ይድረስ ለኢሳት ባልደረቦች፣ በመላው አለም ለምትገኙ የኢሳት ደጋፊዎችና ለነጻ ሚዲያ መኖር ...

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

ይድረስ ለኢሳት ባልደረቦች፣ በመላው አለም ለምትገኙ የኢሳት ደጋፊዎችና ለነጻ ሚዲያ መኖር ...

Postby የሓውዜን ቅሌት » Thu Jun 06, 2019 3:03 pm

ይድረስ ለኢሳት ባልደረቦች፣ በመላው አለም ለምትገኙ የኢሳት ደጋፊዎችና ለነጻ ሚዲያ መኖር የምትታገሉ ዜጎች ሁሉ

June 5, 2019


በኢሳት ውስጥ የተከሰተውን ችግር አስመልክቶ በተለያዩ የመልክት ማድረሻ ዘዴዎች ምላሽ እንድሰጥ ጠይቃችሁኛል።
አሁን አዲስ አበባ የነበረኝን ስራ ጨርሼ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ አሜሪካ ስለምመለስ ነገሮችን በተገቢው መልኩ እውነታውን ለህዝብ እንደማሳውቅ ቃል እገባላችኋለሁ።

ኢሳት ከለውጡ በኋላ ያጋጠመው ከባድ የገንዘብ ችግር እየተንከባለለ መጥቶ ከጊዚያዊ ችግሮች ጋር ተዳምሮ ሁኔታው ለአደባባይ እንዲበቃ አድርጎታል።
በሌላ በኩል በተፈጠረው ችግር ልባችሁ የተሰበረ ወገኖች በትግል ውስጥ መውደቅ መነሳት የነበረና የሚቀጥል ነውና አሁን ብንወድቅ አቧራውን አራግፈን ተነስተን ወደፊት እንራመዳለን እንጅ እንደወደቅን የምንቀር አይደለንምና ተስፋ አትቁረጡ።
ኢሳት ሞተ፡ ቀብሩ ተፈጸመ እያላችሁ ሟርት ቢጤ የተናገራችሁም የእናንተ ሟርት የበለጠ እንድንሰባሰብ እንድንነጋገር በር ይከፍትልናልና በሟርታችሁ ቀጥሉበት።

በተረፈ በተለያዬ ጎራ የተሰለፋችሁ የኢሳት ባልደረቦቼ ለኢሳት ማደግ ቀን ከሌሊት የደከማችሁ ደጋፊዎቻችን ያለምንም ክፍያ ለዘጠኝ አመት የሰራችሁ የቦርድ አባሎች የተነሳነው እዚህ ለመድረስ አይደለምና ከጊዚያዊ ስሜት በመውጣት ለመጨረሻ ጊዜ በአካል ተገናኝተን ለችግሩ መፍትሄ እንድንሰጥ እኔ እስክመጣ ድረስ የአደባባይ ምልልሶችንም ሆነ ምንም አይነት መግለጫ እንዳትሰጡ አብረን ታግለን ያሳለፍናቼውን የመከራ ቀኖች እያስታወስኩ በቅንነትና በትእግስት እንድትጠብቁኝ እለምናችኋለሁ።
ካሰብነው ሳንደርስ አንቆምም!!!!!!

ታማኝ በየነኢሳት ከለውጡ በኋላ ያጋጠመው ከባድ የገንዘብ ችግር እየተንከባለለ መጥቶ ከጊዚያዊ ችግሮች ጋር ተዳምሮ ሁኔታው ለአደባባይ እንዲበቃ አድርጎታል።


Hmmm ..., that sounds not credible. Also because of that Reyot interview and ESAT's reluctance to criticize the Abiy regime prior to that interview.
"He who refuses to be involved in politics must endure being ruled by inferior people."
Plato
የሓውዜን ቅሌት
ዋና ኮትኳች
ዋና ኮትኳች
 
Posts: 723
Joined: Fri Jul 16, 2010 4:42 pm

Re: ይድረስ ለኢሳት ባልደረቦች፣ በመላው አለም ለምትገኙ የኢሳት ደጋፊዎችና ለነጻ ሚዲያ መኖር

Postby ቢተወደድ1 » Fri Jun 07, 2019 11:01 am

ግብጽ በኤርትራ በኩል የምትልከውን ገንዘብ ስላቆመች ተብሎ ቢነገር ተአማኒነት ይኖረዋል፡፡
ድሮም ውሽት አሁንም ውሸት፤ ዋደፊትም ውሸት፡፡ ልክ ሌባ ሲካፈል እንደሚጣላው ቂቂቂ
የኔ ጥያቄ ግን፤ ምነው ኢሳት የመሽረፈትን መንግስት የሚያጠፋውን ስህተት ማጋለጥ ፈራ???
ወደፊት የምናያት ኢትዮጵያ ምን አይነት መልክ እንደምትይዝ ከወዲሁ መገመት ይቻላል፡፡
ኦነግ በእጅ አዙር እየበጠበጠው ነው፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 326
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu


Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests