ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Mon Nov 11, 2019 6:41 pm

በሰላም ግቡ ብለህ ያስገባሃቸውን በሰላም ውጡ ብለህ በእቅፍ አበባ ብትሸኛቸው ሁሉም ነገር ሰላምና ፍቅር ይሆናል
ፍቅር ያሸንፋል ፡

አንድ ነጥብ ከዶክተር ዳኛቸው
ማኪያቬሊ የተፈላሰፈበትን ፖለቲካ ምኒሊክ በትክክል ተርጉሞታል ፡፡
ይህንን የማኪያቬሊ ፍልስፍና ምኒሊክ ሊተረጉመው የበቃው ከገዳ ስርዓት ሲወርድ ሲዋረድ በቀሰመው የአመራር ስልት ነው ፡፡
ለዓቢይ የምለው ፡ ዶክተር ዳኛቸው በትክክል እንዳስቀመጠው ወደ ፍሎረንስ ( ቶስካና ጣሊያን) በሐሳብ መጉዋዝ የሚኖርብን አይመስለኝም፡፡ ብንጉዋዝም ክፋት የለውም እንደውም ትክክል ነው፡፡ ነገር ግን እዚህ እትብታችን የተቀበረባት ፡ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ የምንሆንባት ፤ የፍልስፍና እና የፖለቲካ ትንታኔ የበቀለባት፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሐገር ስላለችን


አንድነታችንና ልዩነታችን ለዘላለም ይኑር
ልዩነታችንና አንድነታችን ለዘላለም ይኑር

ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4145
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Tue Nov 19, 2019 10:33 pm

የስራ ቁዋንቁዋ
ቁዋንቁዋ መግባቢያ ነው ፡፡ የስራ ቁዋንቁዋ ሆኖ መደንገጉ መልካም ነው ፡፡ ሁላችንም የሐገራችንን ቁዋንቁዋ ለመናገር ካልሆነም ለመስማት ብንችል ምንም ክፋት የለውም ፡፡እንደውም የደስታ የሳቅ ምንጭ ለመሆኑ ብዙም መናገር አያስፈልግም ፡፡
በጉልበት ጫና ግን ተናገር ካልተናገርክ ግን ጥፋ የሚል ከሆነ ግን ራሱ ቁዋንቁዋ ነው የሚጠፋው ይላል ፈላስፋው

እዚህ ላይ ፈላስፋው እስከ ዛሬ ድረስ ቁዋንቁዋን በተመለከተ የተመለከተው እና የተገነዘበው ጉዳይ አለ
ኢትዮጵያ የ80 ቁዋንቁዋ ባለሐብት ምድራችን ነች ፡፡
እኔን ያልገባኝ ነገር ግን የፌዴራሊዝሙን ስርዓት " በብሄር ብሄረሰቦች ሕዝቦች " በሚል የተደናበረ ቃል ሲመራ የነበረው የህወሃት ቡድን መቀሌ ሲገባ በትግርኛ ፡ ኦነግ ከድርጅቱ ደጋፊዎቹ ጋር ሲወያይ በኦሮምኛ ፡ መሆኑ የታወቀ ነው '፡፡ መሆንም የሚገባው ነው ፡፡ በዚህ ጠብ የለም
ነገር ግን በአንዲት ኢትዮጵያ፡ 80 ቁዋንቁዎች በሚነገሩባት ሐገር ውስጥ አማርኛ ለሚችለውም ሆነ አማርኛ ለማይችለው ሕዝብ በሙሉ በነጻነት የሚንቀሳቀስ የአስተርጉዋሚ ቡድን መመስረት ይኖርበታል ባይ ነው ፈላስፋው
ስለሆነም የሆነ የሊንጉስቲክ ቡድንና ጋዜጠኛ በልዩ ስልጠና ሰልጥኖ በየትኛውም ቀዳዳ በመግባት የፖለቲካ አስተያየቶችን ፡ የፖለቲካ ውይይቶችን ፡ ክርክሮችን የመሳሰሉትን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የማቅረት ችሎታ እንዲኖር መንግስት በአክብሮት ይጠይቃል ፈላስፋው ፡፡
ለምሳሌ ፡ በካናዳ በእንግሊዘኛ የተቀደደውን በፈረንሳይኛ ፍጥጥ ብሎ ታገኘዋለህ ፡ በአሜሪካ በእንግሊዘኛ የተቀደደውን በአረብኛ ፍጥጥ ብሎ ታገኘዋለህህ
ለምንድነው በኛስ ሐገር እንደዛ የማይሆነው ?
ይህ ለኛ ሐገር ትልቅ ትምህርት መሆን ይገባዋል ፡፡
የሊንጉስቲክ ባለሙያዎች በተለያዩ ቁዋንቁዋዎች ሰልጥነው በየጥጋ ጥጉ ዜናዎችን በማቀናበር የተለያዩ ቁዋንቁዎችን በተለያየ ቁዋንቁዋ በመተርጎም ለሕዝባችን ማቅረብ የሚችሉ ባለሙያዎችን ሐገራችን ኢትዮጵያ ማፍራት አለባት እላለሁ
እስከ ዛሬ ድረስ የምንስሰማቸው የፖለቲካ ዝንባሌዎችና ሹክሽክታዎች በድብቅ በሞባይል የተቀዱ ጉዳጉዶችን ነው ፡፡
የምናያቸው ፎቶግራፎችና ሌሎችም ነገሮች በድብቅ የተነሱ ፎቶውች ናቸው
እንደዛ መሆን የለባትም ሐገራችን ፤ በትክክል በዲሞክራሲ ስርዓት እንጉዋዝ ከተባለ ለምሳሌ ጃዋርም ቢያንስ ቢያንስ የሶስት ቁዋንቁዋ አስተርጉዋሚዎችን ይዞ ወደ መድረኩ ብቅ ማለት ይገባዋል ፡ ደብረ ጽዮንም እንደዚሁ ፡ ሌሎችም እንደዚሁ ማለት ነው
በድብቅ እና በሹክሽክታ የሚገነባ ሐገርም ፌዴራሊዝምም የለም አይኖርምም

ይህ ሲሆን ብቻ ነው በምድረ ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መብት ተከብሮ አንድነታችን ከልዩነታችን ጋር ተመሳጥሮ
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ልትሆን የምትችለው

የሹክሹክታ ዘመን ያብቃ .ለሌላው በማይገባው ቁዋንቁዋ ስለ ፖለቲካ መቅደድ ብልግና ነው ፡፡ ነውር ነው፡
በሐገራችን ቁዋንቁዋ ለመግባባት እንታገል፡
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር

ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4145
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Fri Nov 22, 2019 9:32 pm

ዛሬ ብቅ ብዬ የልደቱ አያሌውን ንግግር ሳዳምጥ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ፡፡

በነገራችን ላይ ቢትወደድ ጥርስ ከሌለው ጅብ ጋር ተድበልብለህ እስከ መቸ ትታሻለህ?
ወደ ቁም ነገሩ
ሰመሐል መለሰ ዜናዊ በዛ ግርግር( ጡረተኞቹ ግራ በተጋባቸው ወቅት ) ውስጥ በተደረገው በሆነ ኮንፈረንስ ላይ አቦይ ስብሃትን አንተርሳ ለበረከት ስምኦን ጥያቄ አቅርባ ነበር ፡፡
" ለኛ ለወጣቶቹ ስልጣን ብታዘዋውሩስ በማለት አቦይ ስብሃት ነጋን እየጠቀሰች ፡ ከዛም በረከት ስምኦን እያነጣጠረች ነበር ይህንን የጠየቀችው "
ሳቁባትና ጃምፕ አሉዋት ፡፡ ማንም መልስ ለመስጠት የፈለገ አልነበረም ፡፡
በዚሁ ያበቃል ስብሰባችን ሲል በረከት ስሞን ስብሰባውን ዘጋው ፡፡

ሰመሐል፡ የመለሰ ዜናዊ ልጅ በመሆኑዋ ይሆን ይህንን ለመናገር የደፈረቸው ?፡
ከሰመሃል መለሰ ሌላ ሌሎች የትግራይ ወጣቶች የነብር ጣቶች የት ደረሱ? የት ናቸው ?
የሚሰማቸውስ አለ ?

ቢትወደድ በጡረተኞች እየተመራህ እስከ መቸድረስ ?
ወይስ አንተው ራስህ ጡረተኛ ነህ ?

ስማ እኛ ፈላስፋዎች የጎጣ ጎጥ ዘረኝነት የለብንም ተወልደን ያደግነው ከመላው የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ክፍል ጋር ነው
የምንፈለገው መልካም አስተዳደርን ነው ፡፡የሰው ልጆች የመብትና እኩልነትን የሚዳኝ ሕግና ስርዓት ነው፡፡
ጭንቀታችን የዜግነት መብት ነው ከዛ በሁዋላ ፌዴራሊዝም በጃችን በደጃችን ነው ፡፡
ማንም ስለፌዴራሊዝም እንከን ያወጣ የለም ፡፡
ምን ዓይነት ፌዴራሊዝም የሚለው ደግሞ በሜንጫ፡ በዲሞትፎር፡ በጉዋንዴ፡ በድንፋታ፤ ወይም በጉራ ሳይሆን በሐሳብ ሲመጣ ብቻ ነው እኛ ፈላስፋዎች የምናምነው
አንድ ቁዋንቁዋ ያላቸው በፌዴራሊዝም የሚተዳደሩበት ሐገር አለ
ቁዋንቁዋቸው ተለያየቶ በተመሳሳይ ፓርቲ የሚተዳደሩበት ፌዴራሊስት ሐገር አለ
የትኛው ፌዴሬሽን ለሐገራችን ይጠቅማል የሚለው ሌላ ትልቅ አጀንዳ መሆን ይገባዋል እንጂ በዲሞትፎርና በአዳፍኔ ወይም በቄሮ ሜንጫ ፡እኔ ያልኩት ብቻ ነው ትክክሉ ብሎ መደንፋቱ ዲሞክራቲክ ሳይሆን ዲክታተራዊ ስርዓት ለመገንባት የሚደረግ ጡርምባ ነው ፡፡

ሐገርህ ኢትዮጵያ የብዙ ሕዝቦች መኖሪያ ነች እንደ ብዝህነታችን ( ብዛታችን ) አስተሳሰባችንም ብዛቱ የትየለሌ መሆኑን ባለማወቅ ይመስለኛል ግራ የተጋባኸው
የሆነ የአንድ ፓርቲ ባወጣው ዝባዝንኬ " አብዮታዊ ዲሞክራሲ ፤ አጋር ድርጅት ፤ እርብቶ አደር በመሆናቸው፡ ገለመሌ " ሳይሆን
የተለያዩ ድርጅቶች ከህዝቡ በመነጨ የጋራ አስተሳሰብ ና፡ ይህ ሕዝብ በሚወክላቸው የፓርቲ አመራሮች ሐገራችን ስትመራ ብቻ ነው፡፡

ፈላስፋው ቆቁ የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4145
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Sun Dec 01, 2019 7:49 pm

ወዳጀ ክቡራን
ተቀነሰ ነው የሚባለው ፡፡
እንደነ ደብረጽዮን ተቀነሰ ነው የሚባለው ፡ ይህ order of operation or BODMAS የሚባለው ሕግ ነው ፡፡
ይህንንም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዓቢይ ተናግሮት ነበር ፡፡
ሲቀነስ ግን order of operation ተከትሎ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጥያቄ ነው ዋናው ጥያቄ
ማለትም
ከእጅ ማውጣቱ በፊት
1. በሐሳብ መጠራጠስ ይቻል ነበር
2. ከስልጣኑ resign ማድረግ ይችል ነበር
3.በአሜሪካ ድምጽ የተናገረው የሱ ንግግር መሆኑ ራሱ ያጠራጥራል
4. በተናጠል ፓርቲም ሆነ በመድበለ ፓርቲ ሐገርን ማሻሻል ፡ የሕዝቦችን ጥያቄ መመለስ አይችልም እንደማለት ይቆጠራል
4. የጽንፈኞች ጥያቄ የቱ ነው የሕዝቦች ጥያቄ የቱ ነው በሚል ግልጽ የሆነ ሐሳብ አላቀረበም

መደመር ከየትም ይምጣ ከየትም ይሩጥ የመድበለ ፓርቲ ሲስተም ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ትክክለኛ መፍትሄ ነው ይላል ፈላስፋው ቆቁ

በመቀሌ ስለተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የሚለው አለ ፈላስፋው
መልካም ነው ሰላማዊ ሰልፉ ነገር ግን እንደዚህ ያለ ሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ከእንግዲህ ወዲያ የሚያመጣው ነገር አለመኖሩን ለመፈላሰፍ አያዳግትም፡፡
ያኔ ደርግ ሲገለበጥ ሕዝባዊ ሐርነት ግንባር የኢትዮጵያን ሕዝብ ከሞላ ጎደል አቅፎ ነበር የተጉዋዘው ፡ ከዛም በየብሄሩ ድርጅቶችን በመፍጠር ኢሐዲግን ለመመስረትና በዋናነት ለመቆጣጠር በቅቶእል
የአሁኑ ጩሀት ግን ይበልጥ ለመለያየት ፡ ይበልጥ ለመቆራረጥ ካልሆነ በስተቀር ፋይዳ የሌለው መግለጫና ፋይዳ የሌለው ሰላማዊ ሰልፍ ነው ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝብ በልዩነቱና በአንድነቱ ለዘላለም ይኖራል
የመድበለ ፓርቲ ሲስተም ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሐሳብ ብልጽግና ፡ የኢኮኖሚ ብልጽግና ዋናው ፕሮግራም ነው ፡፡
የሰው ልጅ እኩልነት የብሄር እኩልነት የሚረጋገጠው በመድበለ ፓርቲ ሲስተም ነው
ምሳሌ
ደብረጽዮን የአዳማ
ሙስጠፋ የመቀሌ ከተማ
ጌታቸው ረዳ የድሬደዋ ከተማ
ታከለ ኡማ የባህርዳር ከተማ

ሰው በሰውነቱ
ሰው በሰውነቱ ለሰው ልጅ ሲያስብ ብቻ ነው ዲሞክራሲ የሚባለው ነገር በኢትዮጵያ ላይ ብልጭ አለ የሚባለው
እንደዚህ ያለ ለሰው ልጅ የሚያስብ ጭንቅላት ብቻ ነው ለዛሬይቱዋ ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት

ባራክ ኦባማ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ፡ አባት ኬንያ ፡ እናት ከእየርላንድ ፣ ከብሪቲሽ ፣ ከጀርመን ከስዊዘርላንድ የተደበላለቁ አያት ቅድመ አያቶች
ዶናልት ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት የአባት ዝርያ ጀርመን የእናት ዝርያ ስኮቲሽ

ዘር ለገበሬ ነው የሚለው የአዲስ አበባ ልጆች አነጋገር የብልህ አነጋገር ነው
ይላል ፈላስፋው ሰው በሰውነቱ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4145
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Mon Dec 02, 2019 5:48 pm

ዛሬ ደግሞ የሰማሁት ምንድነው እባካችሁ ?
አቶ በቀለ ገርባ እና ጉዋዳቸው በሆነ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሰጡት ውይይት የሚገርም ነው
በነገራችን ላይ አቶ በቀለ ገርባ በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የኦሮምኛ ቁዋንቁዋ ለመማር ለሚፈልጉ ለምን ቁቤ አያስተምሩም?
ስለ ቁዋንቁዋ መከበር የሆነ ጉዋዳቸው ሲናገር በጣም ነው የገረመኝ
በመጀመሪያ ደረጃ ቁዋንቁዋ የሚከበረው እንዴት ነው ?
በአጥር በኬላ ተካሎ ይሆን ?
በጎሳ ተካሎ ቁዋንቁዋ በፍጹም አያድግም እንደውም ይከስማል እንጂ
ቁዋንቁዋ በነጻነት ብቻ ነው ሊያድግ ሊስፋፋ የሚችለው ፡፡
በነገራችን ላይ ያለፉት ነገስታት ከቴዎድሮስ እስከ መንግስቱ ቁዋንቁዋን ለማጥፋት ያነሱት ሜንጫ ወይም ግርግር አልነበረም
ቁዋንቁዋ ይወለዳል ያድጋል ወይም ይከስማል ፡፡ለአቶ በቀለ ገርባና ለጉዋዳቸው የምለው ቢኖር
ለምን የኦሮምኛ ቁዋንቁዋ በትምህርት ቤት እንዲሰጥ አይታገሉም ፡፡
ማለትም በመላው ኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች እንደ ተማሪው ፈቃደኝነት ተጨማሪ ቁዋንቁዋ ሆኖ ከሆነ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ ቢሰሩ እኮ የቁዋንቁዋ ብልጽግና ማለት ይህ ነው ፡፡
ለመሆኑ በአሜሪካ ስንት ቁዋንቁዋ በየትምህርት ቤቱ ይሰጣል ?
ለመሆኑ በእንግሊዝ ስንት ቁዋንቁዋ በየትምርት ቤቱ ይሰጣል?
በአውሮፓ ስንት ቁዋንቁዋ በየትምህርት ቤቱ ይሰጣል ?

ይህ ነው አንድነት ይህ ነው ልዩነት

ልዩነታችን እና አንድነታችን ለዘላለም ይኖራል
ፈላስፋው ሰው በሰውነቱ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4145
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 6 guests