢጤ ይረዱ ነበር ካልሆነም ወደፊት መጉዋዝ ነው ወደ መጨረሻው

በኛ ሐገርም እንደዛ ያለ ነገር በጦር ምርኮኞች ላይ ነበር ከተባለ ፡ከዚህ አሰቃቂ ድርጊት ደግሞ የተረፉት በሕይወት ኖረው ታዩ የሚል ታሪክ ካለ ፡፡ ሕክምናው እንዴት ነበር ?
ለመሆኑ በሐገራችን እንደ ስመ ጥሩ አርበኞቻችን ስመ ጥሩ ዶክተሮቻችን እነማን ነበሩ?
ይህንን ስላችሁ ያኔ ማለቴ ነው እንጂ በሐይለስላሴ ዘመንና በደርግ ዘመን ማለቴ እንዳይደለ ግልጽ ይመስለኛል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri May 03, 2019 3:24 pm

ትውፊት ከየትም ይነሳል ፡፡
ትውፊት ከአንድ ግለሰብ ተነስቶ ወደ ማህበረሰቡ እንዲደርስ ብዙ መንገዶች ሊኖሩት ይችላሉ
ለምሳሌ
1. በሕልም ያየውን ለሌላው በመንገር እና ሌላው ለሌላ ሲያስተጋባው
2. የአእምሮ ጭንቀት ያለበት ግለሰብ የሚናገረውን ሌላው ሲያስተጋባው
3. በመጠጥ ሐይል መስመሩን የለቀቀ ንግግር በሰማው ሰው አማካይነት ለሌላ ሲተላለፍ የመሳሰሉት ይሆናል
4. የአነጋገር መዛባት የሚያስከትለው ሌላ መዛባት

የቆሪጥ ነገር
በቆሪጥ ታሪክ ቅንድበ ሙሉ የሆነ ወጣት ሖራ ወንዝ ለቆሪጥ ይጣል ነበር የሚለው ተረት ሰሚ ቢያገኝና እንደዚህ እንደ ቡርቃ ዝምታ ጸሐፊ ያለው ቢያገኝው ለማህበረ ሰቡ ከመተላለፍ የሚያግደው ነገር አልነበረም ፡፡ እናም ምን ይሰራ ነበር ?

ሌላው ደግሞ በጦርነት ዘመን የጦረኛ እና የወታደር አስተሳሰብ እንደ ጭንቅላቱ የተለያየ በመሆኑ ሴቶችን ለመድፈር ወደ ሁዋላ እንደማይል ታሪክ ደጋግሞ ይነግረናል ፡፡
እዚህጋ ደግሞ የሴቶች የዋህነት እንዳለ ሁላ የሴቶች ጀግንነት እንዳለ ደግሞ መዘንጋት አይቻልም
አንድን እብሪተኛ ጦረኛ ወይም ወታደር አንዲት ሴት ከአንተ ጋር አልተኛም ብላ በጥፊ ብታጋየው የጦረኛው ወይም የወታደሩ መልስ ምን እንደሆነ አንባቢ መገመት ይችላል፡፡ በሳንጃ ወይም በጦር የትኛውም የሰውነቱዋ ክፍል ላይ ሊወጋት ይችላል፡፡
ሊተኩስባት ይችላል፡፡
ሰለሆነም ከዚህ በመነሳት እንግዲህ በሕግ እንደተነገገ ወይም መላው የዛ የጦረኛ ወይም የወታደር ሕብረተሰብ እንደዛ አድራጊ ነው ብሎ በመገመት የተነሳ ወሬ እንደ አውሎ ነፋስ ከተቀጣጠለ እና እንደ ቡርቃ ዝምታ ጸሐፊ ያለ ካገኘው ማቀጣጠሉን ያቀጣጥላል ማለት ይሆናል

አርክዮሎጂካል ወይም ጥናታዊ ማረጋገጫ ሳይኖረው አንድን ነገር ሰነድ አለኝ ወይም የሆነ ነገር ሳጥኔ ውስጥ አለ ብሎ መዘባረቅ ግለሰባዊ ችግር እንጂ ታሪካዊ ማረጋገጫ አይሆንም፡፡

ለዚህም ነው የቡርቃ ዝምታ እና እሱን ተከትሎ የተሰራው ሐውልት ለፍቅር ሳይሆን ለማይረባ ጊዜያዊ እርካታ በሰው ልጆች መካከል ጥላቻ ለመፍጠር የተተከለ ሐውልት መሆኑን እኛ ፈላስፋዎች ለመናገር የምንደፍረው ፡፡

በከፋ በተደረገው ጦርነት እንደዛ ያለ ነገር አልተወራም
በወላይታ በተደረገው ጦርነት እንደዛ ያለ ነገር አልተወራም
በመላው ኢትዮጵያ በተደረገው ጦርነት ራስ አሊ በለው ፡ ቴዎድሮስ በለው ዮሐንስ በለው እንደዚህ ያለ ድርጊት አልተሰማም

የቡርቃ ዝምታ ጸሐፊ እንደዚህ ያለ ነገር ለመቃዠት እንደፈለገ ሰነዱንንም ሆነ ዶሴውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቢያቀርብ የተሻለ ይመስላል

ሌላው ደግሞ የኢትዮጵያ ልጆች ታሪክን እንዴት ነው የሚማሩት የሚለው ይሆናል በጥላቻ ከሚንቀለቀሉ አክቲቪስቶች በፌክ ኒውስ እና በዩቱቦዎች በሚተላለፍ አተካራ ???
ይህ የሚያሳየው እድገታችንን እና ብስለታችንን ይሆናል
በአሜሪካ በአውሮፓ ልጆች ታሪክ የሚሩት በትምህርት ቤት ነው ፡፡ የእርስ በርስ ጦርነት በአሜሪካ ፡የባርነት ኑሮ በአሜሪካ ፡ በአውሮፓ የናፖልዮን ጦርነት የሂትለርና የሞሶሎኒ ፡ የ30 ዓመቱ የሐይማኖት ጦርነት፡ በትምህርት ቤት

ሌላው ደግሞ አንድ የታሪክም ሆነ ልብወለድ ጸሐፊ እንደ ቡርቃ ዝምታ ጸሐፊ ያለ ይሆናል ለመሆኑ ራሱ ነው ይህንን መጽሐፍ የጻፈው ወይስ ሌሎችም በዚህ ጉዳይ ላይ ተደምረውበታል የሚለው ጥያቄ ነው

ለማንኛውም በዚች ምድር በኢትዮጵያ ሰላምን የሚያመጣላት እንጂ ጦርነትን የሚፈጥርላት አትፈልግም
ሰላምን መፍጠር ትልቁ ነገር ሆኖ እያለ እንደዚህ ያለ ተራ ቅዠት መጻፍ ግን ለህሊና እረፍት የሚሰጥ ሆኖ ፈላስፋው አያገኘውም ፡፡

ስለዚህም ነው
የጦረንት ዘመን አልፎአል የምንለው እኛ ፈላስፋዎች
ቀስትም በለው መጥረቢያ መትረየስም በለው ታንክ የሚያመጣው ነገር የለም ሐገርን ማህበረሰብን አይገነባም
ነጻነት ማለት የኔ ከሆነ የሱም መሆን እንደሚገባው ማመን
ነጻነት የኛ ከሆነ የነሱም መሆን እንደሚገባው ማመን

ጦርነትን የሚተርክ ሰይጣን ነው

የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun May 05, 2019 4:14 pm

የቅንደበ ሙሉ ለቆሪጥ መጣሉን ከተመለከትን በሁዋላ
እስቲ ወደ ሌላው የምርቃና ትውፊት እንዙር

የጫት ምስጢር
አንድ መነኩሴ ወይም ገበሬ አንዲት ፍየላቸው ወደ ጫካ ሄዳ ስትመለስ መርቅና ይመለከቱዋታል፡፡
ከዛም በሚቀጥለው የፍየሉዋ የጫካ ጉዞ ሰውየው ተደብቀው ፍየሉዋን በመከተል ሁኔታውን ሲመለከቱ ፍየሉዋ የሆነ ቅጠል በልታ ስትመረቅን ይመለከቱዋታል ፡፡ (ዛሬ ይህ ቅጠል እንዲታገድ ለማድረግ ሙስጠፋ ኡመር በመነሳትቱ የሚመሰገን ነው ) ፡፡ ይህ ቅጠል ደግሞ ያ ጫት የምንለው ነው፡፡ ምክንያቱም ፍየሉዋን የተከተሉዋት ግለሰብ እሳቸውም እንደ ፍየሉዋ ቅጠሉን ቀምሰው ስለመረቀኑ ነው ይለናል ትውፊቱ ፡፡
ይህንን ታሪክ በመጽሐፍ ጽፎ ታሪክ ነው ብሎ አንድ ግለሰብ ሊነግረን ይችል ይሆን ? ወይስ እንደ ጆክ ሊያወራን ይጽፈው ይሆን ?

ጦርነትና ችግሩ
በሐገራችን የጦርነት ዘመን ብዙ ጉዳት ደርሶአል ፡፡
የምናወራው ስለ ጀግኖችና ስለ ጦርነቱ ነው፡፡
ቆስሎ ስለታከመው የምናወራው ነገር የለም ፡፡
ጀግና እንጠራለን ፡ ጀግና ማለት ጦረኛ ነው ማለት ነው፡፡ ማለትም ገዳይ ማለት ነው ፡፡
ሐኪሙስ ማን ነበር? የሐኪም ጀግና የለንም እንዴ?
በጥንቱ የጦርነት ዘመን ማን ነበር ዶክተሩ የቆሰለን የተጎዳን የሚያድነው ?
የእስር ምርኮኞች ከባድ የሰውነት አደጋ ይደርስባቸው ነበር ይለናል፡፡ የሆነ ሆኖ ግን ማነው ያክማቸው የነበረው ሐኪም? ይረዳቸው ወይም ትረዳቸው የነበረች ነርስ? ምግብ ይሰጣቸው የነበረ ነርስ እና ረዳቶቻቸው ?
እንዴት አንድ ግለሰብ በታሪክ ከምንሰማው የሰውነት አደጋ ያለ ሐኪም እርዳታ ሊድን ይችላል ? ምክንያቱም ብዙ ደም ስለሚፈሰው

ለምን የዶክተር ጀግና የለንም
ለምን ፈላስፋው ሐኪም ሐኪም ይላል ?
ይህ የሐኪም መኖር ነበር ታሪካዊ ማረጋገጫ ሊሆን የሚችለው ብሎ ስለሚያምን ፡፡
በአሜሪካ በአውሮፓ የታሪክ ማረጋገጫ አብዛኛውን ጊዜ ከነዚህ በጦርነት ዘመን ያገለግሉ ከነበሩ ሐኪሞች ነርሶች እና ረዳቶቻቸው ለመገኘቱ ማረጋገጫ ለዛውም የተጻፈ እና አስተማማኝ ማረጋገጫ ስለሚገኝ ፡፡
በነገራችን ላይ ነበር የሞት ታናሽ ወንድም ነው ለምን ስለትላንትና እናወራለን፡፡
ፈጣሪም ትላንትናን ዛሬ ማድረግ አይችልምና
ቤት ትላንትና ዛሬ ቢሆን ኖሮ አለ አለማየሁ እሸቴ ጥሩ ነገር ለማስታወስ ፈልጎ ፡፡
መጥፎ ነገር ቢያጋጥመው ኖሮ ዛሬ ትላንትና እንዳይሆን ስለት ይገባ ነበር ይህንን ማለቱ ግን አንድ ጠቃሚ ነገር ያስተላልፋል ፡፡ ትላንትናን ዛሬ ማድረግ አለመቻሉን ፡፡

[u]እንደው በደፈና ታሪክ ታሪክ አይሆንም

ሐውልቱ የተሰራው ታሪክ እንዳይደገም የሚለው አባባል ይሆናል ፈላስፋውን ያሳሰበው
በነገራችን ይህንን ያሉን ግለሰቦች በእውነት ሊናገሩ ያሰቡትን ጠንቅቀው ያውቁት ይሆን ?
ለመሆኑ በቅርብ ጊዜ በቲቪ የተመለከትነው አሰቃቂው በእስረኞች ላይ የተፈጸመው ድርጊት ምን ያስተምረን ይኖር ይሆን ?
ሐውልቱ ከቆመበት ጊዜ በፊትና በቆመበት ሰዓት ፡ከዛም ከቆመ በሁዋላ ነበር ሁኔታው በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙት እስርቤቶች ድርጊቱ የተካሄደው ፡ አይደለም እንዴ ?
ለምን አልቆመም እንደዚህ ያለ ኢሰብዓዊ ድርጊት ?
በዚህ ድርጊት ውስጥ ተካፋይ የሆኑት ግለሰቦች ወይስ ስርዓቱ?
ከፍርድ ቤት እንደምንሰማው የሆኑ ግለሰቦች ናቸው ለዚህ አስከፊ ችግር ምክንያት የሆኑት ይለናል
ታዲያ አሁን ሐውልት ይቁም ለዚህ ጉዳይ ቢባል በዚህ በሰለጠነው ክፍለ ዘመናችን የሚገርም አይሆንም?

ከተባለም
በሁኑ ግለሰቦችና ቡድኖች በተፈጠረ ድርጊት ሐውልት ይቁም ከተባለ የኢትዮጵያ መሬት ቦታም አይበቃውም
በሆኑ ግለሰቦችና ቡድኖች በተፈጠረ ድርጊት አንድ ብሄር ሌላውን ብሄር የሚጠላበት መንገድ ከተፈጠረ ፡ ሰላም ሳይሆን አሁንም ነገም ለብጥብጥ መንገድ መክፈቱ ስለሆነ ፋይዳ የለውም ፡፡

አንድ ቀን ለዚህ ወገናችን የሰላም ጮራ ይፈነጥቃል
አንድ ቀን ለዚህ ወገናችን የሰላም ዳመና ያንዣብባል
አንድ ቀን ለዚህ ወገናችን የሰላም ዝናብ የሰላም ዳመና በሰላም ጸሐይ ታጅቦ ይዘንብና ወገናችን እንደ ልጅነቱ በየመንገዱ የሚሮጥበት የሚጨፍርበት የሚስቅበት የሚቡዋርቅበት ዘመን እንደሚመጣ ፈላስፋው ይታየዋል
አንድነታችንና ልዩነታችን ለዘላለም ይኑር
የጎሳ ፖለቲካ ይሰረዝ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri May 17, 2019 7:56 pm

1. የጎሳ ፌሬራሊስም
2. ለውጥ ወይስ ነውጥ

አንደኛው፤ የጎሳ ፌዴራሊስም በጋርዮሽ ስርዓት የነበረ ነው ለዛውም ያኔ በሉሲ ዘመን ሆሞ ሳፒያን እና ሆሞ ኒያንደርታል የሚባሉ ፍጡራን ከመለያየታቸው በፊት ፡፡
ይህንን አስተሳሰብ ዛሬ የኛ ፕሮፌሰሮች ወይም የታሪክ አነብናቢዎች ወዲያና ወዲህ ቢያቀመጣሉት ምንም የሚያመጣ ፋይዳ የለውም ፡ ወደፊትም አይኖረውም ፡፡
ፌዴሬሊስም በሰው ልጆች ላይ የሚደረግ የሙከራ እቃ አይደለም ፡፡
እስከ አሁን ድረስ የጎሳ ፌዴራሊም የፖለቲካ መዋቅር መሆን እንዳልቻለ እየታወቀ በዚህ ጊዜን ማጥፋት አስፈላጊ አይደለም
ይህ የጎሳ ፌዴራሊስም በሐገራችን ይሰራል ብሎ ለማሳመን አንድ የሆነ የጦስ ዶሮ እየተፈለገ ማመካኘት ከተጀመረ ውሎ አድሮአል
ይህ የጦስ ዶሮ " ሕገመንግስቱ ቢተገበር" የሚል ነው፡፡ እንዴት ነው ሕገ መንግስቱ በቁዋንቁዋ በጎሳ የሚተገበረው?
ሕገ መንግስቱን ለመተገበር ካስፈለገ ሕገ መንግስቱ በየቁዋንቁዋው ፡ ሕገ መንግስቱም በየዘሩ ፡ስብሰባው በየጎሳው፡ ሲሆን ብቻ ይህ የጎሳ ፌዴራሊስም የሚተገበረው፡ ምክንያቱም አንድ ጎሳ ብቻ ስለሆነ በፌዴራሊስሙ ውስጥ የሚካተተው፡፡ ይህ ደግሞ የጎሳ ፌዴራሊም ሳይሆን በመላው ዓለም ላይ የሚሰራው ፌዴራሊስም የሚባለው ነው፡፡
ለምሳሌ በኢሐዲግ ስብሰባ ላይ አንድ ነገር ለማጽደቅ ድምጽ ይሰጣል፡፡ በዚህ የድምጽ አሰጣጥ ላይ የትኛው ብሄር ከየትኛው ብሄር ራሱም በማስማማት ይወስናል ነገር ግን አንድ ብሄር ካልተስማማ ለምሳሌ ባለፈው ድምጽ አሰጣጥ 25ቱ የተቃውሞ ድምጽ አሰሙ ስንባል ምን ይሆን ከዚህ የምንረዳው ?
የጎሳ ፌዴራሊዝምን ዋጋ ቢስነትን ይሆናል ፡፡
የብሄር ፌዴራሊዝም የመጨረሻው እጣ የጎሳ ፌዴራሊዝም በመሆኑ ነው ፈላስፋው የጎሳ ፌዴራሊዝም የሚለውን ቃል የሚጠቀመው
ለዛም የጎሳ ፌዴራሊዝም ማለት Back to the roots የጥንታዊው የጋርዮሽ ስርዓት ነው ማለት ነው፡፡
እዚህ ላይ ጥያቄው የፍልስፍናው ፡ አያት ቅድመ አያቶቻችን ከኛ የተሻሉ ሆነው ይሆን ይህንን የጎሳ ስርዓት ወደ ዛ ጥለው አንድ ሐገር ፤ አንድ ኢትዮጵያን መስርተው ያቆዩን ?
ሁለተኛው
ነውጥ ወይስ ለውጥ ፡ እኔ ፈላስፋው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁርሱን፡ ምሳውን፡ ራቱን በልቶ የሚውል ወገኑ ከናፈቀው ዓመታት አለፉ፡፡
የልብስ አለባበሱ ከባለስልጣናትና " አርቲስት " ከሚባሉት ወይም በቲቪ ከሚታዩት ጋር ሲነጻጸር የሚያስደነግጥ ነገር ነው ፡፡
የሰውነት ቅርጽ ሲታይም የቲቪ አስተናጋጆችና የስብሰባ ተካፋዮችን ፈላስፋው ሲመለከት ልዩነቱ የሰማይና የምድር ያህል እንደ ተራራቀ ነው የሚገነዘበው
አርቲስቱ ሚልዮን ብር እርዳታ ሰጠ
ባለ ሐብታሙ ሚሊዮን ብር እርዳታ ስጠ
እኔ የምለው አርቲስቱና ባለ ሐብቱ ይህንን ያህል ሚሊዮን ቢሊዮን ብር ለእርዳታ ሲሰጥ እንዴት የሐገሬ ሕዝብ የሚበላው ዳቦ ይጣ፡ የሚጠጣው ውሃ ይጣ፤ የሚያበራው መብራት ይጣ ?

በፈረንጁ ሐገር ባለሚሊዮኖች ፡ የናጠጡ ዲታዎች ቢኖሩም በሚበሉት ዳቦና ፓስታ ወይም የአሳማ ስጋ ልዩነቱ ብዙም አይደለም የሚለያዩት የቅንጦት መኪና ወይም የግል አይሮፕላን ወይም ለመዝናኛ በሚያወጡት ብቻ ይሆናል

ሌላው ደግሞ
ምላሰ ረጃጅሞች አክቲቪስቶች፡ ምላሰ ረጃጅሞች ፖለቲከኞች ፡ ምላሰ ረጃጅሞች አርቲስቶች የሚቀባጥሩት በትክለኛ ግንዛቤ ነው ወይስ ለማውራት ፍላጎች ስላላቸው ብቻ ?
ጉራ ብቻ አይደለም ወሬ ብቻም ነው

ይህንን መለወጥ ያልቻለ የፌዴራል ስርዓት ዛሬም እንደገና የፌዴራል ስርዓት ያስፈልጋል እየተባል ጡርንባ የሚነፋበት ነገር ፈላስፋውን አይገባውም ሊገባውም አይችልም
በአንድ በኩል አሻጥር ፡ በሌላ በኩል ዝነኛ ለመሆን የሚደረግ ጥረት፡ በሌላ በኩል ወሬ ብቻ በሌላ በኩል ዝርፊያ ፡
አሁንም የጦስ ዶሮ እየተፈለገ የሐሳብ መደምደሚያ ከሆነ ሰንብቶእል ፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ፍቅር በገንዘብ አይመነዘርም ፡፡
ፍቅር ገንዘብ ሁለት የማይገናኙ ነገሮች ናቸው ፡፡
ዝናን ማትረፍና ፍቅር ሁለትት ተቃራኒ ነገሮች ናቸው
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Tue May 21, 2019 8:22 pm

ምኒሊክ ቤተ መንግስት ግብር እንደገና ተበላ
እኛ ፈላስፋዎች የምንሊክን ቤተ መንግስት የምኒሊክ ቤተ መንግስት ብለን ጠርተነው አናውቅም፡፡
ምክንያቱም አያቶቻች ፈላስፋዎች ይህንን ቤተ መንግስት የእንቁላል ግምብ ብለው ይጠሩት ስለነበር
ስለሆነም ይህንን የምኒሊክ ቤተ መንግስት የእንቁላል ግምብ ብሎ በመጥራት ታሪክን መመንዘር ይቻላል ፡፡

ከግብሩ በፊት
በምኒሊክ ዘመነ መንግስት መቸ ግብር እንደተበላ ፈላስፋው ብዙ የሚለው ነገር የለም ፡፡ ነገር ግን በቀዳማዊ ሐይለስላሴ ዘመነ መንግስት የግብሩ ስነ ስርዓት የጊዮርጊስ ማለት የጥቅምት ጊዮርጊስ (ጥቅምት 23) ቀን ጃንሆን የንግስና በዓላቸውን ሲያከብሩ እንደነበረ የታሪክ መጻህፍትን በማገላበጥ ለመረዳት ይቻላል፡፡

ከግብሩ በፊት፡ ማለትም በግምት ከሁለት ሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ ጸጉረ ልውጥ ሰዎች ይታዩ እንደነበር ታሪክ ይዘግባል ፡፡
አዲስ አበባ በቅጽል ስሙዋ ሸገር፡ በሰፈር ስሙዋ ፊንፊኔ፡ በትምህርት ቤት ስሙ በረራ፡ በክርስትና ስሙዋ ገፈርሳ ፤ .... ያን ጊዜ ከግብሩ በፊት በድንኩዋን ሰባሪዎች ብቻ ሳይሆን በመንዙማ ዘማሪዎች፡ ፡ድሪቶና ቡቱቶ በለበሱ የኢትዮጵያ ልጆች ማለትም ለአዲስ አበባ ጸጉረ ልውጥ በሆኑ ሰዎች በየዓመቱ በዚህ በጥቅምት 23 ቀን ትከበብ እንደነበር አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡
ለምን ?

ሌላው አስደናቂ ትርኢት ደግሞ ከግብሩ ከሁለት ቀን በፊት ይከተላል ፡፡
ይህ ደግሞ አዲስ አበባን በዚህ በእንቁላል ግምብ አካባቢ ልዩ የሚያደርጋት ይሆናል ፡፡
በነዚህ ሁለት ቀናት ውስጥ ነበር የቁራ መልክተኛ ተሰባስቦ እንደ ድሮን (Drones) አዲስ አበባን በቅርብ ርቀት ይከታተላት የነበረው ይሉናል የያኔ ታሪክና ፍልስፍና ጸሐፊዎች አያቶቻችን
እንደውም በደርግ ዘመነ መንግስት መንጌ ጠባቂዎችን ግብር ሲያበላ ፡ የት እንደሆነ ቦታውን መናገር ያዳግታል ወይም አይታወቅም
ነገር ግን የቁራ መልክተኞች አካባቢውን በካሜራ ይቆጣጠሩት እንደነበር ለማወቅ በ31 ቁጥር አውቶቡስ ወይም በዘጠኝ ቁጥር አውቶቡስ ያኔ የተሳፈረ ካለ ከነዚህ የቁራዎች ትርኢት ዓይኑን መደበቅ እንደማይችል አያቶች አባቶቻችን ይናገሩ ነበር
ከሁሉም በግብሩ ላይ ያስደንቁ የነበሩት
አንደኛ የክብርዘበኛው ወይም ያን ጊዜ የስራ ቤቶች ወይም የግብር ቤቶች ወይም ወጥ ቤቶች በሉዋቸው የተራረፈውን ምግብ በስልቻ በአቅማዳ ቁዋጥረው ለነዛ ጸጉረ ልውጥ ለሆኑት አዲስ አበባን ከበዋት ለነበሩት የኔ ቢጤዎና ( ለማኖች ) ሲያድሉ

ሁለተኛ ቁራዎች እንደ ዘመኑ ራሺያ የጦር አይሮፕላኖች እየተገለባበጡ የሚያሳዩት ትርኢት ( ቢጫ ከለር ስለማይታይ ነው ) አረንጉዋዴ ቢጫ ቀይ ለማድረግ አስቦ እንደነበር ይታወቅለት )))
ሶስተኛ ከግብሩ በሁዋላ አዲስ አበባ በጸጉረ ልውጡም ሆነ በግብር በላተኛው ጥምብዝብዝ ብላ ሰክራ ደስ የሚል ተስፋ ይታይባት እንደነበር ታርክ አበጥሮ፡ አብጠርጥሮ ያስረዳናል

በግብሩ ላይ የሚገኙት ደግሞ ነጋድራስ ፣ ፊታውራሪ ባላምባራስ ፡ ራስ የመሳሰሉት ሲሆኑ እንደዛሬዎቹ ተጋባዦች 5 ብር ይሆን 50 ብር የሚባል ይክፈሉ አይክፈሉ የሚታወቅ ነገር አልነበረም
በደርጉ ዘመንም ጦንጤውም እንዳገኘ ነበር ቅልጥሙን ይዝቅ የነበረው ይሉናል ያን ጊዜ ጦንጤ የነበሩት፡፡ 5 ሳንቲም ወይም 50 ሳንቲም ይክፈል አይክፈል የሚታወቅ ነገር አልነበረም
ዛሬ ቁራዎች የሚባሉ ነገሮች አይታዩም ፡፡ ምግቡ በሬና በግ ታርዶ ሳይሆን ወይም ጠላ ተጠምቆ ወይም ጠጅ ተጥሎ ሳይሆን ከሸራተን ነው የመጣው አሉኝ ፡፡ ዋ ፈላስፋው
ለማንኛውም በሰላም መጠናቀቁ መልካም ነው
የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
የጎሳ ፌዴራሊዝም ቀስ በቀስ ይሰረዝ
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sat May 25, 2019 4:57 pm

የሆነ ነገር እፈልጋለሁ ብዬ ዘው ስል ጃዋርን አዳመጥኩት
ስለ ኩዋስ ጨዋታ እያወራ ጠላዡ በዛ በማለት ነበር የሐገራንን ሁኔታ ሲተነትን የነበረው፡፡
ከዛም በመቀጠል ለድህነነቱ ሲል የኢትዮጵያ ሕዝብ ተዉኝ እባካችሁ በሰላም ልኑርበት የሚልበት ደረጃ ከደረሰ ዲክታተሮች ተፈጠሩ ማለት ነው በማለት ይመስላል ያስቀመጠው ፡፡ ዲክታተሮችም ይህንን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁኔታ ይፈልጉታል ዲክታተርነታቸውን ለማጠናከር በማለት ይመስላል ሐሳቡን የገለጸው
ከዛም በመቀጠል
የኩዋስ ጠላዡ በዛ ፡ በአንድ ሜዳ ውስጥ ያለው ተጫዋች ወዴት ጎል እንደሚያገባ ፡ ስንት ደቂቃ እንደሚጫወት አያውቀውም ፡፡ዝም ብሎ ነው ኩዋሱን ወዴትም ነው የሚጠልዘው ምክንያቱም ኩዋስ ሜዳው (የፖለቲካ ማህደሩ) በዓቢይ ምክንያት ስለሰፋ ነው ያለው
ከሞላ ጎደል የጃዋር አመለካከት ይህንን ይመስል ነበር
እኔ ፈላስፋው ጃዋርን ስጠይቀው
በዚህ ጎሉ በማይታወቅበት ፡ ጠላዡ በበዛበት ኩዋስ ሜዳ አንድ በሬ ቢገባ ምን ዓይነት ይሆን ጥለዛው? ጠላዡ ምን ያደርግ ይሆን ? ከበሬው ለማምለጥ መሮጫውን ያውቀው ይሆን ?
እሺ የሆነ ውሻ በዚህ ኩዋስ ሜዳ ላይ ዘው ብሎ ቢገባ ጨዋታው ምን ይመስል ይሆን? ጠላዡስ ወዴት ይሆን የሚሮጠው ፡ ወደ ኩዋሱ ወይስ ወደ ውሻው?
እሺ አንድ ግለሰብ በኩዋስ ጥለዛው የፈነደቀ ዘው ብሎ ቢገባ ጨዋታው ምን ይመስል ይሆን ? ሌላውስ የሰፈሩ ሕዝብ አብሮ ኩዋስ ጥለዛው ውስጥ ቢገባስ ?

የፖለቲካ ምህዳሩ ከበዛ እንዴት ነው እንደ ኩዋስ ሜዳ ተጫዋቾቹን ማጫወት የሚችለው ?
እዚህ ላይ ነው ጨዋታው
security በግለሰብም ሆነ በሐገር ደረጃ ዋናው የመጫወታ ሜዳውን የሚያመቻቸው ትልቁ ቁጥር አንድ የሚባል ነገር ይሆናል
ይህንን security የሚበጠብጡት እነማናቸው ? ብለን ብንጠይቅ መልሱ ለጃዋር ቀላል ባይሆንም አደናጋሪ ይመስላል
ይህ የደህንነት ጉዳይ በግለሰብም ሆነ በሐገር ደረጃ ከተስተካከለ የጨዋታው ዳኛ ማነው የሚለው ደግሞ ሌላው ነጥብ ነው
እንኩዋን 109 ፓርቲዎች ይቅሩና 109 ሚሊዮን ፓርቲዎች በኩዋስ ጥለዛው ላይ ቢካፈሉ ፡ ሜዳው ለደህንነት የማያስፈራ ከሆነ፡
ውሻም ሆነ በሬ ኩዋስ ሜዳው ላይ እንዳይገቡ ከተክለከለ፡ ዳኛው ይህንን የኩዋስ ጥለዛ ጨዋታ ለማስተካከል፡ አራጋቢዎች ጎሉንና መረቡን ለማስተካከል፡ ምንም የሚያቅታቸው ነገር አይኖርም ይላል ፈላስፋው
ማነው ዳኛው ?
ዳኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ በምርጫ የሚፈልገውን ፓርቲ መርጦ የማይፈልገውን ከኩዋስ ሜዳው ያስወጣል
ከዛም ጥለዛው ይቆማል፡ ስርዓት ያለው ጨዋታ ለተመልካቹ ይቀርባል ፡፡ ተመልካቹም ዳኛውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ሌላ ማንም የለም ፡፡
ከዛም ደህንነት ሰላምና ዲሞክራሲ የሚባሉት ነገሮች ጭላንጭሎቻቸው መታየት ይጀምራሉ ማለት ነው ፡
በዚህ የጎሳ ፖለቲካ በዛ የፖለቲካው ምህዳሩ ሰፍቶአል ማለት የተበጣበጠ አስተሳሰብ ነው
እንደዚህ ያሉ እርስ በርሳቸው የሚፈነካከቱ ሐሳቦች የሚመጡት ደግሞ በዚህ ጥለዛ በበዛበት ኩዋስ ጨዋታ ላይ ኩዋስ ለመስረቅ በኩዋስ ሜዳው አጥር ዙሪያ ከሚያንዣብቡት የኩዋስ ሌቦች መሆኑን ጃዋር የተረዳው ባይሆንም ያሰበውም አይመስልም

ኩዋሱ ተሰረቀ ከዛስ ?

የጎሳ ፖለቲካ ይገርሰስ
የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4329
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests