የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Fri Oct 25, 2019 5:04 pm

የፖለቲካል ፡ሳይንስ፡ ምሩቅ ፡ወይስ፡ የሆሊገን፡ መሪ !

በፈስ፡ ቡክ፡ ሐገር፡ ተቃጠለ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ እሪታው፡ ተቀጣጠለ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ ዘረፋው፡ ተጡዋጡዋፈ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ ሰው፡ አለቀ፡፡
በፈስ፡ቡክ፡ ቤት፡ ተቃጠለ፡፡ ንብረት ወደመ፡፡
ፈስ ቡክ ታህሪር አደባባይ ሁሴን ሙባረክን ለመጣል ባደረገው አስተዋጽኦ በመላው ዓለም አድናቆንት ሲያተርፍ
በኛስ ?
በፈስ፡ ቡክ፡ ሐገር፡ ተቃጠለ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ እሪታው፡ ተቀጣጠለ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ ዘረፋው፡ ተጡዋጡዋፈ፡፡
በፈስ፡ ቡክ፡ ሰው፡ አለቀ፡፡

ፈላስፋውን፡ ቀልቡን፡ የሳበው፡ ተደረገ ፡ለተባለው፡ የስልክ ፡ጥሪ፡ ማን ፡አንደሆነ ፡የማጣራት ፡ተግባር፡ ይከናወናል ፡የሚለው፡ የሽመልስ፡ አብዲሳ፡ አነጋገር፡ ነው ፡፡
ለመሆኑ፡ በውድቅትም ፡ሆነ፡ በጠራራ ፡ጸሐይ ፡ ማን ፡አንደደወለ፡ ተጣርቶ፡ ቢታወቅ፡ የጠፋውን፡ ንብረት ፡. የጠፋውን፡ የሰው፡ ሕይወት ፡ማስመለስ ፡ይቻል ፡ይሆን ?
በነገራችን፡ ላይ፡ ራስህ፡ ሽመልስ፡ አብዲሳ፡ አንደዚህ፡ ያለ፡ ጥሪ ፡ለጠባቂዎችህ፡ ቢላክ፡ በፈስ፡ ቡክ ፡ድረሱልኝ፡ ልትል ፡ይሆን?
ከዛስ፡ ማን ፡ይደርስልህ ፡ይሆን? ፖሊስ፡ ወይስ፡ ቄሮ?

ሽመልስ፡ ሆይ፡ ለፖለቲካል፡ ሳይንቲስቱ፡ ቦዲ፡ ጋርድ፡ ከማቆም ፡ቄሮን፡ መበታተን፡ የመጀመሪያው፡ ተግባርህ ፡መሆኑን ፡የዘነጋህ፡ ይመስላል፡፡
ለኢትዮጵያ ፡ወጣቶች፡ ስራ ፡መፈለግ ፤
የስራ፡ ስልጠና፡ የሚያገኙበትን፡ መስክ መክፈት፤
በአውቀት፡ አንዲያድጉ፡ ማድረግ፡ ዋናው፡ የስራ፡ ነጥቦችህ ፡መሆን ፡ይገባቸዋል ፡ይላል፡ ፈላስፋው፡፡
ይድረስ፡ ለሚመለከተው፡ ሁላ ፡፡
የፖለቲካል፡ ሳይንቲስቱ፡ ቦዲ፡ ጋርዶች፡ በስልክ፡ ይነሱ፡ ተባለ፡ አይነሱ፡ ተባለ፤ የፖሊስ፡ አዛዥ ይደውል ፡ ግለሰብ፡ ይደውል፡ ያ፡ አይደለም፡ ጥያቄው ፡፡
የሰው፡ ልጅ፡ ተቀጠፈ፡፡
ንብረት፡ ወደመ፡፡
ሐገር፡ ተተረማመሰ፡፡
ሆሊጋኒዝም ፡በፖለቲካል፡ ሳይንስ ፡የሚመራ፡ አይደለም ፡፡
የሆሊገኑ መሪ
እኔን፡ ወጥመድ፡ ውስጥ፡ ሊከቱኝ፡ ነው፡ ይበል፣
ወይም፡ ተንኮል፡ አለበ፡ት ይበል፤
ወይም፡ ሴራ፡ ነው፡ ይበል፡ ያ ፡አይደለም፡ ጥያቄው ፤
የሰው፡ ልጅ፡ ተቀጠፈ፡፡
ንብረት፡ ወደመ፡፡
ሐገር፡ ተተረማመሰ፡

አንግዲህ የሆሊገኑ መሪ በፈስ ቡክ ለማንኛውም የስልክ ጥሪ ( ወፍ፡ በረረ ፡ ነፋስ፡ ነፈሰ፡) ብሎ ፡በፈሳ፡ ቁጥር፡ ሐገር፡ ሊተረማመስ፡ መሆኑ፡ አልገባህ ፡ይሆን?
ለመሆኑ የሚቀጥለው ለሆሊገን መሪ የሚደወለው ስልክ ምን አይነት የጥሪ መልክት ይኖረው ይሆን?
ሐገር፡ የሚያተረማመስ፤
ወይስ፡
ቺኮችን፡ የሚያሳሳቅ፡፡


ፈላስፋው የየትየለሌው
Last edited by ቆቁ on Sun Oct 27, 2019 6:36 pm, edited 1 time in total.
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የፖለቲካል ሳይንስ ምሩቅ ወይስ የሆሊገን መሪ ?

Postby ቆቁ » Fri Oct 25, 2019 8:17 pm

ታየ ደንደአ
ነገሩን በትክክል አስቀምጠኽዋል፡፡

እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ
ይህ ግለሰብ የሆነ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር እንደዚህ ከበረገገ ምን እንደሚመጣ ልብ አድርገህ ይሆን ?
ለምሳሌ ከቦዲጋርዱ አንዱ መሳሪያው ባልታወቀ ምክንያት ቢባርቅበት ስንት ሺ ይሆን የሚያልቀው ?
ወይም ከቦዲጋርዱ አንዱ በሞቅታ ከሆነ ሰው ጋር ሲጨቃጨቅ ቢሰማ በፈስ ቡክ ምን ይጽፍ ይሆን?
ከዛስ ስንቱ ይሆን የሚያልቀው የሚ?ወድመውስ ንብረት ስንት ይሆን ?
ይህ ግለሰብ በፍጹም ለኢትዮጵያ ፖለቲካ እንደማያስፈልግ ተረድተህ ይሆን ?
ታየ ደንደአ
ግለሰቡ ላይ ሳይሆን ማነጣጠር ያለብህ ቄሮ ላይ መሆን አለበት
ስራህ ቄሮን ከግለሰቡ መነጠል ብቻ ነው የሰላምና የፍቅር ሂደት በኢትዮጵያ

ለወልቂጤ ነዋሪዎች ትልቅ ምስጋና እና ክብር
ለቡትታጅራ ነዋሪዎች ትልቅ ክብር ና ምስጋና
የሰው ልጅ በችግር ሲረዳዳ መስማት የፍቅር ምልክት ነው
ፍቅር ያሸንፋል
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የፖለቲካል ሳይንስ ምሩቅ ወይስ የሆሊገን መሪ ?

Postby ቆቁ » Sat Oct 26, 2019 7:32 pm

የሚያስደነግጠው፡ መላ ፡ምት ፡እና፡ የፈስ፡ ቡክ፡ ጥሪ፡፡
መላ ፡ምት 1
የፖለቲካል ፡ሳይንስ፡ ምሩቁ ፡መኪና፡ እያሽከረከረ፡ ሲሄድ ፡ተጋጭቶ ፡አደጋ፡ ቢደርስበት ፡ የመለመላቸው ፡ሆሊገኖች፡ ምን፡ ሊፈጥሩ ፡ይችላሉ፡ ብላችሁ ፡ገምቱ ፡፡
መላ ፡ምት 2
ወይም፡ ከቦዲጋርዶቹ ፡አንዱ ፡ከሆነ፡ ግለሰብ፡ጋር ፡በድንገት፡ በሲጋራ፡ ማቀጣጣያ፡ ክብሪት፡ ምክንያት፡ እሰጥ፡ አገባ፡ ውስጥ፡ ቢገባ ፡ሆሊገኖች ፡ምን ፡ሊፈጥሩ፡ ይችላሉ፡ ብላችሁ፡ ገምቱ ፡፡
መላ ምት 3
ከሆሊገኖች፡ ውስጥ ፡በድንገት፡ አንዱ፡ ሆሊገን፡ ከሌላው፡ ሆሊገን፡ ጋር፡ በሳንቲም ፡ልውውጥ፡ እሰጥ፡ አገባ፡ ውስጥ፡ ቢገባ፡ እና፡ ረብሻ፡ ቢያነሳ ፡ምን፡ ሊፈጠር ፡ይችላል ፡ብላችሁ ፡ገምቱ ፡፡

ሐገር፡ ሊተረማማስ ?
መንደር፡ ከተማ ፡ቤት፡ ንብረት፡ ዓመድ፡ ሊሆን ?
ሰው፡ በየቤተ ፡ክርስቲያኑ፡ በየመስጊዱ፡ እንደ፡ ከብት፡ ሊታረድ ?

ይህ፡ ፖለቲካል፡ ሳይንስ ፡ነው ?
ይህ ፡ፖለቲካ ፡ነው?

ፈላስፋው፡ ቆቁ ፡የየትየለሌው ፡
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የጃዋር ስኩዋዶች

Postby ቆቁ » Sun Oct 27, 2019 6:35 pm

የጃዋር ስኩዋዶች ድብደባ ከቀይ ሽብር የደርግ የጥይት እሩምታ ጋር በመመሳሰሉ
እጅግ እጅግ የሚዘገንን ነው
የሚዘገንን ነው
እንዴት በዚህ በኛ ክፍለ ዘመን እንደዚህ ያለ ነገር በምድረ ኢትዮጵያ ለማየት በቃን ?
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Tue Oct 29, 2019 7:02 pm

ስለ አኖሌ ሲምቦጫረቅ የነበረው አሁን ምን ይናገር ይሆን ?


ምን ነካችሁ ?
አንደኛ
በጃዋር ቤት ለተሰበሰባችሁ እድሜ ለጠገባችሁ ፡ ዓቢይ አህመድ ጠራን ብላችሁ ኢትዮጵያ ለገባችሁ
ዳውድ ኢቢሳ ፣ ከማል ገልቹ ፡ ገለሶ ዲልቡ
ምን ልትሰሩ ነው እዚህ እምቦቃቅላ ቤት ውስጥ ገብታችሁ እንደዚህ ያለ የቀልድ መግለጫ የሰጣችሁት?
ይህንን እምቦቃቅላ ለማስተማርር የገዳው ማህበረ ስርዓት ምንድነው ከዘር ግንዳችሁ ያወረሳችሁ ?
ሁለተኛ
የምን 339 ጥፋተኞች ታሰሩ ነው የምትሉን ?
አህያውን ፈርቶ ዳውላውን ይሆን ? ጥፋተኛው ራሱ ይህንን የእርስ በርስ ግጭት የፈጠረው በፈስ ቡክ ተነሱ ያለው ጃዋር ነው ፡፡
የግድያ ሙከራ ቢሆን ኖሮ ከበሩ የቆሙት ቦዲ ጋርዶች ተታኩሰው ወይ ያድኑት ነበር ወይ ሌላውን ይፈጁት ነበር ፡.
ጃዋር በፈስ ቡክ ፈስ የሆነ ወሬ ባይበትን ኖሮ ይህ ሁላ ባልመጣ ነበር ብሎ መገመት ያዳግት ይሆን ?

ሶስተኛ
የምን እስረኞች ተፈቱ ነው የምትሉን ? ማንን ለማረሳሳት ?
በጃዋር ፈስ ቡክ ሕዝብ እየታመሰ ፡ በድንጋይ እየተወገረ የምን ማዘናጋት ነው?፡፡
ወደፊትስ እንደገና ሌላ ፈስ ቡክ ቢፈሳ ሐገር እንዴት ውላ ልታድር ነው ?
ማዘናጋት ይሆን ?

ከዚህ በፊት ፈላስፋው ባነሳው መላ ምት አንዱ በጃዋር ላይ ቢፈጸም ለምሳሌ መኪና ሲነዳ ተጋጭቶ ችግር ቢደርስበት ወይም በአላህ ምክንያት አንድ ያልታወቀ ምክንያት ቢደርስበት
አዳማ እንዴት አድራ ልትውል ነው? ፡ አምቦ እንዴት አድራ ልትውል ነው ? ድሬደዋ እንዴት አድራ ልትውል ነው? ፡ ናዝሬት እንዴት አድራ ልትውል ነው ?
ኢትዮጵያ እንዴት አድራ ልትውል ነው ? አዲስ አበባ እንዴት አድራ ልትውል ነው?


በሚዘገንነው የድንጋይ ድብደባ ፈዞ የቀረው ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ? እንዴት እንደዚህ ያለ ስኩዋድ ሊፈጥር ቻለ?

Postby ቆቁ » Thu Oct 31, 2019 8:56 pm

እንዲህ ነው፡፡
ሰላማዊ ሰልፍ የእካባቢውን አመራር በመጠየቅ ሲደረገ ነው እንጂ ዘራፍ ብሎ በመነሳት አይደለም
ስላልሆነም ነው በጃዋር የፈስ ቡክ ዘራፍ እንደ ነፍጠኛ ብላችሁ ሐገር ያወደማችሁት ሰው የጨረሳችሁት
ምን አደረጉ ነፍጠኞች ? እነዚያ በድንጋይ የተቀጠቀጡ ሰዎች ፡ በዱላ የተጨረገዱ ሰዎች ፡ በእሳት የተቃጠሉት ሰዎች
ያለ አባት የቀሩት ልጆች

የጃዋር ቦዲጋርዶች አልተታኮሱ ፡ አንዲት ነገር በጃዋር ላይ ብልጭ አላላች እንዴት እንደዚህ ያለ ነገር ሊፈጠር ቻለ ብላችሁ ጠይቁ
እናንተ የዛሬ አበባዎች የነገ ፍሬዎች እንዴት እንደ አህያ በአንድ በጃዋር ትነዳላችሁ ለዛውም በፈስ ቡክ
ጃዋር እንዴት በፈስ ቡክ እነዚህን ወጣቶች እንደ አህያ ትነዳለህ ?
አንድ ነገር ይላል ፈላስፋው
ቄሮውች
እናንተም የነፍጠኛ የልጅ ልጆች መሆናችሁን አትርሱ
የነፍጠኛ ልጆች ባትሆኑም የሰናድር ያዥ የልጅ ልጆች ናቸሁ
የሰናድር ያዥ የልጅ ልጆች ባትሆኑም
የጠብ መንጃ ያዥ የልጅ ልጆች ናቸሁ
ከመፈክራችሁ እንደተሰማው ነፍጠኛ ማለት ምን ማለት ነው?
ነፍጠኛ እኮ ሰው የሰው ልጅ ነው እኮ ፡፡
የሰው ልጅ አይቃጠልም
የሰው ልጅ በድንጋይ ተደብድቦ አይገደለም
ሰው እኮ እናንተም ናችሁ ፡ የናንተ እናትና አባት በድንጋይ ተደብደው ፡ በእሳት ተቃጥለው ቢሞቱ ምን ይሰማችሁ ይሆን
ነፍጠኛ እኮ ሁሉም ነው
ጃዋር የፈስ ቡኩ የነፍጠኛ ልጅ እኮ ነው
ኦሮሞውም ነፍጠኛ ነው እኮ? ለዚህ ምሳሌ መጥቀስ ያስፈልግ አይመስለኝም
ታሪካችሁን በጥብቅ ተከታተሉ
ይላል ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቢተወደድ1 » Fri Nov 01, 2019 3:23 pm

እንደመር ብላቹህ ስትታመሱ የነበራችሁት እናንተው፤ የምትቀነስቱም እናንተው፤ ለምን የአዞ እንባ ትረጫለህ?
ቄጤማው መንግስት ምንም አያደርግም፤ አምቦ ሄዶ መሽረፈት ምን እንደገጠመው ሰምተሃል፡ 31/11/2019 ላይ፡፡
ከዚህ ትርምስ ውስጥ ግን መማር ያለብን ጃዋርና አብዮት በተጣሉበት የሌላው ዘር መገደል ምን አመጣው? ምክንያት እየተፈለገ የሚገደለው ሌላው ኢትዮጵያዊ እንጂ ኦሮሞው አይደለም፡፡ እናንተ ግን ግድም አይሰጣችሁም ስልጣኑን እስካላገኛቹህ ማንም ቢሞት፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 369
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Fri Nov 01, 2019 8:21 pm

ቢትወደድ
ይህ የጃዋር ስኩዋድ ዘር እየመረጠ ሳይሆን የራሱን ዘር ሁላ አደበላልቆ ነው ያረደው ፡፡
ተከታተል ዜናውን ጽሁፉን ፡፡
የኦሮሞ ተናጋሪ ሆነህ ቄሮ የሚያርደውን አብረህ ካላረድክ ፡ትታረዳለህ ፡፡
የኦሮሞ ተናጋሪ ሆነህ ቄሮ በድንጋይ የሚፈልጠውን አብረህ በድንጋህ ካልፈለጥክ ትፈለጣለህ ፡፡
ይህ የዓቢይና የጃዋር ጠብ የሚባል ነገር ሳይሆን የቁቤ አስተማሪዎቹ በወያኔ ዘመነ መንግስት ፡ ሲያሰለጥኑት የነበረው ስልጠና ነው ፡፡
ጸጋዬ አራርሳ፤ሕዝቄል ጋቢሳ፤በቀለ ገርባ ሌሎችም እነ ዶክተር ስማቸው ለጊዜው የጠፋብኝ፤ ከዛም በገዳው ስርዓት ራሱን በራባ ዶሪ እርከን ላይ ነኝ ብሎ የሚጠራው የነሱ ተማሪ የሆነው ጃዋር (33 -40 ወይም ከዛ በላይ ) ለዚህ ምሳሌ ናቸው
ለዛም ነው እነ ሽመልስ አብዲሳ ነፍጠኛ ለማለት የተገደዱት ፡ አዲሱ አረጋ በጥናት ስለ አኖሌ ያቀረበውን ጽሁፍ እኔ አልወጣኝም እስኪል ድረስ የቀባጠረው ፡፡
ቄሮ የወያኔን መንግስት ጣለ ተብሎ ሲደነቅ የማያውቀውን የራሱን አያትና ቅድመ አያት የሆነውን ነፍጠኛን ዛሬ ለምን መውቀስ አስፈለገው ?
ለምን ዛሬ ነፍጠኛን መውቀስ አስፈለገ ? እስኪ ራስህን ጠይቅ ?
ወያኔ ካለ ነፍጠኛ የሚያወራው የለም ፡ ቄሮ ካለ ነፍጠኛ የሚያወራው የለም ፡ጃዋር ካለ ነፍጠኛ የሚያወራው የለ?
ሶስቱም አንድ ናቸው በአስተሳሰብ ፡ አይገርምም ፡፡
የቱ ነው ነፍጠኛ ? የት ነው ነፍጠኛ የሚገኘው?
የወላይታው ተወላጅ ? የኦሮሞው ተወላጅ ? የትግራይ ተወላጅ
በመጀመሪያ ማነው ነፍጠኛ የሚለውን ስም ለአማራ ብቻ የሰጠው ?
የምኒሊክን እግር የተከተለ በሙሉ ነፍጠኛ ፡ ጠመንጃ ያዥ ፡ ሰናድር ያዥ ነው፡፡
ከዛም የምኒሊክን እግር ተከትሎ እስከ ዓቢይ መንግስት በምድረ ኢትዮጵያ ወዲያና ወዲን የሚነጉደው ሁላ ነፍጠኛ ነው የትግራይ በለው የጎንደሬ የሸዋ በለው የጉራጌ የወላይታ በለው የሱማሌ
ራሱ ወያኔ ነፍጠኝነቱ ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ ልክ ደርግን እንዳባረረ አዲስ አበባ ነበር የተኮፈሰው ፡ እና ነፍጠኛ አይደለም ?
ለምን ደብረጽዮን ነፍጠኞች ባቀኑዋት ምድር አዲስ አበባ መዘባነን አስፈለገው?
ይግባህ ወዳጀ ቢትወደድ
ነፍጠኝነት እንዴት እንደመጣ በሌላው ዓምድ ላይ ፈላስፋው ይተነትናል ፡
ነፍጠኝነትት የገዳው ስርዓት ያመጣው ልዩ ታክቲክ ነው
በምድረ ኢትዮጵያ ከምኒሊክ እስከ ዓቢይ ድረስ የምኒሊክን እግር የተከተለ ሁላ ነፍጠኛ ነው ፡፡
ይልሃል ፈላስፋው የየትየለሌው ቆቁ
የሌለ ነገር እንደ ጦስ ውስዶ ህዝብን ግለሰብን መግደል ማረድ ፡ ማስገደል ማሳረድ የሚያስደስት ሳይሆን ከሰው በታች የሚያደርግ አስተሳሰብና ስራ ነው፡፡
ወደድንም ጠላንም ይህ የጥቂት ግለሰቦች እና ግሩፖች ሴራ መጨረሻው ባያምርም የኢትዮጵያ ሕዝብ በድል እንደሚወጣው ፈላስፋው የየትየለሌው ይናገራል ፡፡
ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቢተወደድ1 » Thu Nov 07, 2019 3:41 pm

በጃዋር ስራ መደነቅህ ገርሞኛል፡፡ ጃዋር ኢትዮጵያ ሳይገባ አለነበረም እንዴ ምን እንደሚያደርግ ሲነግረን የነበረው ሚኒሶታ ሆኖ? ሳይቃጠል በቅጠል ነበር፡፡
የሚያሳዝነው ስርአት የሚያሲዝ መንግስት አለመኖሩ ነው፡፡ የእናንተም እውነታውን እያዩ እንዳላዩት ስታልፉትና ምክንያት እየፈለጋቹህ ስታባባብሉት.........

ቆቁ wrote:ቢትወደድ
ይህ የጃዋር ስኩዋድ ዘር እየመረጠ ሳይሆን የራሱን ዘር ሁላ አደበላልቆ ነው ያረደው ፡፡
ተከታተል ዜናውን ጽሁፉን ፡፡
የኦሮሞ ተናጋሪ ሆነህ ቄሮ የሚያርደውን አብረህ ካላረድክ ፡ትታረዳለህ ፡፡
የኦሮሞ ተናጋሪ ሆነህ ቄሮ በድንጋይ የሚፈልጠውን አብረህ በድንጋህ ካልፈለጥክ ትፈለጣለህ ፡፡
ይህ የዓቢይና የጃዋር ጠብ የሚባል ነገር ሳይሆን የቁቤ አስተማሪዎቹ በወያኔ ዘመነ መንግስት ፡ ሲያሰለጥኑት የነበረው ስልጠና ነው ፡፡
ጸጋዬ አራርሳ፤ሕዝቄል ጋቢሳ፤በቀለ ገርባ ሌሎችም እነ ዶክተር ስማቸው ለጊዜው የጠፋብኝ፤ ከዛም በገዳው ስርዓት ራሱን በራባ ዶሪ እርከን ላይ ነኝ ብሎ የሚጠራው የነሱ ተማሪ የሆነው ጃዋር (33 -40 ወይም ከዛ በላይ ) ለዚህ ምሳሌ ናቸው
ለዛም ነው እነ ሽመልስ አብዲሳ ነፍጠኛ ለማለት የተገደዱት ፡ አዲሱ አረጋ በጥናት ስለ አኖሌ ያቀረበውን ጽሁፍ እኔ አልወጣኝም እስኪል ድረስ የቀባጠረው ፡፡
ቄሮ የወያኔን መንግስት ጣለ ተብሎ ሲደነቅ የማያውቀውን የራሱን አያትና ቅድመ አያት የሆነውን ነፍጠኛን ዛሬ ለምን መውቀስ አስፈለገው ?
ለምን ዛሬ ነፍጠኛን መውቀስ አስፈለገ ? እስኪ ራስህን ጠይቅ ?
ወያኔ ካለ ነፍጠኛ የሚያወራው የለም ፡ ቄሮ ካለ ነፍጠኛ የሚያወራው የለም ፡ጃዋር ካለ ነፍጠኛ የሚያወራው የለ?
ሶስቱም አንድ ናቸው በአስተሳሰብ ፡ አይገርምም ፡፡
የቱ ነው ነፍጠኛ ? የት ነው ነፍጠኛ የሚገኘው?
የወላይታው ተወላጅ ? የኦሮሞው ተወላጅ ? የትግራይ ተወላጅ
በመጀመሪያ ማነው ነፍጠኛ የሚለውን ስም ለአማራ ብቻ የሰጠው ?
የምኒሊክን እግር የተከተለ በሙሉ ነፍጠኛ ፡ ጠመንጃ ያዥ ፡ ሰናድር ያዥ ነው፡፡
ከዛም የምኒሊክን እግር ተከትሎ እስከ ዓቢይ መንግስት በምድረ ኢትዮጵያ ወዲያና ወዲን የሚነጉደው ሁላ ነፍጠኛ ነው የትግራይ በለው የጎንደሬ የሸዋ በለው የጉራጌ የወላይታ በለው የሱማሌ
ራሱ ወያኔ ነፍጠኝነቱ ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ ልክ ደርግን እንዳባረረ አዲስ አበባ ነበር የተኮፈሰው ፡ እና ነፍጠኛ አይደለም ?
ለምን ደብረጽዮን ነፍጠኞች ባቀኑዋት ምድር አዲስ አበባ መዘባነን አስፈለገው?
ይግባህ ወዳጀ ቢትወደድ
ነፍጠኝነት እንዴት እንደመጣ በሌላው ዓምድ ላይ ፈላስፋው ይተነትናል ፡
ነፍጠኝነትት የገዳው ስርዓት ያመጣው ልዩ ታክቲክ ነው
በምድረ ኢትዮጵያ ከምኒሊክ እስከ ዓቢይ ድረስ የምኒሊክን እግር የተከተለ ሁላ ነፍጠኛ ነው ፡፡
ይልሃል ፈላስፋው የየትየለሌው ቆቁ
የሌለ ነገር እንደ ጦስ ውስዶ ህዝብን ግለሰብን መግደል ማረድ ፡ ማስገደል ማሳረድ የሚያስደስት ሳይሆን ከሰው በታች የሚያደርግ አስተሳሰብና ስራ ነው፡፡
ወደድንም ጠላንም ይህ የጥቂት ግለሰቦች እና ግሩፖች ሴራ መጨረሻው ባያምርም የኢትዮጵያ ሕዝብ በድል እንደሚወጣው ፈላስፋው የየትየለሌው ይናገራል ፡፡
ፈላስፋው ቆቁ
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 369
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Thu Nov 07, 2019 11:30 pm

ቢትወደድ

ማን አሰበ እንደዚህ ይሆናል ብሎ ?
ጃዋር በቀዘነው ቅዘን ፡በረጨው ፈስ እንደዚህ ሐገር ይታመሳል ብሎ ማን አሰበ?
ነገሩ እኮ ልክ እንደ ካው ቦይ ፊልም ሆነ እኮ
በካው ቦይ ፊልም ላይ ውሃ ለመጠጣት ወደ ፈሳሽ ወንዝ የተጠጉ የቡፋሎ መንጋዎች አዞ ከውሃው ውስጥ ብቅ ቢል እንዴት እንደሚሆኑ ልብ አድርገህ ተገንዝበህ ይሆን ?
እንደዛ እኮ ነው የሆነበኝ እኔ ፈላስፋው
እንድ ቡፋሎ መንጋ ያገኘኽውን ሁላ ደፍጥጠህ ደፍጥጠህ ....... የት ጋ እንደምትቆም እንኩዋ አታውቀውም
የጃዋር ስራና መንጋዎቹም እንደዛ ነው የሆኑብኝ
በነገራችን ላይ
ማንም ጥፋተኛ ማንን ጻድቅ ለማድረግ ነው የአንተ አባባል?
ጃዋር የተፈጠረው በወያኔ ዘመነ መንግስት ነው ፡፡አራት ነጥብ
ይልሃል ፈላስፋው ቆቁ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቢተወደድ1 » Fri Nov 08, 2019 12:23 pm

ቆቁ wrote:ማንም ጥፋተኛ ማንን ጻድቅ ለማድረግ ነው የአንተ አባባል?
ጃዋር የተፈጠረው በወያኔ ዘመነ መንግስት ነው ፡፡አራት ነጥብ
ይልሃል ፈላስፋው ቆቁ


ማንንም ጥፋተኛ ለማድረግ ሳይሆን ጠላትህ ምን እንደሚያደርግህ እየነገረህ፤ ምንጣፍ አንጥፈህ ስትቀበለው፤ ሞኝነት ልበለው ወይስ ዘገምተኝነት?
ከዛም የድረሱልኝ ኡኡታ ምን ዋጋ አለው? የጨቅላው ሚኒስትሩ የአገር ማስተዳደርን ብቃት በዚህ ወቅት በደንብ የተፈተነበትና ክህሎት እንደሌለው ያስመሰከረበት ወቅት ነው ብል ከእውነት አልራኩም፡፡
የሚያሳዝነው የጠፋው ጥፋት ሁሉ በወያኔ ለማላከክ መጣራቹህ ነው፡፡ ያው የሁልጊዜ ጠባያቹህ ስለሆነ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለነዋል፡፡
ጃዋር የተፈጠረበትን ጊዜ ከምትቆጥር ጥፋት እንዳያስከትል በተጠንቀቅ መጠበቅ ነበረብህ፡ እናንተ ግን ኦሮአማራ ብላቹህ በውሸት ቅዠት ስትዋልሉ የተሳለላችሁን ቢላ ማየት ተሳናቹህ፡፡
አንድ ተረት ልንገርህ ሴትዮዋ ምን እንዳለች፡ ልጅ መውለድ እችላልሁ አባቱን ማስመሰል ግን ያቅተኛል፡፡
ተረቱ ጃዋር የተፈጠረው ላልከው ምላሽ መሆኑ ነው፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 369
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Fri Nov 08, 2019 6:04 pm

ቢትወደድ መልካም ነው ፡፡
ጃዋር የተፈጠረበትን ጊዜ ከምትቆጥር ጥፋት እንዳያስከትል በተጠንቀቅ መጠበቅ ነበረብህ

ምን ማለት ነው ተጠንቀቅ ማለት?
1. የተጠነቀቁት አውሮፓውያን የተጠነቀቁት አሜሪካውያን የሳይኮሎጂካል ችግር ያለባቸውን በየትምህርት ቤቱ የተፈጠሩትን ገዳዮችን መከላከል ለምን አልቻሉም ብለህ ጠይቅ እስቲ
2. የቢላደንን የመሳሰሉትን ድርጊቶችን ለምን ለመከላከል አልቻሉም ብለህ ጠይቅ እስቲ
የጨቅላው ሚኒስትሩ የአገር ማስተዳደርን ብቃት በዚህ ወቅት በደንብ የተፈተነበትና ክህሎት እንደሌለው ያስመሰከረበት ወቅት ነው ብል ከእውነት አልራኩም፡፡


እና ማን ነበር ክህሎት ያለው ማለትህ ነው ?
ደርግ ሐይለስላሴን ክህሎት አልነበረውም ሲል ወያኔ ደርግን ክህሎት አልነበረውም ሲል ፡ዛሬ ደግሞ ወያኔ ክህሎት አልነበረውም ሳይሆን የተባለው አብረን እንስራ ፡ አብረን እንለውጥ ፡አብረን እንደመር ሲባል ጥግ ይዞ መግለጫ በመግለጫ መሆኑንስ እንዴት ታየዋለህ ?
ፈሪ ውሻ ግምብ ስር ጭራውን ለጥፎ ይጮሃል የሚባለውን ተረትስ ታውቀው ይሆን ? በትክክል የፈራ ውሻ ቂጡንና ጭራውን የሆነ ጥግ እየቆላ ሲጮህ አንተም አይተሃል አሁንም እያየህ ነው ፡ አይደለም ?

አንድ ተረት ልንገርህ ሴትዮዋ ምን እንዳለች፡ ልጅ መውለድ እችላልሁ አባቱን ማስመሰል ግን ያቅተኛል፡፡

በመጀመሪያ እንደዚህ ያለ ተረት ለፈላስፋው አይገባውም ፡፡
አባቱን ቢመስል ባይመስል ልጅ ግን ተወለደ መሰለኝ ፡ ለመሆኑ አባቱን ቢመስል በምን? በመልኩ፡ በባህርዩ ፡ በጠባዩ ፡ በፈገግታው ፡ በለቅሶው ፡ በአረማመዱ ፡ በአደናነሱ ፡ በአነጋገሩ ፡ ቀጥል እስትቲ በምንድነው አባቱን ለማስመሰል ያሰበቸው
የተጀቦነ ተረት ነው ልክ ብሄር ብሄረ ሰቦች ሕዝቦች እንደሚለው የተጀቦነ ቃል
በነገራችን ላይ ስለ ካውቦይ ፊልም የጀመርኩትን ልጨርስልህ
ቡፋሎ በመንጋ ሆኖ ውሃ ለመጠጣት ይሄዳል፡
የሆነ አዞ አሳ ለመያዝ አንገቱን ብቅ ሲያደርግ የቡፋሎው መንጋ እግሬ አውጭን ብሎ ሲሮጥ፡ ሌላው ቡፋሎ ከፊት ከፊቱ የሚሮጠውን ቡፋሎ በቀንዱ አጋድሞ ፡ከጎኑ ያለውንም ወደዛ ወርውሮ፡ በዛኛው ቡፋሎ ላይ ተራምዶ ፡ እቡዋራውን እያጨሰ ፡ሲፈረጥጥ ተመልክተሃል ?
ከዛስ ብለህ ጠይቅ እስቲ ?
አዞው ውሃ ከሚጠጡት ቡፋሎዎች ውስጥ አንዱን ቢይዝ አንዱ ብቻ ነው የሚሰዋው፡፡
ሌሎቹ በሰላም ውሃቸውን መጠጣት ይችሉ ነበር ፡፡ ከዛም አልፎ የተያዘው ቡፋሎ ሲፈራገጥ አዞውን አናፍጦት ሊያመልጥ ይችል ይሆናል ፡ ማን ያውቃል ?
ይህ ሁላ ግን አይሆንም፡፡
ሲተረማመስ እና ሲፈረጥጥ ከዛም አቡዋራው ሲጨስ የምታየው የቡፋሎውን መንጋ ነው ፡፡
የቡፋሎው መንጋ ገደል አፋፍ ላይ ሲደርስ አይ መዘዙ ብለህ ገደሉን አርቀህ ስትመለከተው አንተው ራስህ የተሰባበርክ እንደሚመስልህ አልጠራጠርም ፡፡

ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sat Nov 09, 2019 6:40 am

'ፈላስፋው' በነካ እጅህ የሌሎቹን እስኳዶችንም አስተዋውቀን
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1204
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Sat Nov 09, 2019 9:44 pm

ዘርዓይ ንገረና
የምታውቀው ስኩዋድ ካለ ንገረና
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Sun Nov 10, 2019 8:52 pm

ግርግር ለሌባ ይመቻል እንደሚባለው በአገራችን ለሚካሄደው እልቂት አንድን ግለሰብ ብቻ ተጠያቂ ለማድረግ የሚደረገው ሩጫ ሊወገዝ ይገባል፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1204
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Next

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 3 guests