ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !!!

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Fri Jul 26, 2019 9:50 pm

ይድረስ ለበቀለ ገርባ
ሐይል ማለት ምን ማለት ነው ?
የሲዳማ ችግር የአሁኑ አመራር ችግር እንደሆነ ማቅረብህ በጣም የሚያሳዝን ነው ፡፡
1. ችግሩ ራስህ እንደገለጽከው አንተው ተሰብስበህ አንተው ፈርደህ ለዚህ ያደረስከው ሕገመንግስት ነው
2. በጥንታዊ የጋርዮሽ ስርዓተ ማህበር ሲካሄድ የነበረውን የክልል ማህበረ ሰብ አንተና የመሳሰሉት እንደገና በኢትዮጵያ እንዲፈጠር ስላደረጋችሁ ነው ፡፡
ያን ጊዜ እናንተ ስተሰበሰቡ ፡ ሕግና የመሳሰሉትን ስታወጡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግራ ገብቶት ይመለከታችሁ ያዳምጣችሁ ነበር ፡፡
ግራ የገባውም በእጁም በደጁም ምንም ስላልነበረ፡ መናገር ስለማይችል ፡ ሰላማዊ ሰልፍ መውጣት ስለማይችል ፡ ለሐገሩ መጮህ ስለማይችል ፡ ነበር ፡፡ ምክንያቱም እናንተ በሐይል ታጅባችሁ ሰፊው ሕዝብ ግን ባዶ እጁን በመሆኑ፡ ደርግ እንዳይ'ጮህ እንዳይናገር አድርጎ ስለቀጠቀጠው ፡፡
በአንድ ትልቅ ሐይል አፉን ተለጉሞ ጆሮው ተደፍኖ ነበር ይህ የጎሳ ክልል በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የታወጀበት ፡፡


ከዛስ ? አንተን ራስህ ይዞ ወደ ወደ እስር ፡ ሌሎችንም አስከትሎ ወደ ወህኒ ?

የኢትዮጵያ ሕዝብ አንተ ከእስር እንድትፈታ ሲጥር የነበረው ለምን እንደሆነ የዘነጋህ ይመስላል?
ለምን ነበር ?

ያኔ ዲሞክራሲ ነበር ነው የምትለን ? ?
ያኔ የተሰበሰባችሁት በሕዝብ ተመርጣችሁ ነበር ነው የምትለን?
ለመሆኑ እናንተ ያወጣችሁት ክልላዊ መስተዳደርና ሕገመንግስት ከአሃዳዊ ስርዓት ሕገመንግስስትና አስተዳደር የሚለየው በምንድነው ?
አሃዳዊ ስርዓት በክፍለ ሐገር እና በወረዳ እናንተ በክልል በጎሳ ፡ የአሰራር ልዩነት ይኖር ይሆን ? ጫና አይደለም ?

ህዝባዊ ምርጫ ባልተከተለ ድርጅት ዲሞክራሲያዊ አሰራር አለ ማለት ባዶ ነገር መሆኑ ቢታወቅም፡ የተሰራው ስራ መልካም ቢሆን ኖሮ
አንተም ወደ እስር ቤት ባልሄድክ ነበር ሕዝባዊ ዓመጽም ባልተነሳም ነበር፡፡

ችግር አለ ችግር የለም አይባልም ፡፡ ችግር ፈጣሪውን ለማወቅ ግን የግድ ብዙ ትምህርትም ሆነ ልሂቅ መሆን አያስፈልግም፡፡

ፌዴሬሽንም በለው ጠቅላይ ግዛት የመድበለ ፓርቲ ሲስተም ብቻ ነው ለኢትዮጵያ ህዝብ አማራጭ
የጎሳ ፖለቲካ የጥንታዊ ጋርዮሽ ስርዓተ ማህበር ፖለቲካ ነው
በልዩነታችን እና በአንድነታችን እንኖራለን
ፈላስፋው

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4175
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Tue Jul 30, 2019 9:08 pm

የልሂቃን የውይይት መድረክ
በቀለ ገርባ ወይም ሕዝቅኤል ጋቢሳ ወደ ባህርዳርም ሄደው ኮንፈረንስ ቢያደርጉ መልካም ነው ፡፡
የመቀሌ ልሂቃን በባህርዳር
የባህርዳር ልሂቃን በመቀሌ
የጅጅጋ ልሂቃን በአዳማ
የአዳማ ልሂቃን በጅጅጋ
እያሉ እንደ ክረምትና በጋ ወራት እየተለዋወጡ ኮንፈረንስ ቢያደርጉ ጥሩ አይደለም እንዴ?
ልሂቃኖች እንደ ከብት አትመሩ ፡ ራሳችሁን አስተካክላችሁ በየትኛውም የኢትዮጵያ ምድር ኮንፈረስን ውይይት የመሳሰሉትን ለማድረግ የህሊና ብቃት የመንፈስ ጥንካሬ እና የወንድማማችነት ፍቅር በላያችሁ ይደር ፡ ዓሜን

የልሂቃን ኮንፈረንስ ለወንድማማችነት ለፍቅር ለበጎ ስራ ቢሆን ይመረጣል፡፡ የጎሳን የበላይነት እንደ ፖለቲካ መስመር ቆጥሮ ለመዘባረቅ ከሆነ የትምህርት ትርጉሙ ለፈላስፋው ግልጽ አይደለም ፡፡
ጤና ካለ ፡ከዛ ደግሞ ደህነንት ካለ ፡የሚፈለገው ወንድማማችነት ነው በዚህ መመሪያ መሰራት ሕዝቦች በጤና በደህንነት እና በወንድማማችነት እንዴት እንደሚኖሩ የሚቻልበትን መስመር ይመስላል ሁሉም ተምሮ ልሂቅ የሆነበት መንገድ፡፡ አይደለም እንዴ ?

የችግኝ ተከላ
ማንነው የጀመረው እያልን እንነታረክ እንዴ ?

ምኒሊክ ነው የጀመረው፡፡ ለዚህም ምሳሌ የማይረሳው የባህርዛፍ ተክል ነው ባህርዛፍን የማያውቅ ካለ አዝናለሁ ወይም ለማወቅ የሚፈልግ ከሌለ በጣም ነው የማለቅሰው ፡፡ ባህርዛፍ ለማገዶ ፡ባህርዛፍ ለጉንፋን ፡ባህር ዛፍ ለቤት ስራ፡ ባህርዛፍ ለስንቱ፡
ዋ ምኒሊክ ለሐገርህ ለወገንህ ታስብ ነበር እንዴ ?
ደርግም ደሞዝተኛ ቀጥሮ ማለትም የስራ እድል ከፍቶ የባህርዛፍ ችግኝ ያስተክል ነበር ይላሉ የታሪክ ጸሐፊዎች፡፡ ይህ የሆነውም ከእድገት በሕብረት ዘመቻ በፊት ወይም አካባቢ እንደሆነ የታሪክ ሰዎች ይናገራሉ

እገሌ ነው በመጀመሪያ ያመጣው፡ እገሌ ነው በሁዋላ ያመጣው፡ እየተባለ የጎሪጥ ከመመለካከት እናት ምድር ፡ እናት ተፈጥሮ እደጊ ተመንደጊ እያልን ያገኘነውን ችግኝ ተክለን ከተፈጥሮ ጋር አብሮ ለመኖር ብንሞክር የተሻለ አይሆንም ፡፡

እይ የጎሳ ፖለቲካ
እኛ ነን አንደኛ ፡ እኛ ነን ልሂቃን ፡ እኛ ነን ፡ እኛ እኝ የሚለው ጨዋታ ቀርቶ ክተፈጥሮ ጋር በሰላም ለመኖር የሚደረግ ጥረት የሁሉም ግለሰብ ግዴታ ነው ይህም የሚሆነው በመንግስት ትእዛዝ ወይም እገሌ ነው የጀመረው በማለት ሳይሆን ዝም ብሎ ሰው በሰውነቱ ከተፈጥሮ ጋር አብሮ መኖርን በማወቁ ብቻ የሚተገበር ድርጊት ነው፡፡ እይደለም እንዴ ?

የጎሳ ፖለቲካ ከምድረ ኢትዮጵያ ይጥፋ
የጎሳ ሕገመንግስት ይሰረዝ
ፈላስፋውው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4175
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Sun Aug 04, 2019 8:00 pm

ሕገ መንግስቱ ይከበር አሉ ልሂቃኖች ተሰብስበው፤ እንደውም በቃለ መጠይቅ ላይ ዱላ ቀረሽ ንግግር ይመስላል በዚህ ጉዳይ ላይ ፈላስፋው የሰማው
እንዴት ይከበር ለሚለው ጥያቄ ግን መልስ የለም
እንዴት ነው ሕገመንግስቱ በጎሳና በብሄር በተከፋፈለና በተካለለ ሐገር የሚከበረው ?
ማነውስ ይህንን ሕገመንግስት የሚያስከብረው ?
ሕዝብ ግዴታና መብቱን ሲያውቅ ወይስ በአዳፍኔ ሕዝብን በመዘወር ?
ልሂቃን ሆይ እስቲ ሐሳብ ካላችሁ መንዝሩ
1. ሕገመንግስቱ የሚከበረው ክልል በመስራት ይሆን ?
2. በእሩምታ እና በዱላ `በአዳፍኔ ይሆን ?
3. በወሬ እና በመግለጫ ይሆን ?
4. ወይስ መልሱ የለም ?
ለመሆኑ ሕጉን እያፈረሰ ያለው ማነው ?
ሁለት ነገሮች አሉ
1. መንግስት ሕግን ሲያፈርስ ሕዝቦች ሕግን ሲያከብሩ
2. መንግስት ሕግን ሲያከብር ሕዝቦች ሕግን ሲያፈርሱ
የትኛው ምህዋር ላይ ነው እኛ የምንገኘው ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4175
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ተገዳደሉ ? ገደሉዋቸው ? ገደሉት? ገደላቸው? እንጠይቅ ? አንጠይቅ? ነፍስ ይማር !

Postby ቆቁ » Wed Aug 07, 2019 8:14 pm

ኩሽ የሚባል ነገድ?

እንዴት ነው ታሪክ ወደ ጋርዮሽ ዘመን በጸሐይ ፍጥነት እየተጉዋዝን ይመስላል

የሴም ነገድ በኢትዮጵያ አለ እንዴ ?

ከብሄር ወደ ጎሳ ይሉሃል ይህ ነው መሰለኝ

ከዛም ወደ ቤተ ሰብ
ኩሽ ማንን ወለደ ?
ሴም ማንን ወለደ
የሴምና የኩሽ አባትና እናት እነማናቸው ?
ወጀ ጉድ የታሪክ ፕሮፌሰርነት? ይህ እኮ ታሪክ ታሪክ ነው ?
የሴም ትውልድ ከጨረቃ የኩሽ ትውልድ ከማርስ ይሆን የመጡት
Semitic,Cushitic, Omotic, and Nilo-Saharan. የቁዋንቁዋው ክፍፍል ይህንን ይመስላል ከዚህ በመነሳት ይሆን ?
ትውልዱ
Noah had three sons born to him,Shem Ham, and Japheth
ከዛ በመቀጠል
Ham, the youngest of Noah’s three sons, had four sons: Cush, Mizraim (Hebrew for “Egypt”), Put, and Canaan
ከዚህ የትውልድ ታሪክ እንደምንማረው ሴም የኩሽ አጎት እኮ ነው ፡፡ ኩሽ እኮ የሴም ወንድም ሐም ልጅ ነው ፡፡ ሁሉም እኮ ከኖህ የተወለዱ ፡፡ አይደለም እንዴ ?
እዚህ ላይ ታዲያ የአንድ ትውልድ ልጆች አብሮ መኖርን ወይስ መናቆርን ?

ፈላስፋው
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4175
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: Google Adsense [Bot], MSN [Bot] and 4 guests