የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Current political, socio-economic and human rights issues.

Moderators: ዘበኛ ፩, ዘበኛ ፫, ዘበኛ ፪, ዘበኛ ፬

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Mon Nov 11, 2019 6:20 pm

ችግሩ እዚህ ላይ ነው ፡፡
ፈላስፋው ፈላስፋ የሚሆነው እዚህ ላይ ነው
ካለህ ምዘዘው ከሌለህ ዝም ማለቱ መጥፎ አይደለም
ግርግር ለሌባ ይመቻል እንደሚባለው በአገራችን ለሚካሄደው እልቂት አንድን ግለሰብ ብቻ ተጠያቂ ለማድረግ የሚደረገው ሩጫ ሊወገዝ ይገባል፡፡


እሱም አድርጎ ነበር ፡ እነሱም አድርገው ነበር ፡ ያኔ ተደርጎ ነበር ፡፡
ይህ ሁላ ሲደረግ ግን ማንም ምንም አልተናገረም ነገር ግን እኔ ሳደርግ ሁሉም ይጮሃል ፡ ይሆን አባባልህ ?

ጥያቄ ነው ነፍሱ ?
መልስ ይኖርህ ይሆን ?
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቢተወደድ1 » Wed Nov 13, 2019 9:38 pm

ቆቁ wrote:አብረን እንደመር ሲባል ጥግ ይዞ መግለጫ በመግለጫ መሆኑንስ እንዴት ታየዋለህ ?


የጎሪጥ አየዋለሁ፤ ምክንያቱም በመደመር ፋንታ የተያዘው መቀነስ ስለሆነ፡፡
ማንስ ነው ከማን ጋር የሚደመረው? ሰው ከአህያ ጋር?
እየተስተዋለ፡፡
ቢተወደድ1
ኮትኳች
ኮትኳች
 
Posts: 369
Joined: Thu Sep 01, 2016 8:48 am
Location: Bisheftu

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Thu Nov 14, 2019 7:14 am

አቶ 'ፈላስፋው' ዝም በል ከምትል እንደ ሎሬት ፀጋዬ ሁላችንም ዝም እንበል ማለቱ ይሻል ነበር፡፡እንዳንተ ሁሉን እናውቃለን ባዮች ናቸው እገር እያጠፉ ያሉት፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1204
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Thu Nov 14, 2019 6:32 pm

ዘርዓይ ደረስ እንዳለው
አቶ 'ፈላስፋው' ዝም በል ከምትል እንደ ሎሬት ፀጋዬ ሁላችንም ዝም እንበል ማለቱ ይሻል ነበር፡፡እንዳንተ ሁሉን እናውቃለን ባዮች ናቸው እገር እያጠፉ ያሉት፡፡

አለ እንዴ ጸጋዬ?
ታዲያ እሱ ካለ ለምን አንተ በመጀመሪያ ዝም አትልም ፡፡
እኔ አውቃለሁ አላልኩም ፈላስፋ ነኝ ነው ያልኩት አንተ ግን ሁሉን እናውቃለን ከሚሉ ከነ ጃዋር ዓይነቱ ጋር ደባለቅኽኝ
ጃዋር
የዩኒቨርስ ፖለቲከኛ ነኝ
እንኩዋን ምድርን ዩኒቨርስን አበጥሬ ነው የማውቀው ከዛም በዩኒቨርስ የፖለቲካ ጥናት አንደኛ ነኝ እንኩዋን ምድር ላይ ይቅርና ማርስ ላይ ያለውን የፖለቲካ ምህዳር በስትራቴጂ ፡ በታክቲክ ፡ በቅንብር በንግግር አበጥሬ አበጣጥሬ ነው የማውቀው እንዳለው ማለትህ ነው ?

ነገር ግን ስኩዋዶቹ በለውን እንጂ የሚያውቁት "ተው" የሚለውን ቃል አያውቁትም ምክንያቱም "ተዉ "የሚለው ቃል ከማርስ እስከ ምድር እስኪወርድ ድረስ ፍጥነቱ እንደ ጸሐይ ፍጥነት በመሆኑ አልፎአቸው በመሄዱ ለዚህም ነው በአባ ገዳዎች እና በሽማግሌ ፖለቲከኞች እባካችሁ ተዉ የተባሉት መሰለኝ ልበል ?
እንደዚህ ከቀጠለ እሱም የገዛ ስኩዋዱ ምሳ ራት እንደሚሆን ፈላስፋው አይጠራጠርም፡፡

ቢትወደድ እንዳለው
የጎሪጥ አየዋለሁ፤ ምክንያቱም በመደመር ፋንታ የተያዘው መቀነስ ስለሆነ፡፡
ማንስ ነው ከማን ጋር የሚደመረው? ሰው ከአህያ ጋር?
እየተስተዋለ፡፡

አህያ ስትል ምን ማለትህ ነው ? ትንሽ መረር ያለህ ትመስላለህ ?
ከጅብ ጋር ለመደመር ፈልገህ ይሆን እንዴ ?
መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ
መደመር እዚህም እዛም ያለ የፖለቲካ ሕግ መሰለኝ ባልሳሳት ?

ቢትወደድ
ችግር የለውም በግጎሪጥ ብታየው እንደ ተቀነስክ ትኖራለህ ፡፡
ጥግ ይዞ ከመጮህ ግን ለምን እንደዛ ይሆናል ብሎ ብልሃትን ማጋራት ትልቅ ቁም ነገር ነው ሕዝብን ማተረማመሱ ቀርቶ ለሰላማዊ አንድነት መታገሉ ትልቅ የሆነ የሰው ልጅ ክብር ነው፡፡ ለሐገርም ግንባታ ነው ፡፡
እኔ ተደመሩ ካላልኩ ሌላው ተደመሩ ሊለኝ አይገባም ከሆነ የዚህ ጨዋታ ጊዜ አክትሞል፡፡
አክትሞአል ጨዋታው ፡ ላይደገም ጨዋታው አክትሞእል
ይህ ጨዋታ የናርዚስቲክ ፐርሶናሊቲ ዲሶርደር እንደሆነ በዋርካ ጀኔራል ላይ ዘግቤው ነበር
ለማስታወስ ያህል እንደገና
እኔ ትክክል ካልሆንኩ አንተም ትክክል አይደለህም
አብዛኛው የኛ ሐገር የፖለቲካ ጫጫታ ከዚህ ከፐርሶናሊቲ ዲሶርደር የመነጨ እንደሆነ ፈላስፋው በጥቅለት እየታዘበው ይገኛል
በዚህ ጉዳይ ላይ እንደገና እመጣለሁ

ብትደመር ተደመር
ካልተደመርክ ሌላ ምን እልሃለሁ መንገዱን ጨርቅ ያርግልህ እልሃለሁ

ወደ ጥንቱ ወደ ጠዋቱ ስመለስ ኢትዮጵያዊነቴ ብልጭ እያለብኝ ነው ፡፡
እንደዚህ ነበር ያኔ ያልኩት
ፍቅር ያሸንፋል
የኢትዮጵያ አንድነትና ልዩነት ለዘላለም ይኑር
የመድበለ ፓርቲ ሲይስተም እንጂ የጎጠኞች ፖለቲካ ይጥፋ
ፈላስፋው ቆቁ የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Fri Nov 15, 2019 5:46 pm

ዘርዓይ አንድ ነገር አስታወስከኝ

1. ዝምታ ወርቅ ነው
2. ዝምታ ለበግም አልበጃት፡ አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት
3. ካልተናገሩበት አፍ እዳሪ ነው ፡
የሚባሉ ተምሳሌቶች ያሉን መሰለኝ ፡፡ አንተ የትኛውን ትመርጣለህ ?
በነገራችን ላይ ጃዋር ተከበብኩ ብሎ የረጨው ፈስ እንደ እንደ ፉኩሺማ ኑክሊያር ሪአክሽን ( fukushima nuclear reaction) ማቆሚያ የሌለው ነገር መሆኑ ነው የሚገርመው፡፡
እንዴት ይቁም ?
ማን ያቁመው ?
እንዴት እንደዚህ ያለ ነገር በምድረ ኢትዮጵያ ሊፈጠር ቻለ ?
ዘርዓይ ነፍሱ አንተ እንዳልከው ጃዋር ብቻ አይሆንም ተጠያቂው ተጠያቂው
1. ጃዋርን ያስተማሩ የቁቤ ፕሮፌሰሮችና ዶክተሮች
2. ጃዋር ራሱ
3. ጋንግስተር የሆኑ ቄሮውች

ታዲያስ
ዝምታ ወርቅ ነው እንበል
ዝምታ ለበግም አልበጃት 12 ሆና አንድ ነብር ፈጃት እንበል
ካልተናገሩበት አፍ እዳሪ ነው እንበል
አፍ የተሰራው ለመብሊያ ብቻ አይደለም ብለን ጣት የተሰራው ኮምፑተር ላይ ለመጠቅጠቅ ነው እንበል

ወደ ጥንቱ ልመለስ
የመድበለ ፓርቲ ሲስተም ብቻ ነው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያዋጣው
የጎጠኛ ፖለቲካ የጥንታዊ ጋርዮሽ ዘመን ፖለቲካ ነው ዛሬ ጊዜው አይደለም


ፈላስፋው ቆቁ የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Sat Nov 16, 2019 5:02 pm

ታየ ደንዳ እንዴት አድርጎ ጃዋርን እንደገለጸው ነው እኔ ፈላስፋው የተነካሁት
ከሞላ ጎደል አባባሉ ከታች የተሰመረበትን ይመስላል፡፡
ይህ አስተሳሰብ የተሰዘነረው በነመራራ ጉዲና ስብሰባ ላይ ነበር

በጋራ መሰባሰባችሁ መልካም ነው ፡፡ ነገር ግን ለፎቶ ብቻ እንዳይሆን
1. በጋራ መሰባሰባችሁ መልካም ነው
2. በጋራ መሰባሰባችሁ ለፎቶ ብቻ እንዳይሆን
አንደኛውን ብንምለከት
ሁኔታዎች በጥሩ ሁኔታ ወደፊት ከገፉ በነመራራ ጉዲና የተሰጠው መግለጫ የኔም አስተሳሰብ ነው ስለሆነም በፖለቲካ አማካሪነት እኔ አንደኛ ፡ ከዓለም የታወቅሁ ነኝ ለማለት ይመስላል
ሁለተኛውን ብንመለከት
ሁኔታው ጠጠር ያለ መሰናክል ቢያግጋጥመው በነመራራ ጉዲና የተሰጠው መግለጫ ለፎቶ ብቻ እንዳይሆን ብዬ ነበር እኮ ለማለት ይመስላል ፡፡
እዚህ ላይ ነው ፈላስፋው የተነካው
ለመኖር የሚደረግ የእስስት አስተሳሰብ ለመሆኑ ታየ ደንዳ በትክክል አስቀምጦታል
በዚህ አገላለጽ ላይ ፈላስፋው የሚደግመው ነገር ባይኖርም አንድ ነገር ግን አለ፡፡
ጃዋር ደጉንም መጥፎውንም የሚያውቅ አይመስልም ማለት ይሆናል
ደጉንና መጥፎውን አለማወቅ ማለት ምን ማለት ነው ? ቀይ መስመር ማለፉን አለማለፉንስ ያውቅ ይሆን ?

ሌላ ጊዜ በዚህ ሁኔታ ጉዳይ ብቅ እላለሁ
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Sun Nov 17, 2019 9:44 pm

በነገራችን ላይ ጃዋር ስኩዋዱን ይዞ ነው ለምርጫ የሚቀርበው ወይስ ስኩዋዱን በትኖ ብሎ ፈላስፋው ይጠይቃል ፡፡
ለመሆኑ የጃዋር ስኩዋድ ሊበተን የሚችል ስኩዋድ ነው ?
ጃዋር በምርጫ አሸንፎ የሆነ ቦታ ቢያገኝ ስኩዋዱ ይበተናል ወይስ ይጠናከራል ?

የጃዋር የእስስት ጠባይ በዚህ ንግግሩ ግልጽ ማወቅ አያዳግትም ፡፡
በምርጫው እሳተፋለሁ ሲል ምን ማለቱ ነው
1. በአሜሪካን ዜግነት አትሳተፍም ቢባል
የሱ መልሱ
የኢትዮጵያ ዜግነት አመልክቼ አልሰጥም አሉኝ ብሎ ለቄሮ መፍሳት ይሆን?
2. በምርጫው ቢሸነፍ ፡ ምርጫው አሻጥር ተደርጎበታል ብሎ ለቄሮ ለመፍሳት ይሆን ?
አቡዋራው ሊጨስ ነው ማለት ነው ፡ በፈስ ቡክ ቄሮን ተነሳ ማለት ነው
3. ዲሞክራቲክ ምርጫ መሆኑን ለማየት ነው ሲልስ ምን ማለቱ ነው፡፡
እንዴት እንደዚህ እንዳለ እንግዲህ ግልጽ ነው ምክንያቱም ስኩዋዱን አውቆትም ሆነ ሳያውቅ ለማስነሳት እንዲመቸው ይሆን ?

አንድ ፖለቲከኛ ምረጡኝ አስመርጡኝ እኔ ለዲሞክራሲ እታገላለሁ ይላል እንጂ ምርጫው ዲሞክራቲክ መሆኑን ለማየት በምርጫ እሳተፋለሁ ማለት ምን ማለት ነው፡፡
ስኩዋዱን ማስነሳት ?
በነገራችን ላይ የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት በሰው ልጅ ደምና ላብ የመኖሪያ ዘዴ ነው
ያለ ፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት አንድ ሰው ሐገርን ለመምራት የበቃ የነቃ ጭንቅላት እንዳለው ለማወቅ ችግር የለም
አባ ጅፋር የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪ አልነበሩም
የገዳ ስርዓት በፖለቲካ ሳይንስ ትምህርት የታጀበ አይደለም
በመላው ዓለም የሚገኙ መሪዎችችአብዛኞቹ የፖለቲካ ሳይንስ ተማሪዎች አይደሉም
አንድ የፖለቲካ ሳይንስ እዋቂ ከፖለቲካው ዓለም በምርጫም ሆነ በሆነ ነገር ቢንሸራተት ሌላ ስራ ሰርቶ የመኖር እድሉ የመነመነ ነው ለዛም ነው ጃዋር ከፖለቲካ ሳይንሱ የሚዲያ ቢዝነሱ ላይ ዋና ትግል የሚያደርገው
የሚዲያ ቢዝነስ ለመስራት ደግሞ ፖለቲካል ሳይንስ መማር አያስፈልግም
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Mon Nov 18, 2019 10:54 pm

ጃዋር ምን ሊያደርግ ነው አሜሪካ የሄደው ? በማለት ፈላስፋው ይጠይቃል ፡፡
ለስኩዋዱ ገንዘብ ለመሰብሰብ ወይስ ለሙዋች ቤተ ሰቦች እርዳታ ለማሰባሰብ ?
ተመራጭ መሆኑን ለማስተዋወቅ ወይስ እቤቱ ሄዶ በርጋታ በሐዘን ለመቀመጥ ?
የጃዋርርን ንግግር ለማዳመጥ የተሰበሰው ሐዘን ላይ ለመቀመጥ ወይስ የተረፉትን ለማጣጣም ?
በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው?
ሳይካትሪስት የለም እንዴ ?
አያት ቅድመ አያቱ 20 ቤተ ክርስቲያን ካሰሩ ምነው ታዲያ ስኩዋዱ የአያት ቅድመ አያቱን ቤተ ክርስቲያን በእሳት ሲያደባይ ለምድነው አንድም ቃል ሳይተነፍስ ወደ አሜሪካ የተጉዋዘው ? እያት እና ቅድመ አያቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸው አሜሪካ ሲገባ ነው እንዴ ብልጭ ያለለት ?
እነሱ ናቸው ፡ እሱ ነው ፡ እነሱ ያወጡብን ፕላን ነው ፡ የሚል የተጨበረበረ ወሬ ምንድነው?
እነማናቸው እነሱ የሚባሉት ?
2 ኛው ነጥብ (አንደኛው የእስስት ባህርይ ሲሆን ማለትም ሁለት ገጽታ ፡ )
እዚህ ላይ የእስስት ባህርይ ማለት
ሁለት ገጽታ
ሁለት ሐሳብ
ሁለት ምላስ
ሁለት ጭንቅላት
እያለ መንታ የሆነ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ፡ ግራ ሲያጋባ ደግሞ ወዲያውኑ ሳይሆን ከረዥም ጊዜያት በሁዋላ ዝብርቅርቅ አድርጎ የሚያደነጋግር አስተሳስሰብ ማለት ነው
ቀላል ምሳሌ፡ ብሄር ብሄረ ሰቦች ሕዝቦች የሚለውን እንውሰድ ዲክሽነሪ ብትፈልግ ዊኪፒዲያ ላይ አፍጠህ ብትውል ፡ መስጊድና ቤተ ክርስቲያን ያሉትን መጻህፍት ብታገላብጥ ፡ ራሳቸው ይህንን ቃል ያወጡትን ብትጠይቅ እድሜህን ትጨርሳለህ እንጂ መልስ የምታገኝበት መንገድም ዘዴም የለም ፡፡ እንደዛ ነው መንታ ጭንቅላት ማለት እንደ መንታ መንገድ ማለት ነው ፡ ተደናብረህ መኖር ማለት ነው፡፡

ሁለተኛው ነጥብ ለሌላው የሚያስብ የሚጨነቅ ፡ አስመስሎ ራስን ማቅረብ ነው
1." አያቶቼ 20 ቤተ ክርስቲያን አሰርተው ይጸልዩ ይሰግዱ ነበር "
2. " ስትቃወሙ በስነ ስርዓት ይሁን" የሚለውና ሌሎችም አባባሎቹ ናቸው ፡

ሰላማዊ ሰልፉ ስነ ስርዓቱን የሚቆጠጠር ሕገ መንግስትና መንግስት ባለበት ሐገረ አሜሪካ መስሎን እየተደረገ ያለው
አይደለም እንዴ?
በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ስነ ስርዓት ከማስተማር ይልቅ የራሱን ስኩዋዶች እንዴት ስነ ስርዓት ማስተማር አቃተው ?
የአሜሪካው ጉዞ ስኩዋዱን አላውቀውም ለማለት ይሆን ? ወይስ እንደ ፉኩሺማ ኑክሊያር ሪአክተር ሲቀጣጠል እኔምም ይጠርገኛል ብሎ ይሆን አሜሪካ የገባው ?
ሪአክተሩ እስኪቀዘቅዝ ድረስ ይሆን የአሜሪካ ቆይታው ?
ነገር ግን ድረሱልኝ ብሎ የጠራው ግን ይህ ስኩዋድ ነበር ፡ አይደለም እንዴ ?
ስለ ፌዴራሊዝምም የሆነ ነገር ሞክሮእል ያንንም በጉልበት የተጫነውን ፌዴራሊዝም ለመተግበር እንደሚጥር

ሌላ የፌዴራል ሲስተም አወቃቀር ቢመጣ አሁንም ስኩዋዱን ተነሳ ሊል ይሆን ?

ምንድነው አሃዳዊ ፡ ፌዴራላዊ ?
ለሰው ልጆች መብትና እኩልነት መታገሉ ቀላል አልነበረም እንዴ ?
የሰው ልጅ እኩልነት ማለት ጃዋር የባህርዳር ከንቲባ ሲሆን

ዋ ጃዋር አይጥ ወልዳ ወልዳ ጅራቱዋን ሲይዙዋት ሲጥጥ አለች አሉ

የኢትዮጵያ ልጆች በልዩነታቸው እና በአንድነታቸው ተከባብረው ይኖራሉ

ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Thu Nov 21, 2019 7:32 pm

1. እስስታዊ ባህርይ
2. ለሌላው የሚጨነቅ ማስመሰል
3. ከሁሉም በላይ ነኝ
ዛሬ በሶስተኛው ነጥብ ላይ እናተኩራለን
" ስንታገላቸው የነበሩት አሁን ሲታገሉን ለኛ ደስ የሚል ነው " የተተረጎመው የጃዋር ንግግር
ምን ማለት ነው እንደዚህ ያለ አነጋገር ፡ ንግግሩ ትክክል ከሆነ በጣም የሚገርም አባባል ነው ፡ የሚገርመውም እንደ " ብሄረ ብሄረሰቦች ሕዝቦች " እንደሚለው ቃል አደናባሪ ቃል መሆኑ ነው፡፡
ይህንን አባባል ትርጉሙን ስትፈልግ 27 ዓመታት ሳይሆን የሚሊዮን ሚሊዮን የሚሆን የትውልድ ዘመን ይፈጅብሃል
እንደዚህ ያሉ ቃላቶች ብዙ ናቸው ለምሳሌ " አብዮታዊ ዲሞክራሲ" የሚለው ቃል እንኩዋን ፈልገኽው ብታልመውም እድሜ ልክህን ብታስበውም ምን እንደሆነ ሳይገባህ ነው ከዚህ ዓለም የምታልፈው
"አርብቶ አደሮች የማህበራዊ ስርዓታቸው ለአብዮታዊ ዲሞክራሲ የሚስማማ አይደለም ስለሆነም አጋር ድርጅቶች ናቸው " የመለሰ ዜናዊ አባባል ፡ የሚገርም አደናጋሪ የቃላት ስኬት ነው ፡፡፡
ሐገራችን በጎሳ ብቻ ሳይሆን የተከፋፈለችው
በአርብቶ አደር
በግምብ አደር
በበርንዳ አደር
በሜዳ አደር
በክንዶሚንየም አደር
ከተሜ
ገጠሬ
ለማኝ
ሐብታም
አማራ ፡ ኦሮሞ ፡ ደቡብ ፡ ትግራይ፡ .....
"አብዮታዊ ዲሞክራሲ በሚባል የተዘበራረቀ አገላለጽ"፡ እንድን ድርጅት ለመፍጠር አርብቶአደር ሳይሆን አውርቶአደር በተጨማሪ ደግሞ የምላስህ ራዲየስ እና የምላስህ ርዝመት በአርኬሚዲክስ የሰርክል ስሌት በጎጠኝነትህ ከፈጠርካት መንደርህ ወደ ሌላኛው የጎጠኛ መንደር በስድብ ሲደርስ ይሆናል ማለት ይሆናል
ለዚህም ነው በሕወሃት በትክክል ያልተገበረውን የጎጠኛ መንደር ጃዋር በትክክል ለመትገበር ስኩዋዱን ለማስታጠቅ ተነስቶእል ተብሎ የሚወራው ፡፡
ለመሆኑ ምንድነው ጃዋር የሚተገብረው ፌዴራሊዝም ?
ለምን ግልጽ አያደርገውም ?
ፌዴራሊዝም ቃል ነው
የሰው ልጅ የእኩልነት መብት ግን እውነት ነው
ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች
በስራ
በትምህርት
በኑሮ
በጤንነት
በደህንነት
ባህልን በማክበር
እኩል መሆን አለባቸው ይላል ፈላስፋው
ከዛም አልፎ እንደፈለጉት ክብራቸው መጠበቅ ይኖርበታል ይላል ፈላስፋው
ወደ ሶስተኛው ነጥብ ስንመጣ ከሁሉም በላይ ነው የሚለው ነው
ምክንያቱም በሆነ ዩኒቨርሲቲ ስለተማርኩ ፡ የሆነ ዲግሪየን ስለያዝኩ ፡ ለዛም ለዚህም አማካሪ ነኝ ፡ ከዛም አልፎ በምስራቅ በምእራብ በደቡብ እና በሰሜን የዓለማችን ክፍል ተዘዋውሬ እንዳየሁት የመሳስሉት ዝባዝንኬዎች በመግለጫው ይሰማሉ ፡፡

ይህ የፌዴራሊዝም ጥሪ ሳይሆን የሳይካትሪስ ጥሪ ነው ይላል ፈላስፋው የየትየለሌው
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Fri Nov 22, 2019 9:02 pm

1. እስስታዊ ባህርይ
2. ለሌላው የሚጨነቅ ማስመሰል
3. ከሁሉም በላይ ነኝ
4. ውሽት
5 ቅናት
አራተኛው ነጥብ ነው አሁን የሚታየው ነው ፡፡ ትላንት የተናገረውን ዛሬ አይደግመውም ፡ ትላንት ምን እንደተናገረ አያውቀውም ፡፡
ይህንን ትላንትና ተናግረሃል ብትለው ፡አንተ ነህ ይህንን የተናገርከው እኔ አይወጣኝም ነው የሚልህ
በውሸት ሌላውን አደንዝዞ ማደናበር ትልቁ መመሪያ ነው
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Sat Nov 23, 2019 8:11 pm

አሁን ደግሞ ከጃዋር ኮሎራዶ ንግግር የተሰማው የማቴዎስ ወንጌልን ይመስላል ፡
ዩኒፎርሙ ተቀየረ ማለት ነው ፡፡
ግራችሁን ሲመታችሁ ቀኛችሁን ስጡ
"ሲሰድብችሁ መልሳችሁ አትስደቡዋቸው አመስግኑዋቸው"
"ምላሳቸውን ሲጎትቱ ምላሳችሁን አታስረዝሙ "
የጎጠኞችን ታሪክ ዘሎ ወደ እምነት ልዩነት ገባ አለ ብሎ ፈላስፋው ይፈላሰፋል
የሚሰማው ስድብ እና ምላስ ማስረዘም ቀጥታ ግለሰቡ ላይ ነው ፡፡ ለምን ወደ ጎሳና እምነት ለመለወጥ አስፈለገ ?
ከየት ይሆን ወይስ ከማን ይሆን ይህንን ጃዋር የወረሰው?
እሱም ሊደግመው ይሆን ? ዩኒፎርሙን ቀይሮ ?
አንድ ጥያቄ አለ ፡፡
ለመሆኑ ጃዋር እስከ ዛሬ የተናገራቸውን ንግግሮች ንግግሮቼ ናቸው ብሎ ያምን ይሆን ?
ተከታዮቹስ እስከ ዛሬ ድረስ የተናገራቸውን ንግግሮች በማነጻጸር ፍርድ የመስጠት ብቃት ይኖራቸው ይሆን ?
እናሸንፋለን አንጠራጠርም ሲል ማንን ነው የሚያሸንፈው ?
ይህንን መፈክር የት ነው የማውቀው ብሎ ፈላስፋው ይጠይቃል?

ፈላስፋው የየትዬለሌው በልዩነትና በአንድነቱዋ አሸብርቃ ከምትገኘው ውድ ሐገሬ ኢትዮጵያ
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: The Conspiracy Theory of ጃዋር እና የሚዘገንኑት ስኩዋዶቹ

Postby ቆቁ » Sun Nov 24, 2019 7:08 pm

1. እነሱ ናቸው ፡፡
እነማናቸው እነሱ ?


2.
ከሳዲቅ አህመድ ጋር ከተደረገው ውይይት በአጭሩ፡
" ለሁሉም ደወልኩ ፡ ከዛም የመንግስት ትእዛዝ መሆኑን አወቅሁ፡
የተለያየ ሐይል እየተጨመረ መጣ ፡፡ እነዚህ ሐይሎች አንድ ትእዛዝ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ እልመሰለኝም ፡፡
የሚጠጉ ከሆነ ( በአማርኛ የጻፍኩትን አይተኸው ከሆነ ) ከነዚህ ልጆች ጋር ሊጋጩ ነው ፡፡ ከተጋጩ ከጸጥታ ሐይሎች ጋር ብቻ ሳይሆን ፡እኔም ከቤተ ሰብ ጋር ነው የምኖረው ፡ የእካባቢው ሕዝብም አለ ፡ ስለሆነም አደጋ መድረሱ ስለገባኝ ነው ፈስ ቡክ ላይ የለጠፍኩት ፡፡ የለጠፉትም 'የምትጠጉ ከሆነ ችግር ይፈጠራል ችግር ከተፈጠረ እናንተ ናችሁ ተጠያቂዎቹ' የሚል ነበር፡፡"
ከዛም በመቀጠል "
"ለምን ከሞት ተረፍክ ከሆነ አይገባኝም አንተ ብትሆን ኖሮ ?
"
በማለት ጃዋር ለሳዲቅ ጥያቄ ያቀርባል

አሁን ይህ ትክክለኛ አባባል ነው ብሎ ፈላስፋው ይጠይቃል
ጃዋር ፈስ ቡክ ላይ የለጠፈው እየተጠጉ ለመጡት ሐይሎች ነው ከሆነ
እልቂቱ የተፈጸመው አምቦ፡ አዳማ ፡ ድሬደዋ ፡

ታዲያ ምን ያገናኘዋል ጉዳዩ?
ከሞት እሱ ተረፈ፡፡
ሌላ የሞተው አይታዘንለትም?
ስለነሱ ይቅርታ አይጠየቅም
ማጽናኛ ለቤተ ሰብ አይተላለፍም ?

እነሱ ናቸው ፡፡
እነማናቸው ?


እንደ አይጥ በጃዋር የፍቅር ወጥመድ የተጠመዳቸው የሐገሬ ልጆች ምን
ልበላችሁ ?
እናንተም እነሱ ናቸው ትሉ ይሆን
እነማናቸው ?


ዓይናችሁን ክፈቱ

ፈላስፋው የየትዬለሌው በልዩነትና በአንድነቱዋ አሸብርቃ ከምትገኘው ውድ ሐገሬ ኢትዮጵያ
ፈላስፋው የየትየለሌው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Mon Nov 25, 2019 9:23 pm

ማን ላይ ሊያላክክ ነው ጃዋር እነሱ ናቸው የሚለው ?
እነሱ እነማናቸው
እዚህ ላይ ጃዋር 99 መንገዶች ይኖሩት ይሆናል፡፡
እነዚህ 99 መንገዶች ቄሮን በጭንቅላት አጠባ እስከመጨረሻው እንዲከተለው ማድረግ ከዛም ተነስ ሲለው የሚነሳ ተቀመጥ ሲለው የሚቀመጥ ለማዳ የቤት እንስሳ ማድረግ፡፡
ቄሮችን ብቻ አይደለም የዲያስፖራ ተከታዮቹን እንደ ቤት እንስሳ ኑ ሲላቸው የሚመጡ ሂዱ ሲላቸው የሚሄዱ ለማድረግ
ቄሮ ታግሎእል ይህንን ለውጥ አምጥቶእል ይህ ገናና ስም እንደተከበረ ለታሪክ ይቀመጣል
ታዲያ ጃዋር ይህንን ገናና ስም ለምን ጋራቤጅ ውስጥ ለመክተት አስፈለገው ?
በሱ የፈስ ቡክ ጥሪ ነው ጣጣው የተፈጠረው ፡፡ አይደለም እንዴ ?
በዲስኩሩ ላይ እየደግጋገም የሚናገረው " እነሱ" የሚል ቃል ነው
እነሱ እነማናቸው ?

ይህን ማለቱ ምን ማለት ይሆን?
እውነቱን ለመደበቅ ?
ሌላው በሌላ እንደተራጠረ እንዲኖር ለማድረግ ?
ቄሮ በዚህ ለማረጋገጥ በማይቻል የጃዋር ፍልስፍና ተጣብቆ እንዲኖር ለማድረግ?
የዲያስፖራ ተከታዮቹን አደንዝዞ ለማፍዘዝ
ሌላውን ሕዝብ ግራ ለማጋባት

በዓለማችን እንደዚህ ያሉ ብዥ ብለው፡ ሕዝብን ብዥ አድረገው የቀሩ ታሪኮች ተፈጥረው አልፈዋል፡፡


ጃዋር የፓርቲ አባል ለመሆን ከፈለገ በመጀመሪያ ደረጃ ከቄሮ ስኩዋድ መሪነት መለያየት ይኖርበታል ይላል ፈላስፋው
ይህ ነው የዲሞክራሲ መጀመሪያው ፡

እነሱ እነማናቸው ?


ፈላስፋው የየትየለሌው ይጠይቃል
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ዘርዐይ ደረስ » Fri Nov 29, 2019 7:29 am

ቆቁ፡-እንደተረዳሁት ከሆነ አንዴ በአንድ ጉዳይ ላይ ራስህን ካሳመንክ በኋላ ለመቀየር ትቸገራለህ ፡፡የጠቀስካቸው ከተሞች ውስጥ የተከሰቱት ግጭቶችና እልቂት በዋነኝነት የነማን እጅ እንዳለበት የሚታወቅ አይመስለኝም፡፡ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች ማየቱ ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡
''ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች ትፍም ብትልባት ትጠፋለች ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ ::''መጽሐፈ ሲራክ 28:12
ዘርዐይ ደረስ
ውሃ አጠጪ
ውሃ አጠጪ
 
Posts: 1204
Joined: Sat Oct 23, 2004 3:52 am
Location: ethiopia

Re: የሚዘገንነው የጃዋር ስኩዋድ ?

Postby ቆቁ » Fri Nov 29, 2019 5:58 pm

ዘርዓይ በትክክል አስቀምጠኽዋል
እኔን ፈላስፋው የሐገራችን ሁኔታ ከእውነታው ወደ ብዥታ መለወጡ ስለገረመኝ ነው እዚህ ላይ ያፈጠጥኩት ፡፡
እገሌ ተገደለ ሲባል ፡ እኛ አይደለንም እነሱ ናቸው ፡፡
እነሱ ፡ እሱ የሚባል ነገር እኔ ፈላስፋው አይገባኝም ፡፡
ሁሉም ማስተባበያ ይሰጣል ፡ ከዛም አልፎ እነሱ ናቸው ይላል፡፡
እነማናቸው እነሱ ?
የኦነግን መግለጫ አስመልክቶ ደግሞ ሌላ ነገር መጣ የመንግስት እጅ አለበት፡፡ ይላል
የተገደሉት የኛ አባላት ናቸው ማለትም ይመስላል ፡፡

በዛም በለው በዚህም በለው
ሰው ይገደላል ፡ እነሱ ናቸው ይሉሃል
ቤት ይፈርሳል ፡ እነሱ ናቸው ይሉሃል
ቦምብ ተወረወረ ፡ እነሱ ናቸው ይሉሃል
ይህ ነገር መፈጠርር የተጀመረው መች ነው ብለህ ጠይቅ ፡፡
ዓቢይና ለማ ብቅ ሲሉ ወይስ ከዛ በፊት ?
ከዛ በፊት ሁለት ብቻ ነበሩ መንግስት ወይም አማጽያን
ሁሉም በዓቢይና በለማ ችሮታ ሲገቡ
ሳምሶናይት ይዘው ግማሾቹ ገቡ ፡ ሌሎቹ ደግሞ የተቀበረ መሳሪያ መፈልፈል ጀመሩ ፡ ሌሎቹም ዘመኑ ባመጣው ዲጂታል ፈስ ቡክ ለመጣረስ ተዘጋጁ ፡፡
ከዛም የብዥታ ቲዎሪ ይለቀቅ ጀመር በዚህ በብዥታ ቲዎሪ ነው ነገር የተበላለሸው ፡፡
አሁንም ከዲሲ የተሰማው ሌላ ብዥታ ነው ፡፡ ይህንን ብዥታ እመለስበታለሁ
ይህ ሁላ ብዥታ ፈጠራ ውጤቱ ምን ይሆን ?
ፈላስፋው
ቆቁ
ዋና አለቃ
ዋና አለቃ
 
Posts: 4254
Joined: Sun Sep 21, 2003 9:57 am
Location: united states

PreviousNext

Return to Warka Politics - ዋርካ ፖለቲካ

Who is online

Users browsing this forum: No registered users and 4 guests