ምኒሊክ በውጫሌ የዓቢይ መልስ ለዋሽንግተን፡የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: ምኒሊክ በውጫሌ የዓቢይ መልስ ለዋሽንግተን ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋ

Postby ቆቁ » Mon Jan 20, 2020 5:32 pm

ጸጋዬ አራርሳ ምንድነው የሚለው
ለሐገራዊ ማንነት መርህ እንጂ ጋብቻ እና መዳቀል መሰረት አይሆንም

በሚል ነው ዝባዝንኬውን የሚጀምረው፡፡ፈላስፋው ይህንን አስመልክቶ በተከታታይ የሚለው ይኖራል

ለመሆኑ ጋብቻ እና አምቻ የሚመሰረተው በሐገር ነው ወይስ ሐገር ነው በእምቻና ጋብቻ የሚመሰረተው ?

የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሐገር እና ባንዲራ ስላላቸው ብቻ ነው ለመጋባት የቻሉት ለመዋለድ የቻሉት
ጥላሁን ገሰሰ እንዳለው ሁሉም በሐገር ነው፡ ፍቅር በሐገር ነው ፡ ጋብቻ በሐገር ነው ፡ ልጅ መሳም በሐገር ነው እንጂ
ሐገር ልጅ በመሳም ፡ ሐገር በሴትና ወንድ ፍቅር ፡ ሐገር በጋብቻ እና በአምቻ አይደለም የሚመሰረተው

ለዚህ ምሳሌ ሲጠቅስ የኤርትራና የትግራይ ሕዝቦችን መለያየትን ይጠቅሳል

ለመሆኑ ጸጋዬ አራርሳ የተዘጋው የዛላ አምበሳ ድምበር ሲከፈት ምን ዓይነት ሁኔታ በኤርትራና በትግራይ ሕዝቦች መካከል እንደተፈጠረ ማስታወስ ይችል ይሆን ?
እዚህ ላይ፡ መርህ ነው ጋብቻ የሁለቱን ህዝቦች በደስታና በልልታ ሊያገናኝ የቻለው


እዚህ ላይ ነው ጥያቄው የኤርትራና የትግራይ ሕዝቦች መነጣጠል ከጋብቻ ከአምቻ ጋር ምን ያገናኘዋል ፡፡

የትግራይን የኤርትራ ሕዝብ ለመለያየት የበቃው በመርህ ነው ወይስ በፍቺ ?

አንድ ሐገር የምትመሰረተው በመርህ ብቻ ነው በማለት ከላይ የጠቀሰውን አርእስት ጸጋዬ ለማጠቃለል ይሞክራል ፡፡
እዚህ ላይ ነው "መርህ " የሚለው ቃል ምን እንደሆነ ያልገባው ፡፡
ለመሆኑ መርህ የሐገር መመስረቻ ከሆነ የሐገር ማፈራረሻ ምን ይሆን ?
ለመሆኑ " መርህ" ሲል ምን ማለት ይሆን ?
ሐገርን ለመገንጠል የሚዋቀረው መርህ ወይስ ሐገርን ለመገንባት የሚዋቀረው መርህ ?
በኤርትራ እና በትግራይ ሕዝቦች መካከል መቃቃር እንዴት ተፈጠረ ለሚለው ጥያቄ ጸጋዬ አራርሳ ምን ይል ይሆን?

ፈላስፋው

በሚቀጥለው


ሱማሌና ሱማሌላንድ ትተን
Last edited by ቆቁ on Sun Mar 01, 2020 5:25 pm, edited 1 time in total.
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Thu Jan 23, 2020 10:34 pm

ዛሬ ሱማሌና ሱማሌ ላንድ በሚለው ትንሽ እንበል
ስለ ሰይድባሬ አገዛዝ ለማውራት አስፈላጊ አይደለም ሁሉም ያውቀቃልና

ሰሜንና ደቡብ ኮርያ
ምስራቅ ጀርመንና ምእራብ ጀርመን

ሰሜንና ደቡብ ኮርያ በጋብቻ ወይስ በአምቻ ነው የተለያዩት ወይስ በመርህ
ምስራቅና ምእራብ ጀርመን የተለያዩት በአምቻና በጋብቻ ወይስ በመርህ እንደገናስ ምስራቅና ምእራብ ጀርመን አንድ የሆኑት በጋብቻ ነው ወይስ በመርህ ነው

መርህ ዝባዝንኬ ነው፡፡ ዝብርቅርቅ ነው ፡፡ዝም ብሎ መርህ መርህ ማለት አይቻልም ምክንያቱም መርህ ለጥፋትም ለልማትም መንገድ በመሆኑ ፡፡

ኮሚኒዝም መርህ ነው
ካፒታሊዝም መርህ ነው
የትራይባል ፌዴራሊዝም መርህ ሆኖ ሐገራችንን እያበጣበጠ ይገኛል ፡፡

ተዋልደናል ተጋብተናል ማለት የሚያንገሸግሸው ግለሰብ ቢኖር ካለ ትክክለኛ ጤንነቱ ለመናገር አያስደፍርም

መዋለድ መፋቀር ፡ ልጅ መውለድ የፈጣሪ ጸጋ ነው ከዚህ በላይ ምን ፍቅር በዚች ምድር ላይ አለ ?

በጋብቻ አብሮ ለመኖር መርህ ይኖራል ፡፡ መርሁ ፍቅር ነው
ለመፋታትም መርህ ይኖራል ፡፡ መርሁ አለመስማማት ነው ፡፡
መዋለድና መዛመድ መፋቀርና መጋባት ከነዚህ መርሃ ግብሮች በላይ ነው፡፡
በዚህ የሕብረተ ሰብ ድራማ ውስጥ ትልቁን ሚና የሚጫወተው ሐገር ነው ፡፡
ጥላሁን ገሰሰ እንዳለው ሁሉም በሐገር ነው፡፡
ለዛም ነው አያት ቅድመ አያቶቻችን ሐገር ፈጥረው ተጋብተው ተዋልደው ይኖሩ የነበረው አሁንም የሚኖሩት
ተፋቅረው ተዋደው ተዋልደው ሐገር ፈጠሩ አላልኩም ፡፡ ምክንያቱም መልሱ ቀላል በመሆኑ
ይህንን ለመመለስ ከዘመነ መሳፍንት በፊት ከነበረው የኢትዮጵያ ታሪክ ፈላስፋው ቀንጨብ ማድረግ ይፈልጋል

በሚቀጥለው ከዘመነ መሳፍንት በፊት የኢትዮጵያ ታሪክ ጸጋዬ አራርሳ እንዳለው ማነው ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር የፈለገው?
የጎሳ ፌዴራሊዝም የጥንታዊ ጋርዮሽ ስርዓት ነው ለኢትዮጵያ አያስፈልግም
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Fri Jan 24, 2020 8:45 pm

ዘመነ መሳፍንት
በዘመነ መሳፍንት ማን ነበር በኢትዮጵያ ምድር ዋና ዋና የፍልሚያ ቦታውን የያዘው?
ጸጋዬ አራርሳ እንደሚለው የ" እማራ መሳፍንት " ብቻ ነበሩ ?
በዛሬይቱዋ ኦሮሚያ ዘመነ መሳፍንት ተብሎ በሚጠራው ዘምን ሁኔታዎች ምን ይመስሉ ነበር ?
ይህንን ለማብራራት ይችል ይሆን ?
እሺ ከዘመነ መሳፍንት በፊት ያለውን ብንመለከት ፡ ለመሆኑ ዘመነ መሳፍንት እንዴት ሊፈጠር ቻለ የሚለው ጥያቄ ላይ ድቅን እንላለን ፡፡

በነገራችን ላይ እዚህ ጥያቄ ላይ ስንደቀን ለኢትዮጵያው አንድነት ኢማሙ ( ግራኝ መሐመድ ) ዋናውን ቦታ ይዘው ይገኛሉ ፡፡ እስከ አክሱም ድረስ በመዋጋት ነው ለዓመታትት ኢትዮጵያን ሲመሩ የነበሩት ቢባል ምንም ስህተት አይኖረውም ፡፡ ሌላውን ትተን ማለት ነው፡፡
የሽምብራ ኩሬ ጦርነት የተካሄደው ሸዋ ውስጥ አይደለም የአባ ባህሬ ኑሮ ሸዋ ውስጥ አልነበረም ፡ የደብረ ሊባኖስ ገዳም የየካው የዋሻው ሚክኤል ፡ የመሳሰሉት ታሪካዊ ቦታዎች ዛሬም አሉ ወደፈትም ይኖራሉ ፡፡ ፡፡ ፡፡ የኢማሙ አነሳስ በዛም በለው በዚህም በለው ከሸዋ ርቆ ነው
ከዛ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘመነ መሳፍንት የሚባለው ነገር የተፈጠረው ፡፡
እዚህ ላይ ነው አንድነትና ልዩነት በተለያዩ መንገዶች መገለጥ የጀመሩት
እዚህ ላይ ነው እንግዲህ መፋቀርና መጋባት መዋለድና ልጅ አቅፎ መሳም የተጀመሩት ፡፡
እዚህ ላይ ነው እንግዲህ የጎንደር የጎጃም የየጁ የትግራይ የሸዋ መሳፍንት እኔ እኔ ማለት የጀመሩት ፡
እዚህ ላይ ነው እንግዲህ ጨዋታው የተጀመረው
ኢማሙ በቀደዱት ትልቁ የአንድነት በር ( በሐይማኖት ) እንደ ዛሬዎቹ በጎሳ ሳይሆን ለኢትዮጵያ አንድነት ዋና በር ከፋች የሆነው ፡
ሱስንዮስ በለው ፡ ራስ አሊ ፡ ቴዎድሮስ በለው ንጉስ ተክለ ሀይማኖት ፡ ሳህለሳላሴ ንጉሰ ሸዋ በለው አጼ ዮሐንስ ከዛም ገናናው ታላቁ ንጉስ ምኒሊክ የኢማሙ ስልትና ጥበብ በቀደደው ፈር ነው ከሸዋ በስተደቡብ መመሪያውን የቀደደው ፡፡
ይህንንም ሲያደርግ ከነጎበና ዳቼ ጋር ከነ ራስ መኮንን ጉግሳ ጋር መሆኑን ማንም ሊዘነጋው የሚችል ሐቅ አይደለም፡፡
ይህ ታሪካዊ ሂደት በመላው ዓለም ከተደረገው ታሪክ ምንም ልዩነት የሌለው ሐቀኛው የምኒሊክ ታሪክ ነው
ገብር አልገብርም ስለሆነ ውጣ ውረዱ በዚህ መካከል ጥፋትም ልማትም እንደነበር ከራሳቸው ከጅማው አባ ጅፋር ታሪክ መማር የሚያቅት አይደለም ፡፡ የዘመነ መሳፍንቱ ብጥብጥ እዛም አባ ጅፋር መንደር እንደነበር ታሪክ ባህል በትክክል ነው ያስቀመጠው እንደው የገዳ ማህበረ ስርዓት ራሱ ዋናው ምስክር ነው ፡፡ ይህንን ሲል ፈላስፋው እንደ አያት ቅድመ አያት ታሪኩ በመመዝገብ ነው እንጂ ለሌላ ጉዳይ እንዳልሆነ ለማስረዳት ይሞክራል ለዛም ነው የገዳ ስርዓተ ማህበርር በምኒሊክ ዘመነ መንግስት ተጠናቁዋል የሚለው ፈላስፋው፡፡ እንዴት ? ከፕሮፌሰር አስመላሽ በርሄ ታሪካዊ ምርምር በመነሳት እንመለስበታለን፡፡ (ስማቸውን ካልተሳስትኩ )

ፈላስፋው
በሚቀጥለው የኮሎኒያል ዘመን አፍሪካን መቀራመት
ለመሆኑ አፍሪካ ከኮሎኒያል ዘመን በፊት ምን ትመስል ነበር ?
የኮሎኒያልዝም መጥፎ ተግባር ጭካኔ ግፍና ተንኮል በአፍሪካ ምድር ምን ይመስል ነበር ?
የአድዋ ድል ከአፍሪካ መቀራመት ጋር ምን የሚያገናኘው ነገር አለ ?

የትራይባል ፌዴራሊዝም የሰው ልጅ በዚንጃትሮፐስ ዘመን ያካሂደው የነበረ ስርዓተ ማህበር ነው
በአሁን ዘመን ይህንን የመንጋ ፌዴራሊዝም የሚያካሂዱ የዱር ተኩላዎች ብቻ ናቸው ጅቦችም ጭምር


ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Sat Feb 01, 2020 9:33 pm

እንዴነው ነገሩ?
ኦነግ መግለጫ ያወጣል
እምኒስቲ መግለጫ ያወጣል
ኦነግ ሸኔ መግለጫ ያወጣል
ልጆቹ ታገቱ ልጆቹ የት ገቡ ይላል የተነካው ሕዝብ
ሌላው ያልተነካው ሕዝብ ደግሞ ዝም ብሎ ሌላ ነገር ያወራል
የከተራ በዓል የነ መራራ ጉዲና የፖለቲካ በዓል ለምን እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ ሌላው ይጠይቃል

ለሁሉም ተጠያቂ መንግስት ነው ይላሉ ሁሉም በአንድነት
ሁሉንም የሚያመሳስል ነገር አለ
ምርጫ ለማሸነፍ መንግስትን መንቀፍ ዋናው መርህ ነው በመሆኑ
መራራ ጉዲና ቤተ መንግስት እንገባለን ይላል ለምርጫ የሚያስፈልገው እሱ በመሆኑ
ጃዋር መንግስትን እንደሚያወርድ ይዝታል ይህም ለምርጫ ስለሚያስፈልግ
ጃዋርም ሆነ መራራ ጉዲና ወይም ዳውድ ኤቢሳ ስለ ወለጋ ችግር የሚያወሩት የላቸውም ፡ መንግስትት ነው ተጠያቂው ከማለት በስተቀር ፡
በውጭ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ የመንግስትን ጀኖሳይድ ነው የሚገልጸው የሸማቂውና የታጋቺውን ጀኖሳይድ ግን እንደ ጀግንነት ይዞ ሲደነፋ ነው የሚታየው የሚሰማው
ምርጫውን ለማሸነፍ
human shield በኢትዮጵያ ተጀመረ እንዴ ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Mon Feb 03, 2020 5:03 pm

እንዴት ነው ነገሩ ከአንዱ ጋር ተጣርሰን ሳናበቃ ሌላ መጣረስ ብቅ ይላል ፡፡
እኔ ፈላስፋው ትላንት የሰማሁት ምንድነው ?
የዓባይ ወንዝ መፍሰስ ከጀመረ 10 ሚሊዮን አመታት በላይ ነው፡፡ እንዴትና ለምን እንደሚፈስ የሆነው በተፈጥሮ ሕግጋት ነው ዓባይን ለሆነ ጥቅም ገንብቶ ስራ ላይ ማዋል የሚጠቅም ሳይሆን የዓለምን የአትሞስፌር ባህርይ የሚለውጥ ነው ማለትም ጎጂ ነው አለ አሉ አንዱ ከናዛ ተመራማሪዎች በእልጃዚራ

የሚደንቅ ነው ለመሆኑ ማርስ ላይ መብረሩ ጨረቃ ላይ ማረፉ ምን ይሆን?
ማርስና ጨረቃ ላይ ለማረፍ የወጣው ገንዘብ የተመራመረው ጭንቅላት ምን አመጣ?
ፈላፋው ብሎ ይጠይቃል
ማርስና ጨረቃ ከተፈጠሩ በሚሊእርድ የሚቆጠር ዘመን ነው ያለፈው ፡፡እንዴት እንደተፈጠሩ ለምን እንደተፈጠሩ ማንም የሚያውቅ የለም ወደፊትም ማንም አያውቅም፡፡
እዚህ ግባ ለማይባል ውጤት መንኮራኩር ከመስራት እንደ ኮሮን ቫይረስ እንደ ኢቡላ ቫይረስ ያሉትን በቅጽበት ለመከላከል የሚያስችል ውጤታማ መድሃኒት መስራት መልካምም ነበር፡፡ ለሚራበው ለዓለም ሕዝብ በዚህ ገንዘብ እህል እና ውሃ ማከፋፈል ሌላው መልካም ነገር ነበር፡፡
የሰው ልጅ የመጀመሪያ ምኞቱ ጤንነት ነው ሌላ ነገር አይደለም

እዛጋ ፡ እዛኛው ዓለም ፡ እዛኛው ፕላኔት ጥቂት የሰው ልጆች ምንድነው የሚፈልጉት እብዛኛው የዓለም ሕዝብ እዚች ምድር ላይ በሆነው ባልሆነው እንደ ቅጠል ሲረግፍ ?
ምንድነው የሚፈልጉት?

ለመሆኑ የሰው ልጅ ከምድር አካላት አንዱ አይደለም እንዴ ?
የዓባይ ወንዝ እየፈሰሰ በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ እንዳልነበር ሲሆን ምነው ዝም ተባለ ?
ከሞላ ጎደል በአባይ ወንዝ ላይ ተስማምቶ ለሰው ልጅ ሲባል አብሮ መኖርን ፈላስፋው ያምናል
ዓባይ ለግብጽ ሕዝቦች የመኖር ዋስትና ነው ፡ ለኛስ ለኢትዮጵያውያን የመኖር ዋስትና መሆን አይችልም እንዴ ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Sun Feb 23, 2020 6:37 pm

ቴዲ አፍሮ

ጥቁር ሰው
ቴዲ ለምን ይሆን ጥቁር ሴት ያላልከው ?
በሚቀጥለው እንደምትል ፈላስፋው ተስፋ ያደርጋል

እንዴት ልግለጸው እኔ ፈላስፋው

አዲስ አበባ የነ እስክንድር ነጋ ሰፈር
አዲስ አበባ የነ ተመስገን ደሳለኝ ሰፈር

አዲስ አበባ መሰልሽ

እኔ ፈላስፋው አንድ ያልገባኝ ነገር እለ
የጣይቱ ብጡል ሐውልት ለምን ጎንደር ?
የጣይቱ ብጡል ሐውልት ፊን ፊን ፊን ፊን ( ፊንፊኔ) ላይ ለምን አልቆመም

ጣይቱ ብጡል = አዲስ አበባ

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በዓድዋ ዓቢይ በኦስሎ ፡ የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል ፡፡

Postby ቆቁ » Fri Feb 28, 2020 6:09 pm

ምኒሊክ
የምኒሊክ ጠብመንጃ አሜሪካ እየተወለወለ ነው ይላል ዜናው ሁላ ፡የጣይቱ ብጡልስ የሚለው ነገር ነው ፈላስፋውን ያልገባው ፡
የት ገባ የጣይቱ ብጡል ዝናር ?
የጊዮርጊስን ጽላት ይዘው ወደ አድዋ ሲነግዱ ጣይቱ ምን ነበር የያዘቼው ?
ምኒሊም በመድፉ ፡ጊዮርጊስ በፈረሱ ፡ ጣይቱ በምን እያላችሁ ነበር ያን ጊዜ ኢለመንታሪ ሆናችሁ ስትዘምሩ የነበረው

የጃዋርና የበቀለ ገርባ ከወደቁ በሁዋላ መፈራገጥ ለመላላጥ ምን ይሆን ?

ጃዋር እንዲሁም በቀለ ገርባ
ፖለቲካ ማለት ጥላቻ ለመግለጥ የምንጠቀምበት መሳሪያ ሳይሆን ሐገርን ለማስተዳደር ሕዝብንን ለመምራት የሚያስችለን ትምህርት ነው ፡ ለዚህም ነው በየዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው

ለምን የብልጽግና ፓርቲ እንደዚህ ያለ ድጋፍ አገኘ የሚለውን
1. ከጃዋር ንግግር ስህተትት ፡
2. ከመራራ ጉዲና አስተያየት ግድፈት
3. ከበቀለ ገርባ ዝብርቅርቅ አስተያየት ለማሻሻል ይሞከራል እንጂ ፡ እንደው በደፈና እንካ ቅመስ ማለት የፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ውጤት አይደለም፡፡

ዮሐንስ ቡያሌው ሹመቱን አልቀበልም ቢል መብቱ ነው
ያልሆነ የሆነ አተካራ ፈጥሮ ከዓቢይ ጋር ለማጋጨት መሞከር ግን የፖለቲካል ሳይንስ ውጤት ሳይሆን ተራ የሆነ ኢንፍሪየሪቲ ኮምፕሌክስ የሆነው ውጤት አሉባልታ ነው ፡፡

አንድን ሰው ለመጥላት የፖለቲካል ሳይንስ መማር አያስፈልግም ምክንያቱም እንስሳትም ያለ ፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት ሌላውን እንስሳ መጥላት ስለሚችሉ
ለምሳሌ አንድ ውሻ የማያውቀን ውሻ ይጠላል ፡ ስለሚጠላው ይጮሃል ፡ ለመንከስ ይንደረደራል ፡ ይቡዋጨቃል ፡፡
የጃዋርና የበቀለ ገርባ በየሚዲያው እየወጡ የሚዘባርቁት ይህንኑ ይመስላል

የሚዲያው ዝባዝንኬ
ዩቱቦውች ፌስቡኮች እንዲሁም OMN እንዳሉ ሆነው ማለትም እነዚህ ሶስቱ እና ሌሎችም ተመሳሳይ የዲጂታል ጋራቤጆች አላዋቂነት የተሞላበት ጥላቻ በሕዝቦች መካከል መርጨታቸው ቢታወቅም
ዋና ዋና የሚባሉት የሚዲያ ኔት ወርኮች ለምሳሌ ቢቢሲ ፡ ቪኦኤ፡ እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የሚዲያ ኔት ወርኮች ኢል ቲቪ (ለምሳሌ) እነ ጃዋርን ፤ እነ በቀለ ገርባን ፡ የመሳሰሉ የፖለቲካ ምስኪኖች በየሳምንቱ አያቀረቡ የሚያስቀባጥሩበት ነገር ነው ያልገባኝ ፡፡
የሚያስረዳኝ ይኖር ይሆን ?

አሁን የምሰማው ነገር ምንድነው
የመለሰ ዜናዊ አካዳሚ ( ፋውንዴሽን ) ምን ማለት ነው?
ምንድነው እዚህ አካዳሚ ውስጥ የሚሰራው ? የሚሰጠውስ ትምህርት ምን ይሆን?
መግቢያው በር ላይ " የአክሱም ሐውልት ለወላይታ ሕዝብ ምኑ ነው ፡ ወይስ ባንዲራ ጨርቅ ነው " የሚል መፈክር ተለጥፎበት ይሆን ?


ምኒሊክና የገዳ ስርዓት

የጎሳ ፌዴራሊዝም የጋራቤጅ የፖለቲካ መዋቅር ነው

ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: ምኒሊክ በውጫሌ የዓቢይ መልስ ለዋሽንግተን፡የገዳ ስርዓት በምኒሊክ አማካይነት ተጠናቁዋል

Postby ቆቁ » Mon Mar 02, 2020 7:41 pm

ይህንን አይደለም እንዴ ፈላስፋው የሚለው
ከሰሜን እሰከ ደቡብ
ከምስራቅ እሰ ምእራብ አንድ ያደረገው የአድዋ ድል በዓል
ከዛም አልፎ በአባይ ወንዝ እንደ ውጫሌ ውል ያስነሳው አቡዋራ መላውን ኢትዮጵያዊ ሲነካ ለዛውም ጃዋር መቀስቀሱን ነው ፈላስፋውን የገረመው
ደብረ ጽዮን እና እኔ በዓባይ ወንዝ አንድ ቃል መናገራችን የሚገርም ነው
ጃዋር የዓባይ ድርድር ከምርጫ በሁዋላ ይሁን የሚለው ለምን ይሆን ? ይህ የዓባይ ችግር መላውን ኢትዮጵያዊ ያስነሳል ከዛም አልፎ ጃዋርን ያሽቀነጥራል የተባለ ይመስል ምነው ደነበረ ? ምርጫው ይካሄዳል ፡ ጃዋር ይሸነፋል ፡ ከዛስ ምን ይሆን የፖለቲካል አስተሳሰቡ እንደ መራራ ጉዲና ኮሮጆውን እንጠብቅ ይሆን ?
ጃዋር እንዴነህ ደህና ነህ
አሜሪካ ማደራደር አይኖርባትም እኮ ነው የሚባለው ? ይገባሃል ?

ልዩነታችንና አንድነታችን ለዘላለም ይኑር
ዓድዋ ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው
ኢትዮጵያ ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው

ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Previous

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 8 guests