አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sat Jun 01, 2019 9:34 pm

1. ስለ ደብረ ጽዮን
Ethiopian tradition states that Kaleb eventually abdicated his throne, gave his crown to the Church of the Holy Sepulchre at Jerusalem, and retired to a monastery.
እንዴት ነው ደብረ ጽዮን እንደ ካሌብ ወደ ገዳም ሊገባ ነው እንዴ ?
በታቦት ጥላ ታጅቦ እንደ ካሌብ ! ወይስ ኩኩሉ አለ ዶሮ የሚባል ጨዋታ ተጀመረ?

2.በሸገር ድግስ . በዲያስፖራ ፈንድ[/u]
ምንም የሚያስደስት ነገር አልተገኘም ተባለ ስለሆነም የሸገር ድግስ ወይም የዲያስፖራ ፈንድ መጠራቱ ትክክል ነው ወይስ አይደለም?
3. ቤት ሊፈርስ ነው
በፌስ ቡክ እና በዩቱብ ነገሩ ከወጣ ወዲያውኑ ድምጽ ማጥፋት ፡ ምን ይሆን ነገሩ ?
4. ዳውድ ኤቢሳ እና ጃል ማሮ
ሁለቱም ታዋቂ በመሆን ላይ ይገኛሉ ፡፡ ነገር ግን ተደመሩ የሚለውን ውጤት በመደመር ሳይሆን በዜሮ ድምር እያሳዩን ይሆን ?
5. ልደቱ አያሌው እንዴት ነው ነገሩ ? ዝምታ ወርቅ ነው ብሎ ሲኖር ፡ ዝምታ ለበግም አልበጃት 12 ሆና አንድ ነብር ፈጃት ማለቱ ይሆን ?
6. ኢሳት ምን ነበር እስከ አሁን አንድ ያደረጋቸው አሁንስ የሚበታትናቸው ? ዲሞክራሲ ሲበዛ ጥራዝ መንጠቅ ተጀመረ እንዴ ?
7. የጎሳ ፖለቲካ ሐኪም ቤቱ በጎሳ ፡ ትምህርት ቤቱ በጎሳ ፡ ገበያው በጎሳ ፡ ሐይማኖቱ በጎሳ ፡ ሁሉም በጎሳ ፡ ዩቲዩብ በጎሳ ፡ ፌስ ቡክ በጎሳ

የኩሽ ሕዝብ ፡ ያኔ ያኔ በቅዱስ ቃሉ የተጠቀሰው ቃል ዛሬ እንደገና እየተጠቀሰ ነው ፡፡ የሚገርም ነው ከቅዱስ ቃሉ በፊት በዳርዊን አጠራር መሰረት ምን ይሆን የሚባለው ሆሞ ሳፒያን ወይስ ሆሞ ኒያንደርታል ወይስ ሆሞ .... የሚገርም ነገር እኮ ነው በሰላም በፍቅር መኖር እዚህ አፍንጫችን ላይ ከጊዜና ቦታ ጋር ተስተካክሎ እያየነው ስለ ኩሽ ስለ ሴም ነገድ ሲታሰብ ፈላስፋዎችን በጣም የሚያሳዝን ሆን ይገኛል
ጊዜና ቦታ ( space and time ) እንደ ታክሲ ቆሞ አይጠብቀንምና ጭንቅላታችን በኦሞ ወይም በእንዶድ ብናጥብ መልካም ይመስለኛል
space ( ቦታ ) ሲባል የግጦሽ መሬት እንዳይመስልህ በጠቅላላው ዩኒቨርስ ማለት ነው ፡ በነገራችን ላይ
አዲስ አበባ የግጦሽ መሬት ሳትሆን የሕዝበ ኢትዮጵያውያን መኖሪያ ነች

የጎሳ ፖለቲካ ዋጋ የሌለው ፖለቲካ ነው ለግላዊ ጥቅም የሚደረግ ሩጫ ነው፡፡
የጎሳ ፖለቲካ በልሂቃን የእርስ በርስ ጥላቻ የሚፈጠር የልዩነት ፖለቲካ ነው ፡፡
የጎሳ ፌዴራሊዝም በዚች ምድር ላይ ቦታ የለውም አይኖረውም ፡፡
በቤልጅግ ይሆን ?

የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነትና አንድነት ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun Jun 02, 2019 8:13 pm

1. እሳት አመድ ይሆናል ፡ የተፈጥሮ ሕግ ነው ስለሆነም ኢሳት አመድ ሆነ ፡፡ኢሳት አመድ ቢሆን አይገርምም ስለሆነም የኢሳት ሰውዎች የራሳቸው ካናል ከፍተው መቀጠል እለበለዚያ በዩቱቦ ካናል ፈጥረው መቀጠል ይቻላል ስለሆነም ብዙ ወሬ አያስፈልግም
ወሬ ብቻ
2. red terror to green terror ቀይ ሽብር ወደ አረንጉዋዴ ሽብር መለወጡ ይሆን ? ማፍረስ ቀላል ነው መገንባት ግን ከባድ ነው ማለት ይሆን ?
ወሬ ብቻ
3. የጎሳ ፖለቲካ ወይም የጎሳ ፌዴራሊዝም ጥርጥርን ፤ ክትትልን አለመተማመንን የሚፈጥር የጥንታዊ ጋርዮሽ ስርዓት ነገር ነው ፡፡
ለዚህ ምሳሌ መጥቀስ አያስፈልግም ፡ ግልጽ ስለሆነ
ወሬ ብቻ
4. የነጻ አውጭ ድርጅት የሚባል ፓርቲ በምርጫው ውስጥ መካተቱ ግራ የሚያጋባ አይሆን ይሆን ? ለምሳሌ በአውሮፓ ሕብረተ ሰብ ምርጫ የእውሮፓን መንግስታት ወክለው የተወዳደሩት የፓርቲ ስሞች ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ድርጅቶች መልካም አርዓያ መሆን አይችሉ ይሆን ?
እነዚህ የነጻ አውጭ የፓርቲ ስሞች ጥርጣሬን አለመተማመንን እና ስጋትን ለሐገር እና ለወገን የሚፈጥሩ መሆናቸው አልታሰበበት ይሆን ?
ወሬ ብቻ
5. እንጀራው ሰጋቱራ ፡ በርበሬው ቀይ አፈር እና ሸክላ ፡ ታዲያ ምን እንበል እኛ ፈላስፋዎቹ ፡ የሆነ ነገር የዜሮ ድምር የሆነ ነገር ይኖር ይሆን ?
6.
አንዴ በዱላ አንዴ በከስክስ እየረገጡን፤
ሰላምና ፍቅር እንዲህ ነው አሉን፤
ስንወዳቸው ስናፈቅራቸው፤
ብቅ ብቅ አሉ ከነ ዱላቸው፤
ሊረጋግጡን በከስክሳቸው ፡፡

ሰላም አዲስ አበባሰላምና ፍቅር ለኢትዮጵያ
ልዩነታችንና አንድነታችን ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Tue Jun 04, 2019 9:05 pm

አንድ በሉ
ይህ የሰዶምና የገሞራ ታሪክ አልገባኝም
1. ለምን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አስፈለገ ?
2. ለምን የኢትዮጵያ አድባራትን በተለይ ?
ከዚህ በፊት የተለመደ ነገር ይኖር ይሆን ?
ከዚህ ታሪክ በስተጀርባ ሌላ ታሪክ ይኖር ይሆን ? ወይስ የሆነ provocation ነገርፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Jun 06, 2019 6:24 pm

አንድ በሉ
ይህ የሰዶምና የገሞራ ታሪክ አልገባኝም
1. ለምን ኢትዮጵያን ለመጎብኘት አስፈለገ ?
2. ለምን የኢትዮጵያ አድባራትን በተለይ ?
ከዚህ በፊት የተለመደ ነገር ይኖር ይሆን ?
ከዚህ ታሪክ በስተጀርባ ሌላ ታሪክ ይኖር ይሆን ? ወይስ የሆነ provocation ነገር

የቀጠለ
ልንመጣ ነው ብሎ ጡሩምባ መንፋት ለምን አስፈለገ?

ማስፈራራት ነው ወይስ ምንጣፍ አንጥፋችሁ ተቀበሉን ?

ለሰሚው ግራ የሚያገባ ጡሩምባ !
ዝም ብለው አይሮፕላን ተሳፍረው ወይም በመርከብ አይመጡም ነበር እንዴ ?

ከዛስ ? የሐገራችንን ባህልና ስርዓትን አክብረው የሚጎበኙትን ጎብኝተው ወደ መጡበት መመለስ ነዋ ?

ምናልባት ለመፈ 'ወስ ፈልገው ይሆን እንዴ ወደ ውድ ሐገራችን በጡሩምባና በቱሪናፋ ለመምጣት ያሰቡት?

ለመፈወስ ከሆነ
1. እነዚህ ምስኪኖች ከመጡ በቀጥታ ሚለኒየም አዳራሽ ውስጥ አስገብቶ በመጀመሪያ ለሶስት ተከታታይ ቀናቶች ትምህርት መስጠት ማለትም የሰዶም የገሞራን ታሪክ ማስተማር
2. መስቀል አደባባይ ሰብስቦ በቅዳሴ ስነ ስርዓት ለሶስት ቀናት ያህል በተከታታይ እንዲጠመቁ ማድረግ
3. ጾምና ጸሎት ለሶስት ቀናት ያህል በማስተማር በተከታታይ ለሶስት ቀናት ወደ ቤተ ክርስቲያን እየሄዱ በእድሜእቸው ቁጥር እንዲሰግዱ ማድረግ

ከዛም ሶስት ቀናት በሐጂዎችና በኢማሞች በካምቦሎጆ መሰረታዊውን ከአላህ የተቀበልነው የተፈጥሮ ሕግጋት እንዲገለጽላቸው ማድረግ
በመቀጠል የገዳ አባቶች ለ5 ቀናት በቢሾፍቱ ሆራ አካባቢ መሰረታዊውን የፈጣሪን ሕግጋት በየመልኩ እንዲያስተምሩዋቸው ማድረግ


ስንት ቀን ቀረ ?


ይህ ነው ቱሪዝም ማለት ፡፡አይደለም እንዴ ?


ከዛስ ተፈውሰው የኢትዮጵያ አድባራት መሪዎችንና የእስልምና እምነት መሪዎችን እንዲሁም የገዳ መሪዎችን አመስግነው ወደ መጡበት ከተመለሱ በሁዋላ የሚያፈቅሩዋቸውን ወጣት ወይም እኩያ ሴቶች ጋር ትዳር ይዘው የልጆች አባት እንደሚሆኑና የቤተ ሰብ ሐላፊ እንደሚሆኑ ተስፋ ያደርጋል ፈላስፋው
አዳምና ሔዋን ማለት ይህ ነው ሌላ ትርጉም የለውምና
በሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን በእንስሳት ዓለምም ይህንኑ ነው የሚመስለው
ለዛም ነው እስከ ዛሬ የሰው ልጅ በሰው ልጅነቱ የቆየው ፡፡
አለበለዚያማ የሰው ልጅ ያኔ እንደተፈጠረ ነበር አቡዋራ ፡የሚሆነው
ለምሳሌ ፈጣሪ አዳምና ሔዋንን ከመፍጠር ይልቅ
አዳምና አዳምን ቢፈጥር የሰው ዘር የሚባል ነገር ያኔ አክትሞ ነበር
ለምሳሌ ፈጣሪ አዳምና ሔዋንን ከመፍጠር ይልቅ
ሔዋንና ሔዋንን ቢፈጥር ኖሮ የሰው ዘር የሚባል ገና ከመፈጠሩ አክትሞ ነበር ፡፡

ለዚህ መሰረታዊ ለውጥ የክርስትና ፡ የእስልምና እና የገዳ እንዲሁም ሌሎችም የኢትዮጵያ ባህላዊ እምነቶች ጊዜያችሁ አሁን ነው

እነዚህን ሰዎች ለማዳን ወደ ፈጣሪ ለመመለስ መንገዱ ቀላል ነው የናንተ ጥረት ብቻ ነው የሚፈለገው ፡፡
ይህንን የናንተን ጥረት የሚፈልግ ከሌለ በቆረጠው ቲኬት በቀጥታ ወደ ሐገሩ ተመልሶ እንደፈለገው መሆን ይችላል መብቱ ነው

ለመፈወስ የሚፈልግ ፡ ለመዳን የሚፈልግ ካለ ግን መፍትሄው በናንተ እጅ ነው
እንደዚህ ያለ ነገር እስከ ዛሬ ድረስ በመላው ዓለም ተደርጎ አያውቅምና ፡፡
ግልጽ ሆነው እንምጣ ካሉ ፡፡ ግልጽ ሆኖ ለማስተማር መጠበቅ መጥፎ ነገር አይደለም ይልቁንስ መልካም ነገር ነው፡፡

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Jun 06, 2019 7:57 pm

Respect
የራስን ትልቅ አድርጎ የሌላውን ማንኩዋሰስ ተገቢ አይደለም
የሰውን ልጅ ሰብአዊ መብት የማክበርም ሆነ የመጣስም ጉዳይ አይደለም በዚህ በተመሳሳይ ጾታ መካከል ባለው ግንኙነት ተቃውሞ ማቅረብ

ተቀበሉኝ ብሎ ማንንም ማስገደድ አይቻልም ይህም ሰብዓዊ መብት መጣስ መሆኑን መዘንጋት ነውና
እንደሆንክ መሆን ትችላለህ ነገር ግን በግድ በሌሎች እምነትና ባህል ውስጥ ገብቶ ደንቃራ ለመፍጠር መሞከር ራሱ ሰብዓዊ መብት መጣስ ነው

የተመሳሳይ ጾታ ያላቸው ግለሰቦች በክርስትና እምነት ውስጥ ለመግባት ቦታ የላቸውም ምክንያቱም የክርስትና እምነት ይህንን ስለማይቀበል
ይህንን የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት በክርስትና እምነት ውስጥ ገብቼ ቅዱስ ቃሉን እንዲሰረዝ ማድረግ አለብኝ ወይም በየቤተ ክርስቲያኑ እየዞርን እንደፈለገን እንሆናለን ከሆነ ነገሩ ፡ ጉዳዩ ሰብዓዊ መብት መጣስ ነው ስለሆነም የሌላውን ባህልና እምነት እንደማጥላላት ይቆጠራል
የራሳቸውን ቅዱስ መጽሐፍ ጽፈው በዛ እምነት ራሳቸውን አጥምቀው መኖር መብታቸው ነው ፡፡ ማንም የሚቃወም የለም የሚቃረንም የለም ፡፡ ነገር ግን ሌላው እምነት ውስጥ ገብተን እንዘባርቅ ካልን ግንወጥ እንደመርገጥ ይቆጠራል ይላል
ፈላስፋው
አበቃ ፡፡
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sat Jun 08, 2019 6:01 pm

ልጉዋዝ ነው እገጠር ልገባ ፡ ልገባ
ልጉዋዝ ነው እገጠር ልገባ ልገባ
ደህና ሁኝ አዲስ አበባ አበባ አበባ
ልጉዋዝ ነው እገጠር ልገባ ልገባ ልገባ

ያለው ማን ነበር ?

ወደ አዲስ አበባ
ኮንዶሚንየም ቤቶች
የፈላስፋው ጥያቄ
የኮንዶሚኒየም ቤቶች በእውነት ለመኖር የሚመቹ ቤቶች ናቸው?
በእውነት እነዚህ ቤቶች ለሕዝቦች ደስታ የሚሰጡ ለልጆች በቂ ጨዋታና ደስታ የሚፈጥሩ ቤቶች ናቸው ቤተ ሰባዊ ፍቅር የሚሰጥ ግምቦች ናቸው ?
እንደዚህ ያሉ በፎቅ ላይ ፎቅ እንደ ባቢሎን ግምብ የሚመስሉ ቤቶች በምድረ አዲስ አበባ ላይ ሲሰሩ በእውነት ለአዲስ አበባ የሆነ ውበት ናቸው ወይስ የሆነ የውበት ጥላ ?

ዛሬ የምናያቸው የኮንዶሚንየም ቤቶች ልክ በፈረንጅ ሐገር ስልጣኔ ውስጥ ራሳችንን ያስገባን እየመሰለን እንደሰት ፡ እንዝናና ይሆን ?
ለመሆኑ በምድረ ኢትዮጵያ በተለይም በየከተማዎቹ የሚሰሩት ቤቶች እንደ ሐገራችን እንደ ጥንቱ የጎጆ ቤቶች ቢሆኑ ምን ይሆን ጥፋቱ ?
ውበት ፡ ደስታ የሚያመጡት የጎጆ ቤቶቻችን ናቸው ወይስ እነዚህ ሰማይ ጠቀስ እንደ ባቢሎን ግምብ የተሰሩ ፎቆች ?
ለመሆኑ እነዚህ ሰማይ ጠቀስ ፎቆች ልክ ስልጤ ላይ እንደደረሰው የመሬት መሰንጠቅ ወይም የመሬት መንሸራተት እና መንቀጥቀጥ አዲስ አበባም ቢደርስ ምን ይሆን እጣችን ?
የኮንዶሚንየም ቤቶች በአሁኑ ሰዓት አዲስ ናቸው በወረትም በጣም የሚገርሙ ናቸው ከዛም ልክ እንደ አሜሪካ ፎቆች ሰማይ ጠቀስ ሆነው ይታያሉ
ክ20 ዓመታት በሁዋላስ ምን ዓይነት ሆነው ይታዩ ይሆን ?
እንደዚህ ያለ የባቢሎን ግምብ ስራ green area or green terror ነበር እሁንስ ምንድነው ???

የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Sun Jun 09, 2019 8:20 pm

ይድረስ ለታከለ ኡማ
ነገሩን ለሰንበት ተማሪዎች እንደገለጽከው በግምብ ላይ ግምብ በመገንባት ባቢሎን ከመስራት ልጆችን በእውቀት መገንባት ትልቅ ቁም ነገር ነው ፡፡
ለዚህ ግንባታ ደግሞ የሚያስፈልገውን እስኪሪብቶና ደብተር እንዲሁም ዩኒፎርም ለልጆች በቅጡ ማዳረስ ፡ ስራ ለሌላቸው ደግሞ የእለት ጉርሳቸውን የሚያገኙበት መንገድ መፈለግ ፤ ትልቁ የሐገር ስራ ነው፡፡
እንደውም የዳቦ ነገር ከግምብ የበለጠ ቢታሰብበት መልካም ነው ይልሃል ፈላስፋው

እስክንድር ነጋ በሚመለከት
የሆነ ነገር ወዳልሆነ ነገር እየተጉዋዘ ይመስላል

እስክንድር ነጋ ስብሰባ ጠራ
ተከለከለ
እስክንድር ነጋ መግለጫ ሊሰጥ ነው
ተከለከለ
አሁንም እስክንድር ነጋ መግለጫ በሂልተን ሊሰጥ ነው
ተከለከለ

ሰው ባገሩ ሰው በወንዙ ቢበላ ሳር ቢበላ መቅመቆ
ይከበር የለም ወይ ሰውነቱ ታውቆ ይለናል ታሪካችን ፡፡
ስለሆነም ነው የእስክንድር ስራ ከጃዋር ስራ ይለያል የሚባለው ፡፡
የሚለይበትም ሰው ባገሩ ቢበላ ሳር ቢበላ መቅመቆ ፡ ይከበር የለም ወይ ሰውነቱ ታውቆ በሚለው ታሪካችን ነው


ፌዴሬሽኑ በትክክል አልተተረጎመም ምክንያቱን የድምበር ክልሉ በትክክል ስላልሆነ
የሚል ነገር ፈላስፋው መስማቱ ትዝ ይለዋል
በእውነት ድምበር ነው ለፌዴሬሽን መስተካከል ምክንያት የሚሆነው ?
በየፌዴሬሽኑ የተከሰተው የተማሪዎች ችግር የድምበር ጉዳይ ነው ?
እንዴት ነው የድምበር ክልል ትክክለኛ ክልል የሚሆነው?
ማነው ድምበር የሚያካልለው ? ዩናይትድ ኔሽን ወይስ የሐገር ሽማግሌዎች ወይስ መንግስት ?

በነገራችን ላይ አንድ ነገር በሐሳብ መልክ ከአንድ ፓርቲ ሲቀርብ ከነመፍትሄው ቢሆን እንደ ትልቅ የሐገር ስራ የሚቆጠር ነው፡፡ ትክለኛም ነው ፡፡ ነገር ግን የራስን ሐሳብ ወርውሮ መልሱን ከመንግስት እንደ ወር ደሞዝ መጠበቅ ግን ቅጥረኛ ሰራተኛ ነው ነው እንጂ የፖለቲካ ፓርቲ የሚከተለው መርሃ ግብር አይደለም
አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ራሱ መንግስት ነው፡ የሐሳብ የበላይነት አለ ሲባል ጥያቄ እቅርቦ መንግስት ይመልሰው ሳይሆን ራሱ ላቀረበው ጥያቄ መልስ ሲኖረውም ጭምር ነው ፡፡ በዚህ በሐገራችን ሁኔታ ምርጫ ውስጥ እገባለው የሚል ፓርቲ በሙሉ መፍትሄ የመፈለግ ግዴታ እንዳለበትት ፈላስፋው ሲያስገነዝብ ይወዳል
አይደለም ፡፡

የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Jun 20, 2019 4:57 pm

ትክክል በማለት ፈላስፋው ይጀምራል ፡፡
1. ሞተረኞች ያኔም ተከልክለው ነበር ፡፡ አሁንም መከልከላቸው ትክክል ነው፡፡
2. በዩቱቦ እስክንድር ነጋ ላይ የዛቻ ቃል የፈጸመው ግለሰብ ለሕግ መቅረብ አለበት ፡ ለህግ መቅረቡ ደግሞ በይፋ መገለጽ ይኖርበታል፡፡ እንደዛ ካልሆነ ነገም እንደዚህ ያለ የሰውን መብት የሚጥስ የፈስቡክ እና የዩቱቦ ቱሪናፋ ይቀጥላልና

ወደ ዋናው ነጥብ
የሐሳብ ጦርነት ፡፡
ስለ ሐሳብ የበላይነት ስናወራ ፡ ስለ ውይይት እና በሐሳብ ስለመተማመን ነው ፡፡
የሐሳብ ትርምስምስ እና ወከባ በዚህም በዛም እንዳለ መዘንጋት ደግሞ እይኖርብንም
ለምሳሌ " የትግራይ ሕዝብ ለመገንጠል አስቦ ነበር" የሚለው አስተሳሰብ በጣም ውዥንብር የሚፈጥር ሐሳብ ብቻ ሳይሆን ወሬም ነው ወይም "ሞገድ" ነው ፡፡
ሐሳብና ፡የወሬ ሞገድ የተለያዩ ነገሮች ናቸው ፡፡
ታስባለህ ትቀዳለህ ፡ ወሬ ነው ቱሪናፋ ነው
ታስባለህ ትወያያለህ ከዛም ትተማመናለህ ደግሞ ሌላ ነው የሐሳብ የበላይነት በመተማመን ማለት ነው ፡፡
ወሬ የትም ይቀደዳል ለማንም ይቀደዳል ፡፡ በተለይም ማይክሮፎን አፍ ስር ካለ ቀደዳው የበለጠ ቀደዳ ነው የሚሆነው ፡፡
ሐሳብ ግን አንድን ነገር በተግባር ለመፈጸም የሚደረግ ንድፍ ነው፡፡ በንድፈ ሐሳብ መሰረት አንድ ተግባር በስራ ላይ ይውላል፡፡
ሐሳብ ብዙ ጊዜ ማይክሮፎን አይፈልግም ፡፡
ይህ የወሬ ውዥንብር ለመላው ኢትዮጵያዊ እና ለራሱም ለ ተናጋሪዊም ዝብርቅርቅ ውዥንብር ነው፡፡
የሐሳብ ጦርነት ዛሬ በዲጂታል ዓለም አይደለም የተጀመረው ፡፡
ስው ሊረዳው የማይችለውን ወይም የሆነ ውሸት ነገር ከቀደዱ በሁዋላ ሰሚው ሕዝብ ወይም ሰሚው ግለሰብ ምን እንደሚሆን መታዘብና መመልከት አንዱ የሐሳብ ጦርነት ዘዴ ነው ፡፡
ሲደናበር ማየት፡ ወይም የተቀደደው ቀደዳ እንደ ፒንግፖንግ (ping- pong ) በፈስ ቡክ ሲዘበራረቅ ማየትና በዩ ቱቦ ሲተረማመስ መስማት ለቀዳጁ ታላቅ ደስታን የሚፈጥር የሳይኮሎጂካል ኤረር (Psychological error) ነው ፡

ለምሳሌ በዩ ቱቦ ላይ የምታዩዋቸው የመግቢያ የቀደዳ ጽሁፎች ለዚህ ምሳሌ ናቸው " አስደንጋጭ ወሬ " አስደሳች ወሬ "
"አርቲስቱ የብር ረብጣ ከሂሊኮፕተር ወረወረ"
" አርቲስቱዋ ሽንት ቤቱዋን ጨረቃ ላይ ገነባች ሽንቱ ወደ መሬት እንዲፈስ "
" ዘፋኙዋ አስቃለሁ ብላ ፈሱዋን ረጨችው" የመሳሰሉት አተላ የሆኑ የዩ ቱቦች መግቢያ አርስቶች ለዚህ የሐሳብ ጦርነት እንደ ምሳሌ ሊጠቀሱ የሚችሉ ናቸው
በሌላ በኩል ደግሞ
ዝምታ ሌላው የሐሳብ ጦርነት ዘዴ ነው ፡፡ እንደ ጎሬላ አድፍጦ የሐሳብ ጦርነትን እንደመክፈት ይቆጠራል
ባንክ ተዘረፈ ፡ ሰው ተገደለ ሲባል ሐላፊነቱ የኛ አይደለም የሌላ ነው በማለት እንደ ጲላጦስ እጅ መታጠብ የኢትዮጵያን ሕዝብ የሐሳብ ጦርነት ውስጥ መክተት ማለት ነው
ሕዝብ ሲተረማመስ ሌላው አድፍጦ ለጠረባ መዘጋጀት ይሉሃል ይህ ነው፡፡ ወይም ደንታ ቢስነት ይሉሃል ይህ ነው፡፡
አሁን በጋራ ማስተካከል ያልተቻለውን በሁዋላ ከምርጫው በሁዋላ ይስተካከላል ብሎ በማሰብ ለምርጫው መቁዋመጥ ነገር አለ የሚያስብል ይሆናል፡፡ እውነትም ነገር አለ፡፡ ባልተረጋጋ የጎጠኛ የፖለቲካ አመለካከት ለምርጫ መቁውዋመጥና ስለ ምርጫ ማውራት ሌላው የሐሳብ ጦርነት ነው ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን የሐሳብ ጦርነት የሚያሸንፍበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም
የኢትዮጵያ ሕዝብ ልዩነትና አንድነት ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Jul 11, 2019 7:28 pm

አንድ ጥያቄ አለኝ
ልዩ ጥቅም ሲባል ፡ ተጠቃሚ ሲባል ?
በአዲስ አበባ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ፡ የመሬት ግብር ቢከፍሉ ለቆሻሻ መኪና ቢከፍሉ ፡ለውሃ ፡ለመብራት ቢከፍሉ ለማነው ጥቅሙ?
ለመንገድ ስራ ገንዘብ ቢከፍሉ ለማነው ጥቅሙ?

ለመሆኑ እስከዛሬ ያልነበረ ታሪክ ለምን ዛሬ ተጀመረ ?
አዲስ አበባ የተሰራቸው በመላው የኢትዮጵያ ልጆች፡ ጥቅሙዋም ጉዳቱዋም ለኑዋሪዎቹዋ አይደለም እንዴ ?
አዲስ አበባ ለመኖር የሚመጣ የሌላ " ብሄር " ሰው የተለየ ግብር መክፈል ሊኖርበት ነው ?
የውሃ ጉዳይ ስለገረመው ፈላስፋው እንደ ምሳሌ ወስዶታል
የገፈረሳ ውሃ ለአዲስ አበባ ሕዝብ ይዳረሳል
ለዚህም የአዲስ አበባ ህዝብ ግብር ይከፍላል የውሃ ይከፍላል
ይህ የሚከፈለው ግብር ለውሃ ክፍል ሰራተኖች የውሃ ጽዳቱን እንዲጠብቁ የቱቦ መስመር እንዲዘረጉ ለመሳሰሉት ስራ ይውላል፡፡
ታዲያ ምንድነው አዲስ ነገር " ልዩ ጥቅም " ሲባል ?
የዓባይ ወንዝ ወደ ግብጽ ይፈሳል ግብጽ ለኢትዮጵያ የምትከፍለው ነገር ይኖር ይሆን ወይስ ልዩ ጥቅም ይኖር ይሆን ?
የገፈርሳን ውሃ የሚጠጡት እኮ የኢትዮጵያ ልጆች ናቸው ለዚህም የውሃ ግብር እየከፈሉ
ቆሻሻን ማስወገድ የሚያስችል ጥበብ ወይም ቴክኒክ መስራት ሌላ ነገር ስለ ጥቅማ ጥቅም ማውራት ሌላ ነገር
ውሃ የአዲስ አበባ ሕዝብ መጠጣት የለበትም ማለት ይሆን ? ምክንያቱም የአዲስ አበባ ሕዝብ ???
ስለ ስራ ጉዳይ የተማረ መስራት ይችላል ዘበኝነትም ፡ ችግኝ ተከላም ቢሆን ፡ ይህ ደግሞ አዲስ አበባ ብቻ መሆን የለበትም
ሁሉም በኢትዮጵያ ከተሞች የመስራት የመኖር መብት ማግኘትት ይኖርበታል ይህ የሚሆነው ደግሞ
የጥንታዊ የጋርዮጭ ዘመን ፖለቲካ የሆነው የጎሳ ፖለቲካ ሲደመሰስ ብቻ ነው፡፡

በአምቦ የአምቦ ነዋሪ ውሃ ይጠጣል፡ በውሃ ልብሱን ያጥባል ፡ ቆሻሻ ይጥላል ፡ ለዚህ ሁላ ግብር ይከፍላል
ለኦሮሞ ሕዝብ ጥቅም ነው ወይስ ለአምቦ ነዋሪዎች ማለት ይሆን ?
በባህርዳልም እንደዚሁ፡፡ ምንድነው ልዩ ጥቅሙ ለአማራ ሕዝብ ወይስ ለባህርዳር ነዋሪዎች ?
በመቀሌም እንደዚሁ፡፡ ምንድነው ልዩ ጥቅሙ ለትግራይ ሕዝብ ወይስ ለመቀሌ ነዋሪዎች ?
አዲስ አበባ ውስጥ የሚኖረው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው ስለሆነም ለነዋሪዎቹዋ ጥቅም ፡ ደህንነት እና ጤና ብቻ ነው ስለአዲስ አበባ መወራት ከተፈለገ መወራት የሚገባው
የጎጠኛ ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አያስፈልግም
ልዩነታችንና አንድነታችን ለዘላለም ይኑር
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri Jul 26, 2019 9:08 pm

ችግሩ በዓል ማክበሩ አለማክበሩ ይሆን ?
ለምን የደመራ በዓል በአዲስ አበባ ይከበራል ?
ለምን የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ይከበራል ?
ለምን የኢድ አልፈጥር በዓል በአዲስ አበባ ይክበራል ?
ለምን የእሬቻ በዓል በአዲስ አበባ አይከበርም ?
ልዩነቱ የደመራና የጥምቀት በዓል የእምነት በዓል ሲሆኑ በዚህ እምነት የሚካተተው ደግሞ አብዛኛው ብሄር በመሆኑ ከዛም አዲስ አበባ የሁሉም ብሄር መናሀሪያ በመሆኑዋ
በኢድ አልፈጥር በዓል የሚካተተውም አብዛኛው ብሄር በመሆኑ ከዛም አዲስ አበባ የሁሉም ብሄር መናሀሪያ በመሆኑዋ
ይህ ሁኔታ ባልተማሩት የኢትዮጵያ መሪዎችና ባለስልጣናት ታስቦ የተደነገገ ነው ፡፡ ይህ ድንጋጌ ማንንም ብሄር ለመበደል ወይም ለመርገጥ አይደለም ፡፡
የተማሩት ባልስልጣናት እንዴት ይሆን የሚያስቡት ? ከዛም የእሬቻስ በዓል ?
የእሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ? እንደ ቁልቢ ገብርኤል እንደ ሐዋሳ ገብርኤል በክርስትና እምነት የሚካተተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያከብረው ይሆን ?
እንደዛ ከሆነ ሁሉም ብሄር በአዲስ አበባ የራሱን ባህላዊ በዓል በየዓመቱ በአዲስ አበባ ማክበር ይኖርበታል ማለት ነው ፡ ታዲያ ባህላዊ በዓሉን ማለቱ ነው ፈላስፋው ለምሳሌ የሱማሌ ነዋሪዎች በአዲስ አበባ ፡ የአፋር ነዋሪዎች በአዲስ አበባ ፡ የጉራጌ ነዋሪዎች በአዲስ አበባ ፡ የትግራይ ነዋሪዎች በአዲስ አበባ ...
ጥሩ ሐሳብ ነው ? አይደለም እንዴ ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Oct 10, 2019 9:46 pm

ቆቁ የጥንት የጠዋቱ:-አሸንዳ፣አሸንድዬ፣ጨምበለላ ሲከበር የት ነበርክ?
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Fri Oct 11, 2019 7:45 pm

እኛ የምናውቀው አበባየሆይ ወይም እንቁጣጣሽ ብለን ነው ፡፡
ሌላ ጣጣ አናውቅም ፡ ስለሆነም
አበባየሆይ እንቁጣጣሽ በአዲስ አበባ የሁላችንም በዓል ነበር ነውም
ሆያሆዬም እንደህዚሁ የመላው አዲስአበባ ልጆች በዓል ነበር አሁንም ነው
ነገሩ ብሄር ጎሳ የሚባል ነገር ተፈጠረና እሬቻ የኦሮሞ አሸንዳዬ የአማራ የትግራይ ተባለና ዝብርቅርቁን አወጣው

ዘርዓይ በአዲስ አበባ የሚኖረው የየትኛውም ብሄርር ልጅ እና ልጃገረዶች ተሰባስበው ነበር ሆያሆዬና ቡሄና እና አበባየሆን የምንጨፍረው
እሬቻንም ቢሾፍቱ ሁላችንም ነበር የምናከብረው
ከዛም አልፎ ራሳቸው ንጉሰ ነገሱት ያከብሩት እንደነበረ ታሪክ ያስረዳል
እሬቻ የኛ ነው
አበባየሆይ የኛ ነው
ቡሄ የኛ ነው
ደመራ የኛ ነው
ጥምቀት የኛ ነው
እኛ የኛ ነን
ፍቅርና ሰላም ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ደስታ ለሁላችንም የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዓቢይ አህመድ የኖቤል ሽልማት ተቀበለ
ምኒሊክ በአድዋ አሸነፈ
ዓቢይ ዓህመድ በስዊድን አሸነፈ

የየትየለለው ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ዘርዐይ ደረስ » Wed Oct 16, 2019 11:12 pm

አቶ ቆቁ፡-ስዊድንም አሸነፈ እንዴ?ኦስሎ የኖርዌይ ዋና ከተማ መስሎኝ ሎል!የዓድዋን ድል ደግሞ ከሆነው ካልሆነው ጋር ማወዳደር አቁሙ!!በተረፈ ከላይ የብሔረሰብ በአላትን በአዲስ አበባ መከበር የሚቃወም የሚመስል ነገር አቅርበህ አሁን ደግሞ ሁሉም የኛ ነው የሚል ማደናገርያ አስነበብከን፡፡አንዱን ምረጥ፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1278
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: አዋሬ የማነው? ፒያሳ አራዳ የማነው?አራትኪሎስ ?ቄራስ ?ካዛንችስስ ጥቅማ ጥቅሙ የማነው

Postby ቆቁ » Thu Oct 17, 2019 7:36 pm

ታዲያስ ነፍሱ
ስማ በአዲስ አበባ የብሄረ ሰቦች በዓል አይከበር ያልኩት እኔ ሳልሆነ አንተ ነህ እንደዛ ያሰብከው ፡፡
ማሰብ ደግሞ አይከለከልም
በአዲስ አበባ የብሄረ ሰቦች በዓል ሳይሆን የኢትዮጵያውያን በዓል ይከበር እንደነበር ፈላስፋው ይናገራል ፡፡
ለምሳሌ በደመራ በዓል የመላው ኢትዮጵያውያን ጨዋታ በመስቀል አደባባይ ይታይ ነበር
በነገራችን ላይ የደመራ መስቀል በዓል የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ በዓል እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል ፡፡
ነገር ግን ሁሉም ኢትዮጵያው በባህላዊ ቁዋንቁዋው፡ ጭፈራው፡ ዘፈኑ ነበር ይህንን በዓል የሚያከብረው
እንቁጣጣሽን ማለትም ወይም አበባየሆይን ወይም ቡሄን የሚያከብረው መላው የኢትዮጵያ ልጆች በአዲስ አበባ የተወለዱ የሚኖሩ ነበሩ ብሄር ብሄረ ሰብ የሚባል መከፋፈል ሳይኖር
እሬቻ እስከሚታወቀው ድረስ የሚከበረው ቢሾፍቱ ነበር ፡ በቡልቡላ ወንዝ ይከበር ነበር የሚል ታሪክ አላነበብንም አልሰማንም አላየንም
ቡልቡላን የአዲስ አበባ ልጆች የሚያውቁት በሌላ መልኩ ነው
ፊንፊኔ ማለትም የፊንፊኔ ውሃ የሚፈላ ህዋ ማለትም የሞቀ ውሃ በመሆኑ ለእሬቻ በዓል ሊሆን ቀርቶ እግርህን ማስነካት የማትችልበት የፈላ የእሳተ ገሞራ ውሃ ነው፡፡
ፍልውሃ ለመታጠብ ሄደህ እንደሆነ እንደዶሮ ቆዳህ ተልጦ ነው እቤትህ የምትገባው ፡፡
ይህንን ስልህ ዘመናዊውን ፍልውሃ ማለቴ እንዳይመስልህ

የኦስሎ እና የስቶክሆልም ነገር እንዲገርምህ አያስፈልግም
አልፍሬድ ኖበል ስዊዲናዊ ነው ስለሆነም እንዴት በኖርዌይ ኦስሎ ሽልማቱ ሊሰጥ ቻለ የሚለው ጥያቄ ምናልባት ስለሐገራችን ሁኔታ ሊያስረዳህ ይችል ይሆናል
የኖበል ኮሚቴ ኖርዌይ ኦስሎ ውስጥ ቢገኝም የሚያስታውሰው ስዊድናዊው አልፍሬድ ኖብልን ነው
አሸነፈ ማለት አሸነፈ ማለት ነው
ስለሆነም እውቅ የሆኑ የኢትዮጵያ ልጆች በዓለም አሸናፊ የሆኑ ሁለት ናቸው ፡፡ በሩጫ ያሸነፉትን ከአበበ ቢቂላ ጀምረህ ልትቆጥር ትችላለህ ነገር ግን
የዓለምን የልብ ትርታ የለወጡ ግን ሁለት ኢትዮጵያውያን ናቸው
ምኒሊክ በአድዋ ዓቢይ በኦስትሪያ ብልህ ምን ትል ይሆን ?
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4307
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot] and 2 guests